ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡- ማር. 7፡1-13፤ ሮሜ 2፡4፤ 1ዮሐ. 2፡15-17፤ 2ቆሮ. 10፡5-6፤ ዮሐ. 5፡46-47፤ ዮሐ. 7፡38።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም” (ኢሳ. 8፡20) ።
እ
ምነቶቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማስረጃነት የማያስደግፍ የክርስቲያን
ቤተክርስቲያን የለም። ነገር ግን የጥቅሶቹ ሚናና የሥነ መለኮት አስተምህሮ
ሀይል በሁሉም ቤተክርስቲያኖች የተለያየ ነው። እንደውም የጥቅሶቹ ሚና
ከቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ደረጃ ይለያያል። ይህ ትምህርት አስፈላጊ
ግን ደግሞ ውስብስብ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶቹ አተረጓጎም ላይ ተፅዕኖ
የሚያመጡ አምስት የተለያዩ ምንጮችን ይፈትሻል፡- ባህል፣ የህይወት ልምምድ፣
ልማድ፣ ምክንያታዊነት እና መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ናቸው።
እነዚህ ምንጮቹ በእያንዳንዱ የስነ መለኮት ትምህርት እና በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን
ላይ ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ። ሁላችንም ተፅዕኖ በሚፈጥሩብን የተለያዩ ባህሎችና
ልማዶች ውስጥ አልፈናል። አስተሳሰቦቻችንንና መረዳቶቻችንን ሲቀርጹም
አይተናል። ሁላችንም የሚያስብ እና ነገሮችን የሚገመግም አዕምሮ አለን። ሁላችንም
መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው እግዚአብሔርንና የእርሱን ፈቃድ ለመረዳት ነው።
ከነዚህ ምንጮች ውስጥ ወይም ደግሞ የእነዚህ ጥምረት በመጽሐፍ ቅዱስ
አተረጓጎማችን ላይ የመጨረሻ ገዥ ሀይል በመሆን እርስ በእርስ በመተሳሰር ጥቅም
ላይ የሚውሉት እንዴት ነው? ቅድሚያ የምንሰጠው ማንኛውም ምንጭ ወደ
ተለያየ ትንተናና ውጤት ያመራናል ያም በስተመጨረሻ የሥነ መለኮት ትምህርቶችን
አቅጣጫ ይወስነዋል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለመጋቢት 26 ሰንበት ተዘጋጁ።
ባህል በራሱ መጥፎ አይደለም። በየዕለት ህይወታችን የምናሳየውን የድግግሞሽ ኑሮ ያሳየናል። ከጥንቱ የመነሻ ማንነታችን ጋር ተቆራኝተን እንድንጸና ያግዘናል። በዚህ ምክንያት ባህል በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ድርሻን ይዞ መታየቱ እምብዛም አያስደንቅም። ማር. 7፡1-13 ላይ የሱስ በዚህ ምድር ላይ በነበረ ጊዜ ለአንዳንድ የሰው ልጆች ባህል የሰጠው ምላሽ ምን ያስተምረናል?
የሱስ የገጠመው ባህል በአይሁድ ማህበረሰብ ውስጥ ከመምህራን ወደ ህዝቡ
በጥንቃቄ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህል ነው። የሱስ በነበረበት ጊዜ ይህ የተነገረው
በባህር ዳርቻ አጠገብ እንደነበር ይገመታል። ባህል በረጅም ጊዜያት ውስጥ እያደገ
የመምጣት አዝማሚያ አለው። ሆኖም እያንዳንዱን ዝርዝር ነገር ለማከማቸት ስንጥር
ከቀደመው የእግዚአብሔር ቃል እና እቅድ ውጪ ይሆናሉ። የሰዎች ባህል በተከበሩ
“ሽማግሌዎች” (ማር. 7፡3፣ 5ን ይመልከቱ) ማለትም በአይሁድ ማህበረሰብ ውስጥ
በሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች ተላልፈው የተሰጡ ቢሆንም ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት
ጋር ግን ፈጽሞ እኩል መሆን አይችሉም (ማር.7፡8-9ን ተመልከቱ) ። እነዚህ የሰው
ባህሎች በስተመጨረሻ የሚያመሩን “የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ” ወደሚለው
ሃሳብ ነው። (ማር. 7:13) ።
1ቆሮ. 11፡2 እና 2ተሰ. 3፡6ን አንብቡ። የእግዚአብሔርን ቃልና
የሰዎችን ባህል እንዴት አድርገን እንለያለን? ይህንን መለያ ማድረጋችን
አስፈላጊነቱ ምን ያክል ነው?
ሕያው የሆነው የእግዚአብሔር ቃል በአምልኮ እና በታማኝነት አመለካከት እርሱን
እንድናይ ያደርገናል። ይህ ታማኝነት ደግሞ አንድ የሆነ ባህልን ይፈጥርልናል።
ታማኝነታችንን ሁልጊዜ ለህያው አምላክ፤ ፈቃዱን በተፃፈው ቃሉ ለገለጠልን ለርሱ
ልናቀርብ ይገባል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጆችን ሁሉ ባህሎች በመተካት
ረገድ የተለየ ሚና አለው። መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉም ባህሎች፣ ጥሩ ከምንላቸው
ባህሎች ይልቅ እንኳን ከፍ ብሎና ልቆ የሚታይ ነው። ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ
ውጪ ያዳበርናቸው ባህሎች በሙሉ ያለማቋረጥ በቅዱሱ መጽሐፍ ገመድ ተለክተው
መፈተሸ አለባቸው።
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የምናደርገውና ‹ባህል› ተብሎ ሊቀመጥ የሚችል ነገር
ምንድው? ለምንድው እነዚህን ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ለይቶ ማስቀመጥ
ሁልጊዜ አስፈላጊ የሚሆነው? በሰንበት ቀን ወደ ውይይት ቡድንዎ ሲመጡ መልሶን
ይዘው ይቅረቡ።
ሮሜ. 2፡4 እና ቲቶ 3፡4-5ን አንብቡ። የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ መቻሉን፣ ይቅር ባይነቱን፣ በጎነቱንና ፍቅሩን በህይወታችን የተለማመድነው እንዴት ነው? እምነታችን ለመረዳት አዳጋች የሆነ፣ የአለም እውቀት ሳይሆን በህይወታችን የተለማመድነው የመሆኑ አስፈላጊነት ምን ያህል ነው? በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ የህይወት ልምምዶቻችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚጣረስ መልኩ እምነታችንን በተሳሳተ አቅጣጫ ሊመራው የሚችልበት መንገድ አለን?
የህይወት ልምምድ ሰው ሆነን ስለመኖራችን ማሳያ ነው። ስሜቶቻችንና
አስተሳሰቦቻችን ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጫና ይፈጥራል። እግዚአብሔር እንደዚህ
አድርጎ የሰራን ከፍጥረታቱ ብሎም ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት በተጨባጭ
የሚቆራኘው እና ቅርጽ የሚይዘው በህይወት ልምምዶቻችን በኩል ነው።
የግንኙነታችንን፤ የሥነ ጥበብንና የሙዚቃን፤ የተፈጥሮን አስደማሚነት እንዲሁም
የማዳኑን ደስታ እና የቃሉን ተስፋ ውበት አይተን እንድንለማመድ የእግዚአብሔር
መሻት ነው። ሃይማኖታችንና እምነታችን ከአስተምህሮ እና ምክንያታዊ ከሆነ
ውሳኔዎች በላይ የሚልቅ ነው። በህይወታችን የተለማመድነው ነገር በእግዚአብሔር
ያለን እይታ እና የቃሉ መረዳታችንን አቅም ይቀርጻል። ነገር ግን የእግዚአብሔርን
ፈቃድ ወደ ማወቅ ስንመጣ የህይወት ልምምዶቻችን በግልጽ የተገደቡና ያልበቁ
መሆናቸውን ማስተዋል ያስፈልገናል።
2ቆሮ. 11፡1-3 ላይ የምናገኘው ማስጠንቀቂያ ምንድነው? የህይወት
ልምምዶቻችንን ማመን ምን ያክል ውሱንነት እንዳለው ምን ይነግረናል?
የህይወት ልምምዶች አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ የህይወት
ልምምድ የራሱ የሆነ ተገቢ ስፍራ አለው። በቃሉ ሊታወቁ እና ቅርጽ ሊይዙ
ብሎም ሊተረጎሙ ያሻቸዋል። አንዳንዴ ከእግዚአብሄር ቃል እና ፈቃድ ጋር
ያልተጣጣመን ነገር መለማመድ እንፈልጋለን። እዚህ ላይ ከኛ ልምምድና መሻት
በላይ የእግዚአብሄር ቃል ላይ መታመንን ልንማር ይገባል። የህይወት ልምዶቻችን
ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ስለመጣጣማቸው እና ግልጽ የሆነውን የመጽሐፍ
ቅዱስ ትምህርት አለመጣረሳቸውን ለማወቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል።
ፍቅር ለእግዚአብሔር እና ፍቅር ለሌሎች የሚለው እምነት (ሉቃስ 12፡
28-31ን ተመልከቱ) ዋነኛው ትዕዛዝ እንደ ሆነ ሁሉ በልምምዶቻችን
ውስጥ ላለው እምነታችንም ይሄ በጣም አስፈላጊ መሆኑ ግልጽ ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ የህይወታችንን ልምምምድ በእግዚአብሄር
ቃል የመመዘን አስፈላጊነት ምን ያክል ነው?
ሁላችንም የአንድ የተወሰነ ልማድ ወይም ልማዶች አካል ነን። ሁላችንም በልማዶቻችን ተፅዕኖ የተደረገብንና የተቃኘን ነን። ከዚህ ሊያመልጥ የሚችል ማንም የለም። በብሉይ ኪዳን የጥንታውያን እስራኤሎችን ታሪክ ስናይ በዙሪያቸው ባሉ ህዝቦች ልማድ መበላሸታቸውን ስናስብ እኛ ዛሬ የተለየን ወይም የተሻልን እንደሆንን እንድናስብ የሚያደርገን ነገር ምን አለ?
የእግዚአብሔር ቃል የተሰጠው በአንድ የተወሰነ ልማድ ውስጥ ቢሆንም ነገር ግን
በዚህ ልማድ ብቻ ታጥሮ የቀረ አልነበረም። ልማዶቻችን የእግዚአብሔር ቃል
መረዳታችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማድረጉ ባይካድም መዘንጋት የሌለብን ነገር ቢኖር
የእግዚአብሔር ቃል በዘር፣ በነገስታትና፣ በኑሮ እርከን ላይ ከተመሰረቱ ልማዶች
ሁሉ እጅግ የላቀ መሆኑን ነው። በዚህ አንድ ምክንያት ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን
ልማድ ሁሉ የሚበልጥ ሲሆን እንደውም በእያንዳንዱ ልማድ ውስጥ የሚገኙትን
የተሳሳቱ ነገሮች የመለወጥና የማረም አቅም አለው።
1ዮሐ. 2፡15-17ን አንብቡ። ዮሐንስ የዚህን አለም ነገር መውደድ
የለብንም ሲል ምን ማለቱ ነው? በአለም ውስጥ እየኖርን ነገር ግን
አለማዊ አስተሳሰብ ላይኖረን የሚችለው እንዴት ነው?
ልማድ ልክ እንደሌሎቹ የእግዚአብሔር ፍጥረታት በሀጢያት የተነሳ ጥቃት
ደርሶበታል። ከዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር ፊትም ይቆማል። አዎን የልማዶቻችን
አንዳንድ ክፍሎች ከእምነታች ጋር በሚገርም ሁኔታ ይጣጣማሉ ነገር ግን ሁለቱን
ለይተን ለማወቅ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። በአስተሳሰብ ደረጃ የመጽሐፍ ቅዱስ
እምነት ልማድን መገዳደር እና ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ የሆነ ልማድን መፍጠር
አለበት። ከሰማይ ጋር የሚያቆራኘን ነገር እስከሌለ ድረስ በከበበን ነገር ተውጠን እጅ
መስጠታችን የማይቀር ነው።
ኤለን ጂ ኋይት የሚከተለውን እሳቤ አስፍራለች “የክርስቶስ ተከታዮች
በመርሆዎቻችውና በፍላጎታቸው ከአለም ይለዩ። ነገር ግን ከአለም ውስጥ ራሳቸውን
አያገሉም። አዳኙ በተደጋጋሚ ከሰዎች ጋር ይቀላቀል የነበረው ከእግዚአብሔር ፈቃድ
ጋር የማይሄድ ነገራቸውን ለማበረታታት ሳይሆን እነርሱን ራሳቸውን ሊያከብራቸው
ነው።”
Ellen G. white, counsel to parents, Teachers, and students Regarding
chrisitan Educaiton, P. 323::
የትኛው የልማድ ክፍል ነው ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ጋር
የሚቃረነው? በጣም አስፈላጊው ነገር ደግሞ፣ እምነታችንን ሊያጎድፉ
የሚሞክሩ ነገሮችን በመቃረን እንዴት ጸንተን መቆም እንችላለን?
2ቆሮ. 10፡5-6፤ ምሳሌ 1፡7 እና ምሳሌ 9፡10ን አንብቡ። በአስተሳሰባችን ክርስቶስን የመታዘዛችን አስፈላጊነት ምን ያክል ነው? ለምንድው የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት የሆነው?
እግዚአብሄር የማሰብና በምክንያት የማሰላሰልን አቅም ሰጥቶናል። የእያንዳንዱ
ሰው እንቅስቃሴ እና የእያንዳንዱ ስነ መለኮታዊ የመከራከሪያ ሃሳቦቻችን የማሰብ
አቅማችንንና ድምዳሜ ላይ እንዴት እንደምንደርስ ታሳቢ ያደርጋሉ። ምክንያት አልባ
የሆነ እምነት የለንም። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በነበረው የመነቃቃትና በነጻነት የማሰብ
ዘመን የሰው ልጆች ምክንያታዊነት በተለይ በምዕራባውያኑ ማህበረሰብ ውስጥ አዲስና
ገዢ ሚና ነበረው። ይህም ከማሰብ አቅማችን በላይ ሄዶ ወደ ትክክለኛው ድምዳሜ ላይ
ይደርሳል።
እውቀቶቻችን ሁሉ የተመሰረቱት በስሜት ካካበትናቸው ልምዶቻችን ነው ከሚለው
እሳቤ በተቃራኒ የሰው ልጆች ምክንያታዊነትን እንደ ዋንኛ የእውቀት ምንጭነት
ያቀርባል። ይህ እይታ ምክንያታዊነት “rationalism” ይባላል። ሀሳቡም እውነት
የሚገኘው በስሜቶቻችን በኩል ሳይሆን አዕምሮአዊው ከሆነው ምክንያታዊነት ነው
የሚል ነው። በሌላ አገላለፅ እርግጥ የሆኑ እውነቶች አሉ የኛ ምክንያታዊነት ብቻ
በቀጥታ ሊጨብጧቸው የሚችሏቸው። ይህም የሰው ልጆች ምክንያታዊነትን መመዘኛ
ወይንም ልማድ አድርጎ ይቆጥራል። የቤተክርስቲያን ስልጣንን ጨምሮ በሚደነቅ ሁኔታ
የእግዚአብሔር ቃል ያለው ስልጣን በሙሉ አዲስ ገዢ ሃይል በሆነው ምክንያታዊነት
ስር ይሰግዳሉ። በሰው ልጆች ምክንያታዊነት ማረጋገጫ ያልተሰጠው ማንኛውም ነገር
ይጣላል ሃሳቡም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይወድቃል። ይህ አመለካከት ብዙ የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍሎች ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ሁሉም ተአምራቶች እና ከተፈጥሮ ውጭ
የሆኑ የእግዚአብሔር ድርጊት ለምሳሌ የክርስቶስ በአካል ከሞት መነሳት፣ የድንግሊቱ
መወለድ ወይንም በስድስት ቀን ፍጡራንን መፍጠር ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያክል ነው፤
እንደ እውነተኛና ተአማኒ ተግባር የሚቆጠሩ አይደሉም።
እውነታው ግን ምክንያታዊ ሀይላይችን ሳይቀር በሀጢያት የተጠቃ እና በክርስቶስ
አገዛዝ ስር መውደቅ እንዳለበት መዘንጋት የለብንም። ሰብአዊ ዘሮች ማስተዋላቸው
በሙሉ የተጨፈነና ከእግዚአብሔር ያፈነገጠ ነው (ኤፌ. 4፡18)። በእግዚአብሔር
ቃል አማካኝነት ብርሃን ሊፈነጥቅልን ይገባል። እግዚአብሔር የኛ ፈጣሪ መሆኑ
የሚያመለክተን ነገር ቢኖር በመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር የሰው ልጆች ምክንያታዊነት ራሱን
ችሎ ከእግዚአብሔር ውጪ በመሆን የተፈጠረ እንዳይደለ ነው። ይልቁንም “የጥበብ
መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።” (ምሳሌ 9፡10ን ከምሳሌ 1፡7 ጋር ያነፃፅሩ)።
ከተፃፈው የእግዚአብሔር ቃል የተዋሀደውን የእግዚአብሔርን መገለጥ ብቻ ስንቀበልና
በቃሉ ውስጠ የተፃፈውን ለመከተል ፈቃደኛ ስንሆን ያኔ ትክክለኛ ምክንያታዊነት
ይኖረናል።
ከመቶ አመታት በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሆነው ቶማስ ጀፈርሰን
የራሱን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ሲጽፍ ከእርሱ ምክንያታዊ እይታ አንፃር
የተቃራኒ የሚመስሉ ነገሮችን በሙሉ ቆርጦ አዘጋጀ። ሁሉም የክርስቶስ
ተአምራቶች ማለት በሚቻል መንገድ ትንሳኤውን ጨምሮ የተወገዱ ሃሳቦች
ናቸው። ይህ ብቻውን እውነትን ለመረዳት የሰው ልጅ ምክንያታዊነት
ውሱን ስለመሆኑ ምን ያስተምረናል?
መጽሐፍ ቅዱስን ለሰብአዊ ዘር የገለፀው መንፈስ ቅዱስ ከቃሉ በተቃራኒ እንድንሆን ወይንም ደግሞ ከቃሉ እንድናፈነግጥ አይመራንም። ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች መጽሐፍ ቅዱስ ከሰዎች ባህል፣ የህይወት ልምምድ፣ ምክንታዊነት እና ልማድ በላይ ከፍተኛውን የገዢነት ሀይል ይይዛል። ሁሉም ነገር ሊፈተሽ የሚገባው በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ዮሐ.5፡46-47 እና ዮሐ.7፡38ን አንብቡ። የሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን ለማስተዋል ዋነኛ ምንጩ ምን ነበር? መጽሐፍ ቅዱሳችን የሱስ እውነተኛ መሲህ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥልን እንዴት ነው?
አንዳንድ ሰዎች የተለየ ‹መገለጥ› በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንደተቀበሉ ያስባሉ ነገር ግን
ሃሳባቸው ግልጽ ከሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት ጋር የሚጋጭ ይሆናል። ለነዚህ
ሰዎች ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ መንፈስ ቅዱስ ትልቁን የገዢነት ስልጣን ይዟል።
የተጻፈውን ቃል የሚሽር እና ግጽ የሆነውን መልዕክት የሚጥስ ማንኛውም ሰው በአደገኛ
መሬት ላይ የሚራመድና የእግዚአብሔር መንፈስ ምሪትን የማይከተል ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛው መንፈሳዊ መከላከያችን ነው። እምነት እና ተግባሮቻችንን
በተመለከተ ልንተማመንበት የሚገባን ብቸኛ ልማዳችን ቃሉ ነው።
“በቃሉ አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ለአይምሮአችን ይናገራል በእውነቱም ልባችንን
ያስደንቃል። ስለዚህ ስህተቶቻችንን በማጋለጥ ከልባቻችን ላይ ያርቃቸዋል። ክርስቶስ
የተመረጡ ህዝቦቹን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የሚማርከው በእውነት መንፈሱ በኩል
በቃሉ እየሰራ ነው።” Ellen G. White, the Desire of Ages, P. 671.
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚተካ ተደርጎ መታሰብ የለበትም። ይልቁንም
እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተጣጥሞ በመስራት ወደ ክርስቶስ ይስበናል። ስለዚህ ቃሉ
ብቻ ነው ትክክኛ የመንፈሳዊነት መስመር እንደያዝን የሚያረጋግጥልን። መጽሐፍ ቅዱስ
ወሳኝ የሆነን አስተምህሮን ይሰጠናል (1ጢሞ. 4፡6ን አንብቡ) ።
የእግዚአብሔር ቃል
ተአማኒ እና ሙሉ ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባ ቃል ነው። ቃሉን ተቀምጠን የመፈረጅ
ስራ የእኛ አይደለም። ይልቁንም የእግዚአብሔር ቃል ነው እኛና ሃሳቦቻችን ላይ
የመፍረድ መብትና ስልጣን ያለው። ቃሉ የተፃፈው በራሱ በእግዚብሔር ነውና።
ከግል ስሜታችን ጋር ከተያያዘው የመደነቅ ሃሳብ በላይ ለመንፈሳዊ
ጥያቄዎቻችን መጽሐፍ ቅዱስ እርግጠኛ መመሪያችን የሆነው ለምንድው?
ሁሉንም ትምህርቶቻችንን መንፈሳዊ ልምምዶቻችንን ጭምር ለመፈተሸ
መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መመዘኛ አድርገን ባናስቀመጥ መዘዙ ምንድነው?
ለመንፈሳዊ ጥያቄዎቻችን ያለን የመጨረሻ ቃልና ምላሽ የግል መገለጥ
ቢሆን ይህ ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው ወደ ቀውስና ስህተት ሊመራን
የሚችለው?
ከኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ ውስጥ የሚከተለውን ርዕስ አንብቡ
“the Scriptures a safeguard` pp. 593-602, in The Great Controversy.
ባህል፣ የህይወት ልምምድ፣ ልማድ፣ ምክንያታዊነት እና መፅሐፍ ቅዱስ ሁሉም
በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተንጸባርቀው ታይተዋል። ወሳኙ ጥያቄ ታዲያ፦በስነ መለኮታዊ
ሃሳቦቻችን ላይ የመጨረሻው ድምጽ እና ስልጣን ያለው የቱ ነው የሚለው ነው?
የተረጋገጠ አንድ ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ ነው ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት
በኩል ነው ህይወታችን በመለወጥ ተጽዕኖን የሚፈጥረው።
“በቃሉ በኩል እግዚአብሔር ለድነት የሚያስፈልጋቸውን እውነት ሰጥቷቸዋል። መጽሐፍ
ቅዱስ የርሱን ፈቃድ ሳይሳሳት የገለፀ ስለሆነ እንደ ገዢ ሀይል ልንቀበለው ይገባናል።
ቃሉ የባህሪ መመዘኛ፣ አስተምህሮን የሚገልጥ እና የህይወት ልምምዶቻችንን የሚፈትን
ነው።” Ellen G. White, the Great Controversey. P.9.
1.የህጉ መንፈስ የሆነውን ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ
በፍጹም ሃሳብህ ውደድ እና ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ (ማቴ.22፡
37-40ን ተመልከት) የሚለውን ሃሳብ ከመኖር ይልቅ የሰዎች ዝርዝር
የሆነውን ባህል መኖር ቀላል የሆነው ለምንድነው?
2.በክፍሎ ውስጥ በእሁድ ክፍል መጨረሻ ላይ ለተጠየቀው ጥያቄ ይዛችሁ
የመጣችሁትን ምላሽ ተወያዩ። ባህል ውስጥ የምናያቸው በረከቶችና
ተግዳሮቶችን የት እናገኛለን?
3.ባህል ምንም ያክል ጥሩ ቢሆን ከተፃፈው ቃል በልጦ የኛ የመጨረሻ
ልማዳችን እና ስልጣን ያለው አለመሆኑን እርግጠኛ የምንሆነው እንዴት
ነው?
4.እንበልና አንድ ሰው /ሴት እግዚአብሔር በህልም ተናግሮኛል ቢል/
ብትልና እሁድ ቀን በአዲስ ኪዳን ጊዜ እውነተኛ የእረፍት ቀን ነበር
ቢለን ለዚህ ሰው ምን ምላሽ ይሰጡታል? ልክ እንደነዚህ ያሉ ታሪኮች
የህይወት ልምምዶቻችን ሁልጊዜ በቃሉ ሊፈተሸ እንደሚገባቸው ምን
ያስተምሩናል?
5.በመወያያ ክፍሎ ውስጥ ቤተክርስትያን ሰጥማ ስላለችበት ልማድ
ተነጋገሩ። ይህ ባህል በእምነታችን ላይ ተፅዕኖን የሚፈጥርብን እንዴት
ነው? አሁን ላይ ሆነን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናይ በታሪክ ውስጥ ልማድ
በቤተክርስቲያ አባላት ላይ በከፍተኛ ደረጃ አሉታዊ በሆነ መንገድ ተፅዕኖ
የፈጠረበት ምሳሌዎች ምንድናቸው? ተመሳሳይ ስህተት እንዳንሰራ ዛሬ
ከዚህ ልንወስደው የሚገባን ትምህርት ምንድነው?