ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳንኤል 2፡-1-16፣ ሐዋሪያት 17፡ -28፣ ዳንኤል 2፡-17-49፣ መዝሙር 138፣ ዮሐንስ 15፡-5፣ ዘዳግም 32፡-4፣ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡-4
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- ”ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ“ (ዳንኤል 2፡-20)
በ
ግሪንላንድ ዙሪያ ውሃ ላይ በተለያየ መጠን ያሉ የበረዶ ግግሮች አሉ። አንዳንድ
ጊዜ አነስተኛ መጠን ያላቸው በአንድ አቅጣጫ ሲንሳፈፉ ፣ ትልልቆቹ ደግሞ
በሌላኛው ይንሳፈፋሉ። ይህ የሚሆነው በምድረ ገጽ ያለው ነፋስ ትንንሾቹን ግግሮች
ወደ አንድ አቅጣጫ ሲነዳቸው፣ ትልልቆቹ ደግሞ በጥልቁ ባህር ባለው የውሃ ሞገድ
ይንቀሳቀሳሉ። በታሪክ ውስጥም የህዝቦች መነሳትን እና መውደቅን ስናይ በተመሳሳይ
መልኩ ልክ በምድረ ገጽ ላይ እንዳለው ነፋስ እና በጥልቁ ባህር እንዳለው የውሃ
ሞገድ ይመስላል።
ነፋሱ ልክ እንደ የሰው ልጆች መሻት የሚለዋወጡትን ነገሮች
እና የማይገመቱን ነገሮች ይወክላል። ነገር ግን በዚያኑ ሰዓት ደግሞ ከእነዚህ ሐይለኛ
ነፋሳት እና ወጀብ ጋር የሚሰራ ሌላ ኃይል አለ፣ በጣም ሐይለኛ እና የባህርን ሞገድ
የሚመስል። እርሱም የተረጋገጠው የእግዚአብሔር በጥብብ የተሞላ እና ሉአላዊ
አላማን የያዘው እንቅስቃሴ ነው።
ኤለን ጂ ኋይት እንድምትናገረው ‹‹ ልክ ከዋክብት
በተወሳሰበውና በሰፊ መንገዳቸው እንደሚሔዱ እንዲሁ የእግዚአብሔርም ሐሳብ
ሲሔድ አይፈጥንም አይዘገይምም ›› (የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 32) ። ምንም እንኳ
ሕዝቦች ቢነሱም ቢወድቁም፣ አስተሳሰቦች፣ እና የፖለቲካ ቡድኖች በሰብአዊ ዘር
ፍላጎት ብቻ የተከሰቱ ቢመስልም፣ ዳንኤል 2 እንደሚያሳየን ግን ወደ ማጠቃለያው
ፍጻሜ የሚያመጣው የሰማይ አምላክ ነው።
ለጥር 9 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ዳንኤል 2፡-1-16ን ያንብቡ። ዕብራውያኑ በንጉሱ ሕልም ምክንያት ምን አይነት ችግር ነው ያጋጠማቸው?
በጥንቱ አለም፣ ሕልሞች በጣም በትኩረት ይወሰዳሉ። ሕልሙ አስጠንቃቂ ሲሆን
ብዙ ጊዜ የሚያሰጋ ጥፋትን ይጠቁማል። ስለዚህ ንጉስ ናቡከደነጾር ስለ ህልሙ ለምን
በጣም እንደተሸበረ የሚስተዋል ነው፣ ነገሩን ደግሞ ያባባሰው ሕልሙን ማስታወስ
አለመቻሉ ነበር። የባቢሎናውያን አዋቂዎች እንደሚያምኑት አማልክቶቻቸው
የህልሙን ትርጓሜ ሊሰጡ ይችላሉ ነገር ግን በዳንኤል መጽሐፍ እንዳለው እንደዚህ
አይነት ህልም አዋቂዎቹ ሊያደርጉት የሚችሉት ምንም ነገር የለም ምክንያቱም ንጉሱ
ሕልሙን እረስቶታል። የህልሙ ይዘት እንኳን ቢገለጽላቸው ንጉሱን ለማስደሰት
ትርጓሜውን ይዘው ይቀርቡ ነበር። ነገር ግን በዚህ ግልጽ በሆነ ሁኔታ የህልም
አዋቂዎቹ ለንጉሱ ያለመው ሕልም ምን እንደሆነ ሊነግሩት አልቻሉም፣ ‹‹ንጉሡም
የሚጠይቀው ነገር የቸገረ ነው መኖሪያቸው ከሰው ጋር ካልሆነ ከአማልክት በቀር
በንጉሡ ፊት የሚያሳየው ማንም የለም አሉ።››(ዳንኤል 2፡ 11) እንዲሉ ተገደዱ።
በበዛ መፍረክረክ ውስጥ ሆኖ ንጉሱ በባቢሎን ውስጥ ያሉ ጠቢባን ሁሉ እንዲገደሉ
አዘዘ። እንደዚህ አይነት ግፍ በጥንቱ አለም አዲስ አይደለም። የታሪክ ማስረጃዎች
እንደሚጠቁሙት በሴራ ምክንያት ቀዳማዊ ዳሪዎስ የጅምላ ግድያን አድርጓል
እንዲሁ አርጤክስስ የገነባው ድልድይ የፈረሰበትን አንድ ኢንጂነርን ገድሏል።
ናቦከደነጾር አዋጁን ሲያውጅ ዳንኤል እና ጓደኞቹ ስልጠናቸውን ጨርሰው ወደ
ንጉሱ አዋቂዎች ጎራ እየተቀላቀሉ ነበር። በዚህ ምክንያት የሞት አዋጁ እነሱንም
የሚያጠቃልል ነበር። በእርግጥ በመጀመሪያ የተጻፈበት ቋንቋ እንደሚገልጸለው
እርምጃው የጀመረው ወዲያውኑ ነበር ፣ እናም ዳንኤል እና ጓደኞቹ ቀጥለው
የሚገደሉ ነበሩ። ነገር ግን ዳንኤል ‹‹ በፈሊጥና በጥበብ ››(ዳንኤል 2፡14) የሞት አዋጁን
የሚያስፈጽመውን ሰው አርዮክን ቀረበው። በመጨረሻ ዳንኤል ከንጉሱ ከራሱ
የህልሙን ሚስጢር ለመፍታት ተጨማሪ ጊዜን ጠየቀ። በሚገርም ሁኔታ ምንም
እንኳን ንጉሱ አስማተኞች ተጨማሪ ጊዜን የመግዛት ሙከራቸውን ቢቃወምም
ለዳንኤል የጠየቀውን ጊዜ ፈቀደለት። ዳንኤል በእርግጠኝነት ይህን ጉዳይ ሰው ምላሽ
ሊሰጥ እንደማይችል ከአስማተኞቹ ጋር ተስማማ ነገር ግን ነብዩ የህልሙን ፍች እና
ሕልሙንም ሊገልጽ የሚችል የሰማይ አምላክ እንዳለ ግን ያውቃል።
የስነ- መለኮት አጥኝዎች እንደሚሉት ምንም እንኳን ለፍጡራን በሁሉም ስፍራ
መገኘት የተለየ ነገር ቢሆንም ለእግዚአብሔር ግን ይቻል ነበር። እግዚአብሔር
በሁሉም ስፍራ የመገኘቱን ሀቅ ለናቡከደነጾር ሕልምን የሰጠበት ሁኔታ ምን
ሊያስተምረን ይችላል? (ሐዋሪያት ስራ 17፡-28ን እንዲሁ ይመልከቱ)
ዳንኤል ሶስቱን ጓደኞቹን ይዞ እግዚአብሔር ህልሙን ካልገለጻላቸው ሊገደሉ እንደሆነ በመንገር ወደ ጸሎት ይዟቸው ሔደ። ትልቅ ችግር በገጠመን ጊዜ ሁሉ እኛም እንዲሁ፣ አምላካችን እግዚአብሔር ለመፍታት የማይቻሉ ተግዳሮቶችንም ጭምር ለመፍታት በቂ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል። ዳንኤል 2፡-17-23ን ያንብቡ። የጸለዩአቸው ሁለቱ አይነት ጸሎቶች ምን ምን ናቸው?
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ሁለት አይነት ጸሎቶች ተጠቅሰዋል። የመጀመሪያው ዳንኤል
ሕልሙን እና የህልሙን ትርጓሜ የጠየቀበት የልመና ጸሎት(ዳንኤል 2፡17-19) ነው።
የዚህ ጸሎት ቃላት አልተሰጡም ነገር ግን ዳንኤል እና ጓደኞቹ ‹‹ስለዚህ ምሥጢር
ምሕረትን ከሰማይ አምላክ ይለምኑ ዘንድ ነገሩን ለባልንጀሮቹ ለአናንያና ለሚሳኤል
ለአዛርያም አስታወቃቸው።›› (ዳንኤል 2፡-18)። ሲጸልዩ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን
መልሶ የንጉሱን ህልም እና ትርጓሜውን ገለጸላቸው። በእርግጠኝነት ልናርፍ
እንችላለን ምንም ጊዜ ‹‹ምህረትን ከሰማይ አምላክ ›› ስንሻ፣ ምንም እንኳን እዚህ
እንደምናየው ድራማዊ በሆነ ሁኔታም ባይሆን ጸሎታችን ወዲያውኑ ይሰማልናል፣
ምክንያቱም የእነ ዳንኤል አምላክ የእኛም አምላክ ነው።
እግዚአብሔር ለሰጣቸው የጸሎታቸው መልስ፣ በምላሹ ዳንኤል እና ጓደኞቹ ወደ
የምስጋና ጸሎት እና ምስጋና ዘለው ገቡ። እግዚአብሔርን የትንቢት ምንጭ ስለሆነ፣
እና ተፈጥሮን እና የፖለቲካውን ታሪክ በቁጥጥሩ ስላደረገ አመሰገኑት። በዚህ ስፍራ
ልንማረው የምንችል በጣም አስፈላጊ ትምህርት አለ። ስለ ብዙ ነገር ወደ እግዚአብሔር
ስንጸልይ እና ስንለምን ምን ያህል ጊዜ ነው ስለ ጸሎት መልሳችን የምናመሰግነው እና
የምናወድሰው? የኢየሱስ ከአስሩ ለምጻሞች ጋር የነበረው ልምምድ ሰዎች ምን ያህል
የማናመሰግን እንደሆነ ያሳያል። ከተፈወሱት አስሩ ውስጥ አንድ ብቻ ነበር ‹‹ ክብርን
ለእግዚአብሔር ለመስጠት›› የተመለሰው (ሉቃስ 17፡-17-18)። የዳንኤል ምላሽ
የሚያስተምረን ስለ ምስጋና እና ውዳሴን ስለመስጠት ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን
የሚገልጸው የምንጸልይለትን እግዚአብሔርን ባህሪም ነው ።
ለእርሱ ስንጸልይ ለእኛ
የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያደርግ ልንተማመንበት እንችላለን ፣ እና እንዲሁም
ሁልጊዜ እርሱን ልናወድሰው እና ልናመሰግነው ይገባል።
መዝሙር 138ን ያንብቡ። ከዚህ የምስጋና ጸሎት ውስጥ፣ በምንም
አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም እግዚአብሔርን አመስጋኝ ለመሆን ሊረዳ
የሚችልን ምን ትምህርት ሊወስዱ ይችላሉ?
ዳንኤል 2፡- 24-30 ዳንኤል በዚህ ስፍራ ያለው፣ ሁልጊዜ እናስታውሰው ዘንድ አስፈላጊ የሆነ ነገር ምንድን ነው? (ዮሐ 15፡5ንም ይመልከቱ)
ለጸሎታቸው ምላሽ፣ እግዚአብሔር ህልሙን እና ትርጓሜውን ገለጸላቸው። እናም
ዳንኤል መፍትሔው ከሰማይ አምላክ እንደመጣ ለንጉሱ ለመናገር አላቅማማም።
እንዲሁ ለንጉሱ ህልሙን እና ፍችውን ከመናገሩ አስቀድሞ ዳንኤል በአልጋው
ላይ ሳለ የነበረበትን ጭንቀት እና ሐሳብም ጭምር ጠቀሰ። ይህ ትልቅ የሆነ መረጃ
የመልዕክቱን ተቀባይነት በተጨማሪ ክፍ አደረገው፣ ምክንያቱም ለንጉሱ ብቻ
የሚታወቅ እንዲህ አይነት መረጃ ወደ ዳንኤል ሊመጣ የሚችለው በአማልክት ኃይል
ብቻ ነው። ነገር ግን ዳንኤል የህልሙን ትርጓሜ መናገሩን ሲቀጥል ሌላ አስጊ ነገርን
የሚያመጣ ነበር ምክንያቱም ህልሙ ለናቡከደነጾር መልካም ዜና ብቻን የያዘ ላይሆን
ይችላል።
ዳንኤል 2፡-31-49 ያንብቡ። ሕልሙ ስል ንጉስ ናቡከደነጾር መንግስት
ዕጣ ምን ነበር የሚለው?
ህልሙ ከእራሱ ጋር ባለ ግርማ ምስልን የያዘ ነበር ‹‹ የዚህም ምስል ራስ ጥሩ ወርቅ፥
ደረቱና ክንዶቹም ብር፥ ሆዱና ወገቡም ናስ፥ ጭኖቹም ብረት፥ እግሮቹም እኩሉ
ብረት እኩሉም ሸክላ ነበረ።›› (ዳንኤል 2፡-32፣ 33)። በመጨረሻም ‹‹ እጅ ሳይነካው
ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና
ሲፈጭ አየህ። ››(ዳንኤል 2፡-34 ) ። እናም ሁሉም ምስል ተፈጨ እና እንደ እብቅ ሆነ
ነፋስም ወሰደው። ዳንኤል የተለያዩት ብረቶች በታሪክ ውስጥ አንዳቸው አንዳቸውን
እየተኩ የሚሔዱ ተከታታይ መንግስታትን እንደሚወክሉ ገለጸ።
ለናቡከደነጾር
መልዕክቱ ግልጽ ነው። ባቢሎን እስከነ ሙሉ ሐይሏ እና ክብሯ ታልፍ እና በሌላ
መንግስት ትተካለች ፣ ከዚያም በተፈጥሮዋ ፍጹም ሌላ በሆነችው እና ለዘለአለም
በምትሆነው የእግዚአብሔር ዘለአለማዊ መንግስት ሁሉም ይተካሉ።
ተመልከቱ የሰው ነገር ምን ያህል ጊዚያዊ እንደሆነ። ይህ እውነት
በኢየሱስ እና በኢየሱስ ብቻ ስላለን ታላቅ ተስፋ ምን ያስተምረናል?
(ዮሐንስ 6፡54፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡18)
ህልሙን እና ትርጓሜውን እንደገና ያንብቡ ( ዳንኤል 2፡31-49)። ይህ እግዚአብሔር ስለ አለም መጻኢ ታሪክ ስላለው እውቀት ምን ያስተምረናል?
በናቡከደነጾር ህልም የቀረበው ትንቢት ጠቅለል ያለ ትንቢታዊ ርዕሰ ጉዳይን እና
እንደ መለኪያ የሚያገለግል በ ምዕራፍ 7፣ 8፣ እና 11 ላይ በዝርዝር ወደ ቀረበው
ትንቢት መዳረሻ ነው። እንዲሁ ዳንኤል 2 በሁኔታዎች የሚወሰን ትንቢት አይደለም።
አፖካሊፕቲክ ትንቢት ነው፣ እርግጠኛ የሆነ ትንቢት እግዚአብሔር አስቀድሞ ያየው
እና ወደፊት መጥቶ የሚያልፍ ነው።
1.የወርቅ ራሱ የሚወክለው ባቢሎንን (626- 539 ቅ.ዓ) ነው። በእርግጥ
ከወርቅ ሌላ የባቢሎናውያንን መንግስት ኃይል እና ሐብት በተሻለ ሊወክል
የሚችል ብረት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ወርቃማዋ ከተማ›› (ኢሳያስ 14፡4) እና
‹‹ በእግዚአብሔር እጅ ወርቃማዋ ጽዋ ›› (ኤርሚያስ 51፡-7ን ከ ራዕይ 18፡- 16 ጋር
ያነጻጽሩ) ይላታል። የጥንቱ የታሪክ ምሁር ሔረዱተስ እንደዘገበው በብዙ ወርቅ
የተለበጠች ከተማ ነበረች።
2.የብሩ ደረት እና እጆቹ የቆሙት የሜዶ ፋርስን መንግስትን (539-331 ቅ.ዓ)
በመወከል ነው። ብር ከወርቅ ይልቅ በዋጋው እንደማነሱ የሜዶ ፋርስ መንግስት
የባቢሎናውያንን የውበት ደረጃ በፍጹም አይስተካከልም። በተጨማሪም ብር ገጣሚ
የፋርሶች መለያ ምልክት ነበር ምክንያቱም በግብር ስርዓታቸው ይጠቀሙት ነበር።
3.ሆዱ እና ጭኖቹ ንሃስ ሲሆኑ የሚወክሉት ደግሞ የግሪክን መንግስት ( 331168ቅ.ዓ) ነበር። ሕዝቅኤል 27፡-13 ግሪኮችን እንደ የነሃስ የመነገጃ እቃ ይመስላቸዋል።
የግሪክ ወታደሮች በነሃስ የጦር መሳሪያቸው ይታወቃሉ። የእራስ ቆባቸው፣ ጋሻቸው
እና የውጊያ መጥረቢያቸው በውስጡ ነሃስ አለው። ሔሮዶቱስ እንደሚነግረን
የግብጹ ሳማቲቹስ አንደኛ፣ የግሪክ ባህረኞች በወረሩ ጊዜ ‹‹ ከውቂያኖስ የመጡ
የነሃስ ሰዎች ›› በማለት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜ ተመልክቷል ።
4.የብረት እግሮች በትክክል ሮምን ይወክላሉ ( 168ቅ.ም - 476ዓ.ም)። እንደ
ዳንኤል ገለጻ ብረት የማድቅቅ እና ከቀደሙት ከሌሎቹ ይልቅ ብዙ ጊዜ የቆየውን
የሮምን ባህሪ ይወክላል ። ይህን መንግስት የሚወክለው ትክክለኛ ነገር ብረት ነበር።
5.እግሮቹ የተወሰኑት ብረት የተወሰኑት ደግሞ ሸክላ የሚወክሉት
የተከፋፈለውን አውሮፓን (476 ዓ.ም እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጻት) ነው። የብረት
እና የሸክላ ድብልቁ የሮም መንግስት ከተፈረካከሰ በኋላ የሆነውን/የተፈጠረውን
ምስል በደንብ የሚወክል እና የሚገልጽ ነው። አውሮፓን አንድ ለማድረግ ብዙ
ጥረቶች ቢደረጉም በነገስታት ቤቶች መካከል የጋብቻ አንድነት ከመፍጠር አሁን
እስካለው የአውሮፓ ሕብረት ድረስ ቢኬድም መከፋፈሉ እና አንድ አለመሆኑ
አሁንም ይታያል፣ እንደ ትንቢቱ ይህ እግዚአብሔር ዘለአለማዊውን መንግስቱን
እስኪመሰርት ድረስ ይቀጥላል።
ዳንኤል 2፡-34፣35፣44 እና 45ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ አለማችን የመጨረሻ ዕጣ ምን ያስተምሩናል?
የህልሙ ትኩረት ‹‹በመጭዎቹ ጊዜ ››(ዳንኤል 2፡-28) ወደፊት በሚሆነው ላይ ነው።
ሐያል እና ሃብታም እንደነበሩት (የብረቱ እና ሸክላው) መንግስታት ምንም ማለት
አይደሉም ነገር ግን ለድንጋዩ መንግስት መቋቋም ግን እንደ መቅድም ነበሩ። በተወሰነ
መልኩ ብረት እና ሸክላ የሰብአዊ ዘር ፋብሪካዎች ውጤት ቢሆኑም ፣ በህልሙ
ውስጥ ያለው ድንጋዩ ግን በሰው እጅ ሳይነካ የመጣ ነበር።
በቀላል አባባል ምንም
እንኳን እያንዳንዱ የቀደሙት ነገስታት ወደ ፍጻሜ ቢመጡም በዲንጋይ የተመሰለው
መንግስት ግን ለዘለአለም ጸንቶ ይኖራል። የአለቱ ምሳሌ እግዚአብሔርን ይመስላል(
ለምሳሌ ዘዳግም 32፡-4፣ 1ኛ ሳሙኤል 2፡-2፣ መዝሙር 18፡-31)፣ እንዲሁ ድንጋዩ
በተመሳሳይ መሲህንም ይወክላል (መዝሙር 118፡- 22፣ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡-4፣7)።
ስለዚህ ከዲንጋይ ምሳሌ በቀር የሚመሰረተውን የእግዚአብሔርን ዘለአለማዊ
መንግስት ለመሳል የሚችል ሌላ ምንም ነገር አይገጥምም።
አንዳንዶች የድንጋዩ መንግስት በኢየሱስ የምድራዊ አገልግሎት ጊዜ ተመስርቷል
በማለት ይሞግታሉ፣ እንዲሁም የወንጌል መሰራጨት ልክ መላውን አለም
የእግዚአብሔር መንግስት ለመውሰዱ እንደ ማመላከቻ ይወስዳሉ። ሆኖም ግን
የድንጋዩ መንግስት የሚከሰተው አራቱ መንግስታት ካለፉ በኋላ እና የሰብአዊ ዘር
ታሪክ ወደ ተከፋፋሉት መንግስታት፣ በምስሉ እንደተገለፀው የእግሮቹ እና የእግር
ጣቶቹ በተወከሉት፣ ዘመን ሲደርስ ብቻ ነው ። ይህ ሐቅ ፍጻሜውን ያገኘው
በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ነው ምክንያቱም የኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት
የተካሔደው በአራተኛው ክፍለ ዘመን በሮማውያን መንግስት ጊዜ ነው።
ነገር ግን ድንጋዩ ወደ ተራራው መንገድን ይሰጣል። ያም ማለት ‹‹ምስሉንም የመታ
ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ ›› (ዳንኤል 2፡-35) የሚለው ነው።
ተራራ በብሉይ ኪዳን ጊዜ ልክ ቤተ መቅደሱ ያረፈበት ቦታ እንደ የጺዮን ተራራ ፣
የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ወክሎ መኖሩን ያሳይ እንደነበረው ቤተ
መቅደስ ማለት ነው። በሚገርም ሁኔታ ከተራራ ላይ ተፈንቅሎ የመጣው ድንጋይ
እራሱም ተራራ ሆነ። ይህ ተራራ በጥቅሱ መሰረት ያለ ተራራ ነው፣ ምን አልባት
የሰማዩን ጺዮንን፣ ሰማያዊዋን ቤተ መቅደስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጣ የሚመሰርተውን
ዘላለማዊውን መንግስቱን ያመላክት ይሆናል። ከሰማይ በምትወርደው ኢየሰሩሳሌም
ውስጥ (ራዕይ 21፡-1-22፡-5) ፣ መንግስቱ የመጨረሻ ፍጻሜዋን ታገኛለች።
ዳንኤል 2 እስካሁን ድረስ በሁሉም መንግስታት ትክክል ነበረ።
ለምን ነው ታዲያ ስለ የመጨረሻዋ መንግስት፣ ዘለአለማዊዋ ስለሆነው
የእግዚአብሔርን መንግስት የሚናገውን ትንቢት ለመቀበል ሎጅካል
እና ጥበብ የሚሆነው? ለምንድን ነው ታዲያ በዚህ ትንቢት አለማመን
መሰረተ ቢስ የሚሆነው?
የዳንኤል 2 ምስል ከወርቅ እና ከብር መሰራቱ በምጣኔ
ሐብት ደረጃ ተመሳሳይ ኃይል እንዳላቸው ለመገንዘብ የሚመራ ነው። ምስሉ
እንዲሁ ከነሃስ እና ከብረት ፣ ለተለያዩ የመገልገያ መሳሪያዎች እና የጦር መሳሪያዎች
አግልግሎት የሚውል፣ እና ሸክላ ሰሪዎች በጥንቱ አለም በቀጥታ እና ለአገር ውስጥ
ፍጆታ የሚያገለግሉ ናቸው። ስለዚህም ምስሉ ስለ ሰብአዊ ዘር እና ክፉ ስራው
ምስልን የሚሰጥ ነው። በጣም በሚገጥም ሁኔታ የምስሉ የተለያዩ አካላቶቹ የአለም
መንግስታትን ስኬት እና የመጨረሻዎቹን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የሚከሰተውን
አንድ አለመሆን የሚያሳይ ነው። ድንጋዩ በግልጽ ‹‹በሰው ልጆች እጅ›› (ዳንኤል
2፡45) ያልተሰራ፣ ሰማያዊ ኃይል እንደሚፈጽመው፣ በዚህች ጊዜያዊ አለም
እንደሚመጣ እና የሰውን ስራና ተግባር ሁሉ ወደ ፍጻሜ እንደሚያመጣ ጠንካራ
ማስታወሻ ነው።
ምንም እንኳን ‹‹እቅም ለሌለው የሰው አይን፣ የሰው ልጅ ታሪክ ልክ እንደ በሃያላት
እና ተጻራሪ ሐያላት መካከል እንዳለ የምስቅልቅል ነገሮች ውህደት መስሎ ቢታይም
… ዳንኤል እንዳረጋገጠልን ከዚህ ሁሉ ጀርባ እግዚአብሔር አለ። በነገሩ ላይ ወደ
ታች ይመለከታል በውስጡም ሆኖ የበለጠውን /መልካሙን ያያል ›› ( ውሊያም
ኤች ሼ፣ ዳንኤል፡ ኤ ሪደርስ ጋይድ( ናምፓ፣ አይዲ ፓፊክ ፕሬስ፣ 2005) ገጽ 98) ።
1.የዚህ አለም ስቃይ እና መከራ ሁሉ በአንድ ላይ ባለበት፣ እግዚአብሔር
በመጨረሻ ሁሉም በቁጥጥሩ ስር እንደሆነ እና ሁሉን ደግሞ ለክብር
እንደሚያደርገው ማወቁ ምን ያህል መልካም ነው? እስከዚያ ግን
መልካምን ነገር ለማደረግ በመፈለግ ፣ በዚህ በወደቀው አለም ውስጥ
ያለውን ስቃይ መፍትሔ ለማምጣት በመርዳት የእኛ ሚና ምንድን
ነው?
2.ዳንኤል እና ማራኪዎቹ ያን ያህል ተቀራርበው መስራታቸውን እና
ለጣዖት አምላኪዎች መሪ፣ በዳንኤል ሕዝብ ላይ ያን ያህል ውድመት
ካመጣ ሰው ጋር ፣ ታማኝ ሆኖ መስራትን፣ እንዴት ነው የምንገልጸው?
3.እንደተመለከትነው፣ አንዳንዶች እጅ ሳይነካት ተፈንቅላ የመጣችውን
ድንጋይ ለአለም የተሰራጨው ወንጌል ነው በማለት እየጠቀሱ
ይሞግታሉ። ዳንኤል 2፡-35 ያለውን ጭምር፣ ድንጋዩዋ የቀደሙትን
ነገስታት መታቻቸው እናም ‹‹ ነፋሱም ወሰደው ቦታውም አልታወቀም
›› እንደተባለ ያ ምን አልባት በተወሰኑ ምክንያቶች እውነት
ሊሆን አይችልም። ያ ደግሞ ከክርስቶስ መስቀል በኋላ አልሆነም።
በተጨማሪም ሌሎች ደግሞ ለማለት እንደሚሞክሩት የድንጋዩ መንግስት
ከቤተክርስቲያን መውደቅ ጋር የድንጋዩ መንግስት ሌሎች አይነት
የሰዎች ህብረቶችን ሁሉ ይተካል ይላሉ። ሁሉንም የአለም ክፍል
የሚያቅፍ የመንግስት አይነት ነው። ስለዚህ የኢየሱስ ዳግም ምጻት
ብቻ ነው በዚህ ትንቢታዊ ህልም ውስጥ ጡዘቱን እላይ የሚያደርሰው።
ለምንድን ነው ታዲያ በፍጻሜ ቀናት ድንጋዩ የሚያደርገው፣ የኢየሱስ
ዳግም ምጻት ፣ ብቸኛው የትርጓሜው ጠቃሚ ነገር የሚሆነው?