ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳንኤል 3፣ ራዕይ 13፡-11-18፣ ዘጸአት 20፡- 3-6፣ ዘዳግም 6፡- 4፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡- 12-26፣ ዕብራውያን 11
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ!” (ዳንኤል 3፡-17)
ስ
ለዚህ እነዚያ ወጣቶች በመንፈስ ተሞልተው ለመላው ሕዝብ ስለ እምነታቸውና
የሚያመልኩት እውነተኛ እና ሕያው አምላክ ስለመሆኑ አወጁ። ስለ እምነታቸው
ያላቸውን መርህ ያሳዩበት ሁኔታ ልብን የሚነካ ነበር። የህያውን አምላከ ኃይል
እና ታላቅነት በጣኦት አምላኪዎች ዘንድ ተጽእኖ በማድረግ፣ ስለ እግዚአብሔር
ያላቸውን አክብሮት መግለጽ/ማሳየት ነበረባቸው። የክብራቸው እና የአምልኳቸው
ዋና እርሱ እንደሆነ መገለጽ ነበረበት፣ እናም ሕይወትን እስከ መስጠትም ድረስ
ቢሆንም እንኳን ትንሽ እንኳን ለጣኦት አምልኮ ሊያሳምናቸው አልቻለም ።
እነዚህ
ትምህርቶች በመጨረሻው ዘመን ሊያጋጥሙን ከሚችሉ ልምምዶች ጋር ቀጥተኛ
እና ወሳኝ ግንኙነት አላቸው (ኤለን.ጂ. ኋይት ፣ ኢን ሔቭንሊ ፕሌስስ ፣ ገጽ 149)።
በአምልኮ ምክንያት የሞትን ፍርሃት መጋፈጥ ምን አልባት በጣም ሳይንሳዊ ያልሆነ
እና የመናፍስታዊ ዘመን ይመስላል፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው በመጨረሻው
ዘመን አለም በጣም ‹አደገ/መጠቀ › በሚባልበት ዘመን አለም አቀፋዊ በሆነ መልኩ
ተመሳሳይ ነገር ይከሰታል። ስለዚህ ከዚህ ታሪክ ጥናታችን ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ
አባባል የእግዚአብሔር ታማኞች ስለሚያጋጥማቸው ነገር የሆኑ ምልከታዎችን
እናገኛለን።
የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለጥር 16 ሰንበት ይዘጋጁ።
ዳንኤል 3፡-17 ያንብቡ። ይህንን ምስል ለመስራት ንጉሱን ያነሳሳው ምንድን ነው?
በህልሙ እና በምስሉ ግንባታ መካከል ወደ ሃያ አመት ያህል አልፏል። ሆኖም ግን
ንጉሱ ህልሙን እና ባቢሎን ወድቃ በሌሎች ሃያላት እንደምትተካ መቼም ሊረሳው
አልቻለም። የምስሉ የወርቅ እራስ መሆኑ ብቻ አላስደሰተውም፣ ንጉሱ በምስሉ
ሁለንተና መመሰልን እና በዘመናት ታሪክ ውስጥ ሁሉ ብቻውን የመጽናትን መልዕክት
ለማድረስ ፈልጓል።
ይህ አይነት የኩራት አስተሳሰብ የባቢሎን ግንብ ገንቢዎችን ያስታውሳል፣
በትዕቢታቸው፣ እግዚአብሔር እራሱን መፈታተን ሞከሩ። የናቡከደነጾር ትዕቢትም
ከዚህ የሚያንስ አይደለም። እንደ ባቢሎን ንጉስነቱ በርካታ ነገሮችን ፈጽሟል፣
መንግስቱ ያልፋል ከሚለው ሐሳብ ጋር መኖር አልቻለም። ስለዚህ ለእራሱ ደስታ
ባደረገው ጥረት፣ ሐይሉን ለማነቃቃት እና በዚያውም ደግሞ ለእርሱ ሐሳብ
ታማኞች የሚሆኑትን ለማጥናት ምስልን አሰራ። ምንም እንኳን ምስሉ ንጉሱን ወይም
አማልክትን ይወክል በግልጽ አይታወቅም። በጥንት ጊዜ ፖለቲካን እና ሐይማኖትን
የሚለየው መስመር ፣ በጣም ግልጽ እንዳይደለ መርሳት የለብንም።
ከእውነተኛ አምላክ ጋር እንዲተባበር ለናቡከደነጾር ሁለት እድሎች እንደነበሩት
እንዲሁ ልናስታውስ ይገባል። አንደኛ፣ ወጣት ዕብራውያኑን በፈተናቸው ጊዜ
ከባቢሎናውያኑ አስር ጊዜ እጥፍ በልጠው ተገኝተዋል። ከዚያም ሁሉም በባቢሎን
የሚገኙ ጠቢባን ለንጉሱ ማድረግ ያልቻሉትን፣ ዳንኤል የንጉሱን ሐሳቦች ፣ ሕልሙን
እና ትርጓሜውን ነግሮታል። በመጨረሻም የእነ ዳንኤል አምላክ የበላይነትን
ተገንዝቧል። ነገር ግን አስገራሚ በሆነ መልኩ እነዚያ ስነ-መለኮታዊ ትምህርቶች
ናቡከደነጾርን ወደ ጣኦት አምልኮው እንዳይመለስ ሊከልሉት አልቻሉም።
ለምን?
ሊሆን የሚችለው ትዕቢቱ/ኩራቱ ነው። ሐጢያተኛ የሰብአዊ ዘሮች ቁሳዊ እና
የዕውቀት ክዋኔአቸው ባዶ እና ጠፊ እንደሆኑ መገንዘብን እንቢ ይላሉ። ምን አልባት
እኛም ከሚገባው በላይ ትኩረትን ለስኬቶቻችን ስንሰጥ፣ በዘለአለማዊነት አንጻር ምን
ያህል ትርጉም አልባ መሆናቸውን ስንረሳ እንደ ትንንሽ ‹ናቦከደነጾሮች› እንሆናለን።
በአሳች ሁኔታም እንኳ ልክ ናቡከደነጾር እንደገባበት ባለ ተመሳሳይ
ወጥመድ ፣ ላለመውደቅ እንዴት መማር እንችላለን?
ዳንኤል 3፡-8-15 እና ራዕይ 13፡-11-18 ያንብቡ። በዳንኤል ዘመን እና በመጨረሻው ዘመን መካከል ምን አይነት ተመሳሳይነትን ማየት እንችላለን?
ዱራ፣ በከለዳውያን ቋንቋ ስሙ ‹‹በግንብ የታጠረ ቦታ›› የሚል ትርጓሜ አለው፣ በዚህ
ሜዳ ላይ የቆመው የወርቅ ምስል ያንን በግንብ የታጠረ ቦታ ልክ የትልቅ ቤተ መቅደስ
አይነትን ስሜት ፈጥሮለታል። ልክ ያ በቂ እንዳልሆነ ሁሉ በአቅራቢያው ያለው
የእቶን እሳት ስፍራ መስዋዕትን በደንብ ማስከተል ይችላል። የባቢሎናውያን ሙዚቃ
ደግሞ የስነ-ስርዓቱ አካል ነው። የአክብሮቱን ስርዓት ሙሉነት እና ውጤታማነት
ለማቅረብ ሰባት አይነት የሙዚቃ መሳሪያዎች ተዘርዝረዋል።
ዛሬ ከየአቅጣጫው በሚወረወሩ በአዳዲስ የኑሮ ዘይቤዎች፣ አዳዲስ አስተሳሰቦች
እና በቃሉ ከተገለጸው የእግዚአብሔር የበላይነት ጋር ያለንን ቃል ኪዳን እና
ታማኝነታችንን ለዘመናዊዋ የባቢሎን መንግስት ተከታዮች አሳልፈን እንድንሰጥ
በሚያስተጋቡ ጥሪዎች እንዋከባለን። የአለም ሳቢነት በኃይል በበዛበት ጊዜ፣
የመጨረሻው ታማኝነታችን ለፈጣሪችን ለእግዚአብሔር መሆኑን እራሳችንን
ልናስታውሰው ይገባል።
እንደ ትንቢታዊ የጊዜ መቁጠሪያ ቀመር እኛ እየኖርን ያለነው በምድራችን የመጨረሻ
ዘመናት ነው። ራዕይ 13 የምድር ነዋሪዎች ሁሉ አውሬውን እንዲያመልኩ ጥሪ
እንደሚደረግላቸው ያስታውቃል። ያም አካል ‹‹ ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ
ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው
ምልክትን እንዲቀበሉ፥ ›› (ራዕይ 13፡-16) ያደርጋል።
ለአውሬው ምስል ታማኝነታቸውን የሰጡ ስድስት አይነት ሰዎች ተነግረዋል። ‹‹
ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ››። የአውሬው
ቁጥር፣ 666 እንዲሁ ስድስት ላይ ያተኩራል። ይህ በናቡከደነጾር የቆመው ምስል
ዘመናዊቷ ባቢሎን በመጨረሻው ዘመን የምታደርገውን የሚሳይ ነው (ዳንኤል 3፡-1ን
ይመልከቱ፣ የስድስት እና የስልሳ ተምሳሌት)። ስለዚህ ከትረካው ውስጥ ስለወጣው
እና እግዚአብሔር የዚህችን ምድር ጉዳይ በሉአላዊነት እንደሚመራ ትኩረት
በመስጠት መልካም አድርገናል።
አምልኮ በአንድ ነገር ወይም አንድ ሰው ፊት መስገድ እና በግልጽ
የመጨረሻ ታማኝነትን መስጠት ብቻ አይደለም። በመጨረሻችን
ከጌታችን ውጭ እንድናመልክ ሊያደርጉን የሚችሉ ሌሎች አታላይ
መንገዶች ምን ምን ናቸው?
በንጉሱ የተጣለባቸው የምስሉ አምልኮ፣ ለሶስቱ ዕብራውያን በቀደመው አመታቶቻቸው የተለማመዱት በእየሩሳሌም የነበረው አምልኮ ተመሳሳይ/ ግልባጭ ነበረ። ምንም እንኳን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የንጉሱ መሳፍንት ቢሆኑም፣ ለአምላካቸው ያላቸው ታማኝነት ለሰብአዊያን ያላቸውን ታማኝነት ገደብ እንዲኖረው አድርጎ ነበር። እንደ ታማኝ አስተዳዳሪ በእርግጠኝነት ንጉሱን ለማገለገል ፈቃደኛ ናቸው፣ ቢሆንም ግን ስርዓቱን ሊቀላቀሉ አልፈቀዱም። ዘጸአት 20፡-3-6 እና ዘዳግም 6፡-4 ያንብቡ። ጥቅሶች የእነዚህ ሰዎች አቋም ላይ በእርግጠኝነት ተጽዕኖ ያደረጉት በምንድን ነው?
በንጉሱ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ ሁሉም ሰዎች የሙዚቃውን ድምጽ በሰሙ
ጊዜ ለወርቁ ምስል ወደቁና ሰገዱ። ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ብቻ ነበሩ ንጉሱን
ያልታዘዙ። ወዲያውኑ የተወሰኑ ባቢሎናውያን ጉዳዩን በንጉሱ ዘንድ አቀረቡ።
ከሳሾቹ ንጉሱን እንዲህ በማለት አበሳጩት፡- 1) በባቢሎን አውራጃዎች ላይ
ንጉሱ እራሱ ነው እነዚህን ያስቀመጣቸው። 2) አይሁዳውያኑ የንጉሱ አማልክትን
አያገለግሉም። 3) ንጉሱ ያቆመውን የወርቅ ምስል አያመልኩም(ዳንኤል 3፡
-12)። ነገር ግን ከንዴቱ ይልቅ መጀመሪያ ሁለተኛ እድል ሰጣቸው። እነዚህ ሰዎች
አካሔዳቸውን እንዲመረምሩ እና ምስሉን እንዲያመልኩ ንጉሱ አጠቃላይ ሂደቱ
እንዲደገም ፈቃደኛ ሆነ። እምቢ ካሉ ወደ እቶኑ እሳት ይጣላሉ። እናም ጥሪውን
ሲያጠናቅቅ በጣም ከፍተኛ በሆነ ትዕቢት ነበር ‹‹ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን
ነው? ብሎ ተናገራቸው።››(ዳንኤል 3፡15)።
በመንፈሳዊ ጽናት ታድለው ለንጉሱ እንዲህ ሲሉ ምላሽ ሰጡ ‹‹ የምናመልከው
አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል፥
ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ
ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት። ›› (ዳንኤል 3፡-17፣18)።
አምለካቸው ነጻ ማውጣት እንደሚችል ቢያውቁም፣ እንደሚያድናቸው ግን
እርገጠኛ አይደሉም። በሕይወታቸው ሊቃጠሉ እንደሚችሉ ቢያውቁም፣ የንጉሱን
ትዕዛዝ ለመቀበል እምቢ አሉ። እንደዚህ አይነት እምነት የት ነው የምናገኘው?
ዳንኤል 3፡-19-27ን ያንብቡ። ምንድን ነው የሆነው? በእሳቱ ውስጥ የነበረው ሰው ማነው?
ሶስቱን ዕብራውያን ወደ እሳቱ ካስጣለ በኋላ፣ ናቡከደናጾር በእሳቱ ውስጥ
አራተኛን ሰው በማየቱ ግራ ተጋባ። የሚያውቀውን ያህል አራተኛውን ሰው ልክ
‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ›› እንደሆነ ለየው (ዳንኤል 3፡-25)።
ንጉሱ ከዚያ ሌላ ምንም አላለም፣ ነገር ግን ያ አራተኛ ሰው ማን እንደሆነ እናውቃለን።
ከሰዶም እና ገሞራ በፊት ለአብርሐም ተገልጦለታል፣ ከያዕቆብ ጋር በያቦቅ ወንዝ ዳር
ታግሏል፣ እንዲሁ በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ውስጥ ለሙሴ ተገልጧል። ስጋ ከመልበሱ
በፊት የነበረው ፣ እግዚአብሔር ከሰዎች ልጆች መከራ ጋር አብሮ እንዳለ ለማሳየት
የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ኤለን ጂ ኋይት ‹‹ እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑትን አይረሳም፣ የእርሱ ምስክሮች ወደ
እቶን እሳቱ ሲጣሉ ፣ አዳኙ እራሱን ለእነርሱ በግል ገለጠ፣ እናም በእሳቱ መካከል
አብረው ተመላለሱ። የሙቀት እና የቅዝቃዜ ጌታ ባለበት፣ እሳቱ የማቃጠል አቅሙን
አጣ ››(ፕሮፌትስ ኤንድ ኪንግስ፣ ገጽ 508፣509) ትላለች።
በኢሳያስ ጌታ እንደተናገረው ‹‹ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥
በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ
አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።››(ኢሳያስ 43፡-2)።
ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት ታሪኮችን ብንወድም፣ ስለ እምነታቸው ከመገደል
ነጻ ስላልወጡ ሌሎች ጥያቄን ማስነሳቱ አይቀርም። እነዚያ ሰዎች በእርግጠኝነት
የኢሳያስን እና የዘካሪያስን ልምምድ፣ በማያምኑ ነገስታት ለሞት የተሰጡትን፣
ያውቃሉ። ሁሉም በሚገርም ታሪክ፣ በእኛም ዘመን ፣ ታማኝ ክርስቲያኖች
በጨረሻቸው በመጥፎ ስቃይ ውስጥ በጽናት አልፈዋል። ቢያንስ በዚህ ፣ በተአምራዊ
ነጻ መውጣት ሳይሆን ነገር ግን በሚያም አሟሟት አልፈዋል። በዚህ ግን አማኞች
ተአምራዊ ነጻ መውጣት አገኙ፣ እንደምናውቀው እንደዚህ አይነት ነገር በብዛት
አይሆንም።
በሌላ ጎን ደግሞ እነርሱ በዚህ ካጋጠማቸው ፍርድ ውጭ ሁሉም
የእግዚአብሔር ታማኞች የሚያገኙት ተአምራዊ ነጻ መውጣት ምንድን
ነው? (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡-12-26ን ይመልከቱ)
በሲድራቅ ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ልምምድ ላይ አስተያየት ስንሰጥ፣ እራሳችንን እንዲህ ስንል ልንጠይቅ እንችላለን፣ ለእንደዚህ አይነት ጠንካራ እምነት ሚስጥሩ ምንድን ነው? ምስሉን ከማምለክ ይልቅ በህይወት በእሳት ለመቃጠል ይመርጡ ዘንድ እንዴት ቻሉ? ለንጉሱ ትእዛዝ እራሳቸውን አስገዝተው ለመስገድ የሚያስችሏቸው ሊጠቅሷቸው የሚችሉአቸውን ምክንያቶች አስቡ። ሆኖም ግን እነዚያን ከማድረግ ይልቅ ሌሎች ብዙዎች እንዳደረጉት ሊሞቱ ይችላሉ፣ ሆነም ቀረ ግን እነሱ ጸንተው ቆሙ። ዕብራውያን 11ን ያንብቡ። እምነት ምን እንደሆነ ይህ ምን ያስተምረናል?
እንደዚህ አይነት እምነትን ለማሳደግ፣ እምነት እራሱ ምን እንደሆነ መገንዘብን
ይፈልጋል። አንዳንድ ሰዎች በመጠን የሚለካ አድርገው ይወስዱታል፣ እምነታቸውን
የሚለኩት ከእግዚአብሔር በሚያገኙአቸው ምላሾች ልክ ነው። ወደ ገበያ ቦታ
ይሔዱ እና ስለ መኪናቸው ማቆሚያ ቦታ ይጸልያሉ። ልክ እንደደረሱ ቦታን ካገኙ
ልክ ጠንካራ እምነት እንዳላቸው እራሳቸውን ይቆጥራሉ። ማቆሚያ ቦታዎች ሁሉ
ግን ከተያዙ፣ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን መስማት እስከሚችል ድረስ የሚያደርስ
ጠንካራ እምነት እንደሌላቸው ሊያስቡ ይችላሉ። ስለ እምነት እንዲህ ያለ አይነት
አስተሳሰብ በጣም አደገኛ ይሆናል፣ ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር ሊያምታታ እና
በእግዚአብሔር ሉአላዊነት እና ጥበብ ላይ ሊያደናግር ይችላል።
በእርግጥ እውነተኛ እምነት፣ በዳንኤል ጓደኞች እንደታየው ያለ ከእግዚአብሔር
ጋር ባለን የግንኙነት ደረጃ እና ሙሉ በመሉ በእርሱ ላይ ባለ መተማመን ይለካል።
እውነተኛ እምነት የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እኛ መሻት እንዲያዘነብል አይሻም፣
ይልቅ የእኛን መሻት ለእርሱ ፈቃድ አሳልፎ ይሰጣል። እንደተመለከትነው ሶስቱ
ዕብራውያን ንጉሱን ሲጋፈጡ እና ለእግዚአብሔር ባላቸው ታማኝነት ጸንተው
ሲቆሙ ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ ስላስቀመጠው ነገር በእርግጠኝነት የሚያውቁት
ነገር አልነበረም። ተከትሎ ከሚመጣው ነገር ይልቅ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ
ወሰኑ። ይህ እንግዲህ የበሰለ እምነት ባህሪ ነው። ስለምንፈልገው ነገር ለጌታ ስንጸልይ
እውነተኛ እምነትን እናሳያለን ነገር ግን ምን እና ለምን እንደሆነ ባልገባን ሰዓትም
ጭምር እንኳ ለእኛ መልካም የሚሆውን እንደሚያደርግ እንታመነው።
እምነትን በዕለት ተዕለት መለማመድ የሚያስችሉን ፣ ‹በትንንሽ
ነገሮችም› እምነታችን እንዲያድግ በማስቻል የሚረዱን እና ለትልልቅ
ተግዳሮቶች የሚያዘጋጁን መንገዶች ምን ምን ናቸው? ለምንድን ነው፣
በብዙ መንገዶች በ ‹ትንንሽ ነገሮች › ላይ ያሉ ፈተናዎች በጣም
አስፈላጊዎች የሚሆኑት?
‹‹ በጣም አስፈላጊው ነገር በዱራ ሜዳ ላይ ከነበረው
የዕብራውያኑ ወጣቶች ልምምድ የምናገኛቸው ትምህርቶች ናቸው። በዚህ
በዘመናችን ብዙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች፣ ክፉን ባለማድረግ መልካም ቢሆኑም
ለውርድት ተላልፈው በመሰጠት ሲሰቃዩ እና በሰይጣን በሚነዱ ፣በቅናት እና
በአክራሪነት በተሞሉ ሰዎች እጅ እንደማይሆን ይሆናሉ። በተለየ የአራተኛው ትእዛዝ
ሰንበትን አክባሪዎች ላይ የሰዎች ቁጣ ይነሳሳል፣ እናም በመጨረሻም በአለም አቀፋዊ
አዋጅ ለእነዚያ ሞት እንሚገባቸው ይታወጃል።
‹‹በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ለተጠራው የመከራ/ጭንቀት ጊዜ ወደማይደናቀፍ
እምነት ይጣራል። ልጆቹ ሊመለክ የሚገባው እርሱ ብቻ መሆኑን ሊያሳዩ ይገባል፣
እናም ለሀሰት አምልኮ ሊያሳምን የሚችል ሌላ ነገር የለም፣ የእራስ ሕይወትም
እንኳን ቢሆን። ለታመኑ ልቦች፣ የሐጥያተኛና የጥቂት ሰዎች ትእዛዝ ከዘለአለማዊው
የእግዚአብሔር ቃል አንፃር ቁም ነገር አልባ ይሆናል። ምንም እንኳን ወጤቱ እስር
ወይም መባረር ወይም ሞት ቢሆንም እውነት ትታዘዛለች ››( ኤለን ጂ ኋይት ፣
ፕሮፌትስ ኤንድ ኪንግስ፣ ገጽ 512፣513)
1. 1ኛ ጴጥሮስ 1፡-3-9ን ያንብቡ። ለምንድን ነው እግዚአብሔር
አንዳንዶችን ከስቃይ ሲያድን ሌሎችን የማያድን? ወይም ለእንደዚህ
አይነት ጥቄዎች ምላሽን አሁን የምናገኘው አይደለም ፣ ተአምራዊ
መዳን/ነጻ መውጣት በማይሆንባቸው ጊዜ፣ ከተስፋ መቁረጥ ይልቅ
በእግዚአብሔር መልካምነት ልንታመን የሚገባው ለምንድን ነው?
2.የዕብራውያኑ ገጠመኝ በቶን እሳቱ ውስጥ ሞት እንኳን ቢሆን ፣ ምን
አይነት ትምህርትን ልንማር እንችል ነበር?
3.ከመጨረሻው ዘመን ክስተቶች መረዳታችን ላይ የምናመልከው
ማዕከል የሚሆንበት ውጫዊው ምልክት ምንድን ነው? አሁን ይህ
በእውነት ሰንበት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ምንድን ነው ሊነግረን
የሚገባው?
4.ሉቃስ 16፡-10ን ያንብቡ። በዚህ ያለው የክርስቶስ ቃል በእምነት
መኖር በእውነት ምን እንደሆነ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?
5.ዳንኤል 3፡-15ን እንደገና ያንብቡ፣ ናቡከደነጾር ‹‹ ከእጄ ሊያድናችሁ
የሚችል አምላክ ማነው ›› ሲል ያን ጥያቄ እርስዎ እንዴት ነበር
የሚመልሱት?