ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ሐዋ. ሥራ 6፣ ሐዋ.ሥራ 7፡48፣ ዕብ.5፡11-14፣ ሚኪያስ 6፡1-16፣ ሐዋ.ሥራ 7፣ሐዋ. ሥራ 8፡4-25፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ፡-የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ የደቀመዛሙርቱም ቁጥር በኢየሩሳሌም እጅግ እየበዛ ሄደ፤ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት የታዘዙ ሆኑ”። /ሐዋ. ሥራ 6፡7/
በ
ጴንጤቆስጤ ቀን ራሳቸውን ለጌታ ከሰጡት አብዛኞቹ ሔለናዊያን አይሁዶች
ማለትም በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ግሪካውያንና ሮማውያን የሆኑ አይሁዶች
ናቸው /ሐዋ. ሥራ 2፡5፣9-11/፡፡ አይሁዳውያን ተብለው ቢጠሩም በሐዋ. ሥራ 6፡1 ላይ
“ዕብራውያን” ተብለው ከተጠሩትና ሙሉ በሙሉ አይሁዳውያን ከሆኑት ጋር ሲታዩ
ግልፅ የሆነ ልዩነት ነበራቸው፡፡ ዋናው ልዩነትም በይሁዳ ምድር ይነገር የነበረውን
አረማይክ ቋንቋ አለመናገራቸው ነው፡፡
ሌሎችም ብዙ ባህላዊም ሃይማኖታዊም ልዩነቶች ነበሯቸው፡፡ በሌላ አገር
የተወለዱ በመሆናቸው ከአይሁድ ወግና ልማድ ጋር እንደ ሃገሩ ተወላጆች ስር
የሰደዱ አልነበሩም፡፡ ከቤተ መቅደሱ ሥርዓቶች ጋር እንዲሁም በእስራኤል አገር ብቻ
ይተገበሩ ከነበሩት የሙሴ ህግጋት ጋር እምብዛም የተቆራኙ አልነበሩም፡፡
አብዛኛውን እድሜያቸውን በግሪካውያንና ሮማውያን ተከበው ከአህዛብ
ጋር ስላሳለፉ ሁሉን አቃፊ የሆነውን የክርስትና እምነት ገፅታ ለመረዳት ይቀላቸዋል፡
፡ እንደውም ለዓለም ሁሉ ምስክር እንዲሆኑ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ከግብ ለማድረስ
እግዚአብሔር ብዙ ሔለናዊ/ግሪካዊ/ አማኞችን ተጠቅሟል፡፡
ለሐምሌ 21 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህንሳምንት ትምህርት ያጥኑ፡፡
ሐዋ. ሥራ 6፡1ን ያንብቡ፡፡ የግሪካውያን አማኞቹ ማጉረምረም ይዘት ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“ማጉረምረሙ የመጣው በየዕለቱ ይከናወን የነበረው ምግብ የማደል አሠራር
ላይ ከግሪክ ወገን የሆኑት መበለቶች ችላ ተብለው ስለነበረ ነው፡፡ ማዳላት ከወንጌሉ
መንፈስ ተቃራኒ ነበር፤ ሰይጣን ግን ጥርጥርን በመዝራት ተሳክቶለት ነበር፡፡ ጠላት
በአማኞች መካከል መከፋፈልን ለማምጣት በሚያደርገው ጥረት ሙሉ ስኬትን
እንዳያገኝና ክፍተትን ሁሉ ለማጥፋት ፈጣን እርምጃዎች መወሰድ ነበረባቸው፡፡” Ellen G. white The Acts of Apostles p.88”
ሐዋርያቱ ያመጡት መፍትሔ እነርሱ በጸሎትና በቃሉ ሲተጉ የማዕዱን
አገልግሎት ያስተናግዱ ዘንድ ሰባት ሰዎችን ከነርሱ መካከል መምረጥ ነበር/ሐዋ. ሥራ
6፡2-4/፡፡ በሐዋ. ሥራ 6፡2 ”ማዕድ” የሚለው ቃልና በሐዋ. ሥራ 6፡4 “ቃሉ” ተብሎ
የተተረጎመው ቃል ዲያኮኖና ዲያኮንያ ከሚሉ ተመሳሳይ ሥር ካላቸው ቃላት የመጡ
ናቸው፡፡
ይህ “በየእለቱ” ከሚለው መግለጫ ጋር የቀዳሚቷ ቤተክርስቲያንን ሁለት ዋና
ዕለታዊ ትኩረቶች ይገልጽልናል:- “ቃሉን” ማስተማርና ህብረት ማድረግ /”ማዕድ”/፡፡
ሁለተኛው በየዕለቱ የሚቆርሱትን እንጀራ፣የጌታ ራትንና አብሮ መጸለይን ይገልፃል፡፡
/ሐዋ. ሥራ 2፡42፣46፣5፡42/፡፡
ይህም ማለት ሐዋርያቱ የክርስቶስን አስተምህሮ በባለ አደራነት ስለተቀበሉ
በአብዛኛው ቃሉን በማስተማርና በጸሎት ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ሰባቱ ደግሞ በተለያዩ
የቤት ለቤት ህብረቶች ህብረት የማድረግን ጉዳይ ይቆጣጠሩ ነበር፡፡ ኃላፊነታቸው
ዛሬ ለዲያቆናት በሰጠናቸው ቦታ ብቻ የተወሰነ አልነበረም፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ
የመጀመሪያዎቹ መሪዎችም ሆነው ነበር፡፡
ሐዋ ሥራ 6፡2-6ን ያንብቡ፡፡ ሰባቱ ዲያቆናት የተመረጡበትና ለአገልግሎት የተለዩበት
ሁኔታ ምን ይመስል ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
እጩዎቹ የተለዩት በግብረገብ፣ በመንፈሳዊና በተግባር መለኪያዎች ነበር፤ በሌሎች
ዘንድ መልካም ተቀባይነት ያላቸው፣ በጥበብና በመንፈስ የተሞሉ መሆን ነበረባቸው፡፡
ከማህበረሰቡ ባገኙት ማረጋገጫ ሰባቱ ሰዎች በፀሎትና እጅ በመጫን ለዚያ አገልግሎት
ተለዩ/ተመረጡ/፡፡ ስርአቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት የማግኘትንና እንደ ዲያቆን
ለማገልገል ስልጣን ማግኘትን የሚያመላክት ነበር፡፡
በስልጣን ባሉት ዘንድ ጠብን መዝራት በጣም ቀላል ነው፤ አይደል? እግዚአብሔር
በሰጠን አቅም በመካከላችን ሰላምን ለመጠበቅና በተልዕኮአችን ላይ ትኩረት ማድረግ
የምንችለው እንዴት ነው?
ኃላፊነት ከተቀበሉ በኋላ ሰባቱ በቤተክርስትያን አገልግሎት ብቻ ሳይገደቡ ውጤታማ
በሆነ ምስክርነት ላይም ተሳትፈዋል፡፡ በውጤቱም ወንጌል መስፋፋቱን ቀጠለ
የአማኞችም ቁጥር ጨመረ/ሐዋ. ሥራ 6፡7/፡፡ ይህ እድገት ሲጀምርም በእርግጥ
በቀደምቷ ቤተክርስቲያን ላይ ተቃውሞ መጥቶባታል፡፡ ከዚያ ታሪኩ ለየት ያለ
መንፈሳዊ ጥንካሬ ባለው እስጢፋኖስ ላይ ያተኩራል፡፡
ሐዋ. ሥራ 6፡8-16ን ያንብቡ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ስለ እስጢፋኖስ፣ ስለ እምነቱና
ስለ ባህሪው ምን ያስተምሩናል?ተቃዋሚዎቹ ያን ያክል እንዲቆጡ ያደረጋቸውና
እስጢፋኖስ ሲሰብክ የነበረው ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከግሪክ የመጣ አይሁዳዊ እንደመሆኑ እስጢፋኖስ በኢየሩሳሌም በሚገኙና ግሪካውያን
በሚሰበሰቡባቸው ምኩራቦች ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ በከተማይቱ እንደዚህ አይነት
ብዙ ምኩራቦች ነበሩ፤ ሐዋ. ሥራ 6፡9 ሁለቱን ይጠቅሳል፡፡ አንዱ ከደቡብ ለመጡ
ስደተኞች /ከቀሬናና አሌክሳንድሪያ ለመጡ አይሁዶች/ ሌላው ደግሞ ከሰሜን ለመጡ
ስደተኞች /ከሲሲሊያና ኢስያ ለመጡት/ ነበሩ፡፡
የክርክራቸው ዋና ጉዳይ የሱስ መሆኑ ባያጠያይቅም በእስጢፋኖስ ላይ የቀረበው ክስ
እርሱ ወንጌልን የተረዳበትና ያስተማረበት ሁኔታ ከአይሁድ አማኞች ማስተዋል ያለፈ
እንደነበረ ያሳያል፡፡ እስጢፋኖስ የተከሰሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ ማለትም
በህጉና በቤተ መቅደሱ ላይ የስድብ ቃል ተናግሯል ተብሎ ነው፡፡ በአንዳንድ ነጥቦች
በስህተት ቢያስተውሉትም ወይም ቃላቱን አውቀው ቢያጣምሙበትና የሐሰት
ምስክር ቢያቆሙበትም ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ ክሱ ሙሉ በሙሉ ውሸት አልነበረም/
ማርቆስ 14፡58፣ ዮሐ.2፡19/፡፡ እስጢፋኖስ በግልፅ ለቤተ መቅደሱ እየሰጡት የነበረው
አክብሮት የበዛ መሆኑን ማውገዙ /ሐዋ. ሥራ 7፡48/ የኢየሱስ ሞት የሚያስተምረንን
ጥልቅ ትምህርት፣ ወዴት እንደሚያመራ ቢያንስ ከቤተ መቅደሱና ከአገልግሎቶቹ
አንፃር ያለውን አንድምታ መረዳቱን ይገልፃል፡፡
በሌላ አባባል ምናልባትም ብዙ አይሁድ አማኞች ከቤተ መቅደሱና ከስርዓቶቹ
ጋር ተሳስረው/ሐዋ. ሥራ 3፡1፣15፡1፣5፣21፡17-24/ ለመተውም ሲከብዳቸው /ገላ.5፡
2-4፣ዕብ. 5፡11-14/ እስጢፋኖስና ሌሎች ከግሪክ የመጡ አማኞች የኢየሱስ መሞት
መላውን የቤተ መቅደሱን አገልግሎት ማብቃት የሚያመለክት መሆኑን አስተውለው
ነበር፡፡
እኛ በምንወዳቸው አመለካከቶች ተጠምደን አዲስ ብርሃን ሲመጣ የተዘጋን እንዳንሆን
ጠንቃቆች መሆን ያለብን ለምንድነው?
ሐዋ. ሥራ 7፡1-53ንያንብቡ፡፡ እስጢፋኖስ ለከሳሾቹ እያላቸው የነበረው ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በእስጢፋኖስ ላይ የቀረቡት ክሶች እንዲታሰርና በሸንጐ ፊት እንዲቀርብ
አደረጉት፡፡ እንደ አይሁድ ልማድ ከሆነ ህጉና የቤተመቅደሱ አገልግሎቶች ዓለም
ከቆመባቸው ሦስት ምሶሶዎች ሁለቱ ነበሩ፡- ሦስተኛው ደግሞ መልካም ሥራ ነበር፡
፡ የሙሴ ስርዓቶች አልፈዋል ብሎ በግልፅ መናገር በአይሁድነት ውስጥ እጅግ ቅዱስ
የነበረው ላይ ጥቃት እንደ መሰንዘርና እግዚአብሔርን እንደ መሳደብ የሚቆጠር ነበር
/ሐዋ. ሥራ 6፡11/፡፡
የእስጢፋኖስ ምላሽ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ረጅሙ ንግግር
ሲሆን ይህም የጉዳዩን አስፈላጊነት የሚያሳይ ነው፡፡ መጀመሪያ ሲታይ የእስራኤልን
ታሪክ በሌላ ቃላት ከመድገም የማያልፍ ንግግር ቢመስልም ይህንን ንግግር ከብሉይ
ኪዳን መመሪያና እስራኤልን ወደህጉ ለመመለስ ነቢያቱ እንደተሐድሶ ሰዎች ይዘቱን
ከተጠቀሙበት መንገድ ጋር አያይዘን ልናስተውለው ይገባል፡፡ ሕዝቡ በሚወድቁበት
ጊዜ ሕዘቡ በቃልኪዳናቸው ስላልፀኑ እግዚአብሔር በራሱ ህዝብ ላይ የሚወስደውን
እርምጃ ለመግለፅ በዕብራይስጥ “ሪብ /rib/”የሚለውንና “ቃልኪዳናዊ ሙግት” የሚል
ትርጓሜ ያለውን ቃል ይጠቀማሉ፡፡
ለምሳሌ በሚክያስ 6፡1-2 ላይ “ሪብ” /ክርክር/ ሦስት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ከዚያም
የሲናውን ኪዳን አካሄድ በመከተል /ዘፀ.20-23/ ሚክያስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ
ያደረገውን ያስታውሳቸዋል/ሚክያስ 6፡3-5/፤ ቃልኪዳኑ ያስቀመጣቸው ነገሮች
መጣሳቸውን/ሚኪያስ 6፡6-12/ እና ጥሰቱ ያመጣቸውን እርግማኖች በመጨረሻ
ይነግራቸዋል /ሚክ. 6፡13-16/፡፡
የእስጢፋኖስ ንግግር መነሻም ይህ ይመስላል፡፡ ያደረገውን እንዲገልፅ
ሲጠየቅ የቀረበበት ክስ ስህተት መሆኑን ለማስረዳት ወይም ያመነውን ለመከላከል
አልሞከረም፡፡ በተቃራኒው ቀደምት ነቢያት ያደርጉት እንደነበረው ድምፁን ከፍ
አድርጐ በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ ራሳቸው እንዳመጡ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ቀድሞ የነበረውን ግንኙነት ያስታወሳቸው አመስጋኝ
አለመሆናቸውንና አመፀኝነታቸውን ለመግለፅ ነበር፡፡
በእርግጥም በሐዋ.ሥራ 7፡51-53 ላይ እስጢፋኖስ ተከሳሽ መሆኑ ቀርቶ
የእግዚአብሔር ጠበቃ ሆኖ በመሪዎቹ ላይ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ሙግት
አቀረበ፡፡ አባቶቻቸው ነቢያትን በመግደል ጥፋተኛ ከነበሩ የእነርሱ ኃጢያት ደግሞ
ጨምሮ ነበር፡፡ “አባቶቻችን” ከማለት /ሐዋ.ሥራ 7፡11፣19፣38፣44፣45/ “አባቶቻችሁ”
ወደ ማለት መሻገሩ ወሳኝ ነው፡- እስጢፋኖስ ከህዝቡ ጋር ያለውን አንድነት ትቶ
ለኢየሱስ ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ ብዙ ችግር የሚያመጣበት ቢሆንም ቃላቱ ፍርሃት ወይም
ቁጭት በውስጣቸው አልነበረም፡፡
እርስዎ ለኢየሱስ ጠንካራና የማይደራደር አቋም ለመያዝ የተፈተኑት መቼ ነበር?
ወይስ ወደቁ? ወድቀው ከነበረ መለወጥ ያለበት ምን ይሆን?
ነቢይ /በእብራይስጥ nabi/ ማለት ለእግዚአብሔር የሚናገር ሰው እንደመሆኑ
እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ፍርድ /ሙግት/ በእስራኤል ላይ በተናገረባት ቅፅበት
ነቢይ ሆኗል፡፡ ሆኖም የነቢይነት ዘመኑ አጭር ነበር፡፡
የሐዋ.ሥራ 7፡55-56ን ያንብቡ፡፡ የእስጢፋኖስ ራዕይ ትርጉሙ ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“እስጢፋኖስ እዚህ ጋ ሲደርስ በህዝቡ መካከል ሁከት ተነሳ፡፡ ክርስቶስን ከትንቢቶቹ
ጋር ሲያያይዝና ስለ ቤተመቅደሱ ሲናገር ሊቀካህኑ እጅግ የተደናገጠ በመምሰል
ልብሱን ቀደደ፡፡ ለእስጢፋኖስ ይህ ማለት ልሳኑ ለዘላለም ሊዘጋ የመሆኑ ምልክት
ነበር፡፡ ለተናገረው ነገር የህዝቡን ተቃውሞ ሲመለከት የመጨረሻ ንግግሩን እያደረገ
እንደሆነ ገባው፡፡ ስብከቱን ባይጨርስም የግዱን ደመደመው፡፡” Ellen G. white,
The acts of the apostles,p.100
እስጢፋኖስ እግዚአብሔር በነርሱ ላይ ያለውን ሙግት በአይሁድ መሪዎች ፊት ቆሞ
ሲያስተላልፍ ኢየሱስ በሰማዩ ሸንጐ ቆሞ ነበር -- ማለትም በሰማዩ ቤተ መቅደስ
በአባቱ ቀኝ ቆሞ ነበር፡፡ ይህም በምድር ላይ የሚሆነው ፍርድ በሰማይ በትክክል
የሚካሄደው ፍርድ መገለጫ መሆኑን የሚያሳይ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በእስራኤል
ውስጥ ባሉት አስተማሪዎችና መሪዎች ላይ የሚፈርድ መሆኑን ያሳያል፡፡
ቀድሞ በሐዋሪያት ሥራ በተሰጡት ንግግሮች ውስጥ የነበረው የንሰሐ ጥሪ በዚህ ቦታ
የሌለው ከዚህ የተነሳ ነበር /ሐዋ. 2፡38፣3፡19፣5፡31/፡፡
የእስራኤል የእግዚአብሔር ወኪልነት ወደ ፍፃሜው መጣ፤ ማለትም የዓለም መዳን
ጥሪ ለአብርሃም ቃል እንደተገባው /ዘፍ.12፡3፣18፡18፣22፡18/ በእስራኤል ሕዝብ
በኩል መሆኑ ቀርቶ በኢየሱስ ተከታዮች በኩል እንዲነገር ሆነ፤ አይሁድና አሕዛብ
ከኢየሩሳሌም ወጥተው ለዓለም ሊመሰክሩ ነበር /ሐዋ.ሥራ 1፡8/፡፡
ሐዋ.ሥራ 7፡57-8፡1-2ን ያንብቡ፡፡ ሉቃስ የእስጢፋኖስን ሞት የዘገበው እንዴት ነበር?
በድንጋይ መውገር እግዚአብሔርን ለመሳደብ የሚሰጥ ቅጣት ነበር /ዘሌ.24፡14/፡
፡ ሆኖም እስጢፋኖስ ሞት ተፈርዶበት ይሁን ወይም በወግ-አጥባቂዎች ግርግር
መፍጠር ብቻ ይገደል ግልፅ አይደለም፡፡ የትኛውም ቢሆን በእምነቱ አማካኝነት
የተገደለ የመጀመሪያው የየሱስ አማኝ ሆኗል፡፡ ምስክሮቹ ልብሳቸውን በሳኦል
እግር ስር ማስቀመጣቸው የእስጢፋኖስ ተቃዋሚዎች መሪ እንደነበረ ይገልፃል፡፡
ሆኖም እስጢፋኖስ ለሚወግሩት ሲፀልይ ለሳኦልም ፀልዩለት ነበር፡፡ ታላቅ ባህሪና
የማይነቃነቅ እምነት ያለው ሰው ብቻ ይህንን ሊያደርግ ይችላል፤ በዚህም ክርስቶስ
በህይወቱ እንደሚሠራና እምነቱ ታላቅ መሆኑ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ታየ፡፡
በእስጢፋኖስ ላይ የተገኘው ድል በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች ላይ ታላቅ ስደት
እንዲጫር ምክንያት ሆነ፡፡ የአሳዳጁ ቡድን መሪና በቤተክርስቲያን ላይ ጥቂት
የማይባል ጉዳት ያደረሰው ሳኦል ነበር፡፡ ሆኖም ስደቱ መልካም ነገርን አምጥቷል፡፡
በእርግጥም በይሁዳና በሰማሪያ የተበተኑት አማኞች ወንጌልን ሰብከዋል፡፡ በነዚያ
ቦታዎች ወንጌልን እንዲያደርሱ የታዘዙት ትዕዛዝ ያኔ ተፈፀመ /ሐዋ.1፡8/፡፡
ሐዋ 8፡4-25ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ምን ምን ትምህርት ተገልጿል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሰማርያውያን ከሃይማኖታዊውም ይዘት አንፃር ግማሽ እስራኤላውያን ነበሩ፡፡ አምስቱን
የሙሴ መጽሐፍት ብቻ የሚቀበሉ፣ አንድ አምላክ አለ ብቻ ባዮች /ሞኖቴይስትስ
ወይም የስላሴን ትምህርት የማይቀበሉ/፣ ግዝረትን የሚያካሂዱና መሲሁን የሚጠብቁ
ነበሩ፡፡ ለአይሁዶች የሰማሪያውያን እምነት የተሳሳተ ነበር፣ ማለትም ሳምራውያን
በእስራኤል የቃልኪዳን በረከት ውስጥ ተካፋዮች አይሆኑም፡፡
የሰማርያውያን ያልተጠበቀ መለወጥ በኢየሩሳሌም ያለችውን ቤተክርስቲያን
ስላስገረመ ሁኔታውን ለማየት ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው፡፡ እግዚአብሐር
ጴጥሮስና ዮሐንስ እስኪመጡ ድረስ መንፈስ ቅዱስን አለመስጠቱ /ሐዋ.ሥራ 8፡1417/ ሰማርያውያኑ እንደ ሙሉ የቤተ እምነቱ አባላት ተቀባይነት ሊያገኙ እንደሚገባ
ለሐዋርያቱ ለማስረዳት ሊሆን ይችላል/ሐዋ.ሥራ 11፡1-18/፡፡
ሆኖም በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ በሐዋ.ሥራ 8፡26-39 የፊሊጶስንና ከመጽሐፍ ቅዱስ
ጥናት በኋላ ለመጠመቅ ጥያቄ ያቀረበውን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ታሪክ እናገኛለን፡፡
“ከዚያም ሁለቱ አብረው ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው /
ሐዋ.ሥራ 8፡38/፡፡
መጀመሪያ ሳምራውያኑ ከዚያም ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣውና ከአይሁድ
ውጪ የሆነው ኢትዮጵያዊ ተለወጡ፡፡ ልክ በትንቢት እንደተነገረው ወንጌል
የእስራኤልን ድንበሮች አልፎ ወደ አለም እየደረሰ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ግን ገና ጅማሮ ብቻ
ነበር፤ እነዚያ ቀደምት አይሁድ አማኞች ያኔ በሚታወቀው ዓለም ሁሉ የኃጢአትን
ቅጣት ስለከፈለውና ለሁሉም የመዳን ተስፋን ስለሰጠው የኢየሱስ ሞት ዜና በፍጥነት
ሊያደርሱ ነበር፡፡
ጴጥሮስ ሲሞንን “በመራራነት ተሞልተህ፣ በዐመፅ ሰንሰለት ተይዘሃል”/ሐዋ. ሥራ 8፡
23/ ብሎ ነገረው፡፡ ለችግሩ የሰጠው መፍትሔ ምን ነበር? በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ
ለሚኖሩትስ የኛ መፍትሔ ምንድነው?
በኢየሩሳሌም በቤተክርስቲያን ላይ የመጣው ስደት ለወንጌል
ሥራ ትልቅ ጉልበትን ሰጥቷል፡፡ ቃሉን የመስበኩ ሥራ በዚያ ቦታ ስኬትን አግኝቶ ነበር፤
ነገር ግን ወደ ዓለም ሁሉ የመሄድን ተልዕኮ ረስተው በዚያ ብዙ እንዳይቆዩ ያሰጋ ነበር፡
፡ ክፉውን መዋጋት /መቃወም/ የሚቻልበት ኃይል የሚገኘው ወደፊት በሚገሰግስ
አገልግሎት አማካኝነት መሆኑን ረስተው በኢየሩሳሌም ያለችዋን ቤተክርስቲያን
ከጠላት ጥቃት ከመጠበቅ የበለጠ ሌላ አስፈላጊ ስራ የለም ብለው ማሰብ ጀመሩ፡
፡ አዲስ አማኞች ወንጌልን ላልሰሙት እንዲያደርሱ ከማሰልጠን ይልቅ ቀደም ብሎ
በተሠራው ሥራ ረክቶ ወደ መቀመጥ አደገኛ ሁኔታ እያዘነበሉ ነበር፡፡ የርሱን ወኪሎች
ለሌሎች ሊሰሩ ወደሚችሉባቸው ቦታዎች ለመበተን እግዚአብሔር ስደት በነርሱ
ላይ እንዲመጣ ፈቀደ፡፡ ከኢየሩሳሌም ሲወጡ በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ፡፡”Ellen
white, The Acts of the Apostles, P.105
1. ከላይ እንደተጠቀሰውና ቀደምቷ ቤተክርስቲያን እንዳጋጠማት ባከናወኑትና
በራሳቸው የመርካትን አደጋ በተመለከተ ኤለን ጂ. ኃይት የፃፈችውን
በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡ በመጀመሪያ በጊዜው ከገነነው አመለካከት በተቃራኒ
ብዙ አይሁዳውያን የኢየሱስን መሲህነት ተቀብለዋል፡፡ ከዚያም በላይ
አስፈላጊው ነገር እንደ ሕዝብ ከዚህ ምን ትምህርት ልንወስድ ይገባናል?
ማድረግ ያለብንን ማለትም ለዓለም መድረስን ትተን ያለንን በመከላከል ብቻ
አለመጠመዳችንን በምን ማረጋገጥ እንችላለን?
2. የሐዋርያት ዘመን በአይሁዳውያንና በሰማርያውያን መካከል ለረዥም
ዘመናት የቆየ ጥላቻ የነገሰበት ነበር፡፡ አይሁድ የሆነው ፊሊጶስ ስለ ኢየሱስ
በሰማርያ መስበኩ ምን ያስተምረናል? እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን
ባህልና ጎሳ ነክ ግጭቶች የማይነኩን አይደለንም፡፡ መስቀሉ በእግዚአብሔር
ዘንድ ሁላችንም አንድ ስለመሆናችን የሚያስተምረን እንዴት ነው? የክርስቶስ
ሞት ለሁሉም የመሆኑ እውነታ ስለ እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ ዋጋ ምን
ያስተምረናል?
3. ፊሊጶስ ኢትዮጵያዊውን የቀረበው እንዴት ነበር /ሐዋ. 8፡27-30/?
ወንጌሉን ለሌሎች ለማድረስ እድሎችን ለመጠቀም የበለጠ ዝግጁዎች
መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
4. ከሐዋ.ሥራ 6 -- 8 ባለው ክፍል ውስጥ ቤተክርስትያናችን የበለጠ ውጤታማ
በሆነ መልኩ እንድትሠራ ሊረዷት የሚችሉ ምን ትምህርቶችን አገኘን?