ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳንኤል 12፣ ሮሜ 8፡ -34፣ ሉቃስ 10፡-20፣ ሮሜ 8፡-18፣ ዕብራውያን 2፡-14፣15፣ ዮሐንስ 14፡-29፣ ራዕይ 11፡-3
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። “ ( ዳንኤል 12፡-3)
የ
ዳንኤል መጽሐፍ የሚጀምረው ናቡከደነጾር ይሁዳን ሲወራት እና ምርኮኞችን
ሲወስድ ነው። የዳንኤል መጽሐፍ ሲደመደም ግን በታጻራሪው ሚካኤል
የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከመጨረሻው ዘመን ባቢሎን ነጻ ሊያወጣ ሲቆምላቸው
ነው። ያ በዳንኤል መጽሐፍ ሁሉ እንደታየው በመጨረሻ ፣ በፍጻሜ ዘመን
እግዚአብሔር የሚሰራው ሁሉ ስለ እራሱ ሕዝብ ጥቅም ነው።
እንዲሁ እንደተመለከትነው ዳንኤል እና ጓደኞቹ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሲሆኑ
እንዲሁ በምርኮኞች ላይ በነበረው መከራ እና ተግዳሮት ውስጥ በጥበባቸው
ተወዳዳሪ አልነበራቸውም። እንዲሁ የእግዚአብሔር የፍጻሜ ዘመን ሕዝብም መከራን
ሲጋፈጥ በተለይም ‹‹ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ
ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል›› (ዳንኤል 12፡-1) ሲል በዚህም ጊዜ ለእግዚአብሔር
በታማኝነታቸው ይጸናሉ። ልክ በባቢሎን እንደ ዳንኤል እና ጓደኞቹ ጥበብን እና
ማስተዋልን ያሳያሉ።
ጥበብን የሚለማመዱት እንደ የግል ጸጋ ብቻ አይደለም ነገር
ግን በዚያም ምክንያት ሌሎችን ወደ ጽድቅ ለመምራት በታማኝነት ይጠቀሙበታል።
አንዳንዶች ይሞታሉ ወይም ለሞት ተላለፈው ይሰጣሉ እናም ስለዚህ ወደ ምድር
ትቢያነት ይለወጣሉ ነገር ግን ለዘለአለማዊ ሕይወት ይነሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ
እንደሚለው ‹‹በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹ ወደ
ዘላለም ሕይወት፥ ›› (ዳንኤል 12፡-2)
የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለ መጋቢት 19 ሰንበት ይዘጋጁ።
ዳንኤል 12፡-1ን ያንብቡ። በመጨረሻው ዘመን የታሪክን ሒደት የሚቀይረው ማነው? ሮሜ 8፡-34 እና ዕብራውያን 7፡-25፣ ይህ ጥቅስ ምን እያለ እንደሆነ እንድናስተውል እንዴት ነው የሚረዱን?
እስከ አሁን ድረስ እያንዳንዱ የዳንኤል መጽሐፍ ምእራፎች ሲጀምሩ በአረመኔአዊ
ንጉሶች ነበር። ዳንኤል 12 ግን በገዥ ይጀምራል ነገር ግን ከሌሎቹ ምዕራፎች በተለየ
ገዥው መለኮታዊ አለቃ ሲሆን የተነሳውም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከጠላቶቻቸው
ነጻ ሊያወጣ ነው።
በዳንኤል 10 ጥናታችን እንዳገኘነው ብልጭታ ሚካኤል ልክ በጤግሮስ ወንዝ ዳር
እንደተገለጠለት የሰማይ አካል ተመሳሳይ ስልጣን ያለው ነው። በዚያ የመጣው
በሰማይ እንደ የእግዚአብሐር ሕዝብ ወኪል ሆኖ ነው። በዳንኤል ሌላ ቦታ ደግሞ
እንደ የሰው ልጅ (ዳንኤል 7)፣ የሰራዊት አለቃ (ዳንኤል 8፣ እና )፣ እና መሲሁ
አለቃ(ዳንኤል 9) ተገልጿል። ስለዚህ ሚካኤል ማለት ‹‹ እግዚአብሔርን የሚመስል
ማን ነው?›› ፣ ከኢየሱስ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም።
ሚካኤል ጣልቃ የገባበትን ጊዜ ማስተዋል አስፈላጊ ነው። እንደ ዳንኤል 12፡-1 ይህ
የሆነው ‹‹በዚያም ዘመን›› (ዳንኤል 12፡-1) ላይ ነው። ይህ አባባል የሚጠቁመው
ልክ በዳንኤል 11፡-40-45 በተጠቀሰው ማለትን ነው። ይህ ጊዜ የጳጳሳዊው ስርአት
ከወደቀበት ከ 1798 እስክ የፍጻሜ ዘመን ትንሳኤ ድረስ ነው (ዳንኤል 12፡-2)።
ስለ ሚካኤል ስራ ሁለት አስፈላጊ አሰራሮችን፣ በዳንኤል 12፡-1 ላይ ከተጠቀሰው
‹‹ይነሳል ›› ከሚለው ቃል መመልከት ይቻላል።
አንደኛ፣ ‹‹ይነሳል›› ከሚለው ቃል የንጉሶችን ለድል እና ለመግዛት መነሳትን
ያሳያል። ቃሉ እንዲሁ የወታደራዊ ስሜትን ያሳስባል። ይህም ሚካኤል ልክ ሕዝቡን
እንደሚጠብቅ እንደ ወታደር መሪ እና በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ ወደ መጨረሻው
ደረጃ እንደሚመራቸው ያሳያል።
ሁለተኛ፣ ‹‹ይነሳል›› የሚለው ቃል ወደ የፍርድ ችሎት ያመላክታል። ሚካኤል
‹‹ይነሳል ›› በሰማያዊው ችሎት ፊት እንደ ጠበቃ ይሆናል። እንደ የሰው ልጅ ፣ በፍርድ
ምርመራ (ዳንኤል 7፡-9-14) ጊዜ በዘመናት በሸመገለው ፊት የእግዚአብሔርን ሕዝብ
በመወከል ይቀርባል። ስለዚህ የሚካኤል መነሳት ወይም መቆም የወታደራዊ እና
የፍርድ ስራን ሁኔታዎችን ያሳያል። በሌላ አባባል የእግዚአብሔርን ጠላት ለማሸነፍ
በኃይል እና የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሰማያዊው ችሎት ለመወከል በስልጣን ማለት
ነው።
ዳንኤል 12፡-1 ስለ ‹‹በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ›› ምን ማለት ነው? ያወራል፣ ያ
ሚካኤል ጣልቃ የገባበት ሰዓት፣ ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደዚያ ያለ መከራ
ሆኖ የማያውቅ የመከራ ዘመን ላይ ነው። ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ ከአማጺው
የሰው ዘር በተነሳ ጊዜ ከሚሆነው ሁኔታ ጋር ይመሳሰላል። ለዚያም የመጨረሻዎቹ
ሰባቱ መቅሰፍቶች እንደ የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይና በመጨረሻዋ ባቢሎን
ላይ ይወርዳሉ (ራዕይ 16፣ ራዕይ 18፡-20-24)። እንዲሁም የጨለማው ሐይላት
በምድር ላይ ይለቀቃሉ። ኤለን ጂ. ኋይት ስለዚህ ሰዓት ስትጽፍ ‹‹ ሰይጣን ለአንድ
ትልቅ እና የመጨረሻ ችግር ወደ ምድር ነዋሪዎች ይገባል። የሰብአዊ ዘርን ሐይለኛ
የውስጥ ፍላጎት የእግዚአብሔር መልአኮች ሲለቁ ሁሉም የጥል እና የሁከት ነገሮች
ይለቀቃሉ። በጥንት ጊዜ በእየሩሳሌም ከሆነው በከፋ ችግር አለም ሁሉ በአመጽ እና
በጥፋት ተሳታፊ ይሆናል ›› (ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 614)።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነጻ ይወጣሉ ምክንያቱም
በሰማያዊው ችሎት በሚደረገው የፍርድ ምርመራ በኢየሱስ ፣ በሰማያዊው ሊቀ
ካህን ነጻ ይወጣሉ እናም ስሞቻቸው በመጽሐፉ ይጻፋሉ።
የዚህን መጽሐፍ ትርጉም ለማስተዋል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሁለት
አይነት መጽሐፎች መኖራቸውን ማወቅ ይኖርብናል። አንዱ የጌታ የሆኑትን ሁሉ
ስም ይይዛል አንዳንድ ጊዜ የሕይወት መጽሐፍ ተብሎ ይጠቀሳል (ዘጸአት 32፡-32፣
ሉቃስ 10፡-20፣ መዝሙር 69፡-28፣ ፊሊጵስዮስ 4፡-3. ራዕይ 17፡-8)።
ከሕይወት መጽሐፍ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ተግባር ሁሉ
ስለሚመዘገብበት መጽሐፍ ይጠቅሳል (መዝሙር 56፡-8፣ ሚልክያስ 3፡-16፣ ኢሳያስ
65፡-6) ። እነዚህ መጽሐፎች ናቸው የእያንዳንዱን ሰው ለጌታ ያለውን ታማኝነት
በሰማይ ችሎት ፊት የሚወስኑት። እነዚህ የሰማይ መዝገቦች፣ የሰብአዊ ዘርን ስም
እና ተግባርን የሚይዙ ‹‹የመረጃ ቋት››ናቸው። አንዳንድ ሰዎች የስሞቻቸውን እና
በተለይ የተግባራቸውን በሰማይ የመመዝገብን ሐሳብ ንቀው ይመለከቱታል። ነገር
ግን አንድ ጊዜ ሕይወታችንን ለጌታ ከሰጠን ስማችን በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ
ይጻፋል እንዲሁ መጥፎ ተግባራችን ደግሞ በሰማይ ፍርድ ይሰረዛል። እነዚህ ሰማያዊ
መዝገቦች ለምንኖርበት አለም ሁሉ የኢየሱስ እንደሆንን እና በችግሩ ጊዜ የመጠበቅ
መብት እንዳለን፣ ፍትሃዊ መረጃን ይሰጣሉ።
“በሕይወት መጽሐፍ ለመጻፍ” የእኛ ብቸኛ ተስፋ የክርስቶስ ኢየሱስ
ጽድቅ ለእኛ መቆጠሩ የሚሆነው ለምንድን ነው? መልስዎን በሰንበት ቀን
ወደ የሰንበት ክፍልዎ ይዘው ይምጡ።
ዳንኤል 12፡-2፣3ን ያንብቡ። በዚህ ስለ ምንድን ኩነት ነው እርሱ የሚያወራው፣ ለምንስ ነው ስለ ሞት ያለንን ግንዛቤ በመውሰድ ይህ ኩነት ለእኛ አስፈላጊ የሚሆነው?
ምን አልባት ዳንኤል ስለሚመጣው ትንሳኤ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የበለጠ ግልጽ ማብራሪያ
ሰጥቷል። በዚህ ሐሳብ ላይ አስተያየት ስንሰጥ ፣ የተወሰኑ በጣም አስፈላጊ እውነቶችን
መማር እንችላለን። አንደኛ፣ በዘይቤአዊ አነጋገር እንደ ምሳሌ የተወሰደው ‹‹እንቅልፍ ››
እንደሚገልጸው በሰብአዊ ዘር ውስጥ የማይሞት ነፍስ የለም። ሰብአዊ ዘር አንደ ግለሰብ
ሰውነት፣ አእምሮና መንፈስን የያዘ ነው። በሚሞት ጊዜ ሰው መኖሩን ያቋርጣል እስከ
ትንሳኤም ድረስ ምንም አያውቅም። ሁለተኛ፣ ጥቅሱ እንደሚጠቁመው በመጭው
ትንሳኤ በሐጢያት ምክንያት የሆነውን በተቃራኒው የሚመለስ ነው።
በእርግጥ የ
‹‹ የምድር ትቢያ ›› የሚለው አገላለጽ በመጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ በዳንኤል 12፡
-2 እንደሚነበበው ‹‹የአፈር ምድር ›› ነው። ይህ ብዙ ያልተለመደ የቃላት ቅደም
ተከተል ወደ ዘፍጥርት 3፡19 ይወስደናል፣ ‹‹ ምድር›› የሚለው ቃል ከ ‹‹አፈር››
ቀጥሎ ይመጣል። ይህ የሚያሳያው አዳም በወደቀ ጊዜ የተዋወቀው ሞት ተቃራኒ
/መመለሻ ነው እናም ሞት ከዚያ በኋላ መያዝ አይችልም። ጳውሎስ እንዳለ ‹‹ሞት
ድል በመነሣት ተዋጠ ›› (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡-54)።
ሮሜ 8፡-18ን እና ዕብራውያን 2፡-14ን ያንብቡ። ሞትን ልንፈራ
የማይገባን በምን በምን ምክንያቶች ነው?
ሞት አጥፍቶ ሁሉንም ነገር እዚህ እንዲደርስ አድርጓል። ነገር ግን ሞት የታማኝ
አማኞችን የመጨረሻ ቃል መያዝ እንደማይችል የተስፋ ቃል ተሰጥቶናል። ሞት
የተሸነፈ ጠላት ነው። ክርስቶስ የሞትን ሰንሰለት በበጠሰ ጊዜ ከመቃብር ሙታን
ተነስተው ወጥተዋል፣ ለሞት ወሳኙን ፊሽካ በመንፋት መፍትሔን አመጣ። አሁን
ጊዜአዊ ከሆነው የሞት እውነታ አሻግረን በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ስለምንቀበለው
ሕይወት እንመለከታለን። ምክንያቱም ሚካኤል ‹‹ተነስቶ ቆሟል ›› (ዳንኤል 12፡-1ን
ይመልከቱ) ፣ ከእርሱ ጋር የሆኑም እንዲሁ ይነሳሉ/ይቆማሉ። ከ ‹‹ ትብያዋ ምድር ››
ተነስተው ለዘለዘአለም እንደ ከዋክብት ያበራሉ።
በህመም እና በትግል መካከል ሆነን እንዴት ነው በመጨረሻ ባለው
የትንሳኤ ቃል ስለ ተስፋ እና መጽናናት ልናስብ የምንችለው?
በትክክለኛ ስሜት ሁሉም በሚባል ደረጃ ከዚህ ሌላ ምንም የማይፈይደው
ለምንድን ነው?
ዳንኤል 12፡-4 እና ዮሐንስ 14፡-29ን ያንብቡ። እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የዳንኤል መጽሐፍ ለምንድን ነው የታተመው?
የመጽሐፉ የመጨረሻ ማጠቃለያው ዋና ክፍል (ዳንኤል 10፡-1-12፡-4)፣ ነብዩ ጥቅሉን
እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ እንዲያትመው ትእዛዝን ተቀበለ። እዚያው መልአኩ እንዲህ
ሲል ተነበየ ‹‹ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።››(ዳንኤል 12፡-4)።
ምንም እንኳን አንዳንድ ተማሪዎች ይህን ወስደው ከሳይንስ ዕድገት ጋር ቢያያይዙትም
አውዱ እንደሚያሳየው ግን ይመረምራሉ የሚለው ቃል የሚያመለክተው እራሱን
የዳንኤልን መጽሐፍን ነው። በእርግጥ ታሪክን ወደ ኋላ ስንመለከት ፣ ለዘመናት
የዳንኤል መጽሐፍ ለመረዳት የሚያስቸግር ጽሑፍ ሆኖ ቆይቷል። በተወሰኑ ቦታዎች
ሊታወቅ እና ሊጠና ይችላል ነገር ግን አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ አስተምህሮቶቹ እና
ትንቢቶቹ ሚስጢር እንደሆኑ ቆይተዋል። ለምሳሌ ከቤተ መቅደሱ መንጻት ጋር
የተያያዙ ትንቢታዊ መልዕክቶች፣ ፍርዱ፣ የትንሹ ቀንድ ማንነት እና ስራው ከእነዚህ
ትንቢቶች ጋር ያሉ ጊዜአቶች ከግልጽነት በጣም የራቁ ነበሩ።
ነገር ግን በቀጣይነት የፕሮቴስታንቱ ተሃድሶ ፣ ብዙ ሰዎች የዳንኤልን መጽሐፍ ማጥናት
ጀመሩ። ቢሆንም ግን በመጨረሻው ሰዓት ነበር መጽሐፉ በግልጽ የተገለጠው እና
ይዘቱ በሙሉ ግልጽ የሆነው። ኤለን ጂ ኋይት ‹‹ ከ 1798 ጀምሮ የዳንኤል መጽሐፍ
ተከፈተ። የትንቢቶቹ እውቀት ጨመረ፣ እናም የፍርዱ ሰዓት ቅርብ መሆኑን ብዙዎች
አወጁ። ›› (ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 356)። ‹‹ ከ 18ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ እና
ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በዳንኤል እና በራዕይ ትንቢቶች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት
በምድር ዙሪያ በመታየት ግንዛቤው ተሰራጨ። የእነዚህ ትንቢቶች ጥናት የክርስቶስ
ዳግም ምጻት በቅርብ እንደነበረ በሰፊው የተሰራጨ እምነት ፈጠረ።
በርከት ያሉ
ለዚህ የተጋለጡ ሰዎች በእንግሊዝ፣ ዮሴፍ ዎልፍ በመካከለኛው ምስራቅ፣ ማኑኤል
ሉካንዛ በደቡብ አሜሪካ እነ ዊሊያም ሚለር በዩናይትድ እስቴት ከሌሎች በርካታ
የትንቢት ተማሪዎች ጋር በዳንኤል መጽሐፍ ጥናታቸው ላይ ተመስርተው የዳግም
ምጻት በደጅ ላይ እንደሆነ አወጁ። ዛሬ ይህ አለም አቀፍ እንቅስቃሴ የጸና እምነት
ነው ያለው። (ዘ ሰቨንዝ ደይ አድቬንቲስት ኮሜንተሪ ቅጽ 4፣ ገጽ 879) ።
ታሪክን ወደ ኋላ ተመልክቶ እነዚህ በዳንኤል የተገለጹት ታሪካዊ
ትንቢቶች ፍጻሜን ለማየት፣ ዛሬ ስላለን ትልቅ እድል አስቡ። ይህ
እግዚአብሔር በሰጠን የተስፋ ቃሎች ላይ እንድንታመን እንዴት ነው
ሊረዳን የሚገባው?
ዳንኤል 12፡-5-13ን ያንብቡ። እንዴት ነው መጽሐፉ የተደመደመው?
የሚገርመው የመጨረሻው ትዕይንት በጢግሮስ ወንዝ፣ የዳንኤል ዋና ራዕይ የታየበት
ቦታ፣ ነበር (ዳንኤል 10፡-4) የተካሔደው። ሆኖም ግን በዚህ ስፍራ የተጠቀመው
ቃል ‹‹ወንዝ ›› የሚለው የተለመደ የዕብራይስጥ ቃል አይደለም ነገር ግን ‹ዮኦር›
የሚለው ቃል ነበር፣ እናም ብዙ ጊዜ ‹‹የአባይን ወንዝ ›› የሚያመላከት ነበር። ይህ ስለ
የእስራኤሎችን መውጣት ያስታውሳል እናም ይህም የሚያሳየው ልክ ጌታ እስራኤልን
ከግብጽ እንደዋጀ፣ እንዲሁ የመጨረሻ ዘመን ሕዝቡንም ይዋጃል።
ሶስት ትንቢታዊ የጊዜ ሰሌዳ ተሰጥቷል። የመጀመሪያው፣ ‹‹›ዘመን ፣ ዘመናት እና
የዘመን እኩሌታ›› ነው ‹‹የዚህ ድንቅ ፍጻሜ እስከ መቼ ነው? ›› (ዳንኤል 12፡-6)
ጥያቄውን ይመልሰዋል። ‹‹ድንቅ ›› የሚለው የሚወክለው በዳንኤል 11 ራዕይ ውስጥ
የተገለጹ ፣ የዳንኤል 7 እና 8 ማብራሪያ የሆኑትን ነገሮች ነው። በተጨማሪ በግልጽ
በዳንኤል 7፡-25 ላይ እና ኋላ ደግሞ በራዕይ 11፡-3፣ ራዕይ 12፡-6፣ 14 እና ራዕይ 13፡
-5 ላይ ተጠቅሷል። ከ1260 የጳጳሱ የበላይነት አመታት፣ ከ 538ቅ.ዓ እስከ 1798ዓ.ም
ከሚደርሰው ፣ ጋርም አብሮ ይሔዳል። እንዲሁም የቆየበትን ጊዜ ሳይጠቅስ ዳንኤል
11፡-32-35 ተመሳሳይ ግድያን ይጠቁማል።
ሌሎቹ ጊዜዎች 1290 እና 1335 ቀኖች ፣ በዳንኤል በእራሱ የበፍታን ልብሰ በለበሰው
ሰው የተሰነዘረውን፣ ‹‹የዚህ ድንቅ ፍጻሜ እስከ መቼ ነው ›› የሚለውን ጥያቄ
ይመልሳሉ።
እንዲሁም ሁለቱም የሚጀምሩት የ ‹‹እለታዊውን›› ማስወገድ እና ‹‹ የጥፋት እርኩሰትን
ባቆመበት ›› ነው። ከዳንኤል 8 ትምህርት የ‹‹የእለቱ ›› የሚለው የሚጠቁመው በኋላ
በተመሳሳዩ ስርዓት የተተካውን የክርስቶስን የማያቋርጥ የማማለድ ስርዓት ነው።
ስለዚህ የትንቢታዊው ጊዜ መጀመር ያለበት ከ 508ቅ.ዓ ክሎቪስ፣ የፈረንሳይ ንጉስ
፣ የካቶሊክን እምነት ከተቀበለበት ነው ። ይህ አስፈላጊ ኩነት ለቤተክርስቲያን እና
ለመንግስት ሕብረት በር የከፈተ ነው፣ እስከ መካከለኛው ዘመን ድረስ የቀጠለ
ነው። ስለዚህ 1290 ቀናት የሚያልቀው፣ የፈረንሳይ ገዥ በነበረው ናፖሊዮን ትዕዛዝ
በታሰረ ጊዜ ነው። እንዲሁ የ 1335 ቀናት በዳንኤል የትንቢት ጊዜ ውስጥ መጨረሻ
የተጠቀሰው የሚያበቃው በ 1843 ነው። ይህ የሚለራይት እንቅስቃሴ እና እንደገና
በተሃድሶ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የተካሔደበት ትንቢት ነው። የማይቀረውን
የኢየሱስ ዳግም ምጻት የታወቀበት እና ተስፋ የተደረገበት ጊዜ ነው።
በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ሁለት ነገሮችን አይተናል፤
የእግዚአብሔር ሕዝብ ተገድለዋል ፣ እናም በመጨረሻ የእግዚአብሔር
ሕዝብ ነጻ ወጥተዋል እንዲሁም ድነዋል። ይህ እውነታ ከፊታችን ካሉ
ችግሮች ይልቅ እንዴት ነው ታማኞች መሆን እንድንችል የሚረዳን?
የቀረቡ ትንቢቶች ወደ ፍርዱ መከፈት የሚመሩ
ተከታታይ ኩነቶች ናቸው። ይህ በተለይ የዳንኤል መጽሐፍ እውነት ነው።
ነገር ግን ያ የትንቢቱ ክፍል ከመጨረሻዎቹ ቀናት ጋር የሚገናኘው ‹እስከ አለም
ፍጻሜ ድረስ › ዳንኤል እንዲዘጋው እና እንዲያትመው ተጠየቀ። እዚህ ሰዓት
ላይ እስክንደርስ፣ በእነዚህ ትንቢቶች ፍጻሜ ላይ መሰረት አድርጎ ፣ ከፍርድ
ጋር የተያያዘ መልዕክት አልታወጀም። ነገር ግን በመጨረሻ ጊዜ ነብዩ ‹‹ብዙ
ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል›› (ዳንኤል 12፡-4) ይላል።
“ሐዋሪያው ጳውሎስ ያስጠነቅቃል ክርስቶስን በእነርሱ ቀን እንዳይጠባበቁ።
‹‹አይደርስምና›› ይላል ‹ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም
የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና › (2ኛ ተሰሎንቄ 2፡-3)›› ። ታላቁ
ክህደት እና ‹የእርኩሰቱ ሰው› እረዥም አገዛዝ ሳይሆን የጌታችንን ዳግም
ምጻት አንጠባበቅም።
የ ‹እርኩሰት ሰው › እንዲሁ ‹የእርኩሰት ሚስጢር› ፣
‹የሲኦል ልጅ›፣ እና ‹ያ እርጉም› የሚወክለው አስቀድሞ በትንቢት የተነገረው
ጳጳሳዊው ኃይል የበላይነቱን ለ 1260 አመታት ያሳየው ነው። ይህ ጊዜ
የሚያልቀው በ 1798 ነው። የክርስቶስ ዳግም ምጻት ከዚያ በፊት ሊከናወን
አይችልም። ጳውሎስ በማስጠንቀቂያው እንዳነሳው አጠቃላይ የክርስቲያን
ስርዓት ለመጣስ የተፈቀደበት ጊዜ እስከ 1798 ነው። የክርስቶስ ዳግም ምጻት
መልዕክት የሚታወጀው በዚያን ጊዜ ውስጥ(በ1260 አመታት) ይህኛው ሰዓት
(1798) ላይ ነው ።” ኤለን ጂ ኋት፣ ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 356)
1.ለሚመጣው የመጨረሻ ጊዜ ኩነቶች፣ ጊዜን ማስቀመጥ ምን
አይነት አደገኛ ነው? የተተነበዩት ኩነቶች ሳይሆኑ ቀርተው ሲያልፉ
በብዙዎች እምነት ላይ ምንድን ነው የሚሆነው? ለእኛ መንፈሳዊ
ጥቅም እና ወጥመድ ከሚሆንብን ወይም በሐሰተኛ ትንቢቶች
ከማመን የሚያድነን፣ በዮሐንስ 14፡-29 ላይ በክርስቶስ ቃል
ላይ ትንቢትን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ግንዛቤ እንዲኖረን
የሚረዳን ምን አይነት ወሳኝ የትንቢት መርህን ነው የምናገኘው?
2.ፈጣን የሆነ ግንኙነት በሚደረግበት እና ለእኛ ሁልጊዜ ለመልካም
ባይሆንም አስደናቂ የሳይንስ እድገት ባለበት ዘመን፣ ‹‹ሆኖ
የማያውቅ የችግር ጊዜ ›› ይሆናል ብሎ ለመገመት አስቸጋሪ
የማይሆነውን ሐሳብ የሚፈጥረው አሁን ስለምንኖርበት ጊዜ ያለው
ነገር ምንድን ነው?
3.በሰኞው የመጨረሻ ጥያቄ መልስ ላይ ተወያዩ። ወንጌል፣
ታላቁ እውነት የሆነው የክርስቶስ ጽድቅ በ“መጽሐፉ ተጽፎ
ለመገኘት” ብቸኛው የእኛ ተስፋችን ነው። ከዚያ ሌላ ምን
ተስፋ ሊኖረን ይችላል?