ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡-ዳንኤል 6፣ 1ኛ ሳሙኤል 18፡-6-9፣ ማቴዎስ 6፡-6፣ ሐዋሪያት ሥራ 5፡-27-32፣ ማርቆስ 6፡-14-29፣ ዕብራውያን 11፡ -35-38
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:-‹‹የዚያን ጊዜም አለቆችና መሳፍንቱ ስለ መንግሥቱ በዳንኤል ላይ ሰበብ ይፈልጉ ነበር ነገር ግን የታመነ ነበረና፥ ስሕተትና በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አልቻሉም። ›› (ዳንኤል 6፡-4)
የ
ሜዶ ፋርስ መንግስት ባቢሎንን ካሸነፈ በኋላ፣ ዳሪዎስ የዳንኤልን ጥበብ እውቅና
ሰጠ እና የአዲሱ መንግስት አካል እንዲሆን ጋበዘው። በእድሜ አንጋፋው ነብይ
ንጉሱ በሰጠው በመላው ሜዶ ፋርስ ግዛት ውስጥ የማስተዳደር ሐላፊነቱ በጣም
በልጦ ተገኘ።
ቢሆንም ግን ምዕራፉ ሲገለጥ ዳንኤል ‹‹የመጨረሻ ዋና ኃጢያት ›› ሊባል በሚችለው
ኃጢያት ምክንያት የመጣን ነገር ተጋፈጠ፤ ያም በቅንአት ነው። ግን ታሪኩ
ከመጠናቀቁ በፊት ዳንኤል በሜዶ ፋርስ ለተሰጠው አለማዊ ስራ ብቻ ሳይሆን፣
ከሁሉም በላይ ለሆነው ለአምላኩ ታማኝ ነበር። ለእግዚአብሔር ያለው ታማኝነት
በሌሎቹም ነገሮች ላይ እንዲሁ ታማኝ እንዲሆን ተጽዕኖ እንዳደረገበት ከፍ ባለ
ደረጃ እርግጠኛ መሆን እንችላለን።
ዳንኤል ያለፈበት የሞት ፍርድ ልምምድ ለመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ሰዎች
እንደ አርአያ ያገለግላል። ታሪኩ የእግዚአብሔር ሰዎች ከመከራ እና ከስቃይ ሁልጊዜ
ይተርፋሉ ሲል አያመላክትም። ዋስትና የሚሰጠው ከክፉ ጋር ባለ ተጋድሎ ውስጥ
በመጨረሻ መልካምነት በአሸናፊነት እንደሚወጣ ፣ እና በመጨረሻ እግዚአብሔር
ሕዝቡን ነጻ እንሚያወጣ ነው።
የዚህ ሳምንት ትምህርት ለ የካቲት 07 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ሁሉም ፍጹም በሆነበት በሰማይም እንኳን ሉሲፈር በክርስቶስ ላይ ቅናት ተሰማው። ‹‹ ሉሲፈር በኢየሱስ ቀና፣ ቀናተኛም ሆነ። ለበላይነቱ ፣ ከፍተኛ ስልጣን እንዳለው እና ትክክለኛው ገዥ እንደሆነ እውቅና ለመስጠት ሁሉም መላዕክት ሲሰግዱለት እርሱም ከእነርሱ ጋር ይሰግዳል ነገር ግን ልቡ በቅናት እና በጥላቻ ተሞልቶ ነበር። ›› (ኤልን ጂ. ኋይት የድነት ታሪክ ገጽ 14)። ቅናት እንደዚህ አይነት ስሜት ነው፣ መጥፎን ነገር ማሰላሰል እራሱ በአስርቱ ትአዛዛት ተከልክሏል። ከ መግደል እና ከመስረቅ ጋር ምኞትን በተመለከተም ትእዛዝ አለ (ዘጸአት 20፡-17ን ይመልከቱ)። ዳንኤል 6፡-1-5ን፣ ከ ዘፍጥረት 37፡-11 እና 1ኛ ሳሙኤል 18፡ -6-9 ጋር ያንብቡ። በእነዚህ ታሪኮች ሁሉ ውስጥ ቅንአት የነበረው ሚና ምን ነበር?
የዳንኤል የማስተዳደር ችሎታ፣ ንጉሱን አስገርሞታል ነገር ግን የሌሎች አስተዳዳሪዎችን
ቅንአት ደግሞ አነሳስቷል። ስለዚህ በሙስና ከሰው ሊያስወግዱት ሴራን ጠነሰሱ።
ነገር ግን የቻሉትን ያህል ቢፈልጉ ፣ በዳንኤል አስተዳደር ውስጥ ምንም ሊያገኙ
አልቻሉም። ‹‹ በዳንኤል ላይ ሰበብ ይፈልጉ ነበር ነገር ግን የታመነ ነበረና፥ ስሕተትና
በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አልቻሉም።
›› (ዳንኤል 6፡-4) ። የአረማይኩ ቃል ‹‹ታማኝ ›› የሚለው ቃል ‹‹ የታመነ›› ተብሎ
ሊተረጎም ይችላል።
ዳንኤል ያለነቀፋ ነበረ፣ እነዚያ ባለሟሎች በእርሱ ላይ የሐሰት ክስን እንዲያነሱ
ሊያደርጋቸው የሚችል ምንም ነገር አላገኙም። ሆኖም ግን ዳንኤል ለአምላኩ ምን
ያህል ታማኝ እንደሆነ እና ለአምላኩ ሕግ ምን ያህል ታዛዥ እንደሆነ ያውቃሉ።
ስለዚህ ወዲያውኑ ዳንኤልን ለማጥመድ ለአምላኩ ሕግ እና ለሃገሩ ንጉስ ሕግ
በመታዘዝና ባለመታዘዝ መካከል ችግር ሊገባበት የሚያስችለውን ሁኔታ ማሰናዳት
ነበረባቸው። እነዚህ አስተዳዳሪዎች ስለ ዳንኤል በእርግጠኝነት ከንጉሱ ይልቅ
ከአምላኩ ሕግ ጎን የሚሆንባቸውን ትክክለኛ ሁኔታዎች እንዳሉ አምነዋል። ስለ
ዳንኤል ታማኝነት እንዴት ያለ ምስክርነት ነው!
ከቅንአት ጋር ምን አይነት ትግል አድርገው ያውቃሉ፣ እናም እንዴት
ነው የተወጡት? ለምንድን ነው ቅንአት ለመንፈሳዊ ውድቀት ገዳይ
እና አሰናካይ የሚሆነው?
ዳንኤል 6፡-6-9ን ያንብቡ። ከዚህ አዋጅ በስተጀርባ ያለው አስተሳሰብ ምንድን ነው? ከንጉሱ ትዕቢት ጋር እንዴት ነው ነገሩ የሄደው?
ዳሪዎስ ወዲያውኑ ሊሽረው የሚሻውን አዋጅ ማወጁ፣ ቂል የሆነ ያስመስለዋል።
በቅርብ ጊዜ የተቋቋመው መንግስት የፖለቲካ ሁኔታን በብልጠት መጠቀም
በቻሉ ባለሟሎቹ በተዘጋጀው ወጥመድ ውስጥ ወደቀ። ዳሪዎስ አሃዳዊ መንግስቱ
አስተዳደሩ ውጤታማ እንዲሆን ወደ መቶ ሃያ ግዛቶች ከፋፍሎታል። ቢሆም ግን
ይህ ድርጊቱ በረዥም ጊዜ የተወሰነ አደጋን አምጥቷል። ተጽዕኖ ፈጣሪ አስተዳደር
የሆኑ አማጺዎችን በማደራጀት በቀላሉ ግዛቱን ሊከፍል ይችላል። ስለዚህ ሁሉን
አስገዳጅ የሆነ እና ለሰላሳ ቀናት የሚቆይ ሁሉም ሰው ጉዳዩን ወደ ንጉሱ ብቻ
የሚያመጣበት ሕግ ሕዝብን በመንግስት ላይ እንዳይነሳ እና ከንጉሱ ጋር አብሮ
ህብረት ለማድረግ መልካም ስልት ይመስላል። ነገር ግን እነዚህ ባለሟሎች፣ ይህ
ጉዳይ ሁሉንም ገዥዎች፣ አስተዳዳሪዎችን፣ አውራጃ መሪዎችን፣ እና አማካሪዎችንየጎደለ እንዳይኖር በማድረግ፣ ምክንያቱም ዳንኤል ስላልተካተተ፣ መጻፍ እንዳለበት
ሀሳብ በማቅረብ ንጉሱን አሳሳቱት። በተጨማሪም እንደ አምላክ ለሚቀርብ ጥያቄ
ንጉሱ ብቻ እንዲጠየቅም አደረጉ።
የፋርስ ንጉስ እራሱን እንደ መለኮት ደረጃ ያየበት መረጃ ምንም የለም። ሆነም ቀረ
ንጉሱ ለሰላሳ ቀናት ብቸኛ የአምላክ ወኪል እንዲሆን አዋጁ ያስገድዳል፣ ያም ማለት
ለአማልክት የሚደረግ ጸሎት በንጉሱ በኩል ይሆናል። እንዳለመታደል ንጉሱ ከአዋጁ
በስተጀርባ ያለውን ነገር አልመረመረም። ስለዚህ የወጣው ሕግ ሴራን ለመከላከል
ተብሎ ነበር ነገር ግን በእራሱ ላይ ዳንኤልን ለማጥቃት የወጣ ሴራ ነበር።
የዚህ ሕግ ሁለት አቀራረቦቹ ትኩረትን ይሻሉ። አንደኛ፣ ይህን ሕግ ለሚተላለፉ
ቅጣቱ በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ መጣል ነው። እንዲህ አይነት ቅጣት በሌላ ስፍራ
ስላልተጠቀሰ የዳንኤል ጠላቶች ያቀረቡት ሐሳብ ይሆናል። የጥንት የምስራቅ ነገስታት
አንበሶችን በዋሻ የሚያስቀምጡት አንዳንድ ጊዜ ለአደን ለመልቀቅ ነው።
ስለዚህ
የንጉሱን አዋጅ ሊጥስ ለሚፈልግ ማንንም ለማንገላታት የሚሆን የአንበሳ እጥረት
ሊኖር አይችልም። ሁለተኛ፣ አዋጁ ሊቀየር አይችልም። የ‹ሜዶንና-የፋርስ ሕግ››
ያለመቀየር ተፈጥሮ በአስቴር 1፡-19 እና አስቴር 8፡-8 ላይ ተጠቅሷል። ዲዎድሮስ
ሲኩሉስ፣ ግሪካዊ የታሪክ ተመራማሪ ነው፣ እንደጠቀሰው ዳሪዎስ 3ኛ (በዳንኤል
ከተጠቀሰው ዳሪዎስ ጋር እንዳይምታታ ) አንድ ሁኔታ ላይ ሐሳቡን ቀየረ ነገር ግን
ንጹህ በሆነ ሰው ላይ ያስተላለፈው የሞት ፍርድ ሊቀየር አልቻለም።
‹‹አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።›› (ማቴዎስ 6፡-6) ዳንኤል 6፡10ን ያንብቡ። ዳንኤል በቀላሉ ማንም ሳያየው በጸጥታ የማይጸልየው ለምንድን ነው?
ዳንኤል ልምድ ያለው የመንግስት ሰው ነው፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር
አገልጋይ ነው። በመሆኑም፣ ከዚህ አዋጅ ጀርባ ያለውን ቅጥፈት ሊያስታውል
የሚችል ብቸኛው የመንግስት አካል እርሱ ብቻ ነበር ። ዳሪዎስ አዋጁ የመንግስቱን
አንድነት የሚያጠናክር እንደሆነ ነው የቆጠረው፣ ነገር ግን ለሴረኞቹ ዳንኤልን
የማስወገጃ ስልት ነበር።
በእርግጥም ከዚህ ሴራ ጀርባ ያለው እውነተኛው ምክንያት እና አላማው የሚያርፈው
በእግዚአብሔር እና በክፉ ኃይል መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ ላይ ነበር።
በዚህን
ጊዜ (539ቅ.ዓ) ዳንኤል በምዕራፍ 7 (553ቅ.ዓ) እና ምእራፍ 8 (551ቅ.ዓ) ላይ
የተዘገበውን ራዕይ ተቀብሎ ነበር። ስለዚህ የንጉሱን አዋጅ ባዶ የሰብዓዊ ፖለቲካ
ጉዳይ እንዳልሆነ ነገር ግን የዚህ ታላቅ ተጋድሎ ክስተት እንደሆነ ይስተዋላል። የሰው
ልጅ መንግስትን ለልዑል ሕዝብ ነጻ ሲያወጣ እና ነገሩን የሚያብራራው መልአክ
እርዳታ እና ማጽናኛ (ዳንኤል 7) ከፊቱ ላለው ጥፋት ድፍረትን አምጥቶለት ይሆናል።
ምን አልባትም ከጓደኞቹ ልምድ የተነሳም፣ የናቡከደነጾርን አዋጅ ለመቋቋም ደፋር
የነበሩትን (ዳንኤል 3) ፣ አቋሙን እያንጸባረቀ ይሆናል።
ስለዚህ የተለመደውን የአምልኮ ስርዓቱን አልቀየረም ነገር ግን ወደ እየሩሳሌም
በየቀኑ ለሶስት ጊዜ ይጸልይ የነበረውን ልማዱን ቀጠለ። ማንኛውንም ጥያቄ ለሰውም
ሆነ ለአማልክት ለንጉሱ ብቻ የሚለውን ክልከላ ፣ ዳንኤል ለመደበቅ ወይንም
ለማስመሰል በእነዚያ ሰላሳ ቀናት ምንም አይነት ጥንቃቄ አላደረገም። ብዙ ደርዘን
ባላሟሎች እና ሌሎች ሰራተኞች በአዋጁ ላይ በተባበሩ ጊዜ እርሱ ብቻውን ስለነበር
እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም ። ግልጽ በሆነው የጸሎት ሕይወቱ ለእግዚአብሔር
ያለው ታማኝነቱ የሚመጣው ለንጉሱ እና ለማይሻረው አዋጁ ጭምር ካለው
ታማኝነት በፊት አንደሆነ ይገልጻል።
ሐዋሪያት ሥራ 5፡- 27-32ን ያንብቡ። ምንም እንኳን በዚህ ያለው
ተግሳጽ ግልጽ ቢሆንም ፣ ለምንድን ነው የሰብአዊ ሕጎችን ስንሞግት፣
ሁልጊዜ የምናደርገው ነገር በእውነት በእርግጠኝነት የእግዚአብሔር
ፈቃድ መሆኑን እርግጠኛ የምንሆነው? (ከሁሉም በላይ እምነታቸውን
ከሚያዋርዱ ወይም ትክክል አይደለም ብለው ላሉት ነገር ከማመን
ይልቅ የሞቱ ሰዎችን ያስቡ )።
ዳንኤል 6፡-11-23ን ያንብቡ:: ንጉሱ ለዳንኤል ምንድን ነው ያለው? ዳንኤል ምን ያህል ለእግዚአብሔር ጠንካራ እና ታማኝ ምስክር እንደሆነ እንዴት ነበር የተገለጸው?
ሴረኞቹ ወዲያውኑ ዳንኤል ሲጸልይ ተመለከቱት፣ ያ ደግሞ አዋጁ በቀጥታ
የከለከለው ነበር። እናም ክሳቸውን ወደ ንጉሱ ሲያቀርቡ፣ ዳንኤልን የጠቀሱበት
ሁኔታ በሚያዋርድ መልኩ ነበር፣ ‹‹የዚያን ጊዜም በንጉሡ ፊት መልሰው። ንጉሥ
ሆይ፥ ከይሁዳ ምርኮኞች የሆነው ዳንኤል በየዕለቱ ሦስት ጊዜ ልመናውን ይለምናል
እንጂ አንተንና የጻፍኸውን ትእዛዝ አይቀበልም አሉት።››(ዳንኤል 6፡-13)።
በእነርሱ አይን የግዛቱ አንዱ ዋና ባለሟል ፣ ለንጉሱ ቅርብ የነበረ፣ ከዚህ በኋላ
‹‹ምርኮኛም›› ያልሆነ ነበረ። በተጨማሪ ዳንኤልን ከንጉሱ ጋር ለማጋጨት እንዲህ
አሉ ‹‹ አንተንና የጻፍኸውን ትእዛዝ አይቀበልም አሉት። ››። አሁን ንጉሱ አዋጁን
በመፈረሙ እንደተጠመደ አወቀ። ጥቅሱ እንሚለው ‹‹ ሊያድነውም ፀሐይ እስኪገባ
ድረስ ደከመ።››(ዳንኤል 6፡-14) ነገር ግን ከተጻፈው ቅጣት ነብዩን ሊያድን ማድረግ
የሚችለው ምንም ነገር አልነበረም። የሜዶንና የፋርስ ሕግ በጽሑፉ መሰረት መፈጸም
አለበት። ስለዚህ ንጉሱ ምንም በቸልተኝነት ቢሆም እንኳን ትእዛዙን ሰጠ፣ ዳንኤል
ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል። ነገር ግን ዳሪዎስ ይህን ቢያደርግም ትንሽ የተስፋን
ብልጭታ የሚየሳይ ነገር ገለጸ፣ ይህን የሚመስል ‹‹ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም።
ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ እርሱ ያድንህ አለው።›› (ዳንኤል 6፡-16)።
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር ምን እንዳደረገ አይገልጽም ነገር ግን
አንድ ሰው ጸልዮአል ብሎ ሊወስድ ይችላል። እናም እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ
የዳንኤልን እምነት አከበረ። በጠዋት ዳንኤል ምንም አልተጎዳም እና በመንግስት
የተሰጠውን ሐላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ሆነ። በዚህ ትእይንት ላይ ሐሳብ ስትሰጥ
ኤልን ጂ. ኋይት እንዲህ ትላለች ‹‹እግዚአብሔር የዳንኤልን ጠላቶች ወደ አንበሶች
ጉድጓድ እንዳይጥሉት አልከለከላቸውም፣ ክፉ መላዕክትና የተኮነኑ ሰዎች ይህን
ያህል ሐሳባቸውን እንዲያከናውኑ ፈቀደላቸው፣ ነገር ግን አገልጋይ ባርያውን ነጻ
ሲያወጣውያ ነበር የበለጠ የሚያስደንቀው።
እናም ለእውነት ጠላቶች ሽንፈት
ለእርሱ ደግሞ ጽድቅ የተፈጸመው ›› (ፕሮፌትስ ኤንድ ኪንግስ፣ ገጽ 543፣544)።
ምንም እንኳን ይህ ታሪክ ፍጻሜው የደስታ ቢሆንም (ቢያንስ ለዳንኤል)፣
ስላልተረፉ ሌሎችስ፣ በመጽሐፍ ቅዱስም ውስጥ ያሉ (ለምሳሌ ፣
ማርቆስ 6፡- 14-29 ይመልከቱ) ነጻ መውጣት መጨረሻቸው ያልሆነስ
እንዴት ነው የምናስተውላቸው?
ዳንኤል 6፡-24-28ን ያንብቡ። ስለ እግዚአብሔር ንጉሱ የሰጠው ምን አይነት ምስክርነት ነበር?
የትረካው በጣም አስፈላጊ ክፍል የዳሪዎስ እግዚአብሔርን ማመስገን እና
የእግዚአብሔርን ሉአላዊነትን መገንዘብ ነው። እንዲያውም ከፍተኛው ደረጃ
ባለፈው ምዕራፍ ውስጥ ለእግዚአብሔር የቀረበ ምስጋና የተገለጸበት ( ዳንኤል 2፡
-20-23፣ ዳንኤል 3፡-28፣29፣ ዳንኤል 4፡-1-3፣ 34-37) መደምደሚያ ነው። ልክ
እንደ ናቡከደነጾር ለዳንኤል ነጻ መውጣት ዳሪዎስ እግዚአብሔርን በማመስገን
ነበር ምላሽ የሰጠው። ነገር ግን ከዚህም የበለጠ አድርጓል እንዲሁ፣ የቀደመውን
አዋጅ በመቀልበስ ሁሉም ‹‹ በዳንኤል አምላክ ፊት እንዲፈሩና እንዲንቀጠቀጡ
አዝዣለሁ››(ዳንኤል 6፡-26) ሲል ተናገረ(አወጀ)።
አዎ! ዳንኤል በተአምራት ተረፈ፣ ታማኝነቱ ተከፈለው፣ ክፉው ተቀጣ፣
የእግዚአብሔር ክብር እና ኃይል ነጻ አወጣው። ነገር ግን በዚህች ትንሽ ምሳሌ ውስጥ
በአለማት ደረጃ ሊሆን ያለውን ያሳየናል፣ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ነጻ ይወጣሉ፣ ክፉ
ይቀጣል እና ጌታም በአለም ፊት ነጻ ያወጣል።
ዳንኤል 6፡-24ን ያንብቡ። ስለዚህ ጥቅስ ምን አስቸጋሪ ነገር ልናገኝ
እንችላለን፣ እናም ለምን?
ቢሆንም ግን አንድ የሚረብሽ ችግር አለ፣ እና ያም እስከምናውቀው ድረስ ምንም
ያልበደሉት ሚስቶች እና ልጆች ልክ እንበደሉት አብረው ተፈረደባቸው። ይህን
ፍትህ የተዛነፈ የመሰለበትን ሁኔታ እንዴት ነው ልንገልጸው የምንችል?
አንደኛ፣ ይህ ድርጊት የተፈጸመው በንጉሱ እና በሜዶን እና ፋርስ ሕግ ነው። በአንድ
ወንጀለኛ ቅጣት ውስጥ ቤተሰብን ያጠቃልላል። እንደ አንድ መርህ በአንድ የቤተሰብ
አባል ጥፋት መላው የቤተሰብ አባል ሐላፊነትን ይወስዳል። ይህ ትክክል ነው ማለት
አይደለም፣ ይህ ታሪክ ከፋርስ ሕግ ጋር ይሔዳል ለማለት ነው።
ሁለተኛ፣ ሌላው መገንዘብ ያለብን የመጽሐፍ ቅዱስ ተራኪ የዘገበው ክስተቱን ነው
እንጅ የንጉሱን ድርጊት ግን አላጸደቀም። በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ልጆች በወላጆች
ኃጢያት ምክንያት እንዲሞቱ አይፈቅድም (ዘዳግም 24፡-16)።
በእንደዚህ አይነት ፍትህ መጓደል እና በሌሎችም ከመጽሐፍ ቅዱስ ምን
አይነት ማጽናኛ ታገኛላችሁ? 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡-5? ምንድን ነው የሚለው?
እናስ የሚያነሳው ነጥብ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው?
የዳንኤል ነጻ መውጣት በ ዕብራውያን 11 ላይ ተዘግቧል። ምን
ሊባል ይችላል ‹‹ የአንበሶችን አፍ ዘጉ›› (ዕብራውያን 11፡-34)። ይህ በጣም አስገራሚ
ነው ነገር ግን ዕብራውያን 11 እንደሚጠቅሰው የእምነት ጀግኖች ሞትን እንደ ዳንኤል
ያመለጡ ብቻ አይደሉም፣ በቆራጥነት የተሰቃዩ እና የሞቱትም ናቸው እንጂ፣ ።
እግዚአብሔር ለምስክርነት ሲጠራ እንዳንዶቼን በመኖር ሲሆን ሌሎቹን ደግሞ
በመሞት ነው። ስለዚህ፣ በኢየሱስ ባላቸው እምነት ምክንያት ሰማዕታት ከሆኑ እጅግ
ብዙ ወንዶች እና ሴቶች እንደምንማረው፣ የዳንኤል ነጻ መውጣት ታሪክ ፣ ነጻነት
ለሁሉም እንደተሰጠ እንደማያመላከት ያሳየናል። ቢሆንም ግን የዳንኤል ተአምራዊ
በሆነ መንገድ መትረፍ እግዚአብሔር እንደሚመራ፣ እና በመጨረሻ ከኃጢያት እና
ከሞት ኃይል ሁሉንም ልጆቹን ነጻ እንደሚያወጣ ያሳየናል። ይህ በቀጣዮቹ የዳንኤል
መጽሐፍ ምዕራፎች ግልጽ ይሆናል።
1.ፈረንሳያዊው ሰው ጅን ፓውል ሳሬት አንድ ጊዜ ሲጽፍ ‹‹
የሰብአዊ እውነታን መሰረታዊ ውጥን ለመረዳት ምርጡ መንገድ፣ ሰው
የእግዚአብሔር ውጥን ፍጡር ነው፣ ብሎ ማለት ነው›› (ጅን ፓውል
ሳሬት፣ ቢንግ ኤንድ ነቲንግለስ፤ ኤ ፊኖሜኖሎጂካል ኢሴይ ኦን
ኦንቶሎጂ፣ ዋሽንግቶን እስኮር ፕሬስ. 1956፣ ገጽ 724) ይላል። ይሄ
ቢያንስ በአንድ ደረጃ ለምን ንጉሱ በወጥመዱ እንደወደቀ እንዴት ነው
እንድንገነዘብ የሚረዳን? ለምንድን ነው ሁላችንም በህይወት ውስጥ
በምንም አይነት ሁኔታ ለእንደዚህ አይነት ዝንባሌ መጠንቀቅ ያለብን
፣ የፈለገ አሳች ሆኖ ቢመጣም? ልክ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን
የምንፈልግባቸው ምን አይነት ሌሎች መንገዶች ናቸው?
2.ለእግዚአብሔር እና ለሕጉ ባለን ታማኝነት አንጻር ለሌሎች የምናቀርበው
ምስክርነት ምን አይነት ነው?
ስራችሁን እንኳን የሚያሳጣችሁ
ቢሆን ወይም ሕይወታችሁንም እንኳን ቢሆን የሚያውቋችሁ ሰዎች
ለእምነታችሁ የቆማችሁ እንደሆናችሁ ያስባሉ?
3.በዳንኤል ውስጥ ፣ እግዚአብሔር ለአላማው በብቃት ሊጠቀምበት
እንደሚችል አድርጎ እራሱን እንዳዘጋጀ ሰው ፣ ምን ታያላችሁ? በጌታ
እርዳታ እንዴት ነው ተመሳሳይ ባህሪን ማሳደግ የምትችሉት?
4.በአዋጁ አንጻር፣ ዳንኤል በምን አይነት መንገዶች ነው የሚጸልይበትን
መንገድ ለመቀየር ማሳመን ይችል የነበረው? ወይም ያ አደገኛ ድርድር
ይሆን ይሆን? ከሆነ ፣ ለምን?