ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኤፌ. 5:2327፣ ማቴ. 20:25-28፣ ቲቶ 1:9፣ ማቴ. 16:19፣ ገላ. 6:1-2፣ ማቴ. 28:18-20፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ :-- “ ‘በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፡፡ ከእናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን፤ የበላይ ለመሆን የሚሻም የእናንተ የበታች ይሁን፡፡’ ” (ማቴ. 20፡26-27)፡፡
እ
ንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን የሱስ ለሰብዓዊው ዘር የፈጸመውን
በማመን ብቻ እንድናለን በሚለው እምነታችን ፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ነን፡
፡ ክርስቶስ ለእኛ ያደረገውን ለመቀበልና ተጠቃሚ ለመሆን ቤተ ክርስቲያን
ወይም የቤተ ክርስቲያን መዋቅር አያስፈልገንም፡፡ በእኛ ምትክ በመስቀል ላይ እንደ
መሞቱና የሰማያዊው መቅደስ ሊቀ ካኅናትነቱ--ከክርስቶስ የምናገኘውን በቀጥታ
ከእርሱ እንቀበላለን፡፡
ሆኖም ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረችው በእግዚአብሔር ነው፡፡ እንደ መዳኛ ሳይሆን-ደኅንነትን ለዓለም የምንገልጽባትና የምናሳይባት መሣሪያ አድርጎ ስለ እኛ በመካከላችን
አኖራት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ለዓለም እንድታሰራጭ የሱስ የፈጠራት ድርጅት
ናት፡፡ ድርጅት የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ እንዲጠናከር የሚፈቅድና የሚያመቻች እንደ
መሆኑ አስፈላጊ ነው፡፡ የየሱስ አዳኝ መልእክት ያለ ቤተ ክርስቲያን ድርጅት ውጤታማ
ሆኖ ከሌሎች ጋር አግባብ መፍጠር አይችልም፡፡ የየሱስን ምሳሌ በአርአያነት እያሳዩ
አንድነት እንዲበረታታና እንዲስፋፋ የሚሠሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም እንዲሁ
አስፈላጊ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ድርጅት ተልዕኮና አንድነት እንዲበረታታ
ለማድረግ ወሳኝ የሆነበትን ምክንያት በዚህ ሣምንት እንመለከታለን፡፡
ቀደም ባለው ትምህርት እንደ ተመለከትነው የአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን
በምሳሌያዊ አካል ተወክላለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፡፡ ይህ ምሳሌያዊ
አነጋገር አያሌ የቤተ ክርስቲያን ገጽታዎችን እንዲሁም በክርስቶስና በሕዝቡ መካከል
ያለውን ግንኙነት ይጠቅሳል፡፡ እንደ ክርስቶስ አካልነቷ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና
የተመሰረተው በእርሱ ላይ ነው፡፡ እርሱ የቤተ ክርስቲያን ራስ (ቆለ. 1፡18፣ ኤፌ. 1፡22)
እና የሕይወቷ ምንጭ ነው፡፡
ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን እምነትና አስተምህሮ ምንጭ ብሎም ጠንሳሽ እንደመሆኑ
አንድነቷን የምታገኘው ከእርሱ ነው፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ አስተምህሮዎች አንገብጋቢ
የማንነቷ መገለጫዎች ቢሆኑም ቤተ ክርስቲያን ከዚያም በላይ ናት፡፡ የቤተ ክርስቲያንን
ማንነት የሚወስነው በክርስቶስና በመጽሐፍ ቅዱስ በተገለጠው ሕያው ቃል ነው፡
፡ በዚህ የተነሳ ቤተ ክርስቲያን ማንነቷን እና ትርጉሟን ያገኘችው በእርሱ በክርስቶስ
ነው፡፡
በክርስቶስ እና በቤተ ክርስቲያኑ መካከል ያለው ግንኙነት ለባልና ሚስት ግንኙነት
ምሳሌ ሊሆን እንደሚገባ ጳውሎስ በኤፌ. 5፡23-27 ይናገራል፡፡ በክርስቶስና በቤተ
ክርስቲያኑ መካከል ያለው ግኙነት ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች ምንድን ናቸው?
ምንም እንኳ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ባለፉት ምዕተ ዓመታት ከሠሯቸው ከባድ
ስህተቶች አኳያ ራስን ማስገዛት የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ይህችን ቤተ ክርስቲያን ይገልጻል
የሚለውን አባባል ለመቀበል ብዙዎች ቢያመነቱም ነገር ግን ክርስቶስ ሁሌም የቤተ
ክርስቲያን ራስ--ቤተ ክርስቲያንም የእርሱ ተጠሪ ናት፡፡ ክርስቶስን እንደ ቤተ
ክርስቲያን ራስ መቀበላችን ታማኝነታችን ለማንም ሳይሆን ለራሱ ለጌታ መሆኑን
እንድናስታውስ ይረዳናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልትደራጅ የሚገባ ቢሆንም ነገር ግን
ሁሌም ቢሆን ይህ ድርጅት ለእውነተኛው የቤተ ክርስቲያን መሪ፤ ይኸውም ለየሱስ
ሥልጣን የተገዛ መሆን ይኖርበታል፡፡
“ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ መሰረቷ ስለሆነ በእርሱ ላይ ተገንብታለች፡፡ ራስዋም ስለሆነ
ትታዘዘዋለች፡፡ በሰው ላይ አትተማመንም፤ በሰው ቁጥጥር ሥርም አይደለችም፡፡ ብዙ
ሰዎች በቤተ ክርስቲያን የአደራ ሥልጣን ሲሰጣቸው ሌሎች ሰዎች ምን ማመንና ምን
ማድረግ እንዳለባቸው የማዘዝ ሥልጣን ያላቸው ይመስላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ይህን
ዓይነት ሥልጣን አይፈቅድም፡፡ አዳኛችን ‘ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ’ ነው
ያለው፡፡ ሁላችንም ለፈተና የተጋለጥን ስንሆን ስህተት መሥራታችን የማይቀር ነው፡
፡ ለመሪነት በማንም ውሱን ፍጡር ላይ መተማመን አንችልም፡፡ የእምነት ዋስትናው
የክርስቶስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ደካሞች በዚህ ጽኑ የእምነት
መሰረት ላይ መተማመን ይችላሉ፤ ብርቱ ነን ባዮች ግን የብርታታቸው መሰረት
ክርስቶስ እንዲሆን ካላደረጉ ደካሞች ይሆናሉ፡፡” (የዘመናት ምኞት ገጽ 426-427)፡፡
በክርስቶስ እንጂ በሌላ በማንኛውም አካል መመካት እንደሌለብን መማር
የምንችለው እንዴት ነው?
የሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በነበረው አገልግሎት በተደጋጋሚ ያይባቸው የነበረው
ክፉ የሥልጣን ቅናት ይረብሸው ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ብርቱ የየሱስ መሪዎች
የመሆን ስጋት ይታይባቸው ነበር (ማር. 9፡33-34፣ ሉቃ. 9፡46)፡፡ ደቀ መዛሙርት
የጌታ ራት አብረው ይበሉ በነበረት ወቅት እንኳ ይህ የበላይነት ስሜት ሳይሰማቸው
እንዳልቀረ መመልከት ይቻላል (ሉቃ. 22፡24)፡፡
የሱስ በአንድ ወቅት ለሕዝቡ በመንፈሳዊ መሪነት ስለሚሰጥ አገልግሎት የነበረውን
አስተሳሰብ በግልጽ አስቀምጦ ነበር፡፡ የሱስ በማቴ. 20፡25-28 ከሰጠው ልባዊ ምክር
ምን ዓይነት የመሪነት መርኅዎችን እንማራለን? ይህን መርኅ በሕይወታችን፣ በተለይ
በቤተ ክርስቲያናችን ገልጠን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
“የሱስ በዚህ እጥር ምጥን ያለ መልእክቱ ሁለቱን ዓይነት የመሪነት ምሳሌዎች
ያቀርብልናል፡፡ የመጀመሪያው የሮማውያንን አገዛዝን ጽንሰ ሀሳብ የተከተለ ነበር፡፡
በዚህ አሠራር ልሒቃን እንደ ሥልጣን ተዋረዳቸው የበላይ ይሆናሉ፡፡ የበታቾቻቸው
ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት ዓይነት የተገዢነት መንፈስ ይታዘዟቸዋል፡፡ በእነርሱ
ላይ ውሳኔ የመወሰን ሙሉ ሥልጣን አላቸው፡፡ የሱስ ‘በእናንተ መካከል ግን እንዲህ
መሆን የለበትም’ ሲል ይህን ዓይነቱን ገዢነት በግልጽ ተቃውሞአል፡፡ በዚህ ፋንታ
የሱስ እነርሱ ከለመዱት ውጪ የሆነውን በዓይነቱ አዲስና አስደማሚ የኃላፊነት
አርአያነትን በጥንቃቄ አቀረበላቸው፡፡”Darius Jankiewicz, “Serving Like Jesus:
Authority in God’s Church,” Adventist Review, March 13, 2014, p. 18.
የሱስ በዚህ ታሪክ ያቀረበው የሥልጣን ጽንሰ ሃሳብ በሁለት ቁልፍ ቃላት ላይ
የተመሰረተ ነው፡ አገልጋይ (ዲያኮኖስ) እና ባሪያ (ዱሎስ)፡፡ በአንዳንድ ትርጉሞች
የመጀመሪያው ቃል “የወንጌል አገልጋይ” በሚል ተደጋግሞ የቀረበ ሲሆን ሁለተኛውም
እንዲሁ “አገልጋይ” በሚል ይታወቃል፡፡ ሁለቱም ቃላት የሱስ ለማለት የፈለገውን
በሚገባ የገለጹለት አይመስሉም፡፡ ምንም እንኳ እርሱ ማንኛውንም ምድራዊ የአገዛዝ
መዋቅር የማስወገድ ምኞት ባይኖረውም፤ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች
ከሁሉም በፊት የእግዚአብሔር ሕዝቦች አገልጋይና ባሮች ሊሆኑ ይገባል ለሚለው
ነጥብ አጽንኦት መስጠት ፈልጓል፡፡ የኃይማኖት መሪዎች የያዙት ኃላፊነት በሕዝቡ
ላይ ገዥነታቸውን የሚለማመዱበት፣ ከሁሉም ከፍ ብለው የሚታዩበት ወይም ግላዊ
ክብርና ዝና የሚሰጣቸው አይደለም፡፡ “ክርስቶስ በልዩ መርኅዎች ላይ የተመሰረተ
መንግሥት በማቋቋም ላይ ነበር፡፡ ሰዎችን የጠራቸው ለሥልጣን ሳይሆን አገልግሎት
እንዲሰጡና ብርቱዎቹ የደካሞቹን ችግር እንዲያቃልሉ ነው፡፡ ሥልጣን፣ ማዕረግ፣ ልዩ
ችሎታ ወይም የትምህርት ዝግጅት የነበረው ሁሉ ሰዎችን የማገልገል ከፍተኛ ግዴታ
ተጥሎበታል፡፡” (የዘመናት ምኞት፡ ገጽ 566)፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዮሐ. 13፡1-20፡፡ የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ም ን ዓይነት
የአመራር ምሳሌ ነበር? የሱስ በዚህ ጥቅስ በተጨማሪ ሊያስተምረን የፈለገው
ነገር ምን ነበር? ከሌሎች ጋር በሚኖረን እያንዳንዱ ግንኙነት እነዚህን መርኅዎች
ገልጠን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ጢሞቴ. 2:15፣ ቲቶ1:9፡፡ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስና ለቲቶ በሰጠው ምክረ ሃሳብ ታማኝ የሆነው የቤተ ክርስቲያን መሪና ሽማግሌ ኃላፊነት ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ኃይማኖታዊ አስተምህሮ በንጽህና የመያዝን አስፈላጊነት
አስመልክቶ ጳውሎስ የሚሰጠውን አጽንኦት ልብ ይሏል፡፡ ይህ ለአንድነት ወሳኝ
ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የእኛ ኃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ከማንኛውም ነገር
በላይ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት እንዲኖራት የሚያደርጉ ለመሆናቸው ማንም
ሊመሰክር ይችላል፡፡ ከተለያዩ የሕይወት መስመሮች፣ ባህሎችና ታሪካዊ ዳራዎች
የመጣን እንደመሆኑ፤ በክርስቶስ ላይ ያለን አንድነት እንደ አድቬንቲስት ክርስቶስ
በሰጠን እውነት ላይ ባለን መረዳት የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ነገር ግን በአስተምህሮዎቹ
ግራ የምንጋባ ከሆነ ውዥንብርና መለያየት መምጣቱ አይቀሬ ነው--በተለይ ወደ
መጨረሻው በተቃረብን ቁጥር፡፡
“በእግዚአብሔር ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ
ኢየሱስ ፊት፣ መገለጡንና መንግሥቱን በማሰብ ይህን ዐደራ እልሃለሁ፤ ቃሉን ስበክ፤
ጊዜው ቢመችም ባይመችም ዝግጁ ሁን፤ በታላቅ ትዕግሥትና ማስተማር አቅና፤ ገሥጽ፤
አበረታታም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ትምህርት የማይቀበሉበት ጊዜ
ይመጣል ከዚህ ይልቅ ለገዛ ምኞቶቻቸው የሚስማማውን፣ የሚያሳክክ ጆሮአቸው
ሊሰማ የሚፈልገውን እንዲነግሯቸው በዙሪያቸው ብዙ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ፡፡
እውነትን ከመስማት ጆሮአቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ዘወር ይላሉ፡፡” (2ጢሞቴ.
4፡1-4)፡፡
ጳውሎስ በእነዚህ ቃላት ትኩረቱን በየሱስ ዳግም ምጽአትና በፍርድ ቀን
ላይ ያደርጋል፡፡ ሐዋርያው ይህን አስፈላጊ ምክረ ሀሳብ ለጢሞቴዎስ በመለገስ
በእግዚአብሔር የተሰጠውን ሥልጣን በሙሉ (1ጢሞቴ. 1፡1) ጥቅም ላይ ሲያውል
ይታያል፡፡ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሐሰት አስተምህሮን ተከትሎ ቅንጡነትና የግብረገብ
ውድቀት ቢነግሥም የጢሞቴዎስ ኃላፊነት የእግዚአብሔርን ቃል መስበክ ነው፡፡
እርሱ የተጠራበት አገልግሎት ይኸው ነውና፡፡
ጢሞቴዎስ የማስተማር የአገልግሎቱ አካል የሆነው ማቅናት፣ መገሰጽና ማበረታታት
የኃላፊነት ድርሻው ነው፡፡ እነዚህ ገላጭ ግሦች በአምላካዊው ቃል የተሰጡ መመሪያዎች
ናቸው (2ጢሞቴ. 3፡16)፡፡ የጢሞቴዎስ ሥራ በይቅርታና በትዕግሥት ክትትል
ማድረግ፣ ማስተማርና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚያገኘውን በተግባር መግለጽ ነው፡
፡ ርኅራኄ የጎደለውና የከረረ ግሳጼ ኃጢአተኛውን ወደ ክርስቶስ የማምጣት ዕድሉ
እምብዛም ነው፡፡ ጳውሎስ የጻፈውን መልእክት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በመከተልና
የአገልጋዩን አመራር አተያይ በመያዝ--ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን በብርቱ ኃይል
የሚያዋህድ አቅም ይሆናል፡፡
የቤተ ክርስቲያን መሪዎቻችን የቤተ ክርስቲያንን ኅብረት ጠብቀው ማቆየት
እንዲችሉ በተጨባጭ እገዛ ልናደርግ የምንችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? በቤተ
ክርስቲያን ጠብ እና አለመግባባት ቢኖርም እንኳ ከመለያየት በተቃራኒ የአንድነት
ኃይል ለመሆናችን እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ከቤተ ክርስቲያን ድርጅት አንገብጋቢ ጉዳዮች አንዱ ከደንብና ሥርዓት ጋር
ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ ደንብና ሥርዓት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት
አስጠብቆ የሚያቆይበት አካሄድ አንዳንዴ በቀላሉ በተሳሳተ መንገድ የሚስተዋልና
የሚያስቆጣ ርዕሰ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው አተያይ ቤተ
ክርስቲያናዊው ደንብና ሥርዓት በሁለት አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ማዕከል ያደርጋል፡
--የኃይማኖታዊ አስተምህሮን ንጽህና ማስጠበቅ እና የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት
ንጽህና እና ተግባር ማስጠበቅ፡፡
በተለይ በመጨረሻው ጊዜ ሊቀሰቀስ ከሚችል ክህደትና የሐሰት አስተምህሮ አኳያ
የመጽሐፍ ቅዱስን ንጽሕና ጠብቆ ስለ ማቆየት አስፈላጊነት--አዲስ ኪዳን የሚለንን
ቀደም ባለው ትምህርት ተመልክተናል፡፡ በተመሳሳይ ማኅበረሰቡን ከብልሹ ግብረገብ፣
ታማኝ ካለመሆንና ከሕገወጥነት በመጠበቅ መልካም ስም እና ዝና እንደሰፈነ ማቆየት
ይቻላል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው እንደመሆናቸው
“ለመገሰጽ፣ ለማቅናት፣ በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ” (2ጢሞቴ. 3፡16)
በሚል ተነግሮናል፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 16፡19፣ 18፡15-20፡፡ እንከን ያለባቸውን ወገኖች ደንብና
ሥርዓት ስለ ማስያዝና ስለ መገሰጽ የሱስ ለቤተ ክርስቲያን የሰጣቸው መርኅዎች
ምንድን ናቸው?
የደንብና ሥርዓት ጽንሰ ሃሳብን እንዲሁም በመንፈሳዊውና ሥነ ምግባራዊው ሕይወታችን አንዳችን የሌላችን ጠባቂ መሆናችንን መጽሐፍ ቅዱስ ይደግፋል፡ ፡ በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን ተለይታ ከምትታወቅባቸው ምልክቶች አንዱ ቅድስናዋ ወይም ከዓለም መለየቷ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግብረገብ በጎደላቸው አስቸጋሪ ባህሪያት ላይ እርምጃ እንድትወስድ የተገደደችባቸውን አያሌ ምሳሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እናገኛለን፡፡ የሥነ ምግባር እሴቶች በቤተ ክርስቲያን ተጠብቀው መኖራቸው የግድ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲከሰት ልንከተላቸው የሚገቡ ምን ዓይነት መርኅዎችን ጥቅሶቹ ይዘዋል፡ ማቴ. 7፡1-5፣ ገላ. 6፡1-2፡፡
በቤተ ክርስቲያን ደንብና ሥርዓት ስለ ማስከበር አስፈላጊነት የተሰጠውን መጽሐፍ
ቅዱሳዊ አስተምህሮ መካድ አንችልም፡፡ ያለዚህ ለአምላካዊው ቃል ታማኝ መሆን
አይቻለንም፡፡ አብዛኞቹ እነዚህ ግሳጼዎች በውስጣቸው የያዟቸውን ከጥፋት የመመለስ
ብቃት ልብ ይሏል፡፡ ግሳጼ በተቻለ መጠን ከጥፋት የሚመልስ ሊሆን ይገባል፡
፡ ደግሞም እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች መሆናችንንና ጸጋው በተመሳሳይ ለሁላችንም
እንደሚያስፈልግ ማስታወስ አለብን፡፡ ደንብና ሥርዓት ማስከበርን በኃላፊነት ስንመራ
በትህትና ብቻ ሳይሆን የገዛ ስሜታችንንም በመቆጣጠር ሊሆን ይገባል፡፡
በስህተት ከወደቁ ወገኖች ጋር ባለን አግባብ ከቅጣት ይልቅ ከጥፋት የመመለስ
መንፈስን መማር የምንችለው እንዴት ነው?
እንደ ቤተ ክርስቲያን ስለ መደራጀታችንና ወደ ሕዝቦች ለመድረስ የተልዕኮ ኅብረት ስለ መፍጠራችን በዚህ ሩብ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ተመልክተናል፡፡ እኛ ቤተ ክርስቲያን እንጂ አንዳችን የምናምንበትን ለሌላው እያካፈልን ሀሳብ የምንለዋወጥበት የሰፈር ማኅበር ወይም እድር አካል አይደለንም (በእርግጥ ያ አስፈላጊ ቢሆንም)። እኛ ራሳችን እንድንወደው የተጠራንበትን እውነት ለዓለም እንድናካፍል እነሆ በአንድነት ተሰባስበናል፡፡ የሱስ ደቀ መዛሙርት ለዓለም ያላቸውን ተልዕኮ አስመልክቶ በማቴ. 28፡18-20 የመጨረሻውን መመሪያ ሰጥቶአል፡፡ የሱስ በትእዛዛቱ ጥቅም ላይ ያዋላቸውን ቁልፍ ቃላት ለይተው ለመገንዘብ ይሞክሩ፡፡ እነዚህ ቃላት ለዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት አንደምታ አላቸው?
የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ታላቁ ተልዕኮ አራት ቁልፍ ግሶችን አካትቷል፡--ሂዱ፣
ደቀ መዝሙሬ አድርጓቸው፣ አጥምቁ፣ አስተምሩ፡፡ መልእክቱ በተጻፈበት የግሪክ
ሥርዓተ ቋንቋ ግስ መሰረት--ዋንኛው ግስ ደቀ መዝሙር ማድረግ ሲሆን ሌሎቹ ሦስት
ግሶች ይህ እንዴት ተግባራዊ መሆን እንደሚችል ያሳያሉ፡፡ አማኞች ወደ ሕዝቦች
ሁሉ ሄደው ወንጌልን ሲሰብኩ፣ ሲያጠምቁና የሱስ የተናገረውን ሲያስተምሩ--ያኔ ደቀ
መዛሙርት የማፍራት ሥራ ይሠራል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ተልዕኮ ምላሽ ስትሰጥ የእግዚአብሔር መንግሥት እየተስፋፋ
ይሄዳል፡፡ አያሌ ነገዶችና ቋንቋዎችም የሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ
ወገኖችን ይቀላቀላሉ፡፡ ሕዝቦች የየሱስን ትእዛዛት በመጠበቅ ሲጠመቁና ትምህርቱ ላይ
በቂ ትኩረት ሲያደርጉ በዓይነቱ አዲስና ዓለማቀፋዊ ይዘት ያለው ቤተሰብ ይፈጠራል፡
፡ እነዚህ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ሌሎች ደቀ መዛሙርትን በማፍራት የሱስ በየቀኑ
አብሯቸው የመሆኑን እውነታ ያረጋግጣሉ፡፡ የየሱስ አብሮነት የእግዚአብሔር መገኛ
ተስፋ መገለጫ ነው፡፡ የማቴዎስ ወንጌል የየሱስ ክርስቶስን መወለድ “እግዚአብሔር
ከእኛ ጋር” (ማቴ. 1፡23) በማለት ይጀምርና የሱስ እስከ ዳግም ምጽአቱ አብሮን
እንደሚሆን በሰጠን ተስፋ ይጨርሳል፡፡
“ደቀ መዛሙርቱ ወደፊት የሚጠብቃቸውን ሥራ ቀላል አድርጎ ባይነግራቸውም…
አብሮአቸው እንዲሚሆን ግን አረጋግጦላቸው ነበር፡፡ በእምነት እስከወጡ ድረስ
በኃያሉ ጌታ ጥላ ስር መንቀሳቀስ ነበረባቸው፡፡ የመላእክት አለቃና የሰማይ ሰራዊት
አዛዥ የሆነው ጌታ ጀግናና ብርቱ እንዲሆኑ አደፋፈራቸው፡፡ ለሥራቸው ግስጋሴ
አስፈላጊውን ሁሉ በመስጠት የስኬታቸውን ኃላፊነት እርሱ ራሱ ወሰደ፡፡ የእርሱን ቃል
እስከታዘዙና ከእርሱ ጋር ትስስር ፈጥረው እስከሠሩ ድረስ ውድቀት አያገኛቸውም”—
Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 29.
የሱስ ዳግም እስኪገለጥ ከሕዝቡ ጋር አብሮ እንደሚሆን በሰጠው ተስፋ ትርጉም
ላይ ጥልቅ ምልከታ ያድርጉ፡፡ በየሱስ የተሰጠንን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ባለን መሻት
የዚህ ተስፋ ሐቅ ተጽእኖ ሊያሳድርብን የሚችለው እንዴት ነው?
፡ Ellen G. White, “Individual Responsibility and Christian Unity,” pp. 485-505, in Testimonies to Ministers and Gospel
Workers; “Unity in Diversity,” pp. 483-485, and “Church Discipline,”
pp. 498-503, in Gospel Workers. Read the articles “Church,” pp. 707710, and “Church Organization,” pp. 712-714, in The Ellen G. White
Encyclopedia.
“የመልካም ግንኙነት መርኅዎች ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ በሁሉም ማኅበረሰባዊ
ገጽታዎች ላይ ገጣሚ እንዲሆኑ ይደረጋሉ፡፡ ሆኖም የቤተ ክርስቲያን መሪ ግን
ከመሪ በላይ ኃላፊነት ይጠበቅበታል፡፡ አገልጋይ መሆንም እንዲሁ ይጠበቅበታል፡፡
አንድ ሰው በተመሳሳይ ወቅት የመሪ እና አገልጋይ ባህሪ መላበስ የሚችለው እንዴት
ነው? የመሪ ኃላፊነት ማዕረግና ከበሬታ የለውምን? ትእዛዝ አይሰጥም? ሌሎች
እንዲታዘዙትስ አይጠብቅም? ነገሩ እንዲህ ከሆነ ትእዛዝ እየተቀበለና መሻታቸውን
እያሟላ ዝቅ ያለውን የአገልጋይ ስፍራ መውሰድ የሚችለው እንዴት ነው?
“እርስ በርሳቸው የሚጻረሩ ለሚመስሉ ነጥቦች የመፍትሔ ሀሳብ ለማግኘት ወደ
የሱስ መመልከታችን የግድ ይሆናል፡፡ እርሱ የአገልጋይነትን መርኅ በከፍተኛ ሁኔታ
ወክሎአል፡፡ መላው የእርሱ ሕይወት የአገልጋይነት ነበር፡፡ በተመሳሳይ ዓለም
አይታው የማታውቅ ታላቅ መሪም ነበር፡፡”—G. Arthur Keough, Our Church
Today: What It Is and Can Be (Washington, D.C., and Nashville: Review
and Herald, 1980), p. 106.
1.
አገልጋይንና መሪን በአንድ ያቀፈው ጽንሰ ሀሳብ ላይ ጠለቅ ያለ ምልከታ
አድርጉ፡፡ ለዚህ ጽንሰ ሃሳብ ምሳሌ መሆን የሚችል ነገር ከመንፈሳዊው ውጪ ከሆነው
ዓለም ማግኘት ይቻላል?
2.
ጥቅሱን በድጋሚ ያንብቡ፡ ማቴ. 20፡25-28፡፡ እግዚአብሔር ትልቅ
(ማቴ. 20፡26) የሚለውን ቃል ትርጉም ከዓለማዊው ፍቺ በተቃራኒ እንዴት
እንደሚያስተውለው ይህ ምን ይነግረናል?
3.
ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች ኃላፊነት አንዱ አንድነትን ጠብቆ ማቆየት ከሆነ፤
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሥጋ ለባሽነታቸው ፍጹም ምሳሌ ከመሆን ሲያግዳቸውና
ይህን ማድረግ ሲሳናቸው ምን ማድረግ ይኖርብናል?
4.
በስህተት የወደቁትን ወገኖች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ
የምናስከብረው በትህትና መንፈስና በፍቅር መሆኑን ማስተዋል በጣም አስፈላጊ
የሆነው ለምንድን ነው? በእንዲህ ያለው ሂደት ማቴ. 7፡12 ሁሌም በአእምሮአችን
ቀዳሚውን ስፍራ ሊይዝ የሚገባው ለምንድን ነው?
ማጠቃለያ፡ መልካም የቤተ ክርስቲያን አወቃቀር ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮና
ለአማኞች አንድነት ወሳኝ ነው፡፡ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ መሆኑ
የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚመሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የእርሱን ምሳሌ መከተል
ይኖርባዋል፡፡ አንድነት ተጠብቆ መቆየት የሚችለው የእግዚአብሔርን ቃል በታማኝነት
በማስተማርና ለቃሉ ታማኝ ሆኖ በመኖር ነው፡፡