በዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡- ፊሊ.2፡12-16፤ ሉቃ. 4፡4፣ 8፣ 10-12፤ መዝ.37፡7፤ መዝ.46፡10፤ መዝ.62፡1-2፣ 5፤ ቆላ.3፡16።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።” (ያዕ 1፡22)።
ከ
ቃሉ የተማርነውን ለመኖር እስካልቆረጥን ድረስ ምርጥ የተባለ የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥናት ቢኖረንም ጥቅም የለውም። በጠቅላላው ለተለያዩ ትምርቶች እውነት
የሆነው ነገር ሁሉ በተለይም መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠናም እውነት ነው። የላቀውን
ትምህርት የምንማረው በማንበብና በማድመጥ ሳይሆን ያወቅነውን በመለማመድ
ነው። መታዘዝ ከመለኮት ግምጃ ቤት የተትረፈረፈ በረከት ሊዘጋብን የነበረውን
በር እንዲከፈትልን ያደርጋል። መታዘዛችን በመደነቅ፤በማስተዋልና እውቀታችንን
በመጨመር ህይወትን ወደሚለውጥ መንገድ ይመራናል። በእግዚአብሔር ቃል
ለመመራት ፈቃደኞች ካልሆንንና ያጠናነውን ተግባራዊ ለማድረግ ካልፈቀድን
አናድግም። ህይወታችን ከቃላችን ጋር ስለማይጣጣም ምስክርነታችን ይጎዳል።
በእግዚአብሔር ቃል መኖር ማለት ምን መሆኑን ባሳየንና ባነሳሳን በርሱ
በኩል በጸጋና በጥበብ እናድጋለን። ከየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ማንም ምሳሌያችንንና
አነቃቂ ሀይላችን ሊሆን አይችልም። እንድንከተለው የሚያደርገንን ፈለግ ተወልን።
ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚስማማን ህይወትም ኖረ።
በዚህ ሳምንት በእግዚአብር ቃል እና በመለኮት ስልጣን ስር መሆን ማለት
ምን ማለት እንደሆነ እናጠናለን።
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለግንቦት 29 ሰንበት ይዘጋጁ።
የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና በጥንቃቄ እና ትክክለኛ በሆነ ዘዴ መሆኑ
በጣም አስፈላጊ ነው። ልክ እንደዚሁ ሁሉ እንደውም በበለጠ ደረጃ አስፈላጊው
ነገር የተማርነውን በህይወታችን መለማመድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት
የመጨረሻው ግብ ታላቅ እውቀትን በሚደንቅ ሁኔታ መያዝ ላይ የተመሰረተ
አይደለም። ግቡ ቃሉን ጠንቅቆ ማወቅ ሳይሆን ጠንቅቀን ያወቅነውን የእግዚአብሔር
ቃል ህይወታችንንና የአስተሳሰባችንን መንገድ መቀየሩ ላይ ነው።
ግድ ሊለን የሚገባው ነገር ቢኖር እርሱ ነው። የተማርነውን እውነት ለመኖር
ፈቃደኛ መሆን ማለት ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ራስን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ
መሆን ማለት ነው። ይህን መምረጥ አንዳንዴ አስጨናቂ ትግል ውስጥ እንድንገባ
ያደርገናል። ምክንያቱም የምንዋጋው ውጊያ ከኛ አስተሳሰብ እና ህይወት በላይ
የበላይነት ካለው ሀይል ጋር ነው። እናም በስተመጨረሻ ወስነን የምንመርጣቸው
ሁለት ጎራዎች ብቻ አሉ።
ፊሊ.2፡12-16ን አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እንዴት መኖር እንዳለብን
ምን ይነግሩናል?
አዎ፣ እግዚአብሔር በኛ ውስጥ ይሰራል ነገር ግን ይህንን የሚሰራው መጽሐፍ
ቅዱስን እንድናስተውል ጥበብን በሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው። ከዚህም
በተጨማሪ እንደ ሀጢያተኛ ሰብአዊ ተፈጥሮአችን የእግዚአብሔርን እውነት ብዙ ጊዜ
በመቃወም የእግዚአብሔርን ቃል ስንታዘዝ ለራሳችን ሀሳብ እንተዋለን (ሮሜ.1፡25፤
ኤፌ.4፡17-18)። ያለ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መልዕክት ልንወድ አንችልም።
ተስፋ የለም፣ መተማመን የለም፣ የፍቅር ምላሽም አይኖርም። በመንፈስ ቅዱስ
አማካኝነት እግዚአብሔር በእርግጥም ይህንን ይለናል። “ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም
ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” (ፊሊ. 2፡13) ።
መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ ወደሆነው ወደ ቃሉ መረዳት እና በቃሉ ወደ መደነቅ
ደስታ ሊመራን የሚሻ መምህራችን ነው። የእግዚአብሔር ቃልን እውነት ወደ እኛ
ትኩረት በማምጣት በእውነቶቹ አዲስ እይታ እንዲኖረን ያደርገናል። በዚህም
የተነሳ ህይወታችንን በሙሉ በታማኝነት እና ለእግዚአብሔር ፈቃድ በፍቅር ወደ
መታዘዝ ባህሪ ያመጣዋል። “ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ማንም ቃሉን ሊያብራራ
አይቻለውም። ነገር ግን ቃሉን በትህትናና ለመማር ፈቃደኛ በሆነ ልብ ስንወስደው
የእግዚአብሔር መላዕክት በእውነቱ ማረጋገጫ ሊያስደምሙን ከኛ ጎን ይቆማሉ።”
Ellen G. white, Selected message, book 1, p. 411። በዚህ መንገድ መንፈሳዊ
ነገሮች የሚተረጎሙት በመንፈስ ነው (1ቆሮ.2፡13-14)። የእግዚአብሔርን ቃል “ማለዳ
ማለዳ” (ኢሳ.50፡4-5) በደስታ ለመከተልም ይቻለናል።
ፊል.2፡16 እንደሚነግረን ከሆነ “የህይወትን ቃል እያቀረባችሁ”
ይለናል። ይህ ምን ማለት ይመስልዎታል? ይህንን ማድረግ የሚቻለን
እንዴት ነው? ተመሳሳይ ነገር የሚያስተምረንን ዘዳ.4፡4ን ተመልከቱ።
በዚህ ሁሉ ሂደቱ ውስጥ የእኛ ሚና ምንድነው?
ከየሱስ ክርስቶስ በላይ የተሻለ ሆኖ ሊያበረታታን የሚችል ምሳሌ የለም። ቃሎቹን ያውቃቸዋል እናም የተፃፈውን የእግዚአብሔር ቃል ለመከተልና በነርሱ ለመኖር ፈቃደኛ ነው። ሉቃስ 4፡4፣ 8፣ 10-12ን አንብቡ። የሱስ የሰይጣንን ፈተና ለመጋፈጥ ቃሉን እንዴት አድርጎ ተጠቀመ? በተለይም በፈተና ወቅት ለእምነታችን ቃሉ ምን ያክል ማዕከላዊ ስፍራን እንደሚይዝ ይህ ምን ይነገረናል?
የሱስ ቃሉን በሚገባ ያውቀዋል። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በቅርበት
ስለሚተዋወቅ ነበር በልቡ ውስጥ ያለውን ጥቅስ የጠቀሰው። ከተፃፈው ቃል ጋር
በሚገባ እንዲተዋወቅ ያደረገው ቃሉን በማጥናት ውድ የሆነ ጊዜውን ከእግዚአብሔር
ጋር በማሳለፉ ነው።
ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት እና የአውዱን ሂደት ባያውቅ
ኖሮ በቀላሉ በሰይጣን ይታለል ነበር። ሰይጣን እንኳን ሌሎችን ለማሳሳት ሲል
መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቅሳል። ልክ ሰይጣን እንዳደረገው ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ጥቅሶችን መጥቀስ በቂ አይደለም። ቃሉ በዚህ ርዕስ ላይ የሚላቸውን ነገሮች
በሙሉ ማወቅ እና ትክክለኛ ትርጉማቸውን መረዳት ያስፈልጋል። በእንደዚህ መልኩ
ከእግዚአብሔር ጋር መተዋወቃችን ብቻ ነው ልክ እንደ የሱስ በእግዚአብሔር
ተቃዋሚዎች እንዳንሞኝ እና የሰይጣንን ጥቃት እንድንቋቋም የሚያደርገን። በተለያየ
ጊዜ ስለ የሱስ ስናነብ የሱስ ተከታዮቹ ያስተውሉ ዘንድ “ተጽፏል” የሚለውን ሀሳብ
ይነግራቸዋል (ሉቃስ 24፡45-46፤ ማቴ.11፡10፤ ዮሐ.6፡45)። መጽሐፍ ቅዱስን
የሚያነቡ ሰዎች ሁሉ ትክክለኛ ወደ ሆነ መረዳት እንዲመጡ ይፈልጋል “በህግ
የተፃፈው ምንድነው? እንዴት ታነበዋለህ? አለ።” (ሉቃስ 10፡26) ። የሱስ በቃሉ
ላይ በተጻፈው መሠረት ልኖር እንደሚገባን እንድንኖር ይፈልጋል።
ዮሐ.7፡38 ላይ የእግዚአብሔር ቃል ስጋ የሆነው የሱስ መጽሐፍ ቅዱስ
ምን እንደሚል መለስ ብሎ ለተከታዮቹ ጠቀሰላቸው። የሱስ ቃል የተገባልን መሲህ
መሆኑን ማወቅ የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ስለእርሱ የሚመሰክርልን
ቃሉ ነው (ዮሐ.5፡39)። የሱስ ራሱ ለተፃፈው የእግዚአብሔር ቃል ለመታዘዝና
ለመኖር ፈቃደኛ ነበር። እርሱ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ እኛ ደግሞ ምን
ማድረግ እንዳለብን ያሳስበናል?
ከፈተናዎ ጋር በሚፋለሙበት ጊዜ ቃሉን የተጠቀሙበት
የህይወት ልምምድዎ ምን ይመስል ነበር? ይህም ማለት ስትፈተኑ
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ትጀምራላችሁ ወይንም ከቃሉ ጥቅሶችን
ትጠቅሳላችሁ በዚህ ምክንያት ውጤቱ ምን ሆነ? ከዚህ የህይወት
ልምምድ ምን ተማራችሁ?
ዮሐ.5፡45-47ን አንብቡ። የሱስ ከቃሉ ጋር ስላለው ግንኙነት ምን አይነት አስደናቂ መልዕክት ተናገረ?
አንዳንድ ሰዎች እንደሚናገሩት የሱስ የተናገራቸው ቃላቶች በብሉይ ኪዳን
ላይ እንዲሁም ከቃሉ ከምናገኛቸው ሀሳቦች ጋር ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ ናቸው።
እነርሱ እንደሚሉት የየሱስ ቃላት ከመጽሀፍ ቅዱስ ቃላት በላይ ሆነው የተቀመጡ
ናቸው።
በአዲስ ኪዳን ላይ እንደምናነበው የሱስ ሲናገር “እንዲህ ሲባል
ሰምታችኋል… እኔ ግን እላችኋለሁ…” (ማቴ.5፡43-44ን ከማቴ.5፤21-22፣ 27-28፣
33-34፣ 38-39 ጋር አነፃፅሩ)። የሱስ እነዚህን ዝነኛ የሆኑ ቃላት በተራራ ላይ ሲናገር
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች እንደሚሉት ብሉይ ኪዳንን እየተወ ወይም
እየደመሰሰ አልነበረም። ከዛ ይልቅ በወቅቱ ለነበሩ እግዚአብሔር ያልፈቀደውንና
ያላዘዘውን የተለያዩ ትርጉሞችንና አፈታሪኮችን ለሚናገሩ ሰዎች ልክ ጠላትህን ጥላ
(ማቴ.5፡43) ተብሎ እንደተነገረው አይነት ለሚሉ ለአንዳንድ ተርጓሚዎች ምላሽ
እየሰጠ ነበር።
የሱስ በምንም አይነት መንገድ እና በምንም አይነት መጠን ብሉይ ኪዳንን
አልሻረም። እንደውም እውነታው ተቃራኒው ነው። የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ራሱ
ነው እርሱ ማን እንደሆነ ያረጋገጠው። ከዚህ ይልቅ እንደውም ወደ እግዚአብሔር
ቀዳሚ የመነሻ ፍላጎት በማመላከት የብሉይ ኪዳንን ትርጓሜ አብራርቶ አጠናከረ።
የሱስ ያለውን ስልጣን ተጠቅሞ ቅዱስ ቃሉን እንደሻረ ማሰብ ወይንም ደግሞ አንዳንድ
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በምሪት አልተፃፉም ብሎ ስም ማጥፋት ምናልባት አንዱ
የማታለል ግን ደግሞ በጣም አደገኛ አካሄድ እና ቃሉን የመተቸት መንገድ ነው።
ምክንያቱም ይህ ሁሉ የሚደረገው በየሱስ ስም ስለሆነ። የሱስ ለቃሉ ማለት እርሱ
በነበረ ጊዜ ለነበረው ብቸኛው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ የሰጠውን ስልጣን እንደ
አብነት ተመልክተናል። ታዲያ ከዚህ በላይ ብሉይ ኪዳንን የምናይበትን መንገድ
የሚገልጽ ሌላ ምን መረጃ ይኖረናል?
የሱስ የቃሉን ሃይል ከማዳከም በራቀ ሁኔታ እንደውም ያለማቋረጥ መጽሐፍ
ቅዱስን እንደ እውነተኛ እና ተአማኒ መመሪያ አድርጎ አቅርቦታል። እንደውም
በማያሻማ ሁኔታ በዛው በተራራው ስብከቱ ላይ “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር
የመጣሁ አይምሰላችሁ፣ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።” (ማቴ.5፡17) ብሎ
ገልጾልናል። ቀጠል አድርጎም እንዲህ ብሏል “እንግዲህ ከእነዚህ ከሁሉ ካነሱት
ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግስተ
ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል።” (ማቴ.5፤19)።
በዚህ ወቅት በብሉይ ኪዳን ላይ መሠረታቸውን የጣሉ አንዳንድ
ወሳኝ አስተምህሮዎች ምንድናቸው? ለምሳሌ ስለ ፍጥረት (ዘፍ.1፡
2) እና ውድቀት (ዘፍ.3)ን አስቡ። በብሉይ ኪዳን ያገኘናቸው ወሳኝ
የክርስቲያን እውነቶች በኋላም በአዲስ ኪዳን የበለጠ ጎልተው የታዩ
ሃሳቦች ምንድናቸው?
ህይወታችን በግርግር በውጥረትና በጭንቀት የመሞላት አዝማሚያ
አለው። አንዳንድ ጊዜ ለመኖርና ጠረጴዛችን ላይ ምግብ እንዳይታጣ ታትረን
መስራት ይጠበቅብናል። ሌላ ጊዜ ደግሞ በህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲኖሩን
ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን ስለምንፈልግ ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ እንገባለን። እኛን
ደስተኛና ሙሉ ያደርገናል ብለን የምናስባቸውን ነገሮች ለማግኘት እንፈልጋለን። ነገር
ግን ሰለሞን በመክበብ መጽሀፍ ላይ እንደሚያስጠነቅቀን ከሆነ ይህ የማይሆን ነገር
ነው።
ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ህይወታችን አስፈሪ በሆነ ሁኔታ በስራ ውጥረት
የተሞላ ነው። ስለዚህ በዚህ የሥራ ውጥረት መካከል እግዚአብሔርን ገሸሽ ማድረግ
ይቀለናል። ስላላመንን ሳይሆን በማንበብ፣ በመጸለይ እና ወደ ጌታ በመቅረብ ጥራት
ያለውን ጊዜ ማሳለፍ ባለመቻላችን ብቻ ነው። እርሱ “ትንፋሽህን በእጁ ይዟል”
(ዳን.5፡23)። ጥራት ያለውን ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ትኩረታችንን
በሌሎች ነገሮች ላይ በማድረግ በቀላሉ አቅጣጫ እንዲቀይር ልናደርግ እንችላለን።
ሁላችንም እያወቅን በዝግታ አዳኛችን ከሆነው የሱስ ጋር የምናሳልፋቸው ጊዜያቶች
ያስፈልጉናል። ለማድመጥ ቆም እስካላልን ድረስ መንፈስ ቅዱስ እንዴት አድርጎ
ይናገረናል? ቃሉን በማንበብ እና በፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት በማድረግ
የተለየ የጽሞና ጊዜ መውሰዳችን ነው የመንፈሳዊ ሕይወታችን ምንጭ የሚሆነን።
መዝ.37፡7፤ መዝ.46፡10 እና መዝ.62፡1-2፣ 5ን አንብቡ። እነዚህ
ጥቅሶች የፀጥታ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ስለማሳለፍ ምን የሚያስተምሩን
ነገር አለ? ለምንድነው ከእግዚአብሔር ጋር የፀጥታ ጊዜ መውሰድ
አስፈላጊ የሆነው።
አንድን ሰው ስትወዱ ከዛ ከምትወዱት ሰው ጋር በማሳለፋችሁ ትደሰታላችሁ።
ያለ ምንም መረበሽ ቃሉን የምታነቡበት እና የምትረዱበትን አንድ ስፍራ ምረጡ።
ግርግር በሞላው ሕይወትዎ ውስጥ ይህ ሊሳካ የሚችለው ለመገናኘት የተለየ ጊዜ ሆን
ብላችሁ መመደብ ስትችሉ ብቻ ነው። ብዙ ጊዜ የቀኑ የመጀመሪያ ጊዜያት የፀጥታ
ደቂቃዎችን ለማግኘት የተመረጡ ጊዜያቶች ናቸው።
ስራ ከመጀመራችን በፊት ያሉት ጊዜያቶች ለቀሪው የቀን ክፍለ ጊዜያቶች ሁሉ በረከት
ሆነው ሊቆዩ ይችላሉ። ምክንያቱም ያገኛችኋቸው ውድ የሆኑ እሳቤዎች ለብዙ
ሰአታት አብረዋችሁ ይዘልቃሉና። ነገር ግን ያለምንም መረበሽ ከእግዚአብሔር ጋር
ለመገናኘት ትክክለኛውን ደስ የሚያሰኝ ጊዜ በማግኘት ረገድ የፈጠራ አቅማችሁን
ተጠቀሙ።
ከማንኛውም ነገር ይልቅ ከህያው አምላክ ጋር በፀሎት መገናኘት
ህይወታችን ላይ ተጽዕኖን ይፈጥራል። በስተመጨረሻም የሱስን እንድንመስል እገዛ
ያደርግልናል።
ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ጊዜ ለማሳለፍ ሆነ ብላችሁ ምን ያክል
ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ? እነዚህ ጊዜያቶች ምን ይመስላሉ? ይህ
እንዴት አድርጎ ነው ስለ እግዚአብሄርና ስለ ፍቅሩ እውነታ የበለጠ
እንድንረዳ ሊያግዘን የሚችለው?
“አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።” (መዝ.119፡11)።
የእግዚአብሔርን ቃል በአዕምሮአችን መያዝ ብዙ በረከቶችን ያመጣልናል።
የከበሩትን የእግዚአብሔር ቃል ጥቅሶች ወደ ውስጣችን ስናስገባ በቃላችን በያዝነው
ጥቅስ በኩል የተሰጠ ህይወትን ለመኖር፣ በአዲስ እና ሁኔታዎችን በሚለውጥ መንገድ
ተግባራዊ ለማድረግ ወደሚቀና ህይወት እንመጣለን። በዛ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ
በቀጥታ አስተሳሰቦች፣ በውሳኔዎቻችን ዋጋ በምንሰጣቸው ጉዳዮች፤ እንዲሁም
ባህርያቶች ላይ ተፅዕኖን ይፈጥራል። መጽሐፍ ቅዱስን በቃላችን ማስታወስ
ቃሉን ወደየእለት የህይወታችን ልምምዶች ያቀርብልናል። ከዚህም በተጨማሪ
እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ እንደቃሉ መሠረት በታማኝት ለመኖር ያግዘናል።
መጽሐፍ ቅዱስን ቃል በቃል ማስታወስ ከመታለልና ሀሰተኛ ከሆነ ትርጓሜ
እንድንጠበቅ ያደርገናል። በልባችን ውስጥ ይዘን የተማርናቸው ጥቅሶች መጽሐፍ
ቅዱስ በማናገኝበት ሁኔታ ላይ እንኳን ቃሉን እንድንጠቅስ ያስቸለናል። ፈተና
ሲነሳብን ወይንም የባላንጣችን ተግዳሮት በገጠመን ጊዜ አስደናቂ ሀይል ይሆነናል።
ከችግሮቻችን ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳኖች ስናስታውስ እና አስተሳሰባችን
በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሲተከል እኛ ማየት ባንችል እንኳን በሺህ መንገዶች ወደ
እግዚአብሔር ሃሳቦቻችን ከፍ እንዲሉ ያደርጋል።
ኤፌ.5፡19ን እና ቆላ.3፡16ን አንብቡ። የእግዚአብሔርን ቃል መዘመር
ቃሉን በአዕምሮአችን ውስጥ እንዲመሰረት እና እንዲጠነክር እንዴት
ነው የሚያደርገው?
የእግዚአብሔርን ቃል መዘመር መጽሐፍ ቅዱስን በቃል ለማስታወስ ትልቁ
መንገድ ነው። ስንዘምር ሳለ የእግዚአብሔር ቃል በቀላሉ ይታወሰናል። የእግዚአብሔር
ቃል ከተዋቡ ዜማዎች ጋር ሲዋሃድ ከአስተሳሰባችን ጋር በጥብቅ ይቆራኛል ውጤታማ
በሆነ መንገድም አስጨናቂ ስሜቶቻችንንም ይበታትናቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥቅሶች ቀለል ባለና በተዋበ ጣዕመ ዜማ ተቆራኝተው በትንንሽ ልጆችና በአዋቂዎች
ዘንድ በቀላሉ ሊዘመሩና በቃል ሊታወሱ ይችላሉ። አያሌ የአለማችን አንደበተ ርቱዕ
ተናጋሪዎችን፣ የኦርኬስትራ ሙዚቃዎችንና ሌሎች ሙዚቃዎችን ቅርፅ በማስያዝ
በምዕተ ዓመታት ውስጥ የክርስቲያኖች ባህል ላይ ተፅዕኖን በማምጣት መነቃቃትን
የፈጠረው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አእምሮአችንን ከፍ የሚያደርጉና አስተሳሰባችንን
ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ቃሉ የሚያቀኑ የሙዚቃ ቅንብሮች በህይወታችን ውስጥ
አስደናቂ በረከቶች እና በጎ ተፅዕኖን የሚፈጥሩ ናቸው።
“ሙዚቃ በላይ በዙፋኑ ፊት እንዳለ እግዚአብሔርን የማምለክ ሁኔታን
ይፈጥራል እናም ልንጥር የሚገባን ነገር ቢኖር የምስጋና መዝሙራችን በተቻለ መጠን
ሰማያዊ ከሆኑ የመዘምራን ጣዕመ ዜማ ጋር ተቀራራቢ እንዲሆን ነው።” Ellen G.
white, Patriarchs and Prophets, p. 549.
Read Ellen G. White, `The Private of prayer` pp. 93104 in steps to chirst
“ተፈጥሮአዊው አይን የክርስቶስን መልካምና የተዋበ አይን ፈፅሞ ማየት
አይችልም። መንፈስ ቅዱስ የውስጥ የመረዳት ብርሃናችንን በማብራት ተስፋ የለሽ
ለሆነች ነፍሳችንና ረዳት አልባ ለሆነው ሁኔታችን፤ ለሁሉ በቂ ወደሆነው ክርስቶስና
ቁጥር ስፍር ወደሌለው ምህረቱ፣ ወደማይለካ ፍቅሩ፣ ወደቅንነት እና ክብሩ
ይመራናል።” Ellen G. White, The upward look, p. 155.
“የቃሉ የተወሰነ ክፍል ወይም ሙሉ ምዕራፉም ቢሆን በቃል ሊታወሱ
ይገባል። ሰይጣን ሊፈትነን ሲመጣ ደጋግመን ልንላቸው እንችላለን… ሰይጣን
አስተሳሰባችን በምድራዊ እና ስሜትን በሚያነቃቁት አለማዊ ምኞቶች ላይ
እንዲያተኩር ሲያደርግ “ተጽፏል እያልን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንቃወማለን።”
The Advent Review and Sabbath Herald, April 8, 1884.
1.እምነት እና መታዘዝን በተመለከተ የነፃ ፍቃድ እና የነፃ ምርጫ
እውነቶች ለውሳኔዎቻችን ሁሉ ትልቅ ሚና የሚጫወቱት እንዴት ነው?
ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ፣ ከዘላለም ህይወት ጋር በተያያዘ
ጉዳዮች ላይ ህይወታችን ምንም እንኳን ከቁጥጥር ውጪ ቢሆንብንም
እግዚአብሔር በሰጣችሁ ነፃ ፈቃድ ምን ታደርጉበታላችሁ? ምን አይነት
መንፈሳዊ ምርጫንስ ትመርጣላችሁ?
2.ሰንበት ከእግዚአብሔር ጋር የጥሞና ጊዜን በመስጠት ረገድ ስላለው
ሚና እስቲ አስቡ። ሰንበትን መጠበቅዎ በስራ ተጠምደው ከእግዚአብሔር
ጋር ጊዜ እንዳያሳልፉ የሚከላከልልዎ እንዴት ነው? ሰንበት ትርጉም
ያለው መንፈሳዊ ባርኮት እንዲሆንልዎ እንዴት መማር ይችላሉ?
3.ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ በፀሎት እና ቃሉን በማጥናት ጊዜ በማሳለፍዎ
ምን የህይወት ልምምድን አገኙ ይህ መንፈሳዊ ልምምድስ እምነትዎ
ላይ ምን ተፅዕኖን አመጣ እምነታች ላይ ምን ፈጠረ በውይይት ክፍሎ
ውስጥ ምቾት ከተሰማዎ በቃሉ ንባብ እና በፀሎት በግልዎ ሲያሳልፉ
ምን እንዳተረፉ ይናገሩ። ከዚህ የተማራችኋቸው ሌሎች ጥቅሞችስ
ምንድናቸው?
4.በቃላችሁ የምታስታውሷቸው የምትወዷቸው አንዳንድ ጥቅሶች
የትኞቹ ናቸው በጣም እንድትወዷቸው ያደረጋችሁ ነገርስ ምንድነው?
እነዚህን በቃል መያዛችሁ ለእናንተ በረከትን ያመጣላችሁ እንዴት
ነው?