ለዚህ ሳምንት ጥናት ለመዘጋጀት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። ዳንኤል 5፣ ራዕይ 17፡-4-6፣ መዝሙር 96፡-5፣ ቆላስያስ 1፡-15-17፣ ሮሜ 1፡-16-32፣ መክብብ 8፡-11፣ ራእይ 14፡-8
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- ‹‹ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። ›› (ዳንኤል 2፡-21)
በ
ዳንኤል 5 የእግዚአብሔር ቃል ኃይለኛ በሆነ ምሳሌ በሚያምር እና ድራማዊ
በሆነ መልኩ ያለቀን የሰብአዊ ዘር ባዶ ጉራን ያቀርብልናል። እንድ ሰው
ናቡከደነጾር ትምህርቱን ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወስዶበታል ለማለት ቢችልም፣ ቢያነስ
ግን ተምሮበታል። የልጁ ልጅ ቤልሻጽር፣ አልተማረም። በቤተ-መንግስቱ በነበረው
መሳከር የቤተ መቅደሱን መጠጫ ጽዋዎች ተጠቀመ። ቤልሻጽር አረከሳቸው።
እንደዚህ አይነት የማርከስ አካሔድ እግዚአብሔርን መገዳዳር ብቻ አይደለም
ነገር ግን እግዚአብሔርን እራሱን ማጥቃት ነው። ስለዚህ ቤልሻጽር ጽዋዎቹን
በኃጢያቱ ሞላቸው፣ ልክ እንደ ትንሹ ቀንድም አደረገ(ዳንኤል 8)፣ የእግዚአብሔርን
የመቅደሱን መሰረት ማጥቃት እንደማለት ነው። ግዛቱን ከቤልሻጽር በማስወገድ
እግዚአብሔር በመጨረሻ ዘመን በሕዝቦቹ ጠላት ላይ የሚፈጸመውን አስቀድሞ
ሳለው። በዳንኤል 5 ላይ የተተረከው ኩነት የተፈጸመው በ 539 ቅ.ዓ.፣ በምሽት
ባቢሎን በሜዶ ፋርስ ጦር ስር ወደቀች። እዚህ ጋ ከወርቅ ወደ ብር ሽግግር ሆነ፣
በዳንኤል 2 እንደተተነበየው። እንደገና አሁንም እግዚአብሔር የምድርን ጉዳይ
እንሚመራ አረጋገጠ።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ ጥር 30 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ዳንኤል 5፡-1-4ን ከ ዳንኤል 1፡-1፣2 ጋር አብረው ያንብቡ። ቤልሻጽር ያደረገው መጥፎ ነገር ምንድን ነው? እውነተኛ ባህሪውን እንዴት ነው የገለጸው? ድርጊቱን በራዕይ 17፡-4-6 ካለው ጋር ያነጻጽሩ። ምን አይነት ተመሳሳይ ነገሮችን ያገኛሉ?
ንጉሱ የተቀደሱ የእየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መጠጫዎች ለመጠጥ መጠጫነት
እንዲውሉ አዘዘ። ናቡከደነጾር መጠጫዎቹን ያመጣቸው ከእየሩሳሌም ነው ነገር
ግን በአማልክቱ ቤት አስቀመጣቸው፣ ቢያንስ ቢያንስ ለእነዚህ የተቀደሱ እቃዎች
ያለውን አክብሮት አሳይቷል። ነገር ግን ቤልሻጽር እነዚህን የተቀደሱ እቃዎች ወደ
መጠጫነት በጣም በረከሰ መንገድ አመጣቸው።
በእነዚህ ቅዱስ እቃዎች የቤልሻጽር መኳንንቶች ‹‹ የወይን ጠጅም እየጠጡ
ከወርቅና ከብር ከናስና ከብረት ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት
አመሰገኑ። ›› (ዳንኤል 5፡-4)። በሚገባ አይነት ማሳታወሻ ስድስት አይነት እቃዎች
ተጠቅሰዋል። ባቢሎናውያን የሴክሳ ድሲማል ( በ60 ቁጥር ላይ የተመሰረተ ስርዓት
ነው) ይጠቀማሉ ፣ አሁን ከምንጠቀመው የ 10 ዴሲማል ሲስተም፣ ( በቁጥር 10
ላይ የተመሰረተ ስርዓት) ስለዚህ ስድስቱ አይነት ጎራዎች አማልክት የሚያመላክቱት
የባቢሎናውያንን ጣኦታት ሙሉነትን ነው። ያም ማለት የባቢሎናውያን የሀይማኖት
ስርዓትን እንደ ማለት ነው።
አስገራሚ በሚባል ሁኔታ የማዕድናቱ ዝርዝር ቅደም
ተከተል የእንጨቱ እና የሸክላው ከመቀያየሩ በቀር በናቡከደነጾር ህልም ላይ ያለውን
ቅደም ተከተልን ይከተላል። በህልሙ ውስጥ ድንጋዩ የሚመጣው በመጨረሻ ነው።
ምንም እንኳን ጣኦቶቹ የተሰሩባቸው እቃዎች ስም ዝርዝር ቢሆንም ድንጋይ ደግሞ
በአለም መንግስታት (ዳንኤል 2፡- 44-45 ይመልከቱ) ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ፣
ባቢሎን የምትወክለውን ያስከትላል።
ይህ ግብዣ ልክ በራዕይ መጽሐፍ እንደምንመለከተው የመጨረሻዋን ጊዜ ባቢሎንን
ያመላክታል። እንደ ቤልሻጽር በመጨረሻው ዘመን ያለችው ሴት፣ ባቢሎንም የወርቅ
ዋንጫን በእጇ ይዛ የረከሰውን መጠጧን ለአህዛብ ሁሉ ታጠጣለች። በሌላ አባባል
በሐሰተኛ አስተምህሮት እና በተደበላለቀ አምልኮ ስርዓት ፣ ዘመናዊቷ ባቢሎን
አለምን ወደ ክፋት ትማርካለች (ራዕይ 17፡-4-6)፣ በቅርቡ በእርሷ ላይ ስለሚመጣው
ፍርድ ግዴለሽ ናት። አንድ ቀን ግን ፍርድ ይመጣል።
በምን አይነት መንገዶች ነው ማህበረሰባችን እና ባህላችን በእግዚአብሔር
ቃል ውስጥ ያለውን እውነት የሚያረክሰው? በዚህ እርኩሰት እድል
ፋንታ እንዳይኖረን እንዴት ነው መጠንቀቅ የምንችለው? በሚያስቱ
መንገዶችም ጭምር? በሰንበት ቀን መልስዎን ወደ ውይይት ክፍልዎ
ይዘው ይምጡ።
ዳንኤል 5፡-5-8 ን ያንብቡ። ምንድነው የሆነው፣ ንጉሱ እንደዛ የሆነው ለምንድን ነው? በዳንኤል 2 ላይ ካለው ሁኔታ ጋር ይህ ሁኔታ እንዴት ነው የሚመሳሰለው፣ እናም መመሳሰሉስ ለምንድን ነው አስፈላጊ የሚሆነው? (መዝ 95፡-5፣ ቆላስያስ 1፡-15-17ም አንሁ ይመልከቱ)
ባለፈው ውድቀት ናቡከደነጾር እንዳደረገው(ዳንኤል 2፡-2፣ ዳንኤል 4፡-7) ፣ ቤልሻጽር
ኮከብ ቆጣሪዎችን፣ ከለዳውያንን፣ እና ትንቢት ተናጋሪዎችን ስለሚስጢራዊው
ጽሑፍ ይገልጹለት ዘንድ ጠራ። የሚችሉትን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ ንጉሱ የተጋነነ ክብር
ሁሉ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው። (1) ሐምራዊ ልብስ፣ በጥንት ጊዜ ንጉሳውያን
የሚለብሱት ቀለም ነው(አስቴር 8፡-15)። (2) የወርቅ ሐብል፣ ከፍተኛ ማህበራዊ
ደረጃን የሚያሳይ(ዘፍጥረት 41፡-42)፣ እና (3) ሶስተኛ የገዥነት ስልጣንን። ይህ
ሶስተኛው ሽልማት በትክክል የባቢሎንን ታሪካዊ ሁኔታ ያመላክታል። ምክንያቱም
ቤልሻጽር ከአባቱ ከናቦንዲዎስ ጋር ሆኖ ሁለተኛ ገዥ ነበር፣ እናም ሶስተኛ የገዥነት
ስልጣንን አቀረበ። ነገር ግን ከእነዚህ ፈታኝ ሽልማቶች ይልቅ አዋቂዎቹ እንደገና
ትርጓሜውን ማቅረብን አልቻሉም።
ከኃጢያቶቹ ሁሉ በላይ ንጉሱ ጥበብን በተሳሳተ ቦታ ላይ ለመፈለግ ሞከረ።
የባቢሎን ጠቢባን የመልዕክቱን ትርጉም ማቅረብ አልቻሉም። የተጻፈው፣ ነገር
እንደምንመለከተው፣ በራሳቸው ቋንቋ በአረማይክ ነው፣ ነገር ግን ምንም ትርጉም
አልሰጣቸውም። ይህ ምን አልባት ጌታ በኢሳያስ የተናገረውን ያስታውሰናል፣
‹‹ድንቅ ነገርን ተአምራትንም፥ እንደ ገና አደርጋለሁ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥
የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።››(ኢሳያስ 29፡-14)። ይህንን ጥቅስ ሐዋሪያው
ጳውሎስ ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ ይላል፣ ‹‹ ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚች
ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን
አላደረገምን? በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ
ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ
ሆኖአልና። ››(1ኛ ቆሮንቶስ 1፡20፣21)
አንዳንድ እውነታዎች የሰው ልጆች እራሳቸው እንዲደርሱባቸው መተዋቸው እጅግ
በጣም አስፈላጊ ነው። ለዚህ ነው እግዚአብሔር ይህንን እውነት ለእኛ የገለጸልን።
ሽልማቱ ወዴት ሊሔድ እንሚችል እና ወዲያውን የሚከተለውን አስቡት፣
ሽልማቶቹ ምን ያህል ዋጋ ቢስ እንደነበሩ አስቡ። በአለም ያሉ ነገሮች
እንዴት ብልጭ ብለው እንሚጠፉ እና ለምን ሁልጊዜ የምናደርገውን
ሁሉ ከዘለአለማዊው አንጻር መመልከት እንደሚያስፈልገን ይህ ሊነግረን
የሚችለው ምንድን ነው?
ዳንኤል 5፡-9-12ን ያንብቡ። ንግስቷ ስለ ዳንኤል ንጉሱ አስቀድሞ የሚያውቀውን ምንድን ነው የተናገረችው? ስለ እርሱ የማያውቅ እንዲያውም የዳንኤልን መኖር እንኳን እንዳላወቀ ሲሆን ምንድን ነው የሚለው?
የእራቱ አዳራሽ በእንግዳው መልዕክት ምክንያት ግራ ሲጋባ ፣ ንግስቷ መጣች እና
ግራ ለተጋባው ንጉስ አቅጣጫን ሰጠች። ንጉሱን ስለ ዳንኤል በናቡከደነጾር ዘመን
ያሳየውን ህልምን የመተርጎም ችሎታ እና ሚስጢራትን ስለ መፍታቱ አስታወሰችው።
ቤልሻጽር ካለፉት ይልቅ ብልህ ቢሆን ኖሮ የዚህን ሚስጢራዊ ጽሑፍ ትርጉም
ለማወቅ የት መሄድ እንደነበረበት ያውቅ ነበር። የንግስቷ ጣልቃ መግባት በዚህ
ሰዓት ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ለገባው ለንጉሱ፣ አስፈላጊ እንደሆነ
አረጋገጠ። ቃላቶቿ፣ ለቤልሻጽር በግዛቱ ውስጥ የዚህን ሚስጢራዊ ጽሑፍ ትርጉም
ሊሰጠው የሚችል ብቸኛ ወደ ሆነው ሰው እንሚመለከት ፣ ልክ እንደ ማንቂያ ነበሩ።
እንዲሁም ለንጉሱ ስለ ዳንኤል ማስተወሻን በቃሏ ነገረችው። ነብዩ የቅዱሱ አምላክ
መንፈስ፣ ብርሃን እና ማስተዋል፣ የመለኮት ጥበብ፣ የመንፈስ ልቀት፣ እውቀት ፣
የማስተዋል፣ ህልምን የመተርጎም፣ እንቆቅልሽን የመፍታት እና ሚስጢርን የመግለጥ
ችሎታ አለው፤ በናቡከደነጾር ዘመን (ዳንኤል 5፡-11፣12) የአስማተኞች፣ የኮከብ
ቆጣሪዎች፣ የከለዳውያን እና የትንቢት ተናጋሪዎች ሁሉ የባለይ ነው።
በዚህን ጊዜ ለምን ቤልሻጽር ዳንኤልን እንደረሳው እንገረማለን። ጥቅሱ ለዚህ ጥያቄ
ቀጥተኛ ምላሽን አይሰጥም ነገር ግን በዚህን ጊዜ ስለ ዳንኤል ልንገምት የምንችለው
ቢያንስ ንጉሱን በዘመኑ ለሶስት አመታት ካገለገለ በኋላ ( ዳንኤል 8፡-1፣27) በቀጥታ
አገልግሎት ላይ አልነበረም። አንዱ ምክንያት ምን አልባት ዕድሜው ሊሆን ይችላል።
ምን አልባት ወደ 80 አመቱ ተጠግቶ ሊሆን ይችላል፣ እናም ንጉሱ አመራሩን በአዲስ
ትውልድ አዋቅሮ ሊሆን ይችላል። ምንአልባት ንጉሱ ዳንኤልን የረሳበት ምክንያት
እራሱን ለዳንኤል አምላክ አሳልፎ ላለመስጠት ይሆናል። ነገር ግን ምክንያቱ ምንም
ቢሆን ወይም የሁሉም ምክንያቶች ጥርቅም ቢሆንም እንደ ዳንኤል ያለ አግልግሎት
እና ልምድ ያለው ሰው እንዲህ በፍጥነት መረሳቱ በጣም የሚገርም ነው።
ሮሜ 1፡-16-32 ን ያንብቡ። በምን አይነት መንገድ ነው በጥቅሱ
ውስጥ ያለው መርህ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሲገለጽ የምናየው፣ በዚህ
ታሪክ ውስጥ ብቻ አይደለም ነገር ግን ዛሬ በአለማችን?
ዳንኤል 5፡-13-28ን ያንብቡ። ዳንኤል በቅርብ ሊሆን ስላለው የንጉሡ መንግስት ማለፍ የሰጠው ምክንያት ምን ነበር?
በሁኔታዎች ተገዶ ንጉሱ ዳንኤልን እንዲያማክር ግድ ሆነበት ነገር ግን ይህን በቸልታ
የሚሰራው ይመስላል። ይህ ምንአልባት ከዳንኤል ይልቅ ስለ ዳንኤል አምላክ ያለውን
አስተሳሰብ ይበልጥ ይናገራል።
በምላሹ፣ ለንጉሱ ሽልማት የዳንኤል ምላሽ ስለ ባህሪው እና ቅድሚያ የሚሰጠው
ለማን እንደሆነ ብዙ ይናገራል። እንዲሁ ዳንኤል፣ የሚስጢራዊውን ቃል ትርጉም
ስላወቀ ሽልማቱ ዋጋ ቢስ መሆኑን በእውነት ተረድቷል።
ከዚያም ዳንኤል በሶስት ነገር ንጉሱን አመላከተው።
አንደኛ፣ ቤልሻጽር ሙሉ በሙሉ የናቡከደነጾርን ልምምድ እረስቷል። ያ ባይሆን
ኖሮ ቀድሞ ንስሃ ይገባ እና እራሱን ያዋርድ ነበር።
ሁለተኛ፣ ቤልሻጽር የቤተ-መቅደሱን መጠጫዎች ወይን ለመጠጣት እና
አማልክቱን ለማመስገን ተጠቅሟል። እዚህ ጋር ዳንኤል ቀደም ሲል እንደ ጠቀሰው
ጣኦትን ለመስራት ስደስት አይነት ማዕድናትን ተጠቁሟል።
ሶስተኛ፣ ንጉሱ እግዚአብሔርን ለማክበር ቸል ብሏል፣ ‹‹ትንፋሽህንና መንገድህን
ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም።›› (ዳንኤል 5፡23)
የንጉሱን ውድቀት ከተናገረ በኋላ ፣ ዳንኤል ወደ ትርጓሜው ሔደ። አሁን የመለኮት
ኪነ-ጽሁፍ ሶስት የአረማይክ ቃላቶችን እንደያዘ እንገነዘባለን ( የመጀመሪያው
ተደግሞ)። መሰረታዊ ትርጓሜያቸው ለንጉሱ እና ለባለሟሎቹ መታወቅ አለባቸው።
ማኔ ‹‹ተቆጠረ››፣ ቴቄል ‹‹ተመዘነ›› እና ፋሬስ ‹‹ተከፈለ›› ።
የሜዶ ፋርስ ሠራዊት የባቢሎን ቅጥር መግቢያ ላይ ሆነው፣ ንጉሱ እና ባለሟሎቹ
በዚያ ጽሑፍ መጥፎን ነገር መጠርጠር አለባቸው፣ ነገር ግን ባለሟሎቹ ለንጉሱ
የማያስደስትን ነገር መናገር አልፈለጉም። ዳንኤል ብቻ ነበር የመልዕክቱን ትክክለኛ
ጽሑፍ ቀይሮ በሚገባ አባባል እስከነ ሙሉ ትርጓሜው ማስቀመጥ የቻለ። ‹‹ቴቄል
ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው። ፋሬስ ማለት፥
መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው።›› (ዳንኤል 5፡
-27፣28)የሚመቹ እና የሚያስፈነድቁ ቃላት ብቻ አይደሉም።
ፍርድ በፍጥነት በንጉሱ ላይ መጣ። በእግዚአብሔር መታመንን
እንዴት ነው ልንማር የምንችለው፣ እንደ አሁኑ፣ ፍትህ እና ፍርድ
ገና ባልመጣበት? (መክብብ 8፡-11፣ ማቴ 12፡-36፣ ሮሜ 14፡-12)
ዳንኤል 5፡-29-31ን ከ ራዕ 14፡-8፣ ራዕይ16፡-19 ፣ እና ራዕይ 18፡-2 ጋር ያንብቡ። ከቤልሻጽር ባቢሎን ውድቀት ስለ መጨረሻዋ ዘመን ባቢሎን ውድቀት ምን ጠቋሚ ነገርን መማር እንችላለን?
ውድቀቱ ምንም ይሁን ፣ ቤልሻጽር ግን ለቃሉ ታማኝ የሆነ ሰው ነበር። ስለዚህ
ከመጥፎው ፍች ይልቅ በዳንኤል በተሰጠው አፈታት ተደስቷል፣ ለዛም ነው ለነብዩ
ሽልማቱን የሰጠው። የመልዕክቱን እውነታ በመቀበሉ ንጉሱ የዳንኤልን አምላክ
ህያውነት ተገነዘበ። በሚገርም ሁኔታ ዳንኤል ቀደም ሲል አልፈልግም ያለውን
ስጦታ ተቀበለ፣ ምን አልባትም እንደዚሁ ስጦታዎቹ በፍችው ላይ ምንም አይነት
ተጽዕኖ ስለማይኖራቸው ይሆናል። ከዚያም ባሻገር በዚያ ሰዓት እንደዚህ አይነት
ስጦታ ትርጉም አልባ ነው ምክንያቱም አገዛዙ እየወደቀ ስለሆነ። ስለዚህ ምን አልባት
በይሉኝታ ፣ ነብዩ ስጦታውን ተቀበለ ለጥቂት ሰዓታትም ቢሆን እያወቀው ሶስተኛው
አገረ ገዥ ለመሆን ማለት ነው።
ልክ በነብዩ እንደተነገረው፣ ባቢሎን ወደቀች። እናም በፍጥነት ተፈጸመ። ንጉሱ
እና ባለሟሎቹ እየጠጡ እያለ፣ ከተማዋ ያለጦርነት ወደቀች። እንደ ታሪክ አዋቂው
ሔሮዱተስ ፋርሳውያን የኤፍራጠስ ወንዝን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሔድ ቦይ
ከቆፈሩ በኋላ በወንዙ መሔጃ አድርገው ወደ ከተማዋ ገቡ። በዚያኑ ዕለት ቤልሻጽር
ተሰዋ። አባቱ ፣ ንጉስ ናምቦዲዬስ ከተማዋን ለቋል፣ በኋላም እራሱን ለአዲሱ ሐገረ
ገዥ እጅ ሰጠ። ስለዚህም የሰብአዊ ዘር የሚያውቃት ትልቋ ግዛት በዚህ ሰዓት ወደ
ፍጻሜዋ መጣች። ባቢሎን የወርቁ እራስ ከዚህ ወዲያ የለም።
‹‹ቤልሻጽር የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያውቅ እና እንዲያደርግ ብዙ አድሎች
ተሰጥተውታል። አያቱ ናቡከደናጾር ከሰዎች ማህበረሰብ ሲወገድ ተመልክቷል።
በኩራተኛው አገረ ገዥ ተከብረው የነበሩ ጠቢባን ፣ ጥበብ በሰጣቸው ሲወሰድባቸው
ተመልክቷል። ንጉሱ ከግዛቱ ሲወገድ ተመልክቷል እናም በሜዳ ከአራዊት ጋር
ሲወዳጅ አይቷል። ነገር ግን የቤልሻጽር የመደነቅ እና እራሱን በክብር ከፍ ከፍ
የማድረግ ፍቅር በፍጹም ሊረሳቸው የማይገቡትን ትምህርቶችን ከእርሱ ወሰዱበት።
እናም ኃጢያትን ፈጸመ ልክ በናቡከደነጾር ላይ ፍርድን እንዳስከተለበት ማለት
ነው። በጸጋ የተሰጠውን ዕድል አባከነ፣ ባለበት አቅም ከእውነት ጋር እንዲተዋወቅ
የተሰጠውን እድል ችላ አለ።
›› (ኤለን ጂ. ኋይት ፣ ባይብል ኢኮ፣ ሚያዚያ 25፣
1898)
ከ ‹‹እውነት ጋር እንድንተዋወቅ ›› ምን አይነት እድሎች አሉን? ይህ
ምን ማለት ነው? ምን ደረጃ ላይ ስንደርስ ነው ልናውቅ የሚገባንን
እውነት ሁሉ አውቀናል ማለት የምንችለው?
በጥንቱ አለም ትላልቅ ግብዣዎችን በአዳራሾቻቸው
ማድረግ የተለመደ ነበር፡፡ ንጉሶች ታላቅነታቸውን እና መታመናቸውን ለማሳየት
ግብዣዎችን በከፍተኛ ወጭ/መጠን እና ቅንጦት ማዘጋጀትን ይወዳሉ፡፡ የዚህን
ፌሽታ ዝርዝር አላማ በትክክል ባናውቅም፣ የሜዶ ፋርስ ሠራዊት ባቢሎንን
ለማጥቃት በተሰናዳበት ጊዜ መሆኑን ግን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን እንደ ሰው አነጋገር
ለዚህ ምክንያት አልነበረም፡፡ ባቢሎን የጠነከረ የምሽግ ግንብ፣ ለብዙ አመት የሚሆን
ምግብ፣ እና ብዙ ውሃ ፣ ምክንያቱም የኤፍራጠስ ወንዝ በከተማዋ አምብርት ላይ
ነው የሚፈሰው፣ ነበራት፡፡ ስለዚህ ሠራዊቱ ከተማዋን ቢከባትም ንጉሱ ቤልሻጽር
ድግሱን በማዘጋጀት ላይ ችግር አልታየውም፡፡ እናም በመጠኑ ከፍ ያለ፣ ወዲያው
ግን የተበላሸን፣ ፌሽታን አዘጋጀ፡፡ የሰብአዊ ዘር ጉራን በተመለከተ በተለይ ከጌታ
ኃይል ጋር ሲስተያይ ምን አይነት ኃይለኛ ምስክርነትን የሚሰጥ ነው፡፡ በዳንኤል
እግዚአብሔር ለንጉሱ እውነትን ለመማር ከተሰጠው እድል ይልቅ ‹‹ትንፋሽህንና
መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም። ›› ( ዳንኤል 5፡23) ሲል
ተናገረው፡፡
‹‹የሕዝቦች ታሪክ ለእኛ ዛሬ ይናገረናል፡፡ ለእያንዳንዱ ሕዝብ እና ለእያንዳንዱ ግለሰብ
እግዚአብሔር በዕቅዱ ውስጥ ስፍራ አለው፡፡ ዛሬ ሰዎች እና ሕዝቦች በማይሳሳተው
እጁ ባለው መለኪያ ይፈተናሉ፡፡ሁሉም በየምርጫቸው መዳረሻቸውን ይወስናሉ፡፡
፣ እናም እግዚአብሔር ለአላማው ስኬት ሁሉንም ይመራል፡፡ ››(ኤለን ጂ. ኋይት ፣
ፕሮፌትስ ኤንድ ኪንግስ፣ ገጽ 536)
1.በውይይት ክፍላችሁ፣
የማህበረሰብ እና የባህል
ባለው መልስ ተወያዩ፡፡
ቤተክርስቲያን እና እንደ
መሆን ይገባዋል?
ስለ የእግዚአብሔርን እውነት የሚያረክሱ
አካሔዶች በሚያነሳው የዕሁዱ ጥያቄ ላይ
እነዚያ መንገዶች ምን ምን ናቸው? እንደ
ግለሰብ ለእነዚህ እርኩሰቶች ምላሻችን ምን
2.ይህ ታሪክ ስለ ድነት፣ በምናውቀው መጠን ያህል ሳይሆን ላወቅነው
ነገር ባለን የእኛ ምላሽ መጠን እንደሆነ ምን ያስተምረናል? (ዳንኤል
5፡-22ን ይመልከቱ)
3.ዳንኤል 5፡-23 ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ምን አይነት
አስፈላጊ መንፈሳዊ መርሆች ይገኛሉ? ለምሳሌ እግዚአብሔርን ስለ
መጋፋት ጥቅሱ እንዴት ነው የሚያስጠነቅቀን? ወይም ጥቅሱ ስለ
እግዚአብሔር ፈጣሪነት ብቻ ሳይሆን ኑሯችንን የሚያስቀጥል እርሱ
እንደሆነ እንዴት ነው የሚያስተምረን?
4.ቃሉ ምን እንደሚል እንኳን ሳያውቅ ቤልሻጽር ፈርቷል( ዳንኤል
5፡-6)፡፡ ይህ በበደለኛ ህሊና መኖር ማለት ምን እንደሆነ፣ ምንድን
ነው የሚነግረን?