ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳንኤል 11፣ ዳንኤል 8፡ -3-8፣ 20-22፣ ኢሳያስ 46፡-9፣10፣ ዳንኤል 8፡-9፣23፣ ማቴዎስ 27፡-33-50
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “እስከ ተወሰነውም ዘመን ይሆናልና ከጥበበኞቹ አያሌዎቹ እስከ ፍጻሜ ዘመን ይነጥሩና ይጠሩ ይነጡም ዘንድ ይወድቃሉ።” (ዳንኤል 11፡-35)
ይ
ህን ፈታኝ ምዕራፍ ስንጀምር የተወሰኑ ነጥቦች ማግኘት እንዳለብን
ከመጀመሪያው አስቀምጦልናል። መጀመሪያ፣ በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ
ቀደም ሲል ከቀረቡት ትንቢታዊ ዝርዝሮች ጋር ይመሳሰላል። እንደ ዳንኤል 2፣ 7፣8
እና 9 ትንቢታዊ መልዕክቶቹ ከ ነብዩ ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ናቸው።
ሁለተኛ፣ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚጨቁን ተከታዩ የአለም ኃይል ብቅ
አለ። ሶስተኛ፣ የእያንዳንዱ ትንቢታዊ ዝርዝር ከፍታ መጨረሻው ደስታ ነው።
በዳንኤል 2 ድንጋይዋ ምስሉን አጠፋችው፣ በዳንኤለ 7 የሰው ልጅ ግዛትን ተቀበለ፣
እናም ዳንኤል 8 እና 9 በመሲሁ ስራ ምክንያት ሰማያዊው ቤተ-መቅደስ ነጻ።ምዕራፍ
11 ሶስት ነጥቦችን ይከተላል። መጀመሪያ፣ የሰሜኑ ንጉስ የእግዚአብሔርን ተራራ
ባጠቃ ጊዜ፣ ከፋርስ ንጉሶች ጀምሮ ስለ ዕጣ ፋንታቸው እና ስለ መጨረሻው ሰዓት
ያነሳል። ሁለተኛ፣ በሰሜኑ እና በደቡቡ ንጉስ መካካል የተከናወነውን ጦርነት እና
እንዴት በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተጽዕኖ እንዳደረጉ ያብራራል። ሦስተኛ፣
በመጨረሻ በደስታ ያጠቃልላል፣ የሰሜኑ ንጉስ ፍጻሜውን በ ‹‹በከበረው በቅዱሱ
ተራራ›› (ዳንኤል 11፡-45) አጠገብ ያገኛል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለመጋቢት 12 ሰንበት ይዘጋጁ።
ዳንኤል 11፡-1-4ን ያንብቡ። በዚህ ስፍራ ቀደም ሲል በዳንኤል ስላየናቸው ትንቢቶች የሚያስታውሰን ምን እናያለን?
ገብርኤል ለዳንኤል አሁንም ሶስት ነገስታቶች ከፋርስ እንደሚነሱ ይነግረዋል።
ከሁሉም ይልቅ በጣም ሐብታም የነበረው እና ግሪኮችን ያነሳሳው አራተኛው
ንጉስ ይከተላቸዋል። ከቂሮስ በኋላ በተከታታይ ሶስት ገዥዎች ፋርስን ገዝተዋል፣
ካምቢየሰስ (520-522ቅ.ዓ) ፣ ሐሰተኛው ስሜርዲስ (522ቅ.ዓ) ፣ እና ዳሪዮስ
የመጀመሪያው (522-486ቅ.ዓ) ። አራተኛው ንጉስ ደግሞ Xerxes ሲሆን፣ በአስቴር
መጽሐፍ አርጤክስስ በመባል ስሙ ተጠቅሷል። በጣም ሐብታም ነበር(አስቴር 1፡-17)፣ እና በትንቢት እንደተነገረው ግሪክን ለመውረር እጅግ ብዙ ሠራዊትን አሰልፏል።
ነገር ግን ከሐይሉ ይልቅ፣ በጣም ትንሽ አቅም ባለው በጀግና የግሪክ ወታደር አመጽ
ተደረገበት።
የመጨረሻው ንጉስ በዳንኤል 11፡-3 ላይ የተነሳው እና የጥንቱ አለም ገዥ የሆነው
ታለቁ እስክንድር እንደነበረ ለማወቅ አስቸጋሪ አይደለም። ግዛቱን የሚያስተዳድር
ሌላ ሳይተካ ገና በ32 አመቱ ሞቷል። ስለዚህ ግዛቱ በአራቱ የጦር ጀነራሎቹ
ተከፋፈለ፣ ሴሉኮስ በሶሪያ እና ሜሶፖታሚያ፣ ፔቶሎሚ በግብጽ ላይ፣ ሊስማቹስ በ
ትራይሴ እና በኢስያ ማይነር፣ እናም ካሳንደር በ ሜቆዶኒያ እና ግሪክ ነበሩ።
ዳንኤል 11፡-2-4 እና ዳንኤል 8፡-3-8፣ 20-22ን ያነጻጽሩ። እነዚህ
ጥቅሶች በዚህ ስፍራ በጋራ እስክንድርን እንደ ሐያል እንድንለየው
የሚረዱን እንዴት ነው?
ከእነዚህ የተለያዩ ስሞች፣ ቀናቶች፣ ቦታዎች፣ እና ታሪካዊ ኩነቶች ምን ልንማር
እንችላለን? አንደኛ፣ ትንቢቱ በመለኮት መልዕክተኛ እንደተተነበየው መፈጸሙን
እንማራለን። የእግዚአብሔር ቃል በፍጹም አይወድቅም። ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር
የታሪክ/ዘመናት ጌታ ነው። ምን አልባት የፖለቲካ ሐይሎች፣ የመሪዎች እና
ነገስታቶች ክንውንን በ ነገስታቶች፣ አምባገነኖች እና በሁሉም አይነት ፖለቲከኞች
ፍላጎት እንደመጣ ሊሰማን ይችላል። ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው
እግዚአብሔር የመጨረሻው ተቆጣጣሪ እና የታሪክን ፍሰት እንደ መለኮት
አላማ፣ ክፉን አስወግዶ የእግዚአብሔርን ዘለአለማዊ መንግስትን ወደ መመስረት
ያሽከረክረዋል።
ዳንኤል 11፡-5-14ን ያንብቡ። በዚህ የሚገለጸው ምንድን ነው?
ከታላቁ እስክንድር ሞት በኋላ ትልቁ የግሪክ ግዛት በአራቱ ጀነራሎቹ ተከፋፋለ።
ሁለቱ በሶሪያ (ሰሜን) ሴሉኮስ እና በግብፅ ፔቶሎሚ(ደቡብ) ምድሩን ለመቆጣጠር
እርስ በእርሳቸው የሚዋጉ ስርወ-መንግስታትን መመሰረትን ቻሉ።
ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪዎች፣ በ ዳንኤል 11፡-5-14 የተጠቀሰው ትንቢት
የሚያመላክተው በ ሰሜኑ እና ደቡቡ ስርወ-መንግስታት መካከል የተደረጉ በርካታ
ጦርነቶች ናቸው ብለው ይረዳሉ። በትንቢቱ መሰረት እነዚህን ሁለት ስርወ
መንግስታት በጋብቻ አንድ ለማድረግ ሙከራዎች ነበሩ፣ ነገር ግን ይህ ሕብረት
የቆየው በጣም ለአጭር ጊዜ ነበር (ዳንኤል 11፡-6)።
የታሪክ ድርሳናት እንሚያስረዱን
አንቲኮስ ሁለተኛ ቲዮስ(261-246ቅ.ዓ) የ ሴሉኮስ አንደኛ የልጅ ልጅ የግብጽ ንጉስ
ፔቴሎሚ ሁለተኛ ፊላደልፉስን ልጅ ቤሪንስን አግብቷል። ቢሆንም ግን ያ ስምምነት
አልቆየም ፣ ወዲያውም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያካተተው ጦርነት ተቀሰቀሰ። ስለዚህ
ዳንኤል 11 ፣ ዳንኤል ከዚህ ትእይነት ካለፈ ከብዙ ዘመናት በኋላ የእግዚአብሔርን
ሕዝብ ሕይወትን የሚነካ በጣም አስፈላጊ ኩነቶችን ያነሳል።
እንደገና፣ ለምንድን ነው ጌታ በዚያ አለም ውስጥ የነበሩ ነገስታት ታላቅነትን ለማግኘት
ስላደረጓቸው ዝርዝር የእርስ በእርስ ጦርነቶች አስቀድሞ የገለጸው የሚልን ጥያቄ
ልንጠይቅ እንችላለን። ምክንያቱ ቀላል ነው፣ እነዚ ጦርነቶች በእግዚአብሔር ሕዝቦች
ላይ ተጽዕኖ ነበራቸው። ስለዚህ ጌታ በሚመጡት አመታት ሕዝቡ የሚገጥማቸውን
ተግዳሮቶች አስቀድሞ አስታወቀ። እንዲሁ እግዚአብሔር የታሪክ ባለቤት እና ጌታ
ነው ፣ እናም የተመዘገቡ ትንቢታዊ መረጃዎችን ከታሪካዊ ኩነቶች ጋር ስናነጻጽር
አንደገና ትንቢታዊ ቃሎች እንደተተነበዩት መፈጸማቸውን እናረጋግጣለን።
እርስ በእርሳቸው ሲጋጠሙ ስለ ነበሩት የግሪክ ነገስታት ውጣ ውረድ የተነበየው
እግዚአብሔር ፣ የወደፊቱን የሚያውቀው እርሱው ነው። የእኛ መታመን እና እምነት
ይገባዋል። በሰዎች ማምረቻ የተሰራ አምላክ ሳይሆን እርሱ ታላቅ አምላክ ነው።
የሚመራው የታሪክ ኩነቶችን ፍሰት ብቻ አይደለም ነገር ግን ፈቃዳችንን ብንሰጠው
የእኛንም ሕይወት መምራት ይችላል።
ኢሳያስ 46፡-9፣10ን ያንብቡ። በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች ውስጥ ምን
ያህል የክርስትና ስነ-መለኮታዊ አስተምህሮቶች ይገኛሉ? እናም ምን
አይነት ታላቅ ተስፋን ከእነርሱ ልንወስድ እንችላለን? እግዚአብሔር
መልካም እና አፍቃሪ ባይሆን እና ቂመኛ እና ስግብግብ ቢሆን ቁጥር
10 ምን ያህል አስፈሪ ጥቅስ ሊሆን እንደሚችል ያስቡ።
ዳንኤል 11፡-16-28ን ያንብቡ። ምንም እንኳን ጥቅሱ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በዳንኤል ውስጥ በሌላ ስፍራ ምን አይነት ምስል ሊከሰትልዎ ይችላል?
በዳንኤል 11፡-16 ላይ ከግሪክ መንግስት ወደ ሮም መንግስት የተደረገን የኃይል
ሽግግር ያመላክታል ፤ ‹‹ በእርሱም ላይ የሚመጣው ግን እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥
በፊቱም የሚቆም የለም በመልካሚቱም ምድር ይቆማል፥ በእጁም ውስጥ ጥፋት
ይሆናል።››። ኢየሩሳሌም፣ የጥንት እስራኤሎች የሚኖሩበት አሁን ግን አረማዊው
ሮም የሚያስተዳድረው የሚያኮራ ምድር ነው። በትንሹ ቀንድ የጎንዮሽ መስፋፋት
ጊዜ ወደ የሚያኮራው ምድር ተመሳሳይ ኩነት ተከስቷል። ስለዚህ ግልጽ ይመስላል ፣
በዚህ ደረጃ አለምን የሚያስተዳድር ኃይል አረመኔአዊው ሮም ነው።
አንዳንድ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ይህንን ሐሳብ ያጠናክራሉ። ለምሳሌ
‹‹የዚያን ጊዜም በመንግሥቱ ክብር መካከል አስገባሪውን የሚያሳልፍ በስፍራው
ይነሣል ነገር ግን በቍጣው ሳይሆን በሰልፍም ሳይሆን በጥቂት ቀን ይሰበራል።››
(ዳንኤል 11፡-20) ። እንዲሁ እንደ ትንቢቱ ይህ ገዥ በ ‹‹መጥፎ ሰው›› ይተካል።
(ዳንኤል 11፡-21)። ታሪክ እንሚያሳየው አውግስጦስ ለጢብሮስ ፣ የጉዲፈቻ ልጁ
ነበር፣ በእርሱ ተተክቷል። ጢብሮስ ከሰው ጋር የማይገጥም እና መጥፎ ሰው እንደሆነ
ይታወቃል።
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በጣም አስፈላጊው፣ የ‹‹ቃል ኪዳኑ አለቃ›› የሚሰበረው
በጢብሮስ አገዛዝ ዘመን ነበር(ዳንኤል 11፡-22)። ይህ በግልጽ የሚያመለክተው
የክርስቶስን መሰቀል ነው፣ ‹‹መሲሁ አለቃ ›› (ዳንኤል 9፡-25፣ እንዲሁም ማቴዎስ
27፡-33-50ን ይመልከቱ)፣ በጢብሮስ አገዛዝ ዘመን ለሞት ይሰጣል። በዚህ ያለው
የኢየሱስ አመላካች ‹‹የቃል ኪዳኑ አለቃ›› የሚለው የታሪካዊ ኩነቶችን አካሔድ
የሚያሳይ ሐይለኛ መለያ ነው። ይህ እንደገና ለአንባቢው የእግዚአብሔርን የወደፊቱን
አዋቂ መሆንን የሚያሳይ ጠንካራ መረጃን ይሰጣል። እግዚአብሔር ከዚህ ትንቢት
በፊት ለመጡት ነገሮች ሁሉ ትክክል ነበር፣ ስለዚህ ወደፊት ይሆናል ባለው ላይ
ሙሉ ለሙሉ እንድንታመነው ያስችለናል።
በፖለቲካዊው እና ሐይማኖታዊው መካከል የናዝሬቱ ኢየሱስ ‹‹
የቃልኪዳኑ አለቃ›› በጥቅሱ ተገልጧል። ይህ ከረብሻው እና ከፖለቲካው
ሴራ ይልቅ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ማዕከል ሆኖ የሚቀጥልበትን
እንዴት ነው በማሳየት የሚረዳው?
ዳንኤል 11፡-29-39ን ያንብቡ። ከ አረመኔአዊው ሮም በኋላ የተነሳው ኃይል ማን ነው?
ዳንኤል 11፡-29-39 ስለ አዲስ ኃይል ስርዓት ያመላክታል። ምንም እንኳን ይህ ኃይል
ከአረመኔአዊው ሮም ቀጠሎ የመጣ እና አንዳንድ ባህሪያትንም ከአረመኔአዊው ሮም
የወረሰ ቢሆንም በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ አንዳንድ ገጾቹ ሌላ ይመስላሉ። የመጽሐፍ
ቅዱስ ጥቅስ እንዲህ ይላል ‹‹ በተወሰነውም ጊዜ ይመለሳል ወደ ደቡብም ይመጣል
ነገር ግን ኋለኛው እንደ ፊተኛው አይሆንም። ›› (ዳንኤል 11፡-29) ። ጨምረን
ስንመለከት እንደ ሐይማኖታዊ ኃይል ሲንቀሳቀስ እናያለን። አላማው እግዚአብሔርን
እና ሕዝቦቹን ማጥቃት ነው። እስኪ በዚህ ንጉስ የተፈጸሙ ወንጀሎችን እንመልከት።
አንደኛ፣ ‹‹ በቅዱሱም ቃል ኪዳን ላይ ይቈጣል፥ ››(ዳንኤል 11፡-30)። ይህ የንጉሱ
ተቃውሞ በእግዚአብሔር የድነት ቃል ኪዳን ላይ መሆን አለበት ።
ሁለተኛ፣ ንጉሱ ኃይልን ያደረጅ እና ‹‹ መቅደሱንም ግንቡንም ያረክሳሉ …
የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ ›› (ዳንኤል 11፡-31) ። በዳንኤል 8 ትንሹ ቀንድ
የእግዚአብሔርን ‹‹የመቅደሱንም›› መሰረትን እንደሚንድ እና የ ‹‹የዘወትሩን
መሥዋዕት፥›› እንደሚሽር ተመልክተናል(ዳንኤል 8፡-11)። ይህ በክርስቶስ የሰማያዊ
መቅደስ አገልግሎት ላይ የሚደረግ መንፈሳዊ ጥቃት እንደሆነ ያስገነዝባል።
ሦስተኛ፣ መቅደሱ ላይ ባደረሰው ጥቃት የተነሳ ይህ ኃይል በእግዚአብሔር መቅደስ
ላይ ‹‹የጥፋትን እርኩሰት ›› ያቆማል። የዚህ ተመሳሳይ አገላለጽ ‹‹ የሚያጠፋ
ሐጢያት›› ሲሆን የሚያመለክተውም በትንሹ ቀንድ የተደረገውን ክህደት እና
አመጽን ነው (ዳንኤል 8፡-13)።
አራተኛ፣ ይህ ኃይል የእግዚአብሔር ሕዝቦችን ይገድላል፣ ‹‹ እስከ ተወሰነውም ዘመን
ይሆናልና ከጥበበኞቹ አያሌዎቹ እስከ ፍጻሜ ዘመን ይነጥሩና ይጠሩ ይነጡም ዘንድ
ይወድቃሉ።››(ዳንኤል 11፡-35)። ይህ ስለ ትንሹ ቀንድ ‹ከሠራዊትና ከከዋክብትም
አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም › የሚለውን ያስታውሰናል(ዳንኤል 8፡-10
ከ ዳንኤል 7፡-25 ጋር ያነጻጽሩ)።
አምስተኛ፣ ይህ ንጉስ ‹‹ እንደ ፈቃዱ ያደርጋል ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፥
በአማልክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ ያደርጋል፥ በአማልክትም አምላክ ላይ በትዕቢት
ይናገራል ›› (ዳንኤል 11፡-36)፣ ትንሹ ቀንድ በእግዚአብሔር ላይም (ዳንኤል 7፡-25)
የ‹‹ትዕቢት›(ዳንኤል 7፡-8) ቃላትን ይናገራል።
ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችም ሊጠቀሱ ይችላሉ፣ ነገር ግን በዳንኤል 7
እና 8 ያነበብነውን በመውሰድ፣ ይህ ኃይል ማነው? ከማህበረሰባዊው
ግፊት(በእኛ ላይ ከሚያመጣው) ይልቅ ይህን ኃይል በመለየት መጽናቱ
ለምንድን ነው ለእኛ በጣም አስፈላጊ የሆነው?
ዳንኤል 11፡-40-45ን ያንብቡ። በዚህ ምንድን ነው እየሆነ ያለው?
የሚከተሉት አባባሎች ይህንን ጥቅስ እንድንገነዘብ ይረዱናል፡የመጨረሻው ሰዓት፡- ይህ አገላለጽ የሚገኘው በ ዳንኤል መጽሐፍ (ዳንኤል 8፡
-17፣ ዳንኤል 11፡-35፣ ዳንኤል 12፡-4፣9) ውስጥ ብቻ ነው። የዳንኤል ትንቢት ጥናት
እንደሚጠቁመው በመጨረሻው ሰዓት ከ ጳጳሳዊው ስልጣን መውደቅ፣ 1798፣
ሙታን እስከሚነሱበት ጊዜ ድረስ ይደርሳል (ዳንኤል 12፡-2) ።
የሰሜን ንጉስ፡- ይህ ስም መጀመሪያ በመልክዓምድራዊ አንጻር የሚያሳየው የሶሪያን
ስርወ-መንግስትን ነው ነገር ግን የአረመኔአዊውን እና በመጨረሻም የጳጳሳዊውን
ሮም ይወክላል። ይህ ስለሆነ የመልክዓምድራዊ ስፍራን አይገልጽም ነገር ግን
የእግዚአብሔር ሕዝብ መንፈሳዊ ጠላትን እንጂ። በተጨማሪ የሰሜኑ ንጉስ እንዲሁ
የእውነተኛው አምላክ ተጻራሪ በመሆን ይወከላል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ በምሳሌያዊ
አገላለፅ ከሰሜን ጋር ይያያዛል (ኢሳያስ 14፡-13)።
የደቡብ ንጉስ፡- ይህ ስም በመጀመሪያ የሚያሳየው የግብጽን ፔቶሎማይክን ስርወመንግስትን ሲሆን፣ ከቅድስት ምድር በስተደቡብ በኩል ነው። ነገር ግን ትንቢት
ሲገለጥ ስነ-መለኮታዊ ገጽታን ያገኛል እናም በአንዳንድ ምሁሮች ዘንድ ከክህደት ጋር
ይያያዛል። እንደ ኤለን ጂ ኋይት በራዕ 11፡-8 ላይ እንደሰጠችው ሐሳብ ‹‹ይህ ክህደት
ነው›› (ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 269) ትላለች።
ቅዱሱ የክብር ተራራ፡- በብሉይ ኪዳን ይህ አገላለጽ የሚጠቁመው የእስራኤል
ዋና ከተማን እና በስነ-ምድራዊ አቀማመጥ ደግም በተስፋይቱ ምድር የሚገኘውን
የጺዮን ተራራን ነው። ከመስቀሉ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በነገዳቸው እና
በስነ-ምድራዊ መስመሮች መገለጻቸውን አቆሙ። ስለዚህ፣ ቅዱሱ ተራራ የሚያሳየው
በአለም ዙሪያ ያሉ የእግዚአብሔር ሕዝብን መሆን አለበት።
ሰለዚህ ኩነቶችን እንደዚህ ልንተረጉማቸው እንችላለን፡(1) የደቡብ ንጉስ የሰሜኑን ንጉስ አጠቃ፤ የፈረንሳይ አቢዮት ሐይማኖትን ለማጥፋት
እና ጳጳሳዊውን ስርዓት ለማጥፋት ሞከረ ግን እልቻለም።
(2) የሰሜኑ ንጉስ
የደቡቡን ንጉስ አጠቃ እና አሸነፈው፤ ሐይማኖታዊው ኃይል በጳጳሳዊው ስርዓት
እና በተባባሪዎቹ የሚመራው፣ የክህደትን ኃይል አሸነፈው እና ከተሸነፈው ጠላት
ጋር ሕብረትን ፈጠረ። (3) ኤዶም ፣ ሞአብ እና የቀድሞ የአሞን ሕዝቦች አመለጡ፤
በመጨረሻው ሰዓት ከእግዚአብሔር እውነተኛ ሕዝብ ጋር ያልተቆጠሩ ጥቂቶች
ጥምረቱን ይቀላቀላሉ። (4) የሰሜን ንጉስ ቅዱሱን ተራራ ለማጥቃት ተዘጋጀ ነገር
ግን ፍጻሜ ሆነበት፤ የክፉ ኃይል ጠፋ፣ እናም የእግዚአብሔር መንግስት ተመሰረተ።
በመጨረሻ እግዚአብሔር እና የእርሱ ሕዝብ እንደሚያሸንፍ ከማወቅ
መጽናናትን እንዴት ልናገኝ እንችላለን?
ቢያንስ ከ ዳንኤል 11፡-29-39፣ ማርቲን ሉተር በ ዳንኤል 11፡
-31 ያለውን የጥፋት እርኩሰትን ከጳጳሳዊው ስርዓት እና አስተምህሮው እንዲሁ
ልምምዱ ጋር መለየት መቻሉ የሚገርም ነው። ስለዚህ በዳንኤል 11 እና ዳንኤል
7 እና 8 ያለው ሕብረት የሉተርን እይታ እና የሌሎች የፕሮቴስታንት ተንታኞች፣
የጳጳሳዊው ስርዓት ተቋም እና የእርሱ አስተምህሮ በታሪክ ውስጥ የእነዚህ ትንቢቶች
ፍጻሜ ነው ለሚሉት እይታቸውን ያጠናክራል። በዚህ ግንኙነት ኤለን ጂ ኋይት
‹‹ በሮም ግዛት ክልል ውስጥ በህሊና ነጻነት ደስታ ውስጥ ሳይረበሽ የቀረ ምንም
ቤተክርስቲያን አልነበረም። የጳጳሳዊው ስርዓት ስልጣንን ሲይዝ እጆቿን ዘርግታ
ለእርሷ (ሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን) መንገድ እውቅና ያልሰጡትን እስክታደቅ እና
አብያተክርስቲያናት አንድ በአንድ እጃቸውን ለግዛቷ እስኪሰጡ ድረስ አልቆየም ››
(ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 62 ) ትላለች።
1.በመጨረሻዎቹ ቀኖች ሮም በሚኖራት ሚና ዙሪያ ያለውን የመጽሐፍ
ቅዱስን አስተምህሮ በተመለከተ ለድርድር ሳናቀርብ ፣ ስለ ሌሎች
ስሜት ምን ያህል መጠንቀቅ እንችላለን?
2.ዳንኤል 11፡-33ን ያንብቡ፤ ‹‹በሕዝቡም መካከል ያሉ ጥበበኞች
ብዙ ሰዎችን ያስተምራሉ ነገር ግን በሰይፍና በእሳት ነበልባል በምርኮና
በመበዝበዝ ብዙ ዘመን ይወድቃሉ።›› ይህ ጥቅስ ስለ አንዳንድ
የእግዚአብሔር ታማኞች ዕጣ ምንድን ነው የሚለው? ስለ እነዚህ
ታማኞች እንዲሁ መስዋዕት ከመሆናቸው በፊት ስለሚያደርጉት ነገር
ጥቅሱ ምን ይላል? ምን አይነት መልዕክትስ አለው ለእኛ ዛሬ?
3.ዳንኤል 11፡-36ን ያንብቡ፤ ‹‹ንጉሡም እንደ ፈቃዱ ያደርጋል
ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ በአማልክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ
ያደርጋል፥ በአማልክትም አምላክ ላይ በትዕቢት ይናገራል ቍጣም
እስኪፈጸም ድረስ ይከናወንለታል፥ የተወሰነው ይደረጋልና።›› ስለ ማን
እና ምንድን ነው ይሔ የሚያስታውስዎ? (ኢሳያስ 14፡-12-17፣ እንሁ
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡-1-4ን ይመልከቱ) ።
4.ዳንኤል 11፡-27፣ 29 ፣ እና 35 ‹ላሞ ኤዴ› ወይም ‹‹የተወሰነው
ዘመን›› የሚል ሐረግን ይጠቀማል። ይህ እንደገና ስለ እግዚአብሔር
ታሪክን ተቆጣጣሪነት ምንድን ነው የሚነግረን?