ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- 2ኛ ነገስት 21፡-10-16፣ ዳንኤል 1፣ ገላትያ 2፡-19፣ 20፣ ማቴዎስ 16፡- 24-26፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡-17፣ ያዕቆብ 1፡-5
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “ለእነዚህም ለአራቱ ብላቴኖች እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ።”(ዳንኤል 1፡-17)
መ
ጽሐፍ ቅዱስ የሰብአዊን ዘር ውድቀት ለማሳየት ምንም የሚደብቀው ነገር
የለም። ከዘፍጥረት 3 ጀምሮ የሰብአዊ ዘር ሐጢያት እና ውጤቱ ጎላ ብሎ
ተገልጿል። በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሁ ለእግዚአብሔር ታላቅ እምነትን ያሳዩ፣ ምንም
እንኳን ተጽዕኖ ሊየያደርጉ የሚችሉ እና የሚገፋፉ ነገሮችም እንኳን ቢኖሩ፣ ታማኞች
የነበሩ ሰዎች ጉዳዮችንም እናያለን። እናም እንደዚህ ያሉ አሳዛኝ ታሪኮች በዳንኤል
መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ።
ሆኖም ግን የዳንኤልን መጽሐፍ ስናጠና በአእምሮአችን ሁልጊዜ ልንዘነጋው
የማይገባው የመጽሐፉ ጀግና/ ጎልቶ ሊታይ የሚገባው እግዚአብሔር መሆኑን ነው።
የዳንኤልን እና የጓደኞቹን የታማኝነት ታሪክን ስንመለከት/ስናጠና በተለምዶ እነዚህን
አራት ወጣቶች ሐይለኛ እና ሳቢ የሆነውን የባቢሎንን መንግስት በተጋፈጡ ጊዜ
ሲመራቸው እና ጸንተው እንዲቆሙ ያደረጋቸውን ማክበርን እንረሳለን። እንኳን
በባዕድ ምድር ፣ ባህል እና ሐይማኖት ተጽዕኖ ስር ሆኖ በእራስ ሀገር በሚገጥሙ
ተግዳሮቶች ታማኝ መሆን እራሱ ከባድ ነው ።
ነገር ግን ሰውነታቸው ይህን ተግዳሮት
ተጋፈጠው ምክንያቱም ልክ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዳለው ‹‹ያመንሁትን(እነሱም
ያመኑትን ) አውቃለሁና ›› (2ኛ ጢሞ 1፡12)፣ እነርሱም በእርሱ ታምነዋል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለጥር 2 ቀን ይዘጋጁ።
የመጀመሪያው የዳንኤል መጽሐፍ ምልከታ የሚጀምረው በሚያስተክዝ የሽንፈት
ማሳሰቢያ ነው። ይሁዳ በናቡከደነጾር ስር ወደቀ እናም የቤተመቅደሱ መጠጫዎችም
በምርኮ ከእየሩሳሌም ወደ ሰናዖር ምድር ተወሰዱ። ሰናዖር የሚለው ቃል በመጽሐፍ
ቅዱስ የተገለጸው በ ዘፍጥረት 11፡- 2 ላይ የባቢሎን ግንብ የተገነባበት ቦታ እንደሆነ
ነው። ሰናዖር የሚለው ቃል እንደ መጥፎ ገድ ምልክት ነው፣ የሚያነሳውም
ከእግዚአብሔር ጋር ግልጽ ግድድሮሽ የተደረገበት ፕሮጀክት የተመሰረተበትን ነው
ምንም እንኳን የባቢሎንን ግንብ ገንቢዎች ወደ ሰማይ መድረስ ባይችሉም ከዚህ ላይ
ሲታይ ግን ናቡከደነጾር እና በሰናዖር ያሉት አማልክቶቹ በቃል ኪዳኑ የእስራኤል
አምላክ ላይ የበላይነትን ያሳዩበት ነበር።
ነገር ግን የዳንኤል መጽሐፍ መክፈቻ ቃላቶች በግልጽ እንደሚያስቀምጡት
የእየሩሳሌም መሸነፍን ጀግንነት ሐያል ለሆነው የባቢሎን ንጉስ አልሰጡም፣
ይልቅ ይህ የሆነው በእግዚአብሔር ነው ‹‹ጌታም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን
ከእግዚአብሔርም ቤት ዕቃ ከፍሎ በእጁ አሳልፎ ሰጠው›› (ዳንኤል 1፡2)። እጅግ
ቀድሞ እግዚአብሔር ሕዝቡ እርሱን ቢረሱ እና ቃል ኪዳናኑን ቢያፈርሱ ለባዕድ
ሐገር አሳልፎ እንደሚሰጣቸው አስታውቋል።
ስለዚህም ዳንኤል ከባቢሎናውያን
ጦር ጀርባ እና ኋላ የሰማይ አምላክ የታሪክን አካሔድ እየመራ መሆኑን አውቋል።
ይህ በግልጽ የሚታይ የእግዚአብሔር ሉአላዊነት ነበር እነዚህን ወጣቶች በባቢሎን
መንግስት ፈተናና ግፊት አጽንቶ ያቆማቸው፣ ጥንካሬን እና ድፍረትን የሰጣቸው።
2ኛ ነገስት 21፡-10-16፣ 2ኛ ነገስት 24፡-18-20፣ እና ኤርሚያስ 3፡
-13 ያንብቡ? ለምንድን ነው እግዚአብሔር ይሁዳን እና እየሩሳሌምን
በባቢሎን እጅ አሳልፎ የሰጣቸው?
የ21ኛው ክፍለ ዘመንን ተግዳሮቶች ስንጋፈጥ፣ በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ በግልጽ
የተንጸባረቀውን የእግዚአብሔርን ሐሳብ እንደገና ልንመለከት ይገባል። እንደዚህ
መጽሐፍ የምናመልከው አምላክ በሐይሉ የሚቆጣጠረው የታሪክን ኡደት
ብቻ ሳይሆን እንዲሁ የራሱ በሆነ ሕዝቡ ሕይወትም ውስጥ በምህረቱ ጣልቃ
በመግባት በሚያስፈልጋቸው ጊዜ እርዳታውን ይሰጣቸዋል።
እንዲሁ ወደ ኋላ
እንደምንመለከተው ለዕብራውያኑ ግዞተኞች ያደረገው በመጨረሻው ዘመንም
ለራሱ ሕዝብ፣ በራሳቸው እና በእምነታቸው ላይ ከሚደርስባቸው ጥቃት ሁሉ
በላይ፣ ያደረገዋል።
ከውጭ፣ ከቤተክርስቲያን ውስጥ ፣ ወይም ከራሳችሁ የባህሪ ጉድለት ጋር
በተያያዘ አሁን በእምነታችሁ ምን አይነት ተግዳሮቶችን ተጋፍጣችኋል?
ከፊታችሁ ያለ ምንም አይነት ነገር ቢሆን ሊረዳችሁ በሚችለው
በእግዚአብሔር ኃይል ስር መታመንን ከዚህ እንዴት መማር ትችላላችሁ?
ዳንኤል ምዕራፍ 1ን ያንብቡ። በእነዚያ ወጣቶች ላይ ይጋፈጡት ዘንድ ምን አይነት ጫና ነበር የተጣለባቸው?
ባቢሎን በደረሱ ጊዜ እነዚያ አራት ወጣቶች በእምነታቸው በጣም ጠንከር
ያለ ተግዳሮት ገጠማቸው። ንጉሱን ያገለግሉ ዘንድ ልዩ በሆነ ስልጠና ውስጥ
እንዲያልፉ ተመለመሉ። የጥንት ነገስታት ከምርኮኞቻቸው መካካል ምርጥ የሆኑት
በቤተመንግስታቸው ያገለግሉ ዘንድ ይመለምሉ ነበር፣ እናም በዚያ ታማኝነታቸውን
ለንጉሱ እና በምርኮ ለያዛቸው መንግስት እንዲያደርጉ ይደረጋል። በእርግጥም ሁሉም
ሒደት ለውጥ የሚያመጣ ተጽዕኖ እንዲያደርግ እና የንጽረተ-ዓለም ለውጥ ውጤትን
እንዲያመጣ የሚታሰብ ነው። ከዚሁ ሂደት ጋር ተያይዞ እነዚያ የዕብራውያን ምርኮኞች
ስማቸው ተቀየረ።
አዲሱ ስም የሚያመላክተው የባለቤትነትን እና የመዳረሻን ለውጥ
ነው። እናም ስማቸውን በመቀየር ባቢሎናውያን በእነርሱ ላይ ባለስልጣንነታቸውን
ለማረጋገጥ እና የባቢሎናውያንን እሴቶች እና ባህልን እንዲያሰርጹ ለማስገደድ ነበር።
ወደ የእስራኤል አምላክ የሚያመላተው የቀደመው ስማቸው ተቀይሮ በባዕድ ሐገር
ያለውን አምላክ ወደ ሚያከብር ስም ተቀየረ።
በተጨማሪ ንጉሱ እነዚህ ወጣቶች
ከእርሱ ማዕድ ይመገቡ ዘንድም ወሰነ። በጥንት ጊዜ የንጉሱን ምግብ መመገብ ጠለቅ
ያለ ትርጉም ነበረው። ከንጉሱ ጋር የማይነጣጠል የሕብረት እና በእርሱ የመታመን
ትርጓሜ አለው። በተለምዶ ምግቡ ለመንግስቱ አምላክ ወይም አማልዕክት ስለሚሰጥ
ከዚያ መመገብ የጠለቀ ሐይማኖታዊ ትርጓሜም አለው። በግልጽ የሚያመላክተውም
በንጉሱ የአምልኮ ስርዓት ውስጥ የመሳተፍ እና የመቀበል ትርጓሜን ነው።
ስለዚህ ዳንኤል እና ወዳጆቹ ፈታኝ በሆነ ተግዳሮት ውስጥ እራሳቸውን አገኙ።
ለእነርሱ ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን እና ሊሰባብር በሚችል የንጉስ ስርዓት
ውስጥ መኖር፣ ከተአምራት የሚተናናስ ጉዳይ አልነበርም። ከዚህ ሌላ የተወሳሰበው
ነገር የባቢሎን ከተማ እራሷ የሰብዓዊ ዘር የደረሰበትን ደረጃ ለመግለጽ የተቀመጠች
ከተማ ናት። የስነ-ሕንጻ ውበቷ እና ቤተ-መቅደሷ፣ ተንጠልጣዩ የአትክልት ስፍራዋ
እና በከተማዋ መሃከል አቋርጦ የሚያልፈው የኤፍራጠስ ወንዝ ከዚህ የተሻለ ምስል/
ውበት እና ክብር የትም እንደሌለ የሚያሳይ ነበር። ስለዚህ ዳንኤል እና ጓደኞቹ
እድገት፣ የዚህን ስርዓት ጥቅም እና ብልጽግናን የመካፈል እድል ነበር የተሰጣቸው።
የዕብራውያን ምርኮኛ መሆናቸውን ማቆም እና ንጉሳዊ ሰራተኞች መሆን ይችላሉ።
መርሖቻቸውን ለድርድር በማቅረብ ወደ ክብር የሚወስደውን ቀላሉን መንገድ
ይወስዱ ይሆን?
እነዚህ ወጣቶች እምነታቸውን ለድርድር ማቅረብ የሚያስችል ምክንያትን
በምን አይነት መንገድ ሊያቀርቡ ይችሉ ነበር? አሁን ላይ በምን አይነት
ተመሳሳይ፣ አሳች ተግዳሮት መንገድ እርስዎ እየተጋፈጡ ይሆን?
ዳንኤል 1፡-7-20ን ያንብቡ። በዚህ ላይ እየሰሩ ያሉ ምን አይነት ሁለት ነገሮችን እናያለን፣ የእነ ዳንኤል ፈቃድ እና የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት? ምን አይነት አስፈላጊ መርህ በዚህ አለ?
እዚህ ላይ እንዳለው አራቱ ዕብራውያን ምርኮኞች የባቢሎናውያን ስማቸውን
አልተቃወሙም። ምን አልባት እርስ በእርሳቸው የዕብራውያን ስማቸውን ከመጠቀም
በቀር ምንም ሊያደርጉት አይችሉም። ነገር ግን ከንጉሱ ማዕድ ያለውን ምግቡን እና
ወይኑን በተመለከተ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል በእራሳቸው ቁጥጥር ስር ነው ።
ስለዚህ በዚህ ላይ ነጻ የሆነው የእነዚህ አራት ሰዎች ፈቃድ ወሳኝ ነው።
አንድ ሰራተኛ ስማቸውን ቢቀይር ፣ ምን አልባት የምግቡንም ዝርዝርም ሊቀይር
ይችላል። ከንጉሱ ማዕድ ላይ የማይመገቡበት ምን አልባት ሁለት ምክንያቶች ሊኖሩ
ይችላሉ።
አንደኛ፣ ከንጉሱ ማዕድ ላይ ያሉት ምግቦች ምን አልባት ያልነጹ (እርኩስ) ስጋዎችን
ይዘው ይሆናል (ዘለዋውያን 11)።
ሁለተኛ፣ ምግቡ መጀመሪያ ለጣኦቱ ይላክ እና ከዚያ በኋላ ንጉሱ እንዲመገበው
ይመጣል። ስለዚህ ዳንኤል ግልጽ ሲያደርገው በድፍረት ያለምንም ማታለል ጥያቄው
የእምነት መነሾ እንዳለው ነበር፣ ያም ማለት ከቤተመንግስት ያለው ምግብ እርሱን
እና ጓደኞቹን እንሚያረክሳቸው ነበር( ዳንኤል 1፡8) ።
የዳንኤልን እና የባቢሎናውያንን ጃንደረቦች አለቃ ንግግር ስንመለከት የተወሰኑ
ጥቂት ነጥቦች ይወጣሉ። አንደኛ፣ ዳንኤል፣ የጃንደረቦች አለቃ ያለበትን አጣብቂኝ
በደንብ ተገንዝቧል ስለዚህም የሙከራ ሐሳብን አቀረበ። ተለዋጩ ምግብ ምን
ያህል የሚፈለገውን ውጤት እንደሚያመጣ እና የጃንደረቦቹን አለቃ ፍርሃት
እንደሚያስወግድ አስር የመመገቢያ የሙከራ ቀናት መሆናቸው። ሁለተኛ፣
በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቱ አወንታዊ እንደሚሆን የዳንኤል እርግጠኝነት
በእግዚአብሔር ላይ ያለው ፍጹም መታመን መሆኑ። ሶስተኛ፣ የአትክልት እና
ውሃ አመጋገብ እግዚአብሔር በፍጥረት ጊዜ ለሰው ዘር የሰጠው አመጋገብ ጠቋሚ
መሆኑ (ዘፍ 1፡29 ን ይመልከቱ) ፣ በዳንኤልም ምርጫ ምንአልባት ተጽዕኖ ያደረገው
እውነታ ይህ ሊሆን ይችላል። ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር ከጥንት ከመሰረቱ
ከሰጠው የተሻለ ምግብ ሌላ ምን ሊበልጥ ይችላል?
እግዚአብሔር እንደ ፈቀደ እንዲሰራ በርን ስለ ከፈተው የዳንኤል ነጻ
ምርጫ በጣም አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው (ዳንኤል 1፡9ን ይመልከቱ)?
ስለምርጫዎቻችን ምን አይነት አስፈላጊ ትምህርትን ከዚህ ማውጣት/
መውሰድ እንችላለን? በእግዚአብሔር ላይ ያለን መታመን እንዴት አድርጎ
ነው በምርጫችን ላይ ተጽእኖ ማድረግ ያለበት?
ዳንኤል እና የእርሱ ጓደኞች ንጉሱን እንዲያገለግሉ የተመረጡበት ምክንያት
በናቡከደነጾር ለተቀመጠው መስፈርት ገጣሚ ስለሆኑ ነው። እንደ ንጉሱ በቤተመንግስት የሚያገለግሉ ሰዎች ‹‹ እንከን የሌለባቸው ›› እና ‹‹ መልከ መልካሞች ››
(ዳንኤል 1፡4) ናቸው።
በሚገርም ሁኔታ፣ በመስዋዕት እና በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎችም
ምንም አይነት ‹‹ እንከን›› ( ዘለዋውያን 22፡17-25፣ 21፡16-24 ) የለባቸውም።
የባቢሎናውያን ንጉስ ፣ በቤተመንግስቱ ለሚያገለግሉት ያወጣው መስፈርት፣ እራሱን
ከእግዚአብሔር ጋር እያመሳሰለ ይመስላል። በሌላ ጎን ደግሞ እንደዚህ አይነት
መስፈርቶች ሳይታወቅ ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎናውያን መንግስት የገጠማቸው
ተግዳሮት ለእግዚአብሔር ሕያው መስዋዕት አድርጓቸዋል።
ገላቲያ 2፡-19፣ 20 ፣ ማቴዎስ 16፡-24-26፣ እና 2ኛ ቆሮንቶስ
4፡-17 ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ምንም አይነት ፈተናን ብንጋፈጥ
በታማኝነት መቆም እንደምንችል ምንድን ነው የሚነግሩን?
እግዚአብሔር የአራቱን ዕብራውያ ምርኮኞች ታማኝነትን አከበረ። እናም ከአስር
ቀናት የሙከራ ጊዜ በኋላ ከንጉሱ ማዕድ ይመገቡ ከነበሩ ሌሎች ተማሪዎች ይልቅ
መልካም ጤንነት እና የተሻለ መስማማትን አሳዩ። ስለዚህም እግዚአብሔር ለአራቱ
አገልጋዮቹ ‹‹ እውቀትን እና ሁሉንም ጽሑፎችን እና ጥበብን የሚረዱበትን እውቀት
እና ችሎታን ›› ሰጣቸው፣ እናም ለዳንኤል እግዚአብሔር ‹‹ ራዕይን እና ሕልምን
እንዲያስተውል ››( ዳንኤል 1፡17) ጥበብ ሰጠው። ይህ ስጦታ በዳንኤል የትንቢት
አገልግሎት ጉልህ ሚናን ተጫውቷል።
ልክ እግዚአብሔር የአገልጋዩን እምነት በባቢሎናውያን ፈራጆች ፊት እንዳከበረ
ሁሉ የዚህን አለም ተግዳሮት ስንጋፈጥ ለእኛም ይሰጠናል። ከዳንኤል እና
ከጓደኞቹ ልምምድ በእርግጥም በማህበረሰባችን ውስጥ ባሉ ነገሮች ሳይበከሉ
መኖር እንደሚቻል እንማራለን። እንዲሁ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔርን ለማገልገል
ከማህበረሰባችን እና ከባህላዊው ሕይወት መለየት አስፈላጊ እንዳልሆነ ልንማር
እንችላለን። ዳንኤል እና ጓደኞቹ በውሸት፣ ፣ ስህተት እና በአፈ ታሪክ በተገነባ
ባህል ውስጥ መኖር ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በእነዚያ ውሸቶች ፣ ስህተቶች እና አፈ
ታሪኮችም ተምረዋል። ቢሆንም ግን በታማኝነታቸው ጸንተው ቆመዋል።
የትም ብንኖር ከእምነታችን ጋር ተጻራሪ በሆኑ ባህሎች እና ማህበረሰባዊ
ተጽዕኖዎች መካከል ታማኞች ሆነን እንድንቆም ተግዳሮቶችን እንጋፈጣለን።
በባህላችሁ ውስጥ ያሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለዩ፣ እናም እራሳችሁን፣ ‹
እንዴት ነው እኔ እየተቋቋምኳቸው ያለሁት?› ብላችሁ ጠይቁ
ዳንኤል 1፡-17-21ን ያንብቡ። ለአራቱ ሰዎች ስኬት ቁልፉ ምንድን ነው? (ኢዮብ 38፡36፣ ምሳሌ 2፡6፣ ያዕቆብ 1፡5 ንም ይመልከቱ)
ከሶስት አመት ‹‹የባቢሎናውያን ዩኒቨርስቲ›› ስልጠና በኋላ አራቱ ዕብራውያን
ለመጨረሻ ፈተና በንጉሱ ፊት ቀረቡ። ከሌሎች ተማሪዎች ይልቅ ጤነኞች ብቻ
አልነበሩም በእውቀት እና በጥብብም ልቀዋቸው ነበር። አራቱ ወዲያውኑ ንጉሱን
እንዲያገለግሉ ተሸሙ። ይህ ‹‹እውቀት እና ጥበብ›› በብዙ የጣኦት አምልኮ የታጨቀ
እንደሚሆን እንደማያጠራጥን ልንረሳው አይገባም። ቢሆንም ግን እሱንም በደንብ
ተምረዋል ምንም እንኳን ባያምኑበትም።
ናቡከደነጾር ምን አልባት አራቱ ተማሪዎች ያለፉበት ስልጠና ለእንደዚህ አይነት
ውጤት ከቤተ መንግስቱ ማዕድ እና ይሰጥ ከነበረው ጋር የተያያዘ ነው ብሎ አስቦ
ይሆናል። ቢሆንም ግን ዳንኤል እና የእርሱ ጓደኞች፣ የእነሱ የበላይነትን ይዞ መፈጸም
ከባቢሎናውያን ስርዓት ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ እንደሚያውቁ ከአነጋገሩ በግልጽ
አሳይቷል። ሁሉም የመጣው ከእግዚአብሔር ነው። እግዚአብሄር ለሚታመኑት ምን
ሊሰራ እንደሚችል የሚያሳይ ምን አይነት ሐይለኛ ምሳሌ ነው። የእግዚአብሔር
ልጅነታችንን (ማንነታችንን) ሊያጠፋ የሚሞክርን በጣም ሐይለኛ ሚዲያ፣ መንግስት
እና ሌሎች ድርጅቶች ልንፈራ አይገባም። መታመናችንን በእግዚአብሔር ላይ
ካደረግን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚያጸናን እና ከክፉ ሁሉ እንደሚታደገን
እርግጠኖች ልንሆን እንችላለን። በእምነታችን ተግዳሮት ሲመጣ ለእኛ ቁልፉ
ትክክለኛውን ምርጫ ማድረግ ነው።
ዳንኤል ምዕራፍ አንድን ተመልከቱ፣ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን ተምረናል።
(1) እግዚአብሔር ታሪክን ይቆጣጠራል። (2) የባህላችን እና ማህበረሰባችንን አሉታዊ
ገጾች መፈተሽ እንድንችል እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣል። (3) እግዚአብሔር
በውስጣዊ እምነታቸው እና የኑሮ ዘዬአቸው በእርሱ ላይ የሚታመኑትን ያከብራል።
ምዕራፉ ሲያጠቃልል ‹‹ዳንኤልም እስከ ንጉሡ እስከ ቂሮስ መጀመሪያ ዓመት
ተቀመጠ። ››(ዳንኤል 1፡21) በማለት ጠቁሞ ነው። የቂሮስ ስም በዚህ ላይ መጠቀሱ
ፋይዳ አለው። ነጻ የመውጣትን የተስፋ ብልጭታን ይሰጣል። ቂሮስ ሕዝቡን
ይለቅና ወደ እየሩሳሌም ይመለሱ ዘንድ በእግዚአብሔር የተመረጠ ነው።
ምንም
እንኳን ምዕራፉ በሽንፈት እና በነጻ መውጣት ቢጀምርም፣ ሲያጠቃልል ግን በተስፋ
ብልጭታ እና ወደ ቤት በመመለስ ነው። ይህ ነው የእኛ አምላክ። ምንም እንኳን
በጣም አስቸጋሪ የህይወታችን ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም ከስቃይ እና ከህመሙ
በኋላ ያለውን ክብር እና ደስታ እናይ ዘንድ ሁልጊዜ የተስፋን መስኮት ይከፍታል።
‹‹ዳንኤል እና ጓደኞቹ ገና በወጣትነታቸው በባቢሎን ነበሩ፣
ዮሴፍ በልጅነት ሕይወቱ ከነበረበት ጊዜ ይልቅ በግልጽ እነርሱ በጣም በመልካም
እድል ላይ ነበሩ። ሆኖም ግን በጣም ከባድ ላልሆነ የባህሪ ፈተና ግን ተጋልጠው
ነበር። ሲነጻጸር በጣም ቀላል ሊባል ከሚችለው የአይሁዳዊ ቤታቸው ተግዘው
ወደ በጣም የደመቀች እና ትልቅ ከተማ፣ ታላቁ ገዥ ወደሚቀመጥበት ፍርድ
ወንበር፣ እና ለንጉሱ ልዩ አገልግሎት ተለይተው ወደ ተመረጡበት ስፍራ ሔዱ ።
እውነታው የጆሆባ አምላኪዎች በባቢሎን ተማረኩ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ
ውስጥ የነበረው ዋንጫ በባቢሎናውያን የጣኦት ማምለኪያ ስፍራ ተቀመጠ፣
የእስራኤል ንጉስ እራሱ በባቢሎናውያን እጅ ምርኮኛ ሆነ፣ በገነነ መልኩ ድላቸው
ልክ ሐይማኖታቸው እና ባህላቸው ከዕብራውያን እንሚበልጥ ማሳያነት ተጠቀሰ።
በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ እስራኤል ከትእዛዙ
በተነጠለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሐያል እንደሆነ የእርሱ መስፈርቶች ቅዱስ እንደሆኑ
እና የመታዘዝ ውጤት ምን እንደሆነ ማስረጃን ሰጠ። እናም ይህ የሰጠው ምስክርነት፣
እንዳለ ታማኝነታቸውን አሁንም ለያዙ ሊሰጥ ይችላል። ›› (ኤለን. ጂ. ኋይት፣ ስነትምህርት፣ ገጽ 54)
1.በቡድናችሁ ውስጥ በማህበረሰባችሁ ውስጥ እንደ ክርስቲያን
ስለምትጋፈጧቸው የተለያዩ የባህል እና የማህበረሰብ ተግዳሮቶች
ተነጋገሩ። ምንድን ናቸው? እንደ ቤተክርስቲያን ለእነዚህ ምላሽ
መስጠት የምንማረው እንዴት ነው?
2.ለዳንኤል እና ለጓደኞቹ ምን ያህል እምነታቸውን ለድርድር
ማቅረብ ምን ያህል ቀላል ሊሆን እንሚችል አስቡ። ከሁሉም
በላይ ባቢሎናውያን አሸናፊ ነበሩ። የአይሁድ ሕዝብ ተሸንፎ
ነበር። ምን አይነት ‹‹ማረጋገጫ›› ያስፈልግ ነበር የባቢሎናውያን
‹‹አማልዕክት›› ከእስራአላውያን አምላክ የሚበልጡ ስለመሆቸው
እና ከዚህ የተነሳ ዳንኤል እና ጓደኞቹ ይህንን እውነታ እንዲቀበሉ?
በዚህ ጉዳይ፣ በእንደዚህ አይነት ሰዓት ሊያቆማቸው የሚችል
ምን አይነት ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ሊይዙ ይችላሉ?
(ኤርሚያስ 5፡19፣ ኤርሚያስ 7፡22-34 ይመልከቱ)። ይህ ምን
ያህል መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማወቅ እና ‹‹ወቅታዊውን እውነት››
ማስተዋልን አስፈላጊ እንደሆነ ይነግረናል?
3.ለእምነት መቆም ምን ያህል አስፈላጊ ነው ፣ ለራሳችን ሳይሆን
ነገር ግን ታማኝነታችን የጌታን ባህሪ ሊመሰክርላቸው የሚችሉ
ለሌሎች፣ ልናገለግላቸው ለተገቡ ማለት ነው?