ትንቢተ ዳንኤል
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 1ኛ ሩብ ዓመት 2020

ከታህሣሥ 18 - 24

1ኛ ትምህርት

Dec 28 - Jan 3



ከማንበብ ወደ መረዳት



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ሉቃስ 24፡ 25-27፣ 2ኛ ጴጥሮስ፡- 3፡ 11-13፣ ዮናስ 3፡-3-10፣ ዘሌዋውያን 14፡- 34፣ ዳንኤል 9፡-23፣ 10፡ -11፣12


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- ‹‹ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና። በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን? አለው። ›› (ሐዋ 8፡-30)

ቤ ተክርስቲያናችን የተወለደችው የዚህ ሩብ አመት ጥናታችን በሆነው በዳንኤል መጽሐፍ ገጾች ውስጥ ነው። ስንጀምር፣ የሚከተሉት ነጥቦች በጥናታችን እንዲረዱን እንደ የማጥኛ መምሪያ በአእምሯችን ልንይዛቸው ይገባል። አንደኛ፣ ሁሉጊዜ ልናስታውሰው የሚገባው ክርስቶስ ልክ እንደ አጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ማዕከልነቱ ሁሉ በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥም ማዕከል መሆኑን ነው። ሁለተኛ፣ የዳንኤል መጽሐፍ የስነ-ጽሑፍን ውበት እንዳሳየ እና ዋናውን የትኩረት ነጥቡን እንድናስታውል እንደረዳን ነው።

ሶስተኛ፣ በጥንት የሮማ እና የግሪክ ትንቢታዊ ጥናት፣ እና አፖካሊፕቲክ ትንቢት መካከል ያለውን ማስተዋል ይኖርብናል። ይህ ደግሞ በዳንኤል ትንቢት እና በሌሎች እንደነ ኢሳያስ፣ አሞጽ እና ኤርሚያስ ባሉት መካከል ያለውን ትንቢት እንድንለይ ይረዳናል።

አራተኛ፣ የዳንኤልን ትንቢታዊ ጊዜን ስናጠና የትንቢቱ አካሄድ እረዥም ጊዜን የያዘ እና የሚለካውም በአንድ አመት-አንድ ቀን መለኪያ እንደሆነ ልናስተውል ይገባል። አምስተኛ፣ የዳንኤል መጽሐፍ ትንቢታዊ መረጃዎችን ብቻ ሳይሆን የሚያሳየው፣ ነገር ግን ዛሬም ለግል ሕይወታችን ረብ የሆነ መሠረት እንዳለው ልናጎላው ይገባል። ለታህሣሥ 25 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።

ታህሣሥ 19
Dec 29

ክርስቶስ፣ የዳንኤል መጽሐፍ ማዕከል


ሉቃስ 24፡-25-27፣ ዮሐንስ 5፡-39፣ እና 2ኛ ቆሮንቶስ 1፡-19፣20ን ያንብቡ። ክርስቶስ የጥቅሱ ማዕከል የሆነው በምን በምን መንገዶች ነው?



ኢየሱስ የጥቅሶቹ ማዕከል ስለመሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፣ ይህ ደግሞ የዳንኤል መጽሐፍን ያጠቃልላል። ለምሳሌ፣ ምዕራፍ 1 እንደሚያሳየው ፣ ምንም እንኳን በተወሰነ እና ፍጹም ባልሆነም መንገድ ቢሆንም የዳንኤል ልምምድ፣ በዚህ ሐጥያተኛ ምድር ለመኖር ሰማይን እንደለቀቀ እና የጨለማን ሐይላት እንተጋፈጠው ልክ እንደ ክርስቶስ ሕይወት ተመሳሳይ ነበር ። ከሁሉም በላይ ዳንኤል እና ጓደኞቹ ልክ የክርስቶስን በመሰለ ጥበብ የባቢሎናውያንን ፈተና ለመጋፈጥ ታደሉ።

ምዕራፍ 2 የፍጻሜውን ጊዜ ምስልን ይገልጻል፣ የክርስቶስ አገዛዝ በመጨረሻ የአለምን አገዛዞች ሁሉ እንደሚለውጥ ይገልጻል። ምዕራፍ 3 ክርስቶስ ከታማኝ አገልጋዮቹ ጋር በእሳቱ ምድጃ ውስጥ ሲረማመድ የታየበት ነው ።

ምዕራፍ 4 እግዚአብሔር ንጉሱ ናቡከደነጾርን ከግዛቱ ያስወገደበት፣ ንጉሱ መገንዘብ የሚችልበትን ያህል ጊዜ የቆየበት እና ሰማይን እንሚያስተዳድር እግዚአብሔር ያሳየበት ነው( 4፡26)። ‹‹ሰማይ ይመራል/ይገዛል ›› የሚለው አባባል ልክ በዳንኤል 7 እንደተገለጸው ‹‹ የሰው ልጅ ›› (ዳንኤል 7፡13) ግዛትን እና አለቅነትን አንደተቀበለ ያሳያል ።

ምዕራፍ 5 የንጉስ ቤልሻጽር መንግስት በምሽት ፈንጠዝያ እና የውርደት ጊዜ መተላለፉን እና በባቢሎን መተካቱን ያሳያል። ይህ የሰይጣንን መሸነፍ እና በመጨረሻው ጊዜ በክርስቶስ እና በመልአኩ አማካኝነት የባቢሎንን ጥፋት የሚያመላክት ማስጠንቀቂያ ነበር።

ምዕራፍ 6 የሚያሳየው በሐሰት ክስ ዳንኤል የተከሰሰበትን እና ልክ በመጨረሻ በሊቀ ካህኑ በሐሰት ክስ በኢየሱስ ላይ የተመሰከረበትን ይመሳሰላል። ከሁሉም በላይ ንጉስ ዳሪዎስ ዳንኤልን ለማትረፍ ያልተሳካ ሙከራ እንዳደረገ ሁሉ ጲላጦስም ኢየሱስን ለማትረፍ ያልተሳካ ሙከራ አድርጎ ነበር( ማቴዎስ 27፡- 17-24)።

ምዕራፍ 7 ክርሰቶስ ልክ እንደ የሰው ልጅ መንግስትን ሲቀበል እና በሕዝቡ ላይ እንደሚነግስ ይገልጻል። ምዕራፍ 8 ክርስቶስን በሰማይ ባለው ቤተመቅደስ ውስጥ እንደ ካህን ያሳያል። ምዕራፍ 9 ክርስቶስን ሞቱ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ያለውን ቃልኪዳን እንደሚያድስ መስዋዕት አድርጎ ይስለዋል። እንዲሁም ምዕራፍ 10-12 ክርስቶስን እንደ ሚካኤል፣ የክፉ ሐይላትን የተዋጋ እና በድሉ ከሞት ኃይል ጭምር የእግዚአብሔር የሆኑትን እንዳዳነ የመልአክት አለቃ አድርጎ ያቀርበዋል።

ስለዚህ ክርስቶስ የዳንኤል መጽሐፍ ማዕከል እንደሆነ በአእምሯችን እንያዝ። እያንዳንዱ ምዕራፍ በሆነ ልምምድ ወይም ሐሳብ ወደ ክርስቶስ ያመላክታል። በተዘጋጁ ትግሎች ፣ በመከራ፣ ወይም በታላቅ ደስታ እና ብልጽግና ውስጥም እንኳ ክርስቶስን የሕይወታችን ማዕከል ማድረግን እንዴት ነው ልንማር የምንችለው? ይህን ማድረግ ለምንድን ነው በጣም አስፈላጊ የሚሆነው?

ታህሣሥ 20
Dec 30

የዳንኤል መጽሐፍ አወቃቀር


የዳንኤል መጽሐፍ የአረማይክ ክፍሉ አዘገጃጃት፣ ከ2-7 ያሉት ምዕራፎች( የዳንኤል መጽሐፍ የተወሰነው ክፍል በዕብራይስጥ ፣ ሌላው ክፍሉ ደግሞ በአረማይክ የተጻፈ ነው) የሚከተለውን አወቃቀር ያሳያሉ። የክፍሉን እና የመጽሐፉን ማዕከላዊ መልዕክቱን ያጠናክራል።

ሀ. የአራቱ መንግስታት፣ የናቡከደነጾዖር ሕልም( ዳንኤል 2) ለ. እግዚአብሔር የዳንኤል ጓደኞችን ከእሳት ውስጥ አዳናቸው ( ዳንኤል 3) ሐ. በናቡከደነጾዖር ላይ የተካሔድ ፍርድ( ዳንኤል 4) ሐ›.በቤልሻጽር ላይ የተካሔደ ፍርድ ( ዳንኤል 5) ለ›. እግዚአብሔር ዳንኤልን ከአንበሶች ጉድጓድ አዳነው ( ዳንአኤል 6) ሀ›. የአራቱ መንግስታት፣ የዳንኤል ሕልም( ዳንኤል 7) ይህ አይነት የስነ-ፅሁፍ አዘገጃጀት ዋናውን ነጥብ፣ በዚህ ውስጥ በ ሐ እና ሐ› ውስጥ ያሉትን ( ዳንኤል 4 እና 5) ማለት ነው፣ በአወቃቀሩ የመሀል ስፍራ ላይ ለማስቀመጥ ይረዳል። እግዚአብሔር የናቡከደነጾዖርን መንግስት (ለጊዜው) እና የቤልሻጽርን መንግስት ( ለዘለቄታው) አስወገደ። ስለዚህ ምዕራፍ 2-7 ትኩረት የሚሰጠው በምድር ላይ ባሉ መንግስታት፣ እንደሚያስነሳቸውና እንደሚሽራቸው፣ ባለው የእግዚአብሔር ሉአላዊነት ላይ ነው። አንድን መልዕክት ለማስረገጥ እና ነገሮችን ግልጽ ለማድረግ ካሉ መንገዶች መካከል ውጤታማው እና አመርቂው መንገድ መደጋገም ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር የግብጽን የቅርብ ጊዜ መጻኢ ሁኔታ የሚመላክቱ ሁለት ሕልሞችን ለንጉስ ፈርኦን ሰጥቶታል

(ዘፍጥ 41፡- 1-7)። በመጀመሪያው ሕልም ውስጥ ሰባት ወፋፍራም ላሞች በሰባት ቀጫጭን ላሞች ሲዋጡ አሳየው። በሁለተኛው ሕልም ውስጥ ደግሞ በሰባት አገዳዎች ላይ የነበሩ መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች፣ በሌሎች ሰባት መልካም ባልሆኑ አገዳዎች ላይ በነበሩ ሰባት እሸቶች ተዋጡ። ሁለቱም ህልሞች ሰባት የብልጽግና አመታት በሰባት የደረቅ አመታት እንደሚተኩ ተመሳሳይ ነጥብን ያስቀምጣሉ።

በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ድግግሞሽን ይጠቀማል። አራት የአጠቃላይ መሰረታዊ ውቅር የትንቢት ድግግሞሾች አሉ። በመጨረሻ ይህ አወቃቀር ዘለላማዊውን የእግዚአብሔርን ሉአላዊነት ያሳያል። ምንም እንኳን እያንዳንዱ ዋና ዋና ትንቢቶችን የሚያሳዩበት ልዩ ልዩ አቀራረብ ቢኖራቸውም በጋራ ግን ሁሉም ተመሳሳይ የታሪክ ወቅትን ያሳያሉ የሚከተለው ስዕል እንደሚያሳየው፣ ከነብዩ ዘመን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የሚደርስን ጊዜ ይሸፍናሉ።

ዳንኤል 2 ዳንኤል 7 ዳንኤል 8፣ 9 ዳንኤል 10-12
ባቢሎን ባቢሎን
ሜዶ ፋርስ ሜዶ ፋርስ ሜዶ ፋርስ ሜዶ ፋርስ
ግሪክ ግሪክ ግሪክ ግሪክ
ሮም ሮም ሮም ሮም
የእግዚአብሔር መንግስት ትመሰረታለች የሰማይ ፍርድ ወደ አዲስ ምድር ይመራል የቤተ-መቅደሱ መንጻት ሚካኤል ይቆማል


ከረዥሙ ጊዜ ምልከታችን ወይም ተስፋችን አንጻር እነዚህ ጥቅሶች ምን ታላቅን ተስፋ ያቀርባሉ? ዳንኤል 2፡-44፣ መዝሙር 9፡-7-12፣ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡-11-13

ታህሣሥ 21
Dec 31

በዳንኤል መጽሐፍ የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች


በዳንኤል መጽሐፍ ተመዝግቦ የሚገኘው ትንቢታዊ ራዕይ በሌሎች የብሉይ ኪዳን ነብያት ከተላለፉት ሌሎች ትንቢታዊ መልዕክቶች የተለየ ነገር አለው። የዳንኤል ትንቢቶች በአለም የመጨረሻ ጊዜ ዙሪያ ከተተነበዩ ትንቢቶች ጎራ ይመደባል፣ ሌሎች አብዛኞቹ ደግሞ የጥንት ትንቢቶች ጎራ ውስጥ ይመደባሉ። የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶችን ለመረዳት በእነዚህ የትንቢታዊ ጽሑፍ አፃፃፍ ዘዬዎች መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች ከሌሎች የጥንት ትንቢቶች የሚለዩአቸው የተወሰኑ ነጥቦች አሉ።

ራዕይ እና ህልም፣ በየአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች ውስጥ እግዚአብሔር ነብያትን በደንብ ለማስጨበጥ ሕልምንና ራዕይን ይጠቀማል። በሌሎቹ የጥንታዊ ትንቢቶች ግን ነቢያት ‹‹የጌታን ቃል ›› ይቀበላሉ፣ ራዕይዎችም ሊኖሯቸው ይችላል። ይህም በጥንታዊ ትንቢቶች ውስጥ በተወሰነ ልዩነት ወደ 1600 ጊዜ ተከስቷል። ከዚህም ከዚያም የተውጣጡ ምስሎች - በጥንታዊ ትንቢቶች ውስጥ ውስን የሆኑ ምስሎች ሲኖሩ እነሱም በእውኑ አለም ያሉ ናቸው። የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች ውስጥ እግዚአብሔር ምስሎች ያሳያል፣ ከሰብአዊው አለም በላይ የሆኑ ሐሳባዊ ምስሎችን፣ ለምሳሌ ከተለያዩ እንስሳት የተውጣጡ ወይም ክንፍ እና ቀንድ ያላቸው የሚያስፈሩ እንስሳትን ያሳያል።

የመለኮት ሉአላዊነት እና በሁኔታዎች አለመገደብ- ጥንታዊ ትንቢቶች ብዙ ጊዜ ተፈጻሚነታቸው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በገባው ቃልኪዳን አውድ አንጻር አንደ ሰዎች ምላሽ ሲሆን የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች ግን በተቃራኒው በሁኔታ የተገደቡ አይደሉም። የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች እግዚአብሔር ከዳንኤል ዘመን እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለውን የመንግስታት መነሳትን እና መውደቅን ያመላከተባቸው ናቸው። እንደዚህ አይነት ትንቢቶች በእግዚአብሔር የወደፊቱን አዋቂነት እና ሉአላዊነት ላይ የሚያርፉ ሲሆን የሚፈጸሙትም ከሰዎች ምርጫ ጋር በተያያዘ አይደለም። ዮናስ 3፡-3-10 ን ያንብቡ። ይህ ጥንታዊ ወይንስ የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢት ነው? ለምላሽዎት ማስረጃ ያቅርቡ። ዳንኤል 7፡-6 ስ ?



አንደ ጥንታዊ እና የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች ሰፊ የትንቢት ስነ-ጽሑፋዊ ዘዬዎችን ማወቁ ታላቅ ጥቅምን ሊያስገኝ ይችላል። በመጀመሪያ፣ ይህ የስነጽሑፋዊ ዘዬ እግዚአብሔር ትንቢታዊ እውነቶችን ለማድረስ የተለያዩ አቀራረቦችን እንደሚጠቀም ያሳያል ( ዕብ 1፡-1) ። ሁለተኛ፣ እንዲህ አይነት እውቀት በተሻለ ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ ውስብስብነትን እና ውበትን እንድናደንቅ ይረዳናል። ሶስተኛ፣ ይህ እውቀት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶችን ከአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ጋር የማይጋጭ ትንታኔን እንድንሰጥ እና በትክክል ‹‹ የእውነትን ቃል ›› (2ኛ ጢሞ 2፡15) መግለጽ አንድንችል ይረዳናል።

በሆሴ 3፡-4፣5፣ አሞጽ 8፡-11፣ እና ዘካ 9፡-1 ላይ ባሉ ጥቅሶች ላይ በመመስረት አንዳንድ ክርስቲያኖች ዛሬ የመጨረሻው የአለማችን ታረክ ኩነቶች የሚሆኑት በመካከለኛው ምስራቅ ነው ይላሉ። የዚህ ትንታኔ ችግር / ስህተት ምንድን ነው? ይህን ጉዳይ ለመግለጽ በጥንታዊ እና የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ እንዴት ነው ሊረዳ የሚችል?

ታህሣሥ 22
Jan 01

የእግዚአብሔር የጊዜ መለኪያ


የዳንኤልን መጽሐፍ ስናጠና ሌላው በአእምሯችን ልንይዘው የሚያስፈልገን የአለም መጻኢ ሁኔታን አመላካች ትንቢቶች የታሪካዊ አቀራረበን/ምልከታን ነው። ይህ አቀራረብ ሒስቶሪሲዚም (ማህበራዊ እና ባህላዊ ክንዋኔዎች በታሪክ ላይ ይመሰረታሉ ብሎ የሚያምን አስተሳሰብ ነው) በመባል ይታወቃል። በተጻራሪው ካሉ አመለካከቶች፣ ፕሪተሪዚም፣ ፊውቸሪዝም፣ እና አይዲያሊዝም ጋር ቢነጻጸር ይበልጥ ሊስተዋል ይችላል።

ፕሪቴሪዚም በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡት ትንቢቶችን ባለፈው ጊዜ ውስጥ እንደተፈጸሙ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያ አለው። ፊውቸሪዚም ደግሞ እነዚህኑ ትንቢቶች ገና ወደ ፊት ይፈጸማሉ ብሎ ይወስዳል። አይዲያሊዝም በተራው ደግሞ የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች፣ ያለምንም የተወሰነ ታሪካዊ ነገር የአጠቃላይ መንፈሳዊ እውነታ ምልክቶች ናቸው ይላል።

ሒስቶሪሲዝም በተቃራኒው የአለም መጨረሻ ጊዜ ትንቢቶች ውስጥ እግዚአብሔር ከነብዩ ዘመን እስከ ፍጸሜ ዘመን ድረስ ያለውን የታሪክ ፍሰት ያለምንም የታሪክ መቆራረጥ የሚገልጽ ነው ይላል። የዳንኤል መጽሐፍን ስናጠና እያንዳንዱ ዋና ዋና ራዕይ በመጽሐፉ ውስጥ (ዳንኤል 2፣7፣8፣11) ከተለያየ እይታ እና ከአዳዲስ ዝርዝሮች ጋር ይህን የታሪክን ፍሰት ይደጋግማል። የአድቬንቲስት ፈር ቀዳጆች፣ ኤለን ጂ ኋይትን ጨምሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የዳንኤል ትንቢቶች አና መገለጥን የሚገነዘቡት ከሒስቶሪሲዚም (ማህበራዊ እና ባህላዊ ክዋኔዎች በታሪክ ላይ ይመሰረታሉ ብሎ የሚያምነውን አስተሳሰብ ነው) ከሚለው እይታ አንጻር ነው። ዘኁልቁ 14፡-34 እና ሕዝቅኤል 4፡-5፣ 6ን ያንብቡ። በትንቢታዊ ቋንቋ ብዙ ጊዜ ‹‹ ቀን›› የሚወክለው ምንን ነው?

ዳንኤል መጽሐፍን ስናጠና ትንቢታዊ ጊዜ የሚለካው በአንድ አመት-አንድ ቀን የመለኪያ መርህ ነው። ይህም ማለት በትንቢት ብዙውን ጊዜ አንድ ቀን በትክክለኛው ጊዜ ካለ አንድ አመት ጋር እኩል ነው። ስለዚህም ለምሳሌ የ2300ማታ እና ጠዋት ትንቢት 2300 አመታት እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል (ዳንኤል 8፡-14)። በተመሳሳይ መንገድ የ70ሳምንት ትንቢት 490አመታት እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል ( ዳንኤል 9፡-24-27)።

ይህ የጊዜ መለኪያ ግልጽ በሆኑ አንዳንድ ምክንያቶች ትክክል ነው። (1) ራዕዩ ምሳሌያዊ እንደሆነ የተጠቀሱት ሰዓቶችም ምሳሌያዊ ናቸው። (2) በራዕይ ውስጥ ያሉ ኩነቶች በጣም እረዥም ዘመንን የሚገልጹ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ‹‹የዘመኑ ፍጻሜ››፣ የጊዜው አካሔድ ከእነዚህ ጋር ያሉ ትንቢቶች እንደየአግባባቸው መተርጎም አለባችው። (3) የአንድ አመት-አንድ ቀን መርህ በዳንኤል መጽሐፍ ትክክል እንደሆነ ተረጋግጧል። ግልጽ የሆነው ምሳሌ ከንጉስ አርጤክስስ እስከ ኢየሱስ ዳግም ምጻት ድረስ ባለው 70 የትንቢት አመት ነው። ስለዚህ በጣም ግልጽ የሆነው እና ትክክለኛው የትንቢታዊ ወቅቶች ስሜት እንዲሰጡ በዳንኤል የተሰጡት ትንቢቶች የሚፈቱት አንድ አመት አንድ ቀን በሚለው መርህ ነው። ከእነዚህ አንዳንዶቹ የጊዜ ትንቢቶች መቶዎችን ፣ ሌሎች ደግሞ አንድ ሺህ አመታትን ይሸፍናሉ። ይህ ስለ ጽናት ምንድን ነው ሊያስተምረን የሚችለው?

ታህሣሥ 23
Jan 02

የዳንኤል መጽሐፍ ወቅታዊ ፋይዳ


ምንም እንኳን ከ 2500 አመታት በፊት ቢጻፍም፣ የዳንኤል መጽሐፍ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላለው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠለቅ ያለው አስፈላጊነቱ እንዳለ ነው። የዳንኤል መጽሐፍ በሶስት ቦታዎች/መንገዶች ለእኛ አስፈላጊ እንደሆነ መመልከት እንችላለን። እግዚአብሔር በሕይወታችን ላይ ሉአላዊ እንደሆነ አለ። ነገሮች መልካም ባይሆኑም እንኳን እግዚአብሔር ሉአላዊ/ሐያል እንደሆነ አለ፣ እናም ለሰዎች ልጆች መሻት እንዲሁም ለልጆቹ መልካም የሆነውን እና የተሻለውን ለማድረግ በስራ ላይ ነው። በባቢሎን የነበረው የዳንኤል ልምምድ ልክ ዮሴፍ በግብጽ፣ አስቴር ደግሞ በፋርስ ውስጥ ከነበራቸው ልምምድ ጋር ይመሳሰላል።

እነዚህ ሶስት ወጣቶች በባዕድ ሐገር በምርኮ ተይዘው ነበር፣ በአሕዛብ ነገስታት የከፋ ጭቆና ውስጥ ነበሩ። ነገሩን እንዲሁ ለሚመለከተው ደካሞች እና እግዚአብሔር የተዋቸው ይመስላሉ። ቢሆንም ግን ጌታ አበረታቸው እንዲሁም ኃይል በተሞላ መንገድ ተጠቀመባቸው። መከራ፣ ስቃይ እና ተቃውሞ ሲደርስብን ዘወር ብለን እግዚአብሔር ለዳንኤል፣ ለዮሴፍ፣ እና ለአስቴር ያደረገውን መመልከት እንችላለን። እግዚአብሔር በዚህም ውስጥ እንኳን ማረፊያችን እንደሆነ ልናረጋግጥ እንችላለን። እንዲሁም መከራችን እና ፈተናችን እንኳ ሊያስተወን ቢፈትነንም እንኳን እርሱ ግን አይተወንም።

እግዚአብሔር የታሪክን ፍሰት ይዘውራል/ይቆጣጠራል። በሐጢያት እና በክፋት በተሞላው፣ እና አላማ የለሽ ሆኖ ግራ በተጋባው አለም የፍርሃት ስሜት ቢሰማንም የዳንኤል መጽሐፍ መልዕክት ግን እግዚአብሔር ተቆጣጥሮት እንዳለ ያሳየናል። በእያንዳንዱ የዳንኤል መጽሐፍ ምዕራፍ ውስጥ እያስተጋባው ያለው ሐሳብ እግዚአብሔር የታሪክን ፍሰት እንደሚቆጣጠር ነው። ኤለን ጂ ኋይት ‹‹ በሰው ልጆች ታሪክ ዘገባ ውስጥ የሕዝቦች እድገት፣ የነገስታት መነሳት እና መውደቅ፣ በሰው ልጆች ኃይል እና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ይመስላል። የነገሮች ቅርጽ፣ በከፍተኛ ሁኔታ በሰው ልጅ ኃይል፣ ጥልቅ ፍላጎት፣ ወይም ምክንያት የሚወሰን ይመስላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት መጋረጃው ሲነሳ፣ እነሆ ከጀርባ፣ ከላይ እና በሁሉ ውስጥ የእያንዳንዱ ሰብአዊ ዘር ፍላጎት እና ኃይል እንዲሁም የውስጥ ፍላጎት አካሔድ እና ምላሹ ሁሉ የምህረት ባለቤት በሆነው በጸጥታ እና በትእግስት በእርሱ ፈቃድ እና ምክር እየተከናወነ ነው። ›› ( ስነ-ትምህርት፣ ገጽ 173 ) ትላለች። እግዚአብሔር ያቀረበው ለፍጻሜ ዘመን ሰዎቹ አርአያ የሚሆኑትን ነው። ዳንኤል እና ጓደኞቹ ንጽረተ አለም እይታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ላለች ሕይወት እንደ አርአያ ሊያገልግሉ ይችላሉ። እምነታቸውን ለድርድር እንዲያቀርቡ ግፊት ሲደርስባቸው፣ ለጌታ ያላቸውን ቃልኪዳን በሚያስተው መልኩ የባቢሎናውያንን ስርአት እንዲያምኑ ግፊት ሲደርስባቸው፣ እነርሱ ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታምነው ቆሙ።

ለጌታ በመታመን እና ሙሉ ለሙሉ በመሰጠታቸው የመጣባቸው ተቃውሞ ስለ ወንጌል ስደትም እንኳን ሲደርስብን መጽናናትን ይሰጠናል። በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ ዳንኤል፣ ለጌታ ታማኝ እንደሆኑም እንኳን ላሉበት መንግስት እና ማህበረሰብ አስተዋዕጾ ማድረግ እንሚቻል የሳየናል። ዳንኤል 9፡-23፣ ዳንኤል 10፡-11፣12 እና ማቴዎስ 10፡-2931ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በግል የህይወት ትግላችን ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ፍላጎት/ መሻት ምን ይናገራሉ?

ታህሣሥ 24
Jan 03


ተጨማሪ ሐሳብ


‹‹ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከፈጣሪያቸው መሻት ጋር መግባባትን ለሚሹ ሁሉ እንደ መመሪያ እንዲሆን የተቀረጸ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተረጋገጠ ትንቢትን ሰጥቷል። መላዕክቶች እንዲሁም ክርስቶስ እራሱ ለዳንኤል እና ለዮሐንስ ነገሮቹ በአጭር ጊዜ ተፈጽመው እንሚያልፉ እንዲያውቁ መጥተዋል። ከድነታችን ጋር የተገናኙ በጣም አስፈላጊ ጉዳዮች ሚስጢራዊ እንዲሆኑ አልተተዉም። በታማኝነት እውነትን ለሚሹ አደናጋሪ እና አሳሳች ሆነው አልተገለጹም። ጌታ በነብዩ እንባቆም ‹‹እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።›› (እንባቆም 2፡-2) ይላል። በጸሎት ሕይወት ለሚያጠናው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል የተገለጠ ነው። እያንዳንዷ ለእውነት ታማኝ የሆነች ነፍስ ወደ እውነት ብርሃን ትመጣለች። ‹‹ ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ። ›› ( መዝሙር 97፡-11) እናም ልክ እንደተሰወረ መዝገብ እውነትን የሚፈልጉ አባላት ካልኖሩት በቀር፣ በቅድስና የትኛውም ቤተክርስቲያን ሊያድግ አይችልም። ›› (ኤል ጂ ኋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 521፣522) ‹‹የዳንኤልን እና የጓደኞቹን ታሪክ አጥኑ። በነበሩበት ቦታ ቢኖሩም እንኳን እራሳቸውን እንዲጥሉ በሁሉም አቅጣጫ ቢፈተኑም በየዕለቱ ሕይወታቸው ግን እግዚአብሔርን አከበሩ። ክፉን ሁሉ ለማስወገድ ወሰኑ። በጠላት መንገድ እራሳቸውን ላለማስቀመጥ እምቢ አሉ። እናም እግዚአብሔር ለጸናው ታማኝነታቸው በብዙ በረከቶቹ ባረካቸው ። ›› ( ማኑስክሪፕተ ሪሊዝ [ቁ. 224], ቅጽ.4 (ኤለን ጂ. ኢስቴት, 1990), ገጽ. 169,170)


የመወያያ ጥያቄዎች




1.የዳንኤልን መጽሐፍ ስናጠና አንድ በጣም ሐይለኛ ነጥብ እናገኛለን። እግዚአብሔር በነገስታት ላይ ብቻ ሐያል ሳይሆን ነገር ግን በጠለቀው ውስጠታችን ጭምር እያንዳንዳችንን በቅርበት ያውቀናል፣ ። ለምሳሌ በዳንኤል ምዕራፍ 2 እንደምናየው፣ ለአሕዛቡ ንጉስ እንኳን ሕልምን መስጠት ችሏል። አንድ ሰው ተኝቶ ሳል በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ መግባት እና ሕልምን ማስቀመጥ፣ መረዳት የማንችለው አይነት ቅርበት ነው። እንዲሁ ደግሞ እንደምንመለከተው የሕልሙ ይዘት፣ እግዚአብሔር የአለምን ሰፊ ግዛት በቁጥጥሩ ስር እንዳደረገ እና እንዴት ደግሞ እያንዳንዱን ነገር ወደ ፍጻሜ እንደሚመጣ ማወቁን ያሳያል። ከዚህ ስዕላዊ እውነታ ምን አይነት ምቾትን እና ተስፋን እንወስዳለን? በተመሳሳይ ሰዓት ጌታ የውስጥ ሐሳባችሁን ለማወቅ ቅርብ ስለመሆኑ ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል? በዚህ አውድ ለምንድን ነው የመስቀሉ ቃል ኪዳን በጣም አስፈላጊ የሚሆው?

2.በውይይት ቡድናችሁ ውስጥ በክላሲካል እና በአፖካሊፕቲክ (የአለም መጻኢ ሁኔታን አመላካች ትንቢቶች) ትንቢት መካካል ስላለው ልዩነት ተወያዩ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሁለቱ አይነት ትንቢቶች ሌላ ምን ምሳሌዎችን ልታገኙ ትችለላችሁ?