ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘዳግም 32፡46፣47፣ 1ኛ ነገስት 3፡6፣ ዘኁ 6፡24-26፣ ዘፍ 1፡26፣ 27፣ ዘፍ 2፡ 15-23፣ 15፡ 1- 5
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ ‹‹ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፥ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት።›› (ዘዳግም 31፡26)
በ
አለም ባሉ ሚሊዮኖች ዘንድ ከ6000 በላይ ቋንቋዎች ይነገራሉ። ሙሉ መጽሐፍ
ቅዱስ ከ600 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሟል፣ አዲስ ኪዳን እና የተወሰኑ
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከ 2500 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች እንዲሁ ተተርጉመዋል።
ያ ማለት በእርግጠኝነት በጣም ብዙ ቋንቋዎች ናቸው። ነገር ግን ይህ ማለት በአለም
ካሉ ቋንቋዎች ከግማሽ በታች እንደማለት ነው።
ከ 1.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች በራሳቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ምንም አይነት
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አልተተረጎመላቸውም። በጣም ብዙ ሊሰራ የሚገባው ስራ
ቢኖርም፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር 6 ቢሊዮን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ
እንደሚችሉ ግን አረጋግጧል።
እናም መጽሐፍ ቅዱስን በእራስ ቋንቋ ማግኘት አንዴት መታደል ነው! ብዙ ጊዜ ይህን
እንደ መብት እናየዋለን ሌሎች ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንደሌላቸው ማስታወሱን
እንተወውና ነገር ግን ለብዙ መቶ አመታት በአውሮፓ መጽሐፍ ቅዱስ ሆን ተብሎ
ከሕዝቡ እንዲጠፋ ይደረግ ነበር። ለማተሚያ ቤቶች ምስጋና ይድረሳቸውና
ተሃድሶው ይህ ጉዳይ፣ ጉዳይ እንዳይሆን አደረገው። በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ያለን
በመንፈስ መሞላትን፣ እንዴት እንደምናጠናው መማርን እና በገጾቹ የተገለጸውን
ጌታን ማወቅን እንዴት እንደምንችል መመልከታችንን እንቀጥል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ ግንቦት 08 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17ን ያንብቡ። መጽሐፍ ቅዱስ ለምን አላማ ነው የተሰጠን?
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር የሰራውን ስራ ለመመስከር፣
የወደቀውን የሰብአዊ ዘር የማዳንን እቅድ እና እኛን ወደ ጽድቅ መንገድ ለመምራት
ነው። ጌታ ይህን ለማድረግ የሰብአዊ ቋንቋን መረጠ፣ ሐሳቡን በሰብአዊ ቋንቋ
እንዲታይ አደረገ። እስራኤልን ከግብጽ ለማዳን እግዚአብሔር መልእክቱን ለህዝብ
ሁሉ እንዲያደርሱ የተወሰኑ ሕዝቦችን መረጠ። እነዚያን ሕዝቦች በቋንቋቸው
መልዕክቱን እንዲያደርሱ ፈቀደ፣ እብራይስጥ (የተወሰነው ክፍል ደግሞ በአረማይክ
ቋንቋ፣ ከእብራይስጥ ቋንቋ ጋር ይቀራረባል)።
የግሪኮች ባህል መግነን አዲስን እድል ይዞ መጥቷል፣ አዲስ ኪዳን አለም አቀፍ
በሆነው የግሪክ ቋንቋ በዚያኑ ሰዓት በዚያ የአለም ክፍል ይነገረም ነበርና እንዲሰራጭ
አደረገው። (በእርግጥ እንደዚሁ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ በግሪክም ቋንቋ ተተርጉሞ
ነበር። ) ይህ ‹‹አለም አቀፍ›› ቋንቋ ሐዋሪያትን እና የጥንት ቤተክርስቲያንን
መልእክቱን በእሩቅ እና በስፋት ከክርስቶስ ሞት በኋላ እንዲያሰራጩ አስቻላቸው።
ኋላም ሐዋሪያው ዮሐንስ ‹‹ እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ
ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ። ›› (ራዕ 1፡2) ሲል ይናገራል። በዚህ መንገድ መጽሐፍ
ቅዱስ በመንፈስ የተነዱ ‹ምስክርነቶች› እና ‹ ማስረጃ ማቅረቡን› ከመጀመሪያዎቹ
ጸሐፊዎች እስከ መጨረሻው ጸሐፊ ድረስ መቀጠሉን ይጠቅሳል።
ዘዳግም 32፡46፣47ን ያንብቡ። ለእስራኤል ልጆች ‹‹ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ
ይጠብቁና ያደርጉ›› (ዘዳ 32፡46) ዘንድ ቶራ ወይም ‹‹መመሪያ››የተባለውን
መታዘዘ በጣም አስፈላጊ የነበረው ለምን ነበር? እንዴት ነው የእግዚአብሔር ቃል
እድሜአችንን ‹የሚያረዝመው› ? ዛሬ ባለንበት አገባብ ምን ማለት ሊሆን ይችላል?
አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው መተርጎም ብቻ ሳይሆን
ነገር ግን በእራሳቸው ቋንቋ የተለያየ ቅጅም አላቸው። ያም ቢሆን አንዳንዶች ደግሞ
ምን አልባት አንድ ትርጉም ብቻ ይኖራቸዋል። ነገር ግን ያላችሁ ምንም ቢሆን ቁልፍ
ነገሩ ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል ወስዶ መደሰቱ እና በጣም አስፈላጊው ደግሞ
አስተምህሮቱን መከተሉ ነው።
ለምንድን ነው የእግዚአብሔርን ቃል መከተሉ እና ልጆችን ማስተማሩ
በፍጹም ‹‹ ከንቱ ›› (ዘዳ 32፡47) የማይሆነው?
በእያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ በጣም ያካበቱ እና የጠለቀ ትርጉም ያላቸው ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም ተመጣጣኝ የሆነ አንድ ቃል ለማግኘት የሚከብዱ ቃላት አሉ ። እንደዚህ አይነት ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋሉ ልዩ ልዩ ትርጉማቸውን ለማስተዋል ሰፊ ጥናት ይጠይቃል። 1ኛ ነገስት 3፡6፣ መዝሙር 57፡3፣ መዝሙር 66፡20፣ መዝሙር 143፡8 እና ሚኪ 7፡20ን ያንብቡ። የእግዚአብሔር ምህረት እና መልካምነት ለፈጠረው ፍጥረቱ የበዛው እንዴት ነው?
የእብራይስጡ ቃል ‹ቸስድ›(ምህረት ወይም ቸርነት) አንዱ በጣም በትርጉሙ
የበለጸገ እና በብሉይ ኪዳን መሰረት የሆነ ቃል ነው። የእግዚአብሔርን ፍቅር ፣
በፍቅር የሆነ ቸርነት እና በሕዝቡ አንጻር የተደረገን የቃል ኪዳን ሐሳብ ይገልጻል።
በዚህ ጥቂት መልእክት /ክፍል ውስጥ እርሱን እናያለን ‹‹ ከባሪያህ ከአባቴ ከዳዊት
ጋር ታላቅ ቸርነት ‹ቸስድ› አድርገሃል ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ
ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን ‹ቸስድ› አቆይተህለታል።››(1ኛ ነገስት 3፡6) ይላል። እርሱ
‹‹ ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው እግዚአብሔር ቸርነቱን
‹ቸስድ› እና እውነቱን ላከ። ›› (መዝ 57፡ 3) ይላል።
እስራኤልን በተመለከተ ‹‹ከቀድሞ
ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ‹ቸስድ›
ለአብርሃም ታደርጋለህ። ›› (ሚኪ 7፡20)። እንዳለ መጽሐፉ የእግዚአብሔርን
ምህረት/ቸርነት ጥልቀት እና በእኛ አንጻር የተገለጸውን ፍቅሩን ለመግለጽ ‹ቸስድ›
በሚል ቃል የተሞላ ነው።
ዘኁ 6፡24-26፣ ኢዮብ 3፡26፣ መዝ 29፡11፣ ኢሳ 9፡ 6 እና ኢሳ
32፡17ን ያንብቡ። በዚህ ምንባብ ውስጥ ‹ሠላም› ወይም ሻሎም
የሚለው ቃል በእነዚህ ዘንድ ምንድን ነው የሚያወራው?
የእብራይስጡ ቃል ሻሎም ብዙ ጊዜ የሚተረጎመው ‹ሠላም› ተብሎ ነው ነገር ግን
የቃሉ ትርጉም በጣም የጠለቀ እና ከዚህም የሰፋ ነው። ‹‹ ሙሉነት፣ እንከን አልባነት
እና መልካም ሁኔታ ላይ መሆንን ›› ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የእግዚአብሔር
በረከት እና ጸጋ በሻሎም ደረጃ ይጠብቀናል/ያኖረናል። ያ ደግሞ የእግዚአብሔር
ስጦታ ነው (ዘኁ 6፡ 24-26)። በተጻራሪው የኢዮብ የችግር ልምምድ ‹‹ ‹በምቾት
አይደለሁም › ›› እርሱም ‹‹ ‹ዝምም › ›› አላለም ነበር ሻሎምን ባጣ ጊዜ። በዚህ
አስቸጋሪ አለም የሰንበትን ቀን ሻባት ሻሎም በሚል ቃል መቀበል በጣም የተረጋገጠ
በረከት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት የመጨረሻውን ሰላም እና
ሕይወታችን የሚፈልገውን ሙሉነት ይሰጠናል።
በምንም አይነት ቋንቋ ብንናገር እና ብናነብ ምንአልባትም የመጀመሪያውን
ትርጉም እንኳን ባናውቅ በተረዳነው መጠን እነዚህ ቃላቶች የሚሉትን
እውነታ በህይወታችን መለማመድ የምንችለው እንዴት ነው?
በእብራይስጥ አስተሳሰብ ትርጉምን የሚያጠናክሩ እና የንድፈ ሐሳቡን አስፈላጊነት የሚያጎሉ ሐሳብን መግለጫ የተለያዩ አይነት መንገዶች አሉ። እንደ አውሮፓውያን ቋንቋዎች በመጀመሪያው የእብራይስጥ ቋንቋ ምንም አይነት ስርአተ ነጥብ አልነበረም ስለዚህ የቋንቋው አወቃቀር እነዚህን ሐሳቦች የሚያስተላልፍበት የእራሱን መንገድ አሳድጎ ነበር። ዘፍጥረት 1፡26፣ 27 እና ኢሳያስ 6፡1-3ን ያንብቡ። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የትኛው ቃል ነው የተደጋገመው? እንዴት ነው እነዚህ ተደጋጋሚ ቃላቶች በተለያዩ ሐሳቦች በድግግሞሽ ውስጥ ሀሳቦችን የሚጨምሩት?
የእብራይስጥ ጸሐፊዎች የሆነን የእግዚአብሔር ባህሪ ትኩረት ለመስጠት ሲፈልጉ
ሶስት ጊዜ ያህል ሊደጋግሙ ይችላሉ። የእግዚአብሔር የፍጥረት ስራ ወደ ፍጻሜ
ሲመጣ እና ስለ ፍጥረት መግለጫ ሲሰጥ ጽሑፉ የተፈጠረው ሰብአዊነት ላይ
በተለየ አስፈላጊነቱን ያጎላዋል። ‹ባራ› የሚለው አባባል ‹‹ መፍጠር ›› እንደ ባለቤት
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ይይዛል። ቀደም ሲል በነበረ ቁስ ላይ ሳይደግፍ መፍጠር
የሚችል ሐይል ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለ ሰው አፈጣጠር የሚገልጸው
ቃል እንዲህ ይላል ‹‹እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ
ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ›› (ዘፍ 1፡27)። ይመልከቱ ሶስት ጊዜ
የተደጋገመውን ‹ፈጠረ› የሚለውን ቃል። ሙሴ ሰብአዊ ፍጥረት በእግዚአብሔር
እንደተፈጠረ ፣ በመልኩ እንደፈጠረውም ጭምር ትኩረት ሰጠ። ትኩረቱ እውነታው
ላይ ነበር።
በኢሳያስ እና ራዕይ እና ጥሪ ሱራፌል ‹‹ አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ
ነበር። ››(ኢሳ 6፡3) በማለት ቃላቱን ደጋገመው። ትኩረቱ ቤተመቅደሱን በሞላው
በአስደናቂው አምላክ ቅዱስነት ላይ ነበር። እንዲሁ ይህን ቅድስና በኢሳያስ ቃልም
ውስጥ እናያለን። በሐያሉ ፊት በቆመ ጊዜ ‹‹ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ
››(ኢሳ 6፡5) ብሎ ነበር። እንደ ኢሳያስ ያለ ነብይ እንኳን ከእግዚአብሔር ቅድስና እና
ባህሪ ጋር ሲጋፈጥ ስላለመገባቱ ያለቅሳል። ስለዚህ በሰው ሐጢያተኝነት እና አዳኝ
እንደሚያስፈልገው የጳውሎስን ማብራሪያ (ሮሜ 1-3) ገና ሳንመለከት እንደ ኢሳያስ
ባለ ‹‹መልካም ›› ሰውም እንኳን ስለ ወደቀው የሰው ተፈጥሮ መጽሐፍ ቅዱስ ገለጻን
እንደሚሰጥ ማየት እንችላለን።
በዳንኤል 3 ላይም በተለያየ አይነት ‹‹ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል›› (ዳንኤል 3፡1፣
2፣ 3፣ 5፣ 7፣12፣ 14፣ 15፣ 18) የሚለው ሀረግ ድግግሞሽ አለ። ይህ ሐረግ ወይም
የተለያየ አይነቱ እግዚአብሔር በዳንኤል አማካኝነት ለእርሱ ከገለጸው ምስል (ዳን
2፡ 31-45) በተጻራሪ ያለውን የናብከደነፆር ድርጊት ባለበት ምዕራፍ ውስጥ ከ 10
ጊዜ በላይ ተደጋግሟል። ትኩረቱ እውነተኛ አምላክ ከሆነው እግዚአብሔር እና
ብቸኛው አምልኮ ከሚገባው አምላክ በተጻራሪ ባለው በሰብአዊያን አምላክ የመሆን
እና የመመለክ ፍላጎት ላይ ነው።
በመጽሐፍት ውስጥ ቃላት ሁልጊዜ የሚከሰቱት በአገባብ ነው። ብቻቸውን አይቆሙም። ቃላት በአረፍተ ነገሩ ውስጥ ወዲያው አገባባቸውን ያገኛሉ እናም መጀመሪያ ሊረዱት የሚገባ ይህን ክፍል ነው ። ከዚያ ደግሞ የአጠቃላዩ ክፍል አገባብም አለ ፣ አረፍተነገሩ የሚገኝበት። ይሄ ምንአልባት የአንድ ጽሑፍ ክፍል፣ ምዕራፍ፣ ወይም ምዕራፎች ሊሆን ይችላል። ወደ ተሳሳተ መደምደሚያ ከመደረሱ በፊት ቃላቶች እና አረፍተ ነገሮች የገቡበትን አገባብ መገንዘቡ በጣም አስፈላጊ ነው። ዘፍጥረት 1፡27ን ከ ዘፍጥረት 2፡7 ጋር ያነጻጽሩ። ከዚያ ዘፍጥረት 2፡ 15-25ን ያንብቡ። ከእነዚህ የተለያዩ ንባቦች እና አገባቦች ስለ አዳም፣ የእብራይስጡ ቃል ‹‹ሰው›› የሚለውን ቃል ትርጉም እንዴት ነው ልንረዳ የምንችለው?
በ ዘፍ 1፡27 ላይ ያለውን ‹ ባራ › የሚለውን አባባል ድግግሞሽ ቀደም ሲል ተመልክተነዋል፣
ትኩረት የሚያደርገው በሰው ፍጥረት ላይ ነው። አሁን ሰው በዚህ አገባብ ውስጥ
ሲተረጎም ‹‹ወንድ እና ሴት ›› ተብሎ እናያለን። ይህ ማለት የእብራይስጡ አዳም የሚለው
አባባል በዚህ ክፍል ውስጥ በአጠቃላይ የሚያመለክተው ጠቅላላ የሰውን ዘር ወይም
ሰብአዊ ፍጥረትን በሙሉ ነው።
ቢሆንም ግን በ ዘፍ 2፡7 ባለው ተመሳሳይ አባባል አዳማ የሚለው ከአፈር ውስጥ ‹ከምድር
› የተሰራውን ያመላክታል። በዚህ ወንድ የሆነውን አዳምን ብቻ ያመላክታል፣ ሔዋን
አልተፈጠረችም ነበር። እስከሚቀጥለው የተለየ ሁኔታ ድረስ። ስለዚህ በእያንዳንዱ
ንባብ ውስጥ በሁለት ምዕራፎች አውድም ውስጥ በአዳም የ ‹ሰብአዊነት › (ዘፍ 1፡27)
እና ወንድ የሆነው አዳም( ዘፍ 2፡7)ትርጓሜ እንኳን ልዩነትን እናያለን። በዘር ውስጥ ኋላ
እንደተረጋገጠው (ዘፍ 5፡1-5፣ 1ኤና 1፡1፣ ሉቃ 3፡38) እና ኢየሱስ ‹ሁለተኛው አዳም›
(ሮሜ 5፡12-14) ሆኖ በተጠቀሰ ጊዜ ማለት ነው ያ አዳም ግለሰብ ነበር።
ልክ አዳም የሚለው ቃል በተወሰነ ጽሑፍ እንደመቅረቡ ሁሉ እንዲሁ የአዳም እና የሄዋን
አፈጣጠር አገባብ በትልቁ የፍጥረት ሁኔታ ውስጥም በዘፍ 1-2 ላይም ይገኛል። ይሔ
ነው እንግዲህ ትልቁ ክፍል የምንለው። እነዚህ ትልልቅ ክፍሎች ለተርጓሚው ተጨማሪ
አርእስት፣ ሐሳብ እና እድገትን ይሰጣሉ። ዘፍ 2፡ 4-25 አንዳንድ ጊዜ ሁለተኛው የፍጥረት
መግለጫ በመባል ይታወቃል ነገር ግን በሚሰጠው ትኩረት ላይ ብቻ የሚለይበት ልዩነት
ብቻ ነው ያለው(የሚቀጥለውን ሳምንት ይመልከቱ)። በሁለቱም መግለጫ ፣ በጥንካሬ
እንድናይ ያለው የተረጋገጠው የሰብአዊያን ምንጭ ነው።
መመልከት እንደምንችለው ወንድ፣ ሴት እና ሰብአዊ ዘር በቀጥታ
የእግዘአብሔር ፍጥረቶች ናቸው። በእውነት እኛን በማስተማር ይሔ በእድል
ብቻ እንደተነሰሳን አድርጎ የሚያስተምረው ‹‹የዚህ አለም ጥበብ›› (1ኛ
ቆሮ 1፡20) ሞኝነት እንደሆነ፣ ምን ይነግረናል?
ከቅዱሳት መጽሐፍ ትልቁ የሚባለው ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መጽሐፎች ለተለያ አላማ እና በተለያየ መቸት የተጻፉ ናቸው።
አንዳንዶች እንደ ትንቢታዊ መልእክት ሲያገለግሉ ሌሎች ደግሞ እንደ ስብስብቦች
ናቸው፣ ለምሳሌ እንደ መዝሙረ ዳዊት። ታሪካዊ መጽሐፍትም አሉ እንደ 1ኛ እና 2ኛ
ነገስት። እንዲሁም ለተለያዩ ቤተክርስቲያናት የተጻፉ ደብዳቤዎችም አሉ ለምሳሌ
በጳውሎስ እና በሌሎችም እንተጻፉት ያሉ።
የመጽሐፉን መልዕክት እና ትርጉም ለማወቅ ስንፈልግ እና ስንሻ ከባለቤትነት እና
ከመቸቱ መጀመር አስፈላጊ ነው። የመጀመሪያዎቹ የብሉይ ኪዳን አምስቱ መጽሐፍት
በሙሴ እንደተጻፉ ተለይተዋል ( ኢያሱ 8፡31፣ 32፣ 1ኛ ነገስት 2፡3፣ 2ኛ ነገስት
14፡ 6፣ 21፡ 8፣ ዕዝራ 6፡18፣ ነህሚያ 13፡1፣ ዳንኤል 9፡11-13፣ ሚልክ 4፡4)። ይሔ
በኢየሱስ (ማር 12፡26፣ ዮሀ 5፡46፣ 47 ፣ ዮሐ 7፡19 ) እና በሐዋሪያት ( ሐዋ 3፡22፣
ሮሜ 10፡5) ተረጋግጧል። በሌሎቹ ሁኔታዎች አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች
አልተለዩም። (ለምሳሌ የአስቴር መጽሐፍ ፣ እንዲሁም የሩት መጽሐፍ እና የብዙዎቹ
የታሪክ መጽሐፍት እንደ ሳሙኤል እና ዜና ያሉት ጸሐፊዎች አልተለዩም)
ዘፍጥረት 15፡1-5 እና ዘፍጥረት 22፡17ን ፣18ን ያንብቡ። የዘፍጥረትን
መጽሐፍ ሙሴ መጻፉ ለእኛ ምን ፋይዳ አለው?
ከዘጸአት እስከ ዘዳግም ድረስ የተጻፉት በሙሴ አማካኝነት ፣ ከዘጸአት በኋላ ነው።
ነገር ግን ዘፍጥረት ከእግዚአብሔር ስራ ጋር በተያያዘ ከፍጥረት እስከ ነገስታት ድረስ
መሰረታዊ በመሆኑ ምክንያት ከዘጸአት በፊት መጻፉ አሳማኝ ነበረ።
‹‹አመታት ሲሔዱ እና ሙሴ ከሚጠብቃቸው በጎች ጋር ጭር ባሉ ስፋራዎች ሆኖ
ሲገረም ሳለ ሕዝቡ ላይ ተጭኖ ያለውን የጭቆና ሁኔታ በሐሳቡ ያወጣና ያወርድ
ነበር። እግዚአብሔር ከአባቶቹ ጋር እና ከሕዝቡ ጋር የገባውን ኪዳን እና ሲተላለፍ
የመጣውን የተመረጠውን ሕዝብ የታሪክ ቅርስ እንደገና ያስብ ነበር እናም ስለ
እስራኤል የሚጸልየውን ጸሎት በቀን እና በማታ ያደርስ ነበር። ሰማያዊ መላእክት
ብርሃናቸውን በዙሪያው ያደርጉ ነበር። እዚህ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ግፊት የዘፍጥረትን
መጽሐፍ ጻፈ። ›› (ኤለን ጅ. ኋይት አበው እና ነብያት ገጽ 251)
በዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ምንጫችን ብቻ ሳይሆን ስለ ድነት ዕቅድም ተነግሮናል
ወይም እግዚአብሔር የወደቀውን አለም ስለሚያድንበት መንገድ ተነግሮናል።
እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን የበለጠ ዕቅዱ ግልጽ ሆነ። በእርሱ
አማካኝነት ስለሚያስነሳው ታላቅ ሕዝብ የገባውን ቃል ኪዳን ያካተተ ነበር ‹‹
በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር
እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ ዘርህም የጠላቶችህን ደጅ ይወርሳል ›› (ዘፍ 22፡17)
በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ያ ባይሆን ኖሮ ልናውቃቸው የማንችላቸው
ምን ሌላ ታላላቅ እውነታዎችን ተምረናል? የእግዚአብሔር ቃለ
ለእምነታችን ያለውን አስፈላጊነት ይህ እንዴት ያስተምረናል?
የኤለን ጂ . ኋይትን , “John Wycliffe,” ገጽ. 79–96; “Luther Before the Diet,” ገጽ 145–170እንዲሁ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ ክፍል 4.a.–
j. ከዶሴው ውስጥ “Methods of Bible Study,”የሚለውን ያንብቡ በሚከተለው
ድረ ገጽም ሊገኝ ይችላል፡ www.adventistbiblicalresearch.org/materials/
bible- interpretation-hermeneutics/methods-bible-study.
‹‹በቃሉ እግዚአብሔር ለሰዎች ድነት አስፈላጊውን እውቀት አስቀምጧል። ቅዱሳት
መጽሐፍት ስልጣን እንዳላቸው፣ የማይለወጥ የፈቃዱ መገለጥ እንደሆኑ መቀበል
ያስፈልጋል። የባህሪ መለኪያ፣ የስነ መለኮት አስተምህሮ መግለጫ፣ እና የልምምድ
መፈተኛ … ሆኖም ግን እውነታው እግዚአብሔር ፈቃዱን ለሰዎች በቃሉ ውስጥ
ገልጧል። ይህ ግን የመንፈስ ቅዱስ ተከታታይ እና የማያቋርጥ ምሪት አያስፈልግም
ማለት ግን አይደለም ። በተጻራሪው ለአገልጋዩ እንዲከፈት እንዲያበራ እና
በትምህርቱ እንዲኖር መንፈሱ በአዳኛችን ቃል ተገብቶልናል። የእግዚአብሔር
መንፈስ ነድቶ ስላጻፈው የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት ከቃሉ ጋር ተጻራሪ ሊሆን ከቶ
አይችልም ››(ኤለን ጅ ኋይት ፣ ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 9)
1.በቋንቋዎ ምንም ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ቢኖርም ባለዎት
ግን የበለጠን ነገር ለማድርግ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስን
እንደ የእግዚአብሔር ቃል ወስዶ ከፍተኛ ዋጋ ለመስጠት እና በእምነት
ለመፈለግ፣ አስተምህሮቱን ለመከተል አንዴት ነው ሊማሩ የሚችሉት?
2.የእግዚአብሔር ቃል ስለ ሰው አፈጣጣር የሚያስተምረውን
(በእግዚአብሔር በፍጥረት ሳምንት በስድስተኛው ቀን ተፈጠርን) እና
ሰብአዊያን እራሳቸው በሳይንስ ስም የሚያስተምሩትን ከ ቢሊዮን
አመታት በፊ በዝግመተ ለውጥ መጣን ከሚለው ጋራ ያለውን ልዩነት
አስቡ። ይሄ በሁለቱ መካካል ያለው ትልቅ ተቃርኖ መጽሐፍ ቅዱስ
በሚያስተምረው ላይ መጣበቅ አስፈላጊ እንደሆነ እናም ሰብአዊ ፍጥረት
ከእምላኩ እና በግልጽ ካለው አስተምህሮ ምን ያህል እንደሚርቅ
ምንድን ነው የሚነግረን?
3.ምን አይነት የበለጠ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የሚረዳ የመጽሐፍ
ቅዱስን የማጥኛ መሳሪያ አልዎት? ሌላ ተጨማሪ መሳሪያ ባይኖረዎትም
እንኳ በዚህ ሳምንት የተማርናቸውን አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስን
የመተርጎሚያ ትምህርቶችን መተግበር እንዴት ይችላሉ?
4.የእስራኤል ልጆች ለእነርሱ የተሰጣቸውን ታላቅ እውነት ለልጆቻቸው
እንዲያስተምሩ እና እግዚአብሔር በህይወታቸው እንዴት እንደመራቸው
ታሪካቸውን እንዲያስተላልፉ ተነግሯቸዋል (ዘዳ 4፡9 )። እምነትን
ማስተላለፍ ያለውን የታወቀ ጥቅምን እንኳ ብንተወው፣ በህይወታችን
እግዚአብሔር የመራንን ታሪክ ማስተማር እና መናገር አንዴት ነው
የእራሳችንን እምነት የሚያሳድገው? የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት
ከሌሎች ጋር መካፈል ትርፉ ለእራሳችንም እንዲሁ ይሆናል።