ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳንኤል 9፣ ኤርሚያስ 25፡-11፣ 29፡-10፣ 2ኛ ነገስት 19፡-15-19፣ ማቴዎስ 5፡-16፣ ያዕቆብ 5፡-16
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- ‹‹አቤቱ፥ ስማ አቤቱ፥ ይቅር በል አቤቱ፥ አድምጥና አድርግ አምላኬ ሆይ፥ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና ስለ ራስህ አትዘግይ። ›› ( ዳንኤል 9፡-19)
ዳ
ንኤል 9 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ታላላቅ ጸሎቶች መካከል አንዱን
ይዟል። በሕይወቱ ወሳኝ በሆኑ ጊዜአት በፊቱ የተጋረጡ ተግዳሮቶችን
ለመወጣት ዳንኤል የጸሎት ጊዜን ይወስዳል። በአረመኔያዊው ንጉስ ሚስጢራዊ
ህልም ምክንያት ዳንኤል እና ጓደኞቹ ሊገደሉ በነበረበት ሰዓት፣ ነብዩ ወደ
እግዚአብሔር በጸሎት ቀረበ(ዳንኤል 2)። እንዲሁ ለንጉሱ ብቻ እንጂ ለየትኛውም
አምላክ ልመና ማቅረብ የሚከለክል አዋጅ በወጣበትም ጊዜ ዳንኤል ፊቱን ወደ
እየሩሳሌም አድርጎ በየቀኑ መጸለዩን ቀጥሏል(ዳንኤል 6)። ስለዚህ በዳንኤል 9 ላይ
ያለውን ጸሎቱን ስንወስድ የ2300 ማታ እና ጠዋት የዳንኤል 8 ትንቢት በሐይል
ተጽዕኖ አንዳደረገበት እናስታውስ።
ምንም እንኳን አጠቃላይ ሁኔታው ቢብራራም
፣ ዳንኤል ግን በሁለቱ ሰማያዊ አካላት ቃለ ምልልስ ላይ የቀረበው የጊዜ ዘመንን
አልተረዳም ነበር። ‹‹ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው ከዚያም
በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።›› (ዳንኤል 8፡-14)። በዳንኤል 9 ላይ ተጨማሪ ብርሃን
ለነብዩ የተሰጠው አሁን ነው ፣ በጸሎት የተመለሰው በዚህ ጊዜ ነበር ።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለየካቲት 28 ሰንበት በማጥናት ይዘጋጁ።
ዳንኤል 9፡-1፣2 ን ያንብቡ። ዳንኤል ፣ በጥንቃቄ ያጠናውን ትንቢት ‹‹መጽሐፉን አስተዋልሁ›› ይላል። የቱን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ወይም መጽሐፍትን ማለቱ ነው?
ይህንን ጸሎት ስንመለከት፣ ከቀደሙት ራዕይዎች እግዚአብሔር ለሙሴ እና ለነብያት
ከሰጠው ራዕይ የጠለቀ ጥናት ላይ የተነሳ እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው። ከኤርምያስ
መጽሐፍ እንደተረዳው የምርኮ ዘመናቸው ሰባ አመታትን እንደሚደርስ ነው(
ኤርሚያስ 25፡-11፣ 12፣ ኤርሚያስ 29፡-10)፣ ዳንኤል ይኖርበት የነበረውን የታሪክን
ዘመን ማስተዋል አስፈላጊነቱን ተረድቷል።
በአእምሯችን እንያዝ ዳንኤል ይህንን ጸሎት ያቀረበው የፋርስ መንግስት የባቢሎንን
መንግስት በተካበት ዘመን በ 539ቅ.ዓ ነው። ስለዚህ ናቡከደነጾር እየሩሳሌምን
አጥቅቶ ቤተ መቅደሱን ካወደመው ወደ ሰባ አመት እየሆነ ነው። ስለዚህ እንደ
ኤርሚያስ ትንቢት፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ በቅርቡ ወደ ትውልድ ሐገሩ ይመለሳል።
በእግዚአብሔር ቃል በመታመን፣ ዳንኤል በጣም ከፍ ያለ ነገር በሕዝቡ ላይ
እንደሚሆን አውቋል፣ ልክ እግዚአብሔር ቃል እንደገባው፣ በባቢሎን ያለው ስደት
በቅርቡ ያበቃል እናም አይሁዶች ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።
ለእርሱ ከቀረበው መጽሐፍ እዳጠናው ፣ የሕዝቡ ሐጢያት ምን ያህል ቀላል
እንዳልነበር ተገንዝቧል። ምክንያቱም ቃል ኪዳናቸውን አፍርሰዋል፣ ከእግዚአብሔር
ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አበላሽተዋል። ስለዚህም ተከትሎ የመጣው ውጤት
ስደት (ዘለዋውያን 26፡-14-45) ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ራዕይ ማጥናቱ
ለዳንኤል ጊዜውን እንዲያስተውል እና በሕዝቡ ስም በእግዚአብሔር ፊት ለመቅርብ
አጣዳፊ መሆኑ እንዲሰማው አደረገው።
ወደ ምድራችን የመጨረሻ ጊዜአት በቀረብን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ማጥናት እና
እንደ እግዚአብሔር ቃል መኖር ያስፈልጋል። የምንኖርበትን አለም መጽሐፍ ቅዱስ
ብቻ ነው በስልጣን የሚያብራራልን። ከሁሉም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ በመልካም
እና በክፉ መካከል ስላለው ታለቅ ተጋድሎ ይነግረናል፣ እናም የሰብአዊ ዘር ታሪክ
ክፉን በማጥፋት እና የእግዚአብሔርን ዘለአለማዊ መንግስት በማቋቋም እንደሚዘጋ
ይነግረናል። መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ ባጠናን ቁጥር የበለጠ ዘመናዊውን የአለም
ሁኔታ እና የእኛን ቦታ እናስተውላለን እንዲሁም አለም ሊሰጥ የሌለውን ፣ ተስፋ
ለማድረግ ምክንያታችንን እንመለከታለን።
በተወሰነ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ መጣ እና ሔድ የሚለውን አለም
እናስተውል ዘንድ እንዴት ነው የሚረዳን፣ በቀላሉ ምንም እንዳልተሰማን
መሆን እንችላለን?
ዳንኤል 9፡-3-19ን ያንብቡ። በምን መሰረት ላይ ነው ዳንኤል ልመናውን ለምህረት ያደረገው?
በዚህ ጸሎት ውስጥ የተወሰኑ ነጥቦችን ልንጨብጥ ይገባል።
አንደኛ ነጥብ፣ በዳንኤል ጸሎት ውስጥ የትም ቦታ በአይሁድ ሕዝብ ላይ
ስለደረሰው አስከፊ ነገር ምንም አይነት ማብራሪያ ሲጠይቅ አናይም። በእርግጥ
የጸሎቱ አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው ዳንኤል እራሱ ምክንያቶቹን ሲቆጥር ነው።
‹‹ በባሪያዎቹም በነቢያት እጅ በፊታችን ባኖረው በሕጉ እንሄድ ዘንድ የአምላካችንን
የእግዚአብሔርን ቃል ምንም እንኳ ባንሰማ፥›› (ዳንኤል 9፡-10) ። ለመጨረሻ ጊዜ
ዳንኤልን ትተነው የመጣነው በዳንኤል 8 መጨረሻ ላይ የሆነን ነገር ማስተዋል ፈልጎ
እንደ ነበር ነው፣ የ2300 ማታ እና ጠዋት ራዕይን እንዳላስተዋለ ሲናገር (ዳንኤል 8፡
-27) ነበር።
ሁለተኛ ነጥብ ፣ ጸሎቱ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ ተማጽኖ ነው፣ ምንም እንኳን
ሐጢያትን ቢያደርጉ እና ክፉ ቢያደርጉ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሕዝቡን ይቅር
እንዲል ነበር። በአንድ በኩል ሐይለኛ ወንጌልን እናያለን ፣ የእራሳቸው የሆነ
መልካም ስራ የሌላቸው ፣ ሆኖም የማይገባቸውን ጸጋ ይሻሉ ያላገኙትን ይቅርታንም
ይጠይቃሉ። እያንዳንዳችን ፣ በግለሰብ ደረጃ በእግዚአብሔር ፊት ያለንበትን
የሚያሳይ ምሳሌ አይደለምን?
ዳንኤል 9፡-18፣19ን ያንብቡ። ጸሎቱ እንዲመለስ ሌላ ምን አይነት
ምክንያት ነው ዳንኤል የሰጠው?
ሌላው የዳንኤል ጸሎት ገጽታ መጥቀስ የሚፈለገው ፣ ለተከበረው የእግዚአብሔር
ስም ተማጽኖ ነው። ያም ጸሎቱ ለዳንኤል የግል እና ለሕዝቡ ምቾት አልነበረም
ነገር ግን ለእራሱ ለእግዚአብሔር ነበር(ዳንኤል 9፡-17-19)። በሌላ አነጋገር ልመናው
ሊሰጠው ይገባል ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስም ይከበራልና።
2ኛ ነገስተ 19፡-15-19ን ያንብቡ። በምን መንገዶች ነው የሕዝቅኤል ጸሎት
ከዳንኤል ጸሎት ጋራ የሚመሳሰለው? ማቴዎስ 6፡-16 የእግዚአብሐሔርን
ስም እንዴት ማክበር እንደምንችል ምንድን ነው የሚለው?
ዳንኤል 9፡- 5-13ን ያንብቡ። ዳንኤል እኛ በድለናል እያለ ደጋግሞ መናገሩ፣ ከዚያም ደግም እንደዚህ አይነት መቅሰፍትን በሕዝቡ ላይ ባመጣው ሐጢያት ውስጥ እራሱን የማካተቱ ትርጉም ምንድን ነው?
የዳንኤል ጸሎት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ትርጉም ካላቸው የምልጃ ጸሎቶች
መካከል አንዱ ነው። እንደዚህ አይነት ጸሎት የእግዚአብሔርን ልብ ይነካል፣ ኩነኔን
ያስቀር እና ከዚያ ይልቀ ከጠላት ነጻ ያወጣል። እግዚአብሔር የአይሁድን ሕዝብ
ሊያጠፋ ሲል የሙሴ ምልጃ እጁን አስቀረው( ዘጸአት 32፡-7-14፣ ዘኁልቁ 14፡-1025)። ክፉ ድርቅ ምድሪቱን ሊውጥ ሲል እግዚአብሔር የኤልያስን ጸሎት መለሰ እና
ዝናብን በወንዞች አመጣ።
ለቤተሰብ አባላት፣ ለወዳጆቻችን ፣ እና ለሌሎች ሰዎች ወይም ሁኔታዎች ሰንጸልይ፣
እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይሰማና ጣልቃ ይገባል። አንዳንድ ጊዜ ጸሎት እንዲመለስ
እረዥም ጊዜን ሊወስድ ይችላል፣ ነገር ግን ታምነን ልናርፍ እንችላለን እግዚአብሔር
ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን በፍጹም አይረሳም (ያዕቆብ 5፡-16)።
በዚህ ጉዳይ፣ ዳንኤል በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል የማማለድ ሚናውን
ተጫወተ። በእርሱ የመጽሐፍ ጥናት ነብዩ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በተላለፉ
ጊዜ እና የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያ አልሰማም ባሉ ጊዜ ምን ያህል ሐጢያተኛ
እንደሆኑ ተረዳ። ስለዚህ ተስፋ የሚያስቆርጡ መንፈሳዊ ሁኔታቸውን አይቶ ዳንኤል
ለፈውስ እና ለይቅርታ ጸለየ። በተወሰነ መልኩ ዳንኤል አማላጃችንን ክርስቶስን
አሳይቷል(ዮሐንስ 17)። ቢሆንም ግን ወሳኝ የሆነ ልዩነት አለ፣ ክርስቶስ ‹‹ያለ
ሐጢያት›› (ዕብራውያን 4፡-15) ነበር ስለዚህ ስለ ራሱ ሐጢያት ይቅርታን መጠየቅ
አያስፈልገውም ወይም ለግል ይቅርታ መስዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም(ዕብራውያን
7፡- 26፣27) ነገር ግን እራሱን ከሐጢያተኞች ጋር በተለየ ሁኔታ ለይቷል፣ ‹‹ እኛ
በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ
እኛ ኃጢአት አደረገው። ›› (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡-21)።
‹‹የሰውን ነፍስ ለማዳን ወይም እንደ መልካም ስራ፤ በሰው ውስጥ ያለ
መልካም ፣ ቅዱስ ፣ ጨዋ እና ፍቅር የሆነ ነገር ሁሉ አንድ ላይ
ቢሰበሰብ እና ጉዳዩ ወደ እግዚአብሔር መላዕክት ቢቀርብ ፣ እንደ
ክህደት ተቆጥሮ የቀረበው ሐሳብ ውድቅ ይሆናል ›› ( ኤልን ጂ
ኋይት፣ ኤዝ እና ወርክ፣ ገጽ 24)። እነዚህ ቃላት በእኛ ፋንታ አማላጅ
እንደሚያስፈልገን የሚያስተምሩን ምንድን ነው?
የዳንኤል የምልጃ ጸሎት ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያነሳል፤ የሕዝቡን ሐጢያት እና የእየሩሳሌምን ባዶነት። ስለዚህ የእግዚአብሔር ምላሽ ለእነዚህ ሁለት ልመናዎች መፍትሔ ይሰጣል። በመሲሁ ስራ ሕዝቡ ይዋጃል እንዲሁም ቤተ መቅደሱ ይቀባል/ ይነጻል። ሁለቱ ልመናዎች ከዳንኤል የታሪክ እውቀት አድማስ በበለጠ መንገድ ተመልሰዋል። የመሲሁ ስራ መላውን የሰብአዊ ዘር ይጠቅማል። ዳንኤል 9፡-21-27ን ያንብቡ። በ70 ሳምንት ውስጥ ምን ሥራ ነው የሚሰራው? ለምንድን ነው ኢየሱስ ብቻ ሊፈጽመው የሚችለው?
1.‹‹አመጽን ይጨርስ ›› የእብራይስጡ ቃል ለ‹‹አመጽ›› (ፐሻ) እያወቁ የሚሆን
ሕገን መጣስ፣ ዝቅተኛው በበላዩ ላይ (ለምሳሌ ምሳሌ 28፡-24 ) የሚል ሐሳብን
ይይዛል። ይህ ቃል እንዲሁ እግዚአብሔር ከሰብአዊያን ጋር በተከራከበትም ጊዜ
ተጠቅሷል (ሕዝቅኤለ 2፡-3)። ሆኖም ግን በኢየሱስ ደም በእግዚአብሔር ላይ
ያለ አመጽ ተደምስሷል እና ሰብአዊ ዘሮች ከቀራኒዮ የሚፈሰውን መልካምን ስራ
ታድለዋል።
2.‹‹ሐጢያትን ይፈጽም›› ግሱ ‹‹ለማተም ›› የሚል ትርጉምን ይዟል እናም
ሐጢያት ይቅር ይባላል። ከውድቀት ጀምሮ የወደቀው ሰው በእግዚአብሔር ልኬት
መኖር አልቻለም፣ ነገር ግን መሲሁ ለወድቀታችን መፍትሔን ያበጅለታል።
3.‹‹በደልን ያስተሰርይ›› ጳውሎስ እንዳለው ‹‹እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ
እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት
ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። ›› (ቆላስያስ 1፡-19፣ 20)። በዚህም
እንዲሁ ይህንን እውነታ ሊያመጣ የሚችል፣ ኢየሱስ ብቻ ነው ።
4.‹‹የዘለአለምን ጽድቅ ያገባ ›› ክርስቶስ በመስቀል የእኛን ቦታ ወሰደ
ከእግዚአብሔር ጋር ‹‹ትክክል መሆንን ›› በእኛ ላይ አኖረ። ይህንን ከእግዚአብሔር
የሚመጣውን ጽድቅ መቀበል የምንችለው በእምነት ብቻ ነው ።
5.‹‹ራዕይንና ትንቢትን ያትም ›› ክርስቶስ በመስዋዕት እራሱን ሲሰጥ፣ ወደ
እርሱ ያመላክቱ የነበሩ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች የእርሱ የስርየት ስራ እንደተፈጸመ
በመገንዘብ ተዘጉ።
6.‹‹ቅዱሰ ቅዱሳኑን ይቀባ ዘንድ›› ቅዱሰ ቅዱሳን ተብሎ እዚህ ላይ የተጠቀሰው
ሰው /ግለሰብ ሳይሆን ስፍራ ነው። ስለዚህ ይህ አነጋገር የሚያመላክተው በሰማያዊው
ስፍራ የክርስቶስን የማማለድ አገልግሎት መጀመሩን ነው ( ዕብራውያን 8፡-1)።
በ2300 ማታና እና ጠዋት ራዕይ ነብዩ በጣም ተገርሟል ምክንያቱም ሊያስተውለው
አልቻለም (ዳንኤል 8፡-27)። ከአስር አመት በኋላ ራዕዩን ያስተውል ዘንድ መልአኩ
ገብርኤል (ዳንኤል 9፡-23 ) መጣ። ይሄ ኋላ የመጣ ራዕይ የጎደለውን መረጃ ሰጠ፣
እናም የመሲህን ስራ በሰባኛው ሳምንት ፍጻሜ ላይ እንደሚደርስ ገለጸ። እናም አንድ
አመት - አንድ ቀን መርህ እና የኩነቶቹ አካሔድ እንደተተነበየው ሰባ ሳምንታት 490
አመታት እንደሆኑ ይስተዋላል። እናም የዚህ ጊዜ መጀመሪያ የኢየሩሳሌም እንደገና
መታደስ አዋጅ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው(ዳንኤል 9፡-25)።
ይህ ትእዛዝ የታወጀው
በንጉስ አርጤክስስ በ 457ቅ.ዓ ነው። በዕዝራ መሪነት እየሩሳሌም መልሰው እንዲገቡ
እና እንዲገነቡ አይሁዶችን ፈቅዶላቸዋል (ዕዝራ 7)። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሰባው
ሳምንት ‹‹ተወስኗል›› ወይም ‹‹ተቆርጧል›› ። ይህ የሚጠቁመው 490ዓመታት
ከትልቁ ጊዜ ላይ የተቆረጠ እንደሆነ ነው። ያም ማለት በዳንኤል 8 ከተጠቀሰው
የ 2300 አመታት ላይ ማለት ነው። ከዚህም ተከትሎ 2300 አመታት እና 490
አመታት ተመሳሳይ መነሻ አላቸው ፣ ያም 457ቅ.ዓ ላይ ማለት ነው።
የሰባው ሳምንታት ትንቢት በሶስት ክፍሎች ይከፈላል፣ ሰባት ሳምንት፣ ስልሳ ሁለት
ሳምንት እና ሰባኛው ሳምንት ናቸው።
ሰባቱ ሳምንታት(49አመታት) ምን አልባት ሊወክል የሚችለው እየሩሳሌም እንደገና
ልትታደስ ያለችበትን ሰዓት ነው። ከእነዚህ ሰባት ሳምንታት በኋላ፣ ስልሳ ሁለቱ
ሳምንታት (434አመታት) ወደ ‹‹መሲሁ አለቃ ›› (ዳንኤል 9፡-25 ) ይመሩናል።
ከአርጤክስስ አዋጅ በኋላ ከመጡት ከእነዚያ 434አመታት በ27ዓ.ም መሲሁ
ኢየሱስ ተጠመቀ እናም በመንፈስ ቅዱስ ለመምጣቱ አገልግሎት ተቀባ።
በሰባኛው አመት ሌላ በጣም አንገብጋቢ ኩነት ተከናወነ። (1) ‹‹መሢሕ ይገደላል
›› (ዳንኤል 9፡-26)፣ ይህ የሚያመላክተው የክርስቶስን ሞት ነው። (2) መሲሁ ‹‹
ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል›› (ዳንኤል 9፡-27) ይህ
ለአይሁድ ሕዝብ ልዩ የኢየሱስ እና የሐዋሪያው ጳውሎስ አገልግሎት ነው። ይህ
በመጨረሻው ሳምንት ተከናውኗል ከ 27ዓ.ም እስከ 34ዓ.ም ። (3) ‹‹በሱባዔውም
እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል ››(ዳንኤል 9፡-27)።
ከጥምቀቱ ሶስት
አመት ተኩል (በሳምንቱ መካከል ማለት ነው) እራሱን በአዲሱ ኪዳን ፍጹም
መስዋዕት በማድረግ እና በማቅረብ ኢየሱስ የመስዋዕት ስርዓቱን ወደ ፍጻሜ አመጣ፣
ስለዚህም የእንስሳትን መስዋዕት አስፈላጊነትን አስወገደ። እስጢፋኖስ በተወገረ
እና ወንጌል አይሁድን ብቻ ሳይሆን አሕዛብንም መድረስ በጀመረበት ጊዜ የሰባው
ሳምንት የመጨረሻው ሳምንት ትንቢት በ34ዓ.ም አለቀ፣።
ዳንኤል 9፡-24-27ን ያንብቡ። በታላቁ ተስፋ እና በመሲሁ የተስፋ ቃል
መካከልም እንኳን ስለ አመጽ፣ ጦርነት ፣ሐዘን እናነባለን። በሕይወት ስጋትስ
መካከልም እንኳን ተስፋ አሁንም እንዳለ እርግጠኛ እንድንሆን የሚረዳን
እንዴት ነው?
ከዚህ ቀጥሎ የዳንኤል 9፡-24-27 የ70 ሳምንት ትንቢት
እንዴት የ 2300 አመታት ትንቢት አጀማመርን እንደሚሰራ እና እንዴት ደግሞ
እንደተሳሰረ የሚያሳይ ስዕላዊ መግለጫ አለ። 2300አመታን ከ 457ቅ. ዓ ጀምሮ
መቁጠር ቢጀምሩ (ዜሮ አመትን ማስወገድን አስታውሱ) 1844ን ያገኛሉ፣ ወይም
ከ 34ዓ፣ም ጀምሮ 1810 አመታትን ቢቆጥሩ እንዲሁ 1844 ላይ ይደርሳሉ። ስለዚህ
የቤተ-መቅደሱ መንጻት በዳንኤል 8፡-14 በ1844ዓ.ም እንደጀመረ ማየት ይቻላል።
እንዲሁ ልብ ይበሉ፣ የ1844 ቀን በዳንኤል 7 እና 8 ካየነው ጋርም ይገጥማል። ያም
ማለት በዳንኤል 7 ያለው ፍርድ ፣ በዳንኤል 8 ደግሞ የቤተ መቅደሱ መንጻት ጋራ
አንድ አይነት ነው (ያለፉትን ሁለት ሳምንታት ጥናት ይመልከቱ) የሚሆነው (ዳንኤል
7፡25)፣ እንዲሁ ከክርስቶስ ዳግም ምጻት እና የእግዚአብሔር ዘለአለማዊ መንግስት
ከመመስረቷ በፊት ከ 1260 አመታት ግድያ በኋላ ነው።
1.ምሁራን የ2300 ቀናት ትንቢት እና የ70 ሳምንታት ትንቢት በእውነት
አንድ ናቸው ይላሉ፣ ትክክል ነው። ለምንድን ነው ይህንን የሚሉት?
ይህንን አባባል ለመደገፍ ምን አይነት ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ?
2.ሕይወታችንን ሊረዳን ከሚችለው የዳንኤል የምልጃ ጸሎት ለእራሳችን
ምን እንማራለን?
3.በእኛ ፈንታ መስዋዕት የሆነው ክርስቶስ ብቸኛ ተስፋችን ነው።
ይህ እርዳት ትሁት እንድንሆን ፣ በበለጠ ዋናው ነገር ደግሞ ሌሎችን
በተለየ እንድንወድ እና ይቅር እንድንል እንዴት ሊረዳን ይችላል?
ሉቃስ 7፡-40-47 ለሁላችን ሊለን የሚችለው ምንድን ነው?
4.መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለዳንኤል ጸሎት ተስፋ ምን ያህል ማዕከላዊ
እንደሆነ ይመልከቱ። ከሁሉም በላይ ሕዝቡ አረመኔአዊ በሆነ መንገድ
ተሸንፏል፣ ሕዝቡ ተሰዷል፣ ምድራቸው ጠፍቷል፣ እናም ዋና
ከተማቸውም ጠፍቷል። ከዚህ ሁሉ በኋለም ግን ሕዝቡ ወደ ሐገራቸው
እንሚመለሱ እርሱ ተስፋ አለው። ይህንን ተስፋ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና
በውስጡ ከተጻፈው የተስፋ ቃል ካልሆነ ከየት ሊያገኘው ይችላል?
እኛም እንዲሁ በቃሉ ካለው የቃል ኪዳን ተስፋ ልናገኝ ስለምንችለው
ተስፋ ምንድንነው ሊለን የሚገባው?