ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡- ሐዋ.15፣ገላ.2፡11-13፣ ዘዳ.12፡4349 ሮሜ 3፡30፤ ዘሌ.3፡30፤ ዘሌ.18፡30፤ ራዕይ2፡14-20፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ፡-‹‹እኛም እንደነርሱ በጌታ በኢየሱስ እናምናለን››(ሐዋ፡15፡11)፡፡
የዳንነው ልክ
ፀጋ መሆኑን
ከ
ሁለት አመታት ቆይታ በኋላ ጳውሎስ እና በርናባስ ወደ አንጾኪያ ወረዱ፡፡ እንደ
ወንጌል መልዕክተኛ(ሚሲዮናዊ) እነርሱንሲልኳቸው መላው የቤተክርስትያን
አባላት ስለተሳተፉለቤተክርስትያን የደረሰቡበትን ሁኔታ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅ
ነው፡፡ ሪፖርቱ ትኩረት ያደረገው እነርሱ ባሳኩት ጉዳይ ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር
በእነርሱ በኩል ባከናወነውላይ ነበር፡፡
የሪፖርቱ ፍሬ ነገር ብዙ አይሁዶች ወደ ማመን መጥተው የነበረ ቢሆንምበዋናነት
በአህዛብ መካከል ተልእኮው ስላመጣው ስኬት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ቆርኔሌዎስ
ወደ ትዕይንቱ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ያልተገረዙ አህዛብ የመዳን ጉዳይ ትልቅ
መነጋገሪያ ሆነ (ሐዋ. ሥራ 11፡1-18)፡፡ ነገር ግን አያሌ ቁጥር ያላቸው አህዛብ ወደ
ቤተክርስትያን አባልነት እንዲቀላቀሉ ሲፈቀድነገሮችተወሳሰቡ፡፡ በኢየሩሳሌም ያሉ
ብዙ ምዕመናን ጉዳዩ አላስደሰታቸውም፡፡እንደነርሱ ኃሳብ አህዛብ ከእግዚአብሔር
ህዝብ ጋር ለመቀላቀልበቅድሚያ መገረዝናአይሁዳዊ መሆን ይገባቸዋል፡፡
ሐዋ. ሥራ 15 በሙሉ የሚያወራው የአህዛብ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለ መድረሱና
ቤተክርስቲያን መፍትሄ ለማምጣት በህብረት ስለ ሰራችውሥራ ነው፡፡ የኢየሩሳሌም
ጉባኤ የሐዋሪያት ቤተክርስቲያን ለመላው አለም ካላት ተልእኮ ጋር በተያያዘ ወሳኝ
የታሪክ አቅጣጫ የተቀየረበት ክስተት ነበር፡፡
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለነሐሴ 19 ሰንበት ይዘጋጁ፡፡
ከጅማሬው አንስቶ በአንጾኪያ የነበረችው ቤተክርስቲያን በሰላምናበህብረት ይኖሩ
የነበሩ አይሁዳውያንንና ያልተገረዙ አህዛብንየያዘች ነበረች (ሐዋ.11፡19-21፣ ገላ.3፡1113):: ይህ ህብረት ግን ከኢየሩሳሌም በመጡ የተወሰኑ አማኝ ቡድኖች ተበጠበጠ፡፡
ሐዋ.15፡1-15ን ያንብቡ፡፡ ቤተክርስቲያን እየተጋፈጠች የነበረችው ችግር ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከይሁዳ የመጡት በተለምዶ አክራሪ ይሁዳውያን(ጁዳይዘርስ)የተባሉት ቁጥር 5
ላይየተጠቀሱትአማኝ ፈሪሳውያን እንደሆኑ ይታመናል፡፡ በዚህ ቤተክርስቲያን
የፈሪሳውያን መገኘት እምብዛም አይደንቅም ምክንያቱም ጳውሎስ ራሱ ከመለወጡ
በፊት ፈሪሳዊ ነበርና (ፊሊ.3፡5)፡፡ እነዚህ ቡድኖች በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ አንጾኪያ
የመጡ ይመስላሉ (ሐዋ.15፡24)፡፡ሆኖም በሌላ ክፍል ላይ በአንጾኪያ በተከናወነ
ክስተት ያልተገረዙ አህዛብ በቤተክርስቲያን መገኘታቸውሐዋሪያትን ጨምሮ ብዙ
አይሁዳውያንን ምቾት ነስቷቸው እንደነበር ተፅፏል(ገላ.2፡11-13)፡፡
ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው መልእክት ላይ ይሁዳውያን ስለሆኑ ሰዎች የተነገረው
በበጎ ጎኑ ሳይሆን እንደውም ችግር ፈጣሪዎች ስለመሆናቸው ነበር (ገላ.1፡7፣ 5፡10)፤
‹‹ሐሰተኛ ወንድሞች››ም ብሎ ይጠራቸዋል(ገላ.2፡4)፡፡ ውስጣዊ መሻታቸውም
በወንጌል ያገኘነውን መንፈሳዊ ነፃነት ማጣጣልና የተለወጡ አህዛብን የህጋዊነትባሪያ
ማድረግ ነው፡፡
ኃሳባቸው ለማስተዋል በጣም ቀላልነበር፤ አህዛብ ካልተገረዙና የአይሁድን ሜዳዊ ህግ
ካልታዘዙ መዳን አይችሉም የሚል ነበር፡፡ ድነት እነርሱ እንደሚያምኑት የተሰጠው
እግዚአብሔር ቃል ኪዳን በገባላቸው ህዝቦችውስጥ ብቻ ነው፤ስለዚህ በብሉይ ኪዳን
መሰረት የእግዚአብሔር የተመረጠ ህዝብ የመሆኛው መንገድ መገረዝ ብቻ እንጂ
ሌላ መንገድ የለም (ዘፍ.17፡9-14፣ ዘዳ.12፡48)፡፡ በአጭሩ አህዛብ መዳን የሚችሉት
በቅድሚያ የአይሁድ ተከታይና ወገን ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡
ጳውሎስ እና በርናባስ የቀረበው መስፈርት (ቅድመ ሁኔታ) ከወንጌል ባህሪ እና አላማ
ጋር የሚፃረር እንደሆነ ስላወቁ አልተስማሙም፡፡ ከይሁዳ የመጡት አክራሪዎች
ያቀረቡበት ጠብ አጫሪ አቀራረብበሐዋ.15፡2 ላይ እንደምናነበው ክርክርን‹‹የከረረ››
ግጭትንና ጠብን አስከተለ፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ የሚፈታ
ቀላል ጉዳይ አልነበረም፡፡ የቤተክርስትያን ህብረት ጉዳይ አደጋ ውስጥ ገባ፡፡በአንጾኪያ
የነበሩ ወንድሞችም የተወሰኑ ሰዎችን ወክለው በመምረጥ ጳውሎስንና በርናባስን
በመጨመር መፍትሄ እንዲያመጡ ወደ ኢየሩሳሌም ላኳቸው፡፡
በአክራሪ አይሁዳውያን ቦታ ራስዎንያስቀምጡ፡፡ ለዚህ ጉዳይ የሚያስቀምጧቸው
የመከራከሪያ ነጥቦች ምን ሊሆኑይችላሉ?
በዚህ ክርክርላይ ታላቁ የግጭት መንስኤ ግዝረት ነበር፡፡ ይህ ሰብአዊ ዘር ያቋቋመው
አይደለም (ማቴ.15፡2፣9 ጋር ያነፃፅሩ) ፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር ራሱ ለአብርሃም
እና ለዘሩ ቃልኪዳን የገባለትን የራሱ የተመረጠ ህዝብ ስለመሆኑ የሰጠው ምልክት
ነበር (ዘፍ.17፡9-14)፡፡
ዘፀ.12፡43-49ን ያንብቡ፡፡ እስራኤላዊ ሆኖ ከተወለደ ሰው በተጨማሪ ሌላ መገረዝ
ያለበት ሰው ማን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የቃል ኪዳን በረከት ተወስኖ የተሰጠው እስራኤላዊ ተወላጅ ለሆኑግለሰቦች ብቻ
አልነበረም፡፡ ማንኛውም ባርያ ለነበረ ወይንም እንግዳ (መጻተኛ) ሆኖ ይኖር ለነበረና
ይህንን አብሮ ለመካፈል ብሎም ለመገረዝ ፈቃደኛ ለሆነ ሰው ሁሉ ነበር፡፡ ከግዝረት
በኋላ እንግዳ (መፃተኛ) የነበረው ሰው በእግዚአብሄር አይን እንደ እስራኤል ተወላጅ
ይታያል፡‹‹ከዛም እንደ ተወላጅ ይቆጠራል›› (ዘፀ. 12፡48)፡፡
ስለዚህ ግዝረት(ለወንዶች) የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች ይሆኑ ዘንድ
የሚያስችል አስፈላጊ ስርአት ነበር፡፡ ስለዚህ የሱስ የእስራኤል መሲህ ሆኖ ስለመጣ
አህዛብ ከዚህ ድነት ተጠቃሚ ለመሆን አስቀድመው አይሁድ መሆን ይገባቸዋል
ብለውአክራሪ አይሁዳውያኑ ማሰባቸው የሚጠበቅ ነው፡፡
ሮሜ3፡30፣ 1ቆሮ.7፡18፣ ገላ.3፡28፣5፡6ን ያንብቡ፡፡ ስለግዝረት ጳውሎስ የነበረው
መረዳት ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አይሁዶችን ሳይቀላቀል ማንም አህዛብ መዳን አይችልም በማለታቸው እነዚህ ግለሰቦች
ሁለት የተለያዩ እሳቤዎችን እየደበላለቁ ነበር፤ቃልኪዳንንና ድነትን፡፡ የእግዚአብሔር
የቃልኪዳኑ ህዝብ አባል መሆን ብቻውን ድነታችንን አያረጋግጥልንም (ኤር.4፡4፣
9፡25)፡፡ በተጨማሪም አብርሃም ራሱየዳነው(የፀደቀው) በእምነት ነበር፤ ያ ደግሞ
የሆነው ከመገረዙም አስቀድሞ ነው እንጂ ስለተገረዘ አልነበረም (ሮሜ4፡9-13)፡፡
ድነት ሁልጊዜም የሚሆነው በእምነት ነው ቃልኪዳን ደግሞ እግዚአብሔር ራሱንና
የድነት እቅዱን በጸጋውአማካኝነት ለመላው አለም የሚያሳውቅበት መንገድ ነው፡፡
እስራኤል የተመረጠውም ለዚሁ አላማ ሲባል ነበር (ዘፍ.12፡1-3)፡፡
ችግሩ ግን ቃልኪዳኑንና ድነትን በቅርበት የዚህን ያህል ማስተሳሰር አማኞች ግዝረትን
እንደ ወሳኝና ዋነኛ ተግባር እንዲወስዱትአድርጓቸዋል፡፡ የእግዚአብሄር የማዳን ፀጋ
ግን የሰው ስራ በሚከናወንበትአይሠራም፡፡ስለዚህ ግዝረትን እንደ መዳንመንገድ
አማኝ በሆኑ አህዛብ ላይ መጫንየወንጌልን ትክክለኛ አቅጣጫ የሚያፋልስ ነበር (ገላ.1፡
7፣ 2፡3-5)፡፡ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ዋጋ ያሳጣል(ገላ.2፡21)፤ የሱስም አይጠቅመንም
ማለት ነው(ገላ.5፡2)፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የድነትን አለማቀፋዊ ባህሪ የሚክድ ሆነ
ማለት ነው (ቆላ.3፡11፣ ቲቶ2፡11)፡፡ጳውሎስ ፈጽሞ ከእንደዚህ አይነት አስተሳሰብ
ጋርአይስማማም፡፡
ድነት የሚገኘው የትክክለኛይቱ ቤተክርሰቲያን አባል በመሆን ብቻ ነው የሚለው
አስተሳሰብ አደገኛነት ምን ላይ ነው?
ሐዋ.15፡7-11ን ያንብቡ፡፡ በኢየሩሳሌም ለነበረው ክርክር ጴጥሮስያበረከተውአስተዋጽኦ
ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በርግጥም ሉቃስ በስብሰባው ላይ ስለተከናወኑጉዳዮች ሙሉ ዝርዝር አላቀረበልንም፡
፡የአክራሪ አይሁዳውያኑን መከራከሪያ ነጥቦች (ሐዋ.15፡5) እንዲሁምጳውሎስና
በርናባስ የሰጡትን ምላሽ ማወቅ የሚጠቅም ነው(ሐዋ.15፡12)፡፡ የጴጥሮስና የያዕቆብ
ንግግር ብቻ መፃፉእነዚህ ሰዎች ከደቀመዛሙርት መካከል ምን ያክል ከፍ ያለ ቦታ
እንደነበራቸው የሚያሳይ ነው፡፡
ጴጥሮስ ለሐዋሪያትና ሽማግሌዎች ባደረገው ንግግር ከአመታት በፊት ከቆርኔሌዎስ
ጋር ስላጋጠመው ልምምድ በማውሳት ተናገረ፡፡ በዚህ ስፍራም ቀድሞ በኢየሩሳሌም
ወገኖች መካከል ያቀረበውን መከራከሪያ የሚመስል ኃሳብ ነበር ያቀረበው (ሐዋ.11፡
4-17)፡፡ እግዚአብሔር ራሱ የቆርኔሌዎስን መለወጥ መቀበሉን በጴንጤቆስጤ
ቀን ለሐዋሪያቱ እንደሆነው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለርሱና ለቤተሰቡ በመስጠት
አረጋግጧል (ምንም እንኳን እርሱ ያልተገረዘ አህዛብ ቢሆንም)፡፡
በመለኮታዊ እቅዱ የተነሳ እግዚአብሔር ድነትን በተመለከተ በአይሁድ እና በአህዛብ
መካከል ምንም ልዩነት እንደሌለ ለማስረዳት ጴጥሮስን ተጠቀመ፡፡ ምንም እንኳን
ከብሉይ ኪዳን ህግና ደንብ የመንጻት ጥቅምን ባያገኙም ያልነፁ አይባሉም፤ ምክንያቱም
እግዚአብሔር ራሱ ልባቸውን ስላነፃው ነው፡፡ የጴጥሮስ የመጨረሻ ንግግር ከጳውሎስ
ከምንጠብቀው ንግግር ጋር ተመሳሳይ ነው፡- ‹‹እኛም የዳንነው ልክ እንደነርሱ በጌታ
በኢየሱስ ፀጋ መሆኑን እናምናለን፡፡›› (ሐዋ.15፡11)፡፡
ሐዋ.15፡13-21ን ያንብቡ፡፡ ለአህዛብ ችግር ያዕቆብ ያቀረበው የመፍትሄ ሀሳብ ምን
ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የያዕቆብ ንግግር በአመራር ላይ እንደነበርየሚያሳይ ነው (ከሐዋ. ሥራ 12፡17፣ 21፡18፣
ገላ.2፡9-12 ጋርያነጻጽሩ)፡፡ስለ ዳዊት ቤት እንደገና መጠገንበአሞጽ ትንቢት(አሞፅ 9፡
11-12) የዳዊት ዙፋን ስለመመለሱ የተነገረውን ትንቢት የተረዳበትን መንገድ ባናውቅም
የያዕቆብ ዋነኛ አላማ እግዚአብሔር አህዛብ እንዲቀላቀሉአስቀድሞ እድል እንደሰጠና
ዳግም ‹‹የእግዚአብሔር ህዝብ›› በመሆናቸው ከእሰራኤላውያን ጋር ስለመቀላቀላቸው
ለመግለጽ ነው፡፡
በዚህ የተነሳ የርሱ ውሳኔ በተለወጡ አህዛብ ላይ በእስራኤል ምድር መኖር የሚሹ
መፃተኞች ከሚጠበቅባቸው ውጪ ምንም አይነት ገደብ እንዳይጫንባቸው ነበር፡፡
ሐዋ.15፡28-29ን ያንብቡ፡፡ ጉባኤው በተለወጡ አህዛብ ላይ ያስተላለፈው አራት
ድንጋጌ ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጉባኤው ለተሰበሰበበት ዋነኛ አጀንዳ በቂ በሚባል ደረጃ መፍትሄ ሰጠ፡፡ ድነት በፀጋ
ከመሆኑ የተነሳ አህዛብ ወደ ቤተክርስቲያን ለመቀላቀል የግድ መገረዝ እንደሌለባቸው
ተወሰነ፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ አራት ነገሮች መራቅ ግድ ይላቸዋል፡፡
1ኛ. ለጣኦት ከተሰዋ በኋላ ለግብዣወይም ለገበያ ሽያጭ የቀረበን ሥጋ ከመብላት
2ኛ. ደም ከመብላት 3ኛ.ታንቆ የሞተ እንስሳን ሥጋ ማለትም ደሙ በስጋው ውስጥ
እያለ ከመመገብና4ኛ. ከተለያየ አይነት የዝሙት እርኩሰት መራቅ ነበር፡፡
አያሌ ክርስትያኖች ዛሬ ላይ እነዚህን የምግብ ድንጋጌዎች (ከ1-3 ያሉትን ድንጋጌዎች)
ለዚያ ጊዜ ብቻ እንደነበሩ ይቆጥራሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ለአይሁድ ማህበረሰብ አፀያፊ
ስለነበሩ ይህ ድንጋጌ በአይሁድና በአህዛብ አማኞች መካከል የነበረውን ክፍተት
ለማጥበብ ብቻ የታቀዱ ናቸው ብለው ይሞግታሉ፡፡ ሌሎቹ የብሉይ ኪዳን ህግጋት
ማለትም በዘሌዋውያን ላይ የሚገኘውየአመጋገብ ህግ (ዘሌ.11) እና የሰንበትትእዛዝ
(ዘፀ.20፡8-11)በዚህ ዝርዝር ውስጥ ስላልተካተቱ ክርስትያኖችም ሊጠብቋቸው
አይገባም ብለው ያስባሉ፡፡
የሐዋሪያት ድንጋጌ ተብሎ የተጠራው ግን ጊዜያዊ ወይንም ለክርስትያኖች ግብረገብ
አዲስ ትእዛዝን በማምጣት ከብሉይ ኪዳን ጋር የተያያዙ ነገሮችን ሁሉ ያስወገደ ሂደት
አልነበረም፡፡ እንደውም በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አማካኝነት (ሐዋ.15፡28) ሐዋሪያት
እና የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች ከእስራኤል ጋር ለሚኖሩ መፃተኞች የተነገረውን
የዘሌዋውያን 17-18ንመመሪያ አስቀጥለውታል፡፡
ከዘሌዋውያን አውድ አንጻር እነዚህ ድንጋጌዎች አረማዊነትን ስለመተው ይናገራሉ፡
፡ ማንኛውም መፃተኛ በእስራኤል መኖር ከፈለገ በእግዚአብሄር የማያምኑ
ሰዎችየሚያደርጉትን ያደገበትንድርጊት መተው አለበት (ዘሌ.18፡30)፡፡ ልክ
እንደዚሁአምኖቤተክርስቲያንን መቀላቀል የፈለገ አህዛብ ሁሉ አረማዊ የሆነ ተግባርን
ላለመፈጸም ቁርጥ አቋም ማሳየት ነበረበት፡፡
ሆኖም ይህ የመጀመርያው ደረጃ ብቻ ነበር፡፡ ይህን ካደረገ በኋላ እርሱ/እርሷ
አለማቀፋዊ የሆነውን ትእዛዝ በመጠበቅ የእግዚአብሄር ፈቃድ ይፈጽሙ ዘንድ
ይጠበቅባቸዋል፡፡ይህም የሜዳዊ ህግ ያልሆኑትን(ከሙሴ ህግ በፊት የነበሩትን)
ለምሳሌ ሰንበትን (ዘፍ.2፡1-3)መጠበቅ እና ንጹህ የሆነውንና ያልሆነውን መለየት
ይገባቸዋል(ዘፍ.7፡2)፡፡
ድንጋጌዎቹጊዜያዊ ብቻ አለመሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ለምሳሌ ራእይ2፡14፣20 ላይ
የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ድንጋጌ ተደጋግሞ ተጽፏል፤በውስጠ ታዋቂነት
ሌሎች ሁለቱ ህጎች መኖራቸውም ግልጽ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የታሪክ ማስረጃዎች
የሚያሳዩን ድንጋጌዎቹ ከአዲስ ኪዳን ዘመን በኋላም ቆይተው ለኖሩ ክርስትያኖች
ይሰሩ እንደነበረ ነው፡፡
ግጭቶች በሚነሱበት ጊዜ አብረን ለመቀመጥ፣እርስ በርስ ለመስማማትና በጉዳዩ ላይ
ለመወያየት በአክብሮትና በትህትና መንፈስ ለማውራት እንዴት መማር እንችላለን?
ሐዋ.15፡22-29ን ያንብቡ፡፡ የጉባኤውን ውሳኔ በተመለከተ የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን
ምን ተጨማሪ እርምጃን ወሰደች?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የመጀመሪያ እርምጃ የነበረው ለአህዛብ አማኞች ምን እንደተወሰነ የሚገልጽ ደብዳቤ
ጽፎ ማሳወቅ ነበር፡፡ኢየሩሳሌም በነበሩሐዋሪያትና ሽማግሌዎች ስም የተጻፈው
ደብዳቤ የኢየሩሳሌም ቤተክርስትያንን የሥልጣን ተዋረድ የሚያንጸባርቅ ይፋዊ ሰነድ
ሲሆን ይህም የሐዋሪያት አመራር በሌሎች የክርስቲያን ማህበረሰብ ላይ ስለነበር ነው፡
፡ የተጻፈውበ49ዓ.ም ሲሆን ምናልባትም ጉባኤው የተቀመጠበት ቀን ነው፡፡ ይህ
ደብዳቤ ከቀደምት ክርስትያን ሰነዶች አንዱ ነው፡፡
የኢየሩሳሌምቤተክርስትያንም ሁለት ልኡካንን ማለትም ይሁዳና ሲላስ ጳውሎስን
አጅበው ወደ አንጾኪያ እንዲወርዱ መደቡ፡፡ ተግባራቸውም ደብዳቤን ማድረስ እና
ስለ ደብዳቤው ይዘት አረጋግጦ መናገር ነበር፡፡
ሐዋ.15፡30-33ን ያንብቡ፡፡ በአንጾኪያ ያለችው ቤተክርስቲያን ለደብዳቤው የሰጠችው
ምላሽ ምን ይመስል ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ደብዳቤው በሚነበብበት ጊዜ ከማበረታቻ መልእክቱ የተነሳ ቤተክርስትያኒቱ
በከፍተኛ ደስታ ተዋጠች፡- ለተለወጡ አህዛብ ግዝረት የግድ የሚያስፈልግ መስፈርት
አልነበረም፡፡ እንዲያደርጉ ደብዳቤው የጠየቃቸውን ድንጋጌም አልተቃመውም
(አራቱ ድንጋዌዎችን)፡፡በቀዳሚዋ ቤተክርስቲያን ተነስቶ የነበረው አሳሳቢ መከፋፈል
ቢያንስ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ተፈታ፡፡
በጉባኤው ማገባደጃ ላይ የጳውሎስ ወንጌል በኢየሩሳሌም በሚገኙ የቤተክርስቲያን
መሪዎች ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትን ስላገኘለጳውሎስና በርናባስ አመኔታቸውን ለማሳየት
የትብብር ቀኝ እጃቸውን ሰጧቸው (ገላ.2፡9)፡፡ ነገር ግን አይሁዳዊ የሆኑ ክርስትያኖች
በአይሁድ ህግ መኖራቸውን ሲቀጥሉ የመንፃት ስርዓት ካልፈፀሙት አህዛብ ጋር
በማእድ መቀመጥ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር፡፡
ይህ ጉዳይ ለአብነት ያህል ጴጥሮስ በገላ.2፡11-14 ታሪክ ላይ ያደረገውን ይነግረናል፡
፡ኤለን ኋይት ስትናገር ‹‹ደቀመዛሙርቱ እንኳን የጉባኤውን ውሳኔ በፈቃደኝነት
ለመቀበል ልባቸውን አላዘጋጁም፡፡›› The Acts of the Apostles, P.197፡፡
እስቲ ለራስዎ ሀቀኛ ይሁኑና ከሌላ ዘር ፤ባህል ብሎም የኑሮ ደረጃ ከመጡ ሰዎች ጋር
ለመቀላቀልና ህብረት ለማድረግ ምን ያህል ያስቸግሮታል? ለወንጌል ፀር የሆነውን
ይህንን ጉዳይበመከላከል ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው?
ነሐሴ 18
‹‹የተለወጡ አይሁዳውያን እግዚአብሔር አቅዶ በከፈተው መንገድ
በፍጥነት መሄድ አልቻሉም፡፡ በአህዛብ መካከል ሐዋሪያት በሰሩት የስራ ውጤት
የተነሳ ቆይተው የተለወጡ ሰዎች ብዛት ከተለወጡ አይሁዳውያን ቁጥር ይልቃል፡
፡ አይሁዳውያን የፈሩት የህጋቸው ደንቦችና ስርአቶች አህዛብ የቤተክርሰቲያን አባል
እንዲሆኑ እንደቅድመ ሁኔታ ካልተቀመጡ ለዘመናት ከሌሎች የተለዩ ህዝቦች ሆነው
እንዲቆዩ ያደረጋቸው ብሔራዊ መታወቂያ የወንጌልን መልእክት በሚቀበሉት ዘንድ
እንዳይጠፋ ነው፡፡››-Ellen G white, The Acts of the Apostles, P.189፡፡
<<በቤተክርስቲያን እይታ ውስጥ ያሉ የአይሁድ ክርስቲያኖች የአይሁድ መመረጥና
የተለየ ህዝብ መሆን ወደ ነበረበት ተመልሶ እንዲመጣ ፈልገዋል ፡፡ የክርስትያን
ቤተክርስቲያን ከአይሁድ ስርአት እና ባህል እየራቀ መሄዱን ያዩት ለአይሁድ ተሰጥቶ
የነበረው ቅዱስና የተለየ የነበረው ይህ ስርአት አዲስ በመጣው የእምነት ብርሃን
አማካኝነት ጠፋ፡፡ በዚህ ውስጥ ትልቁን ሚና በተጫወተው ጳውሎስ ላይ ብዙዎች
ተበሳጩበት፡፡ ደቀመዛሙርቱ እንኳን የጉባኤውን ውሳኔ ለመቀበል ሙሉ በሙሉ
ዝግጁዎች አልነበሩም፡፡ አንዳንዶች ለስርአታቸው ቀናኢ ስለነበሩ ጳውሎስን ጠሉት
ምክንያቱም የአይሁድን ህግ በተመለከተ የእርሱ መርህ ልል እና ግድየለሽነትን
የሚያንፀባርቅ ነው ብለው አስበዋልና፡፡››- page 197.
1. በክፍልዎ ውስጥ ወደ ሰኞ ክፍል የመጨረሻ ጥያቄ ተመልሰው ይወያዩ፡
፡ ‹‹የትክክለኛዋ ›› ቤተክርስቲያን አባል መሆናችን ብቻ ድነታችንን
እንደማያረጋግጥልን የምናስተውለው እንዴት ነው? ለምሳሌ ጥንታዊ
እስራኤላውያን በርግጥም ‹‹ትክክለኛ ቤተክርትያን›› ውስጥ ነበሩ ያ ማለት ግን
ሁሉም ይድናሉ ማለት አይደለም፡፡ በትክክለኛው ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆን
ብቻ ድነታችንን አያረጋግጥም ታዲያ የቤተክርስቲያኒቱ አካል የመሆን ጥቅሙ
ምንድነው?
2. ያልተገረዙ አህዛብን ወደ እምነት ማህበር በመቀበል የቀደመችው ቤተክርስቲያን
የተጋፈጠቸው አንዱና ዋነኛው የአስተዳደራዊ ጉዳይ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር
የሚነፃፀር ዛሬ በቤተ ክርስትያናችን ያለ ምን ጉዳይ አለ? የሐዋ.15 ምሳሌ
ጉዳያችንን እንዴት መፍታት እንዳለብን ምን ያስተምረናል?
3. በክፍልዎ ውስጥ የተወሰኑ ሰዎችን መድቡና አህዛቦች ቤተክርስቲያንን
ከመቀበላቸው በፊት የአይሁድ ተከታይ መሆን አለባቸው ምክንያቱም ቃልኪዳኑ
ለእስራኤል ነው የተሰጠው ብለው እንደሚከራከሩበት አይሁዳውያን ይሁኑ፡፡
የመከራከሪያ ነጥባቸው ምንድነው እናንተስ ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድነው?
እንደዚህ አይነት ክርክሮች አሁን ላይ ግልጽ የሆኑ ቢሆንም በተለያየ ጊዜ ምን
ያህል አስቸጋሪ እንደነበሩ እንዴት እንረዳለን?