ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዳንኤል 7፣ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡-1-12፣ ሮሜ 8፡-1፣ ማርቆስ 13፡-26፣ ሉቃስ 9፡-26፣ ሉቃስ 12፡- 8፣ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡-5ን ያንብቡ።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።”(ዳንኤል 7፡-27)
የ
ዚህ ሳምንት ርዕሳችን የሆነው የዳንኤል ምዕራፍ 7 ራዕይ ፣ ከዳንኤል ምዕራፍ
2 ህልም ጋር ይመሳሰላል። ነገር ግን ዳንኤል ምዕራፍ 7 በዳንኤል ምዕራፍ 2
የተገለጸውን ያብራራል። አንደኛ፣ ራዕዩ የታየው በማታ ሲሆን የሚያሳየውም
በአራቱ ነፋሳት የተነሳውን ባህር ነው። ጨለማ እና ውሃ ፍጥረትን ያስታውሳሉ፣
ነገር ግን እነዚህ ፍጥረታት በሆነ መንገድ ሲበጠበጡ ወይም በጥቃት ላይ ሲሆኑ
ይታያል። ሁለተኛ፣ በራዕይ ውስጥ ያሉት እንሰሳዎች እርኩስ እና ድቅል ናቸው፣
ያም የሚያሳየው የተፈጥሮ ስርዓትን መጣስ ነው። ሶስተኛ፣ እንሰሳዎቹ ግዛትን
ሲያስፋፉ ይታያሉ፣ ስለዚህ ለአዳም እግዚአብሔር የሰጠው ግዛት በኤድን ገነት
ውስጥ በእነዚህ ሀይሎች ያለአግባብ ሲያዝ ያሳያል። አራተኛ፣ ከሰው ልጅ መምጣት
ጋር ተያይዞ የእግዚአብሔር ግዛት ለሚገባቸው ተመልሷል። በኤደን አዳም ያጣውን
፣ የሰው ልጅ በሰማያዊ ፍርድ መለሰው።
ቀደም ሲል የቀረበው ሐሳብ ፣ በዚህ ከፍተኛ የሆነ ስዕላዊ ራዕይ ውስጥ ለውስጥ
እተካሔደ ያለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስዕል፣ ሰፊ የሆነ ምልከታን በማሳየት ገለጻ
የሚሰጥ ነው። እንደ እድል ሆኖ በጣም ወሳኝ የሆኑ የራዕዩ ዝርዝሮች በመልአኩ
አማካኝነት ተገልጸዋል፣ ስለዚህ የዚህን አስደናቂ ትንቢት ዋናውን ቅርጽ እንረዳለን።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ የካቲት 14 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ዳንኤል 7ን ያንብቡ። ዳንኤል ያየው ፍሬ ነገር ምንድን ነው? እናም ራዕዩ ስለምንድን ነው?
ዳንኤል የያቸው እንሰሳዎች እያንዳንዳቸው ናቡከደነጾር ያየው ምስል የአካል
ክፍሎች ናቸው፣ ነገር ግን ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ስለ መንግስታቱ አልተጻፈም።
እነዚህ ፍጥረታት ሁሉም ያልነጹ አራዊት ነበሩ። የሚወክሉት አረመኔ ሕዘቦችን
ነበር፣ ይህ እንዴት የሚገርም ነው። እንዲሁም ከአራተኛው አውሬ በቀር ፣ ዳንኤል
እንደገለጸው የሚታወቁ አይነት ፍጥረታት ናቸው። ስለዚህ እንሰሳዎቹ እንዲሁ
በዘፈቀደ የተሳሉ አይደሉም፣ በተቻለ መጠን የእያንዳንዳቸውን ባህሪያት ወይም
የመንግስታቱን ገጽታ በመወከል ይጠቁማሉ።
አንበሳ፡- አንበሳ የባቢሎንን መንግስት በትክክል ይወክላል። ክንፍ ያለው አንበሳ
በጣም የተዋበውን የቤተመንግስቱን ግድግዳ እና ሌሎች የባቢሎናውያንን ስነ-ጥበብ
ያስውብ ነበር። በራዕዩ የታየው አንበሳ በመጨረሻ ክንፎቹ ይነቃቀላሉ፣ እንደ ሰውም
ቀጥ ብሎ ይቆማል፣ እንዲሁም የሰውን ልብ ይቀበላል። ይህ ሂደት የሚያመላክተው
የባቢሎንን መንግስት ለጥቂት አስርት አመታት በሌሎቹ ነገስታት የቀጠለበትን ነው።
ድብ፡- ድቡ የሚወክለው የሜዶ ፋርስ መንግስትን ነው። በአንድ ጎኑ ቀና ማለቱ
የሚያሳየው የፋርሳውያንን ከሜዶናውያን በላይ የበላይነት እንደነበራቸው ነው።
ሶስቱ የጎድን አጥንቶች በጥርሶቹ መካከል የነበሩት የሚወክሉት በሜዶ ፋርስ
መንግስት ድል የተደረጉትን ሶስቱን መንግስታት፤ ሊይዳ፣ ባቢሎን እና ግብጽን ነው::
ነብር፡- ፈጣኑ ነብር የሚወክለው በታላቁ እስክንድር የተመሰረተችውን ታላቋን
የግሪክን መንግስት ነው። አራቱ ክንፎች ይህን አውሬ ፈጣን እንዲሆን አድርገውታል፣
በትክክል እስክንድርን የሚወክል ነው፣ በጣም በጥቂት አመታት የሚታወቀውን
አለም በጠቅላላ በእራሱ ግዛት ስር አጠቃሎ ነበር።
አሰቃቂ እና የሚያስፈራ እንሰሳ፡- ቀደም ሲል የተጠቀሱት እንደስማቸው
የሚመስሉት እንስሳ ነው፣ ይህኛው ግን እራሱን ብቻ የሚመስል ነው። ያም ማለት
የመጀመሪያዎቹ ልክ አንበሳን ወይም ድብን ይመስላሉ ነገር ግን ይህኛው ከምንም
ጋር አይመሳሰልም። ይህ ብዙ ቀንዶችን የያዘ አውሬ ከበፊቶቹ ይልቅ ጨካኝ እና
አድኖ የሚኖር ነው ። ስለዚህም ፣ አለምን በብረት እግር ያሸነፈ፣ የገዛ፣ እና የረገጠ፣
የአረመኔያዊው ሮም ገጣሚ ወኪል ነው።
እነዚህ በሺ አመታት የሚቆጠሩ የሰብአዊ ዘር ታሪኮች ሁሉም ልክ
እንደተተነበየው መጥተው አልፈዋል፣ ። በእነዚህ ሁሉ ጩኸቶች ፣
ሁከቶች፣ እና በትርምስ ሰዓት እግዚአብሔር ገዥ እንደሆነ ሲያውቁ
ምን ያህል እረፍት /መጽናናትን ሊያገኙ ይችላሉ? ይህ እንዴት ነው
የመጽሐፍ ቅዱስን ተአማኒነት ሊያስተምረን የሚችለው?
ዳንኤል 7፡-7፣8፣ 10-25ን ያንብቡ። በቀጥታ ከአራተኛው አውሬ የተነሳው፣ እና የአካሉ ክፍል ሆኖ የቀረው የትንሹ ቀንድ ሐይል ማነው?
ትላንት አስር ቀንዶች ይዞ አለምን ይመራ የነበረው የሚያስፈራው እንስሳ አረመኔያዊው
ሮምን እንሚወክል አይተናል። አሁን ትንሹን ቀንድ እና የሚወክለውን ኃይል
ልንመለከት ይገባናል። በራዕዩ እንደተመለከተው፣ አራተኛው እንስሳ አስር ቀንዶች
አሉት፣ ከእነርሱ መካካል ግን ለትንሹ ቀንድ ቦታ ይለቁ ዘንድ ሶስቱ ተነቀሉ። ይህ
ቀንድ አይኖች ሲኖሩት ‹‹የትዕቢትን ቃል››(ዳንኤል 7፡-8) የሚናገርበት አፍ አለው።
ግልጽ ነው ትንሹ ቀንድ የወጣው በጣም ከሚያስፈራው እንስሳ ፣ ከአረመኔያዊው
ሮም ማለት ነው። በዚህ መንገድ ቀንዱ አንዳንድ የአረመኔያዊው ሮምን መገለጫዎች
አስቀጥሏል። ልክ የአንድ ሀይል ቀጣይ ደረጃ ማለት ነው።
ዳንኤል ይህ ሌላኛው ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነትን ሲከፍት አይቷል። መልአኩ
ለዳንኤል ሲገልጽለት ይህ ቀንድ ንጉስ ሲሆን ሶስት ሕገወጥ ነገሮችን እንደሚደረግ
ገልጾለታል፤ (1) በልዑል ላይ የትዕቢትን ቃል ይናገራል፣ (2) የልዑልን ቅዱሳን
ይገላል፣ (3) ጊዜን እና ሕግን ሊቀይር ይሞክራል። እናም ውጤቱ ቅዱሳን በእጁ
አልፈው ይሰጣሉ። ቀጥሎ፣ መልአኩ የትንሹን ቀንድ እንቅስቃሴ ጊዜ ይሰጠዋል፤
ዘመን እና ዘመናት፣ እና የዘመን እኩሌታ። በዚህ ላይ በትንቢታዊ አነጋገር ፣ ዘመን
የሚለው ቃል ‹‹አመት›› ማለት ነው ፣ በእጽፍ መልኩ ‹‹ሁለት አመት ›› ይሆናል።
ስለዚህ ይህ ሶስት አመት ተኩል የትንቢታዊ ጊዜን ይወክላል፣ ይህ ደግሞ በአንድ
አመት-አንድ ቀን መርህ መሰረት 1260 አመታትን ጊዜ ይወክላል። በዚህን ጊዜ
ውስጥ ትንሹ ቀንድ በእግዚአብሔር ላይ ጥቃትን ያውጃል፣ ቅዱሳንን ይገድላል፣
እንዲሁም የእግዚአብሔርን ሕግ ሊቀይር ይሞክራል።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡-1-12ን ያንብቡ፡፡ በሕግ አልባው ሰው እና በትንሹ
ቀንድ መካካል ምን አይነት መመሳሰል ይታያል? ይህ በሚያወራው
ምን አይነት ሀይል ነው የምናምነው? እናስ ለምን? ከአረመኔያዊው
ሮም የወጣ እና የሮም አካል ሆኖ የቀረ፣ ከሮም ጊዜ አንስቶ እስከ
አለም ፍጻሜ ድረስ የሚዘልቅ፣ ያም ማለት አሁንም በአለም ያለ ማለት
ነው፣ ብቸኛ ኃይል ማን ነው?
ከአራቱ እንስሳት ከራዕይ እና ከትንሹ ቀንድ እንቅስቃሴ በኋላ፣ ነብዩ በሰማይ
የተሰየመ ችሎትን ተመለከተ (ዳንኤል 7፡-9፣10፣13፣14)። ችሎቱ ሲሰየም፣ ዙፋናት
በቦታቸው ተቀመጡ እና በዘመናት የሸመገለው ስፍራውን ያዘ። የሰማዩ ትዕይንት
እየታዬ፣ የሰማይ ፍጥረታት ሺዎች እና ሺዎች በዘመናት በሸመገለው ፊት ያገለግሉ
ነበር፣ ችሎቱ ተሰየመ እናም መጽሐፍት ተገለጡ።
ስለዚህ ችሎት ግንዛቤ ሊወሰድ የሚገባው አስፈላጊ ነገር ይህ ፍርድ እየተካሄደ
ያለው ከ 1260 አመታት የትንሹ ቀንድ እንቅስቃሴ በኋላ መሆኑ ነው ( 538ዓ.ም1798ዓ.ም፣ የአርቡን ትምህርት ይመልከቱ)፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር የመጨረሻ
መንግስት ከመቋቋሙ በፊት ነው። በእርግጥ በራዕዩ ውስጥ የሚከተለው ቅደም
ተከተል ተደጋግሟል
የትንሹ ቀንድ ጊዜ (538-1798)
የሰማዩ ፍርድ
የእግዚአብሔር ዘለአለማዊ መንግስት
ዳንኤል 7፡-13፣ 14፣ 21፣ 22፣ 26፣ 27ን ያንብቡ። በምን መንገድ
ነው ፍርዱ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ትርፋማ የሚሆነው?
የብሉይ ኪዳን መጻህፍት የተለያዩ አይነት ፍርዶችን ከታቦቱ እና ከመቅደሱ ጋር
በተያያዘ ይገልጻሉ፣ እዚህ የተጠቀሰው ፍርድ ግን ይለያል። ይህ ፍርድ የአለማት
ሁሉ ነው፣ ትንሹን ቀንድ ብቻ ሳይሆን የልኡል ቅዱሳንን፣ በመጨረሻ መንግስትን
የሚቀበሉትንም ጭምር የሚነካ ነው።
ዳንኤል 7 ስለ ፍርዱ አያብራራም ወይም ስለ ጅምሩ እና ማብቂያው ዝርዝር ነገር
አያብራራም። ነገር ግን የሚጠቁመው ነገር ይህ ፍርድ የሚካሔደው ትንሹ ቀንድ
በእግዚአብሔር እና በህዝቡ ላይ ጥቃት በሚፈጽምበት ሳምንት ውስጥ ነው።
ስለዚህ፣ እዚህ ላይ ነጥቡ አለማቀፋዊ ይዘት ያለው ፍርድ መጀመሩን ትኩረት
ለመስጠት ነው። ከዳንኤል 8 እና 9 (ተከታዩን ሳምንት ይመልከቱ) ስለ ፍርዱ
መጀመሪያ እና ይህ ፍርድ በስርዓት ቀን በሰማይ ካለው ከ ቤተመቅደሱ መንጻት ጋር
የተገናኘ ነገር እንዳለው እንማራለን። እዚህ ላይ ያለው ትምህርት በግልጽ ከምጻቱ
በፊት የፍርድ ምርመራ በሰማይ ውስጥ እንደሚኖር እና ያም በእግዚአብሔር ሕዝቦች
በኩል ለጥቅማቸው እንደሚሆን ነው።
ለምንድን ነው ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ያከናወነልን ነገር በፍርድ ቀን
ዋስትና ለመሆን ማዕከላዊ የሚሆነው? ያለ መስቀሉ፣ ምን አይነት ተስፋ
ነበር የሚኖረን ወይም ሊኖረን የሚችል? (ሮሜ 8፡-1ን ይመልከቱ)
ዳንኤል 7፡-13ን ያንብቡ። እዚህ ላይ የሰው ልጅ ማነው፣ እናም እንዴት ነው ሊለዩት ቻለው? (ማርቆስ 13፡-26፣ ማቴዎስ 8፡-20፣ መቴዎስ 9፡-6፣ ፤ሉቃስ 9፡-26፣ ሉቃስ 12፡-8ን ይመልከቱ)
ፍርዱ ሲገለጥ በጣም አስፈላጊ አካል ወደ ትዕይንቱ ገባ፣ የሰው ልጅ። ማነው እርሱ?
አንደኛ፣ የሰው ልጅ ልክ ሲመጣ እንደ አንድ የሰማይ አካል ነው። ነገር ግን ማዕረጉ
እንደሚጠቁመው የሰው ባህሪን ያሳያል። በሌላ አነጋገር፣ ሰውም አምላክም የሆነ እና
በፍርዱ ሒደት ዋና የሆነን ሚና ለመጫወት የመጣ ነው። ሁለተኛ፣ የሰው ልጅ
የመጣው በሰማይ ደመናት ተከቦ ነው ፣ ይህ ደግሞ በአዲስ ኪዳን የዳግም ምጻት
የተለመደ ስዕል ነው። ቢሆንም ግን በዳንኤል 7፡-13 በቀጥታ የሰው ልጅ ከሰማይ
ወደ ምድር እንደሚመጣ አላሳየም ፣ ነገር ግን በሰማይ በዘመናት በሸመገለው ፊት
ለመቅረብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚሔድ ነው ።
ሶስተኛ ፣የሰው ልጅ በደመናት ሲመጣ መታየቱ ሊታይ እንደሚችል እንደ ማሳያ
ሐሳብን ይሰጣል። ነገር ግን ይህ ስዕል ታላቁን ካህን ያስታውሳል። በእጣን ጭስ
የሚከበበውን፣ መቅደሱን ለማንጻት በስርዓት ቀን ወደ ቅድስተ ቅድሳኑ የሚገባውን
ካህንን ያስታውሳል።
የሰው ልጅ እንዲሁ የንጉሣዊ አካል ነው። ‹‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም
የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው ግዛቱም
የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።››(ዳንኤል 7፡-14)
ይላል። ይገዙለታል የሚለው ቃል ሲተረጎም ያመልኩታል ሊሆን ይችላል።
እስከ
ምዕራፍ 7 ድረስ ከ 1-7 (ዳንኤል 3፡-12፣14፣17፣ 18፣28፣ ዳንኤል 6፡-16፣20፣ዳንኤል
7፡-14፣27) ዘጠኝ ጊዜ ተጠቅሷል። ለአምላክ አክብሮትን የማምጣት ሐሳብ አለው።
ስለዚህ፣ በትንሹ ቀንድ የሚመራው የሐይማኖታዊ ኃይል የእግዚአብሔርን ሕግ
ለመቀየር ሙከራ ማድረጉ መጨረሻው ለእግዚአብሔር የሚሆነውን አምልኮ
አበላሸው/በከለው። እዚህ ላይ ፍርዱ እንደሚያመላክተው እውነተኛው አምልኮ
በመጨረሻ ተመልሷል። ከሌሎች ነገሮች ጋር ሰብአውያንን በእግዚአብሔር እና
በሰብአውያንን መካከል እንደ አማላጅ አድርጎ አስቀመጠ። ዳንኤል እንዳመላከተው
ግን በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ብቸኛው አማላጅ የሰው ልጅ ነው።መጽሐፍ
ቅዱስ እንደሚለው ፣ ‹‹ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም
መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ
ነው፤ ››(1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡-5)።
ስለ ኢየሱስ ሕይወት እና ባህሪ ከመጽሐፍ ቅዱስ ካነበብነው ሁሉ፣
ለምንድን ነው እዚህ በተጠቀሰው ፍርድ ሒደት ውስጥ ማዕከላዊ
መሆኑን ማወቃችን መጽናናት የሚሆነን?
እንደሚከተለው ጥቅስ እግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ምንድን ነው የሚሆነው? ዳንኤል 7፡-8፣ 21፣22፣25፣27
የ‹‹ልዑል ቅዱሳን›› የእግዚአብሔር ሕዝብ መለያ ነው። ጥቅሱ በቅድሚያ
በሚወክለው ኃይል ይጠቃሉ። ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ለመሆን ሙጭጭ
በማለታቸው ምክንያት በጳጳሳዊው አገዛዝ ጊዜ ተገድለዋል። በአረመኔአዊው ሮም
(አራተኛው አውሬ እራሱ) ጊዜ ክርስቲያኖች ተገድለዋል ፣ ነገር ግን በዳንኤል 7፡
-25 የተጠቀሰው የቅዱሳን ግድያ ትንሹ ቀንድ ከአረመኔአዊው ሮም ማብቂያ ላይ
በተነሳው ትንሹ ቀንድ የተካሔደ ነው።
ሆኖም ፣ የእግዚእሔር ሕዝብ አረመኔያዊው ሐይል ለዘላለም አይጨቁነውም።
የእግዚአብሔር መንግስት የአለም መንግስትን ይተካል። በሚገርም ሁኔታ ትክክለኛው
ራዕይ ለሰው ልጅ ‹‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት
ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥
መንግሥቱም የማይጠፋ ነው። ›› (ዳንኤል 7፡-14) ይላል። ነገር ግን በመልአኩ
አማካኝነት እደተሰጠው ትርጉም የእግዚአብሔርን መንግስት የሚወርሱት ‹‹ቅዱሳን
›› ናቸው (ዳንኤል 7፡-18)። እዚህ ጋ ምንም አይነት መጣረስ የለም። የሰው ልጅ
ከእግዚእሔር እና ከሰብአውያን ጋር ስለሚጠጋ፣ የእርሱ ድል ለሚወክላቸው ሁሉ
ነው።
ሊቀ ካህኑ ኢየሱስ መሲህ መሆኑን ሲጠቅስ፣ የእግዚእሔር ልጅ፣ ኢየሱስ ወደ ኋላ
መዝሙር 110፡-1 እና ዳንኤል 7፡-13፣14 በማመላከት እንዲህ አለ ‹‹ እኔ ነኝ፤ የሰው
ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።›› (ማርቆስ
14፡-62)። ስለዚህ ኢየሱስ እና ሰማያዊው ስፍራ የሚወክል እርሱ ነው። የጨለማው
ኃይል አልፎዋል እናም ወደ እርሱ ለሚቀርቡ ሁሉ ድልን ያካፍላቸዋል። ስለዚህ
ሊያስፈራ የሚችል ምንም ምክንያት የለም። ልክ ሐዋሪያው ጳውሎስ እዳለው ‹‹በዚህ
ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም
ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም
ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም
ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል
ተረድቼአለሁ።›› (ሮሜ 8፡-37-39)።
የዳንኤል ራዕይ ታሪክ ከሺህ አመታት ቀድሞ እንዴት እንደሚገልጽ
ተመልከቱ። ይህ ስለ ወደፊቱ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ላይ እድንታመን
እንዴት ነው የሚረዳን?
ታሪክ በወፍ በረር ለሚመለከተው ከሮማውያን መንግስት
ውድቀት በኋላ፣ ከሰሜን በኩል ባርቤሪያውያን እያጠቃ የመጣው የሮም ቢሾፕ
የሶስቱን ባርቤሪያውያን ጎሳ መስፈንጠርን እድል ተጠቅሞ እራሱን የሮም አቻ የለሽ
ሐይል ማድረግ ከ 530 ዓ.ም ጀምሮ ተቋቁሟል። በዚህ ሒደት የተለያዩ ተቋማዊ እና
ፖለቲካዊ ስራዎች ከሮም መንግስት ወርሷል። ከዚህ በናፖሊዮን በ1798 እንዲያቆም
እስኪደረግ ድረስ ጳጳሳዊው ሐይል በአለማዊ እና ሃይማኖታዊ ኃይል ላይ ሰርቷል።
ይህ ሮምን ወደ ፍጻሜ አላመጣም፣ ነገር ግን ለዚያ ለተጠቀሰው ግድያ ብቻ ነበር
ያቆመው። ጳጳሱ የክርስቶስ ወኪል ብቻ አልነበረም ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ
የሚቃረኑ አዳዲስ አስተምህሮዎችን እና ልምዶችን አስተዋውቋል።
የንስሃ መግቢያ
ቦታ፣ ንስሃ፣ ኑዛዜ የሚሰማበት ስርዓት ፣ እንዲሁም የሰንበትን ትዕዛዝ ወደ እሁድ
መቀየር ‹‹ሕግ እና ዘመንን›› ይቀይራል ከተባለው መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።
‹‹በራሱ ኃይል ሰው፣ የጠላትን ክስ ሊቋቋም አይችልም። በመርገም ጨርቁ ፣
ሐጢያቱን በመናዘዝ፣ በእግዚእሔር ፊት ይቆማል። ነገር ግን ኢየሱስ ፣ ጠበቃችን፣
ውጤት የሚያመጣ ልመናን በእምነት እና በንስሃ ነፍሳቸውን ለእርሱ ማስረከብ
ለሚሹ ሁሉ ያቀርባል። ጉዳያቸው በቀራንዮ አንጻር ከሳሻቸውን ድል ይነሳል።
ለእግዚአብሔር ፍጹም የሆነው መታዘዙ በሰማይ እና በምድር ኃይል አሰጥቶታል።
እናም ሐጢያተኛ ለሆኑ ሰዎች ከአባቱ ምህረት እና ማሳታረቅን ይጠይቃል።
ለሕዝብ ከሳሾችም እንዲህ ሲል ያውጃል ‹ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ
ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ
አይደለምን? አለው። › እናም በእምነት በእርሱ ላይ ለሚታመኑት፣ እንዲህ ሲል
ያረጋግጥላቸዋል ‹እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ
አውልቁ አላቸው። እርሱንም። እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም
አለብስሃለሁ አለው። › (ዘካሪያስ 3፡-4) ›› ( ኤለን ጂ ኋይት ፣ ፕፌትስ ኤድ ኪግስ
ገት 586፣ 587)
1.እንደገና ፣ ከአራተኛው አውሬ ከሮም መንግስት የተነሳው እና
አካሉ ሆኖ የቀረውን የትንሹን ቀንድ ኃይል ባህሪያት ተመልከቱ።
የእግዚአብሔርን ሕዝብ የገደለ፣ አሁንም በዚህ ዘመን ያለ ከብዙ
ዘመናት በፊት ከአረመኔአዊው የሮም መንግስት የወጣ ብቸኛው ኃይል
ማነው? ይህ ግልጽ የሆነ መለያ ስለ ማንነቱ ከመገመት እንድንጠበቅ
የሚረዳን እንዴት ነው? ከኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ከመቶ ሃምሳ
አመታት በፊት መጥቶ የጠፋው የአረመኔአዊው ግሪክ መንግስት ንጉስን
ያመላክታል ከሚሉ ሐሳቦች ሁሉ ሊጠብቀን የሚችለው እንዴት ነው?
እነዚህ ግልጽ ምልክቶች ትንሹ ቀንድ ገና ወደፊት የሚነሳ ኃይል ነው
ከሚል እምነት ሊጠበቁ የሚገባው እንዴት ነው?