የሐዋሪያት ስራ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2018

ነሐሴ 26-ጳጉሜ 2

አስረኛ ትምህርት

Sept 1-7


ሦስተኛው ሚስዮናዊ ጉዞ



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ የሐዋ. ሥራ 18፡24-28፤ ሐዋ. ሥራ 19፤የሐዋ. 20፡ 7-12፣15-27፤ 2 ቆሮ. 4፡8-14፤ የሐዋ. ሥራ 21፡1-15፡፡


መታሰቢያ ጥቅስ፡-“ይሁን እንጂ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት።” (የሐዋ. ሥራ 20፡ 24)

ሉ ቃስ የጳውሎስን ሦስተኛ ጉዞ እንደ ጻፈው ጉዞው የቀጠለው ሁለተኛውን ጉዞ ወዲያውኑ ተከትሎ ነበር፡፡ ጽሑፉ እንደሚለው የጳውሎስ የአገልግሎት ማዕከል በሆነችው በአንጾኪያ የተወሰነ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ሐዋሪያው ሌላ ጉዞ አድርጓል። አከታትሎ ‘‘በገላትያናበፍርግያአገሮችከቦታቦታበመዘዋወርደቀመዛሙርትንሁሉአበረ ታታ’’ሐዋ. 18፡23፡፡በመሆኑም የመጀመሪያዎቹ 2414 ኪሎ ሜትሮች(1,500 ማይሎች) ጉዞ የተጠቃለለው በአንድ አረፍተ ነገር ነው።

ይህም የሆነበት ምክንያት የጉዞው መዳረሻ ኤፌሶን ስለነበረች ነው፤ ጳውሎስ በጉዞው ላይ በሌሎች ከተሞች ሲያልፍ ከነበረው የቆይታ ጊዜ ይልቅ በዚህች ከተማ ረዘም ያለ ጊዜ አሳልፏል፡፡ ከወንጌል አገልግሎት አንጻር በኤፌሶን የነበረው አገልገሎት ፍሬያማ ነበር፤የጳውሎስም የስብከት ተፅዕኖ በእስያ አውራጃዎች ሁሉ ላይ ተዳርሶ ነበር(የሐዋ. ሥራ 19፡10፣26)፡፡ ምናልባትም የቆላስያስ፣የኢያራ እና የሎዶቅያ አብያተ ክርስቲያናት ምናልባትም በኤጳፍራ አማካኝነት የተመሰረቱት በዚህ ወቅት ሳይሆን አይቀርም(ቆላ. 4፡12፣13)፡፡ ይህም ሰው ከጳውሎስ ጋር ከሰሩት ሰዎች መካከል አንዱ ነው(ቆላ. 1፡7፤ ፊሊሞ. 23)፡፡

ስለዚህ ጉዞ የሚያስገርመው ነገር በሐዋርያት ሥራ ከተመዘገቡት የጳውሎስ ጉዞዎች የመጨረሻ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ጳውሎስ ነጻ ሰው ሆኖ ከተጓዛቸው ጉዞዎች ማለታችን እንጂ ከዚህ ጉዞ በኋላም ሉቃስ እራሱ ወደ ሮም ያደረገውን ጉዞ መዝግቦት እናገኛለን፤ ነገር ግን ያን ጉዞ ያደረገው እንደ እስረኛ ነበር፡፡ *የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለጳጉሜ 3 ሰንበት ይዘጋጁ፡፡

ነሐሴ 27
Sep 02

ኤፌሶን፡ ክፍል አንድ


በሐዋርያት ሥራ 18፡24-28 እንደ ተመዘገበው ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን በጉዞ ላይ እያለ አጵሎስ የተባለ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፡፡ ይህም ሰው አንደበተ ርቱዕና የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ ያስተዋለ ሰው ነበር፡፡ ሉቃስ እርሱን የገለጸበት መንገድ በትክክልም አጵሎስ የኢየሱስ ተከታይ እንደ ነበር ያስረዳል።‘‘ይህሰው፣የጌታንመንገ ድየተማረ፣ስለኢየሱስምበትክክልየሚናገርናበመንፈስእየተቃጠለ የሚያስተምርነበር፡ ፡’’ (የሐዋ. ሥራ 18፡25)፡፡ነገር ግን እርሱ ያውቅ የነበረው የዮሐንስን ጥምቅት ብቻ ነበር፡፡ አጵሎስ በዮሐንስ መጥመቁ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስ ከነበረው ምድራዊ የአገልግሎት ሕይወት ጋር የሚተዋወቅ ሲሆን፤ ነገር ግን በዚያ አካባቢ ብዙም ሳይቆይ እርቆ ሳይሄድ አልቀረም፤ምን አልባትም ከሕማማቱ/ከበዓለ ሃምሳ ትዕይንቶች/ በፊት ወደ አሌክሳንድሪያ ተመልሶ ሊሆን ይችላል፡፡

ለዚህም ነበር አቂላና ጵርስቅላ ተጨማሪ ግንዛቤን ሲሰጡት የነበረው፡፡ እናም ከቅዱሳት መጽሐፍት ኢየሱስ እርሱ የእስራኤል መሲህ እንደነበር አሳዩት (ሐዋ 18፡28)፤አጵሎስ ከክርስቶስ ኢየሱስ አገልገሎት ጀምሮ የነበረውን ተጨማሪ የክርስትና እድገት መስማት ነበረበት፡፡ ሆኖም ግን አቂላና ጵርስቅላ ለአጵሎስ ከዚህ የሚበልጥም ነገር ነው ያደረጉለት፤ በኤፌሶን ከሚገኙ ሌሎች አማኞች ጋር በመሆን በአካያ ወደሚገኙ አብያተ ክርስትያናት የድጋፍ ደብዳቤ አስይዘው በመላክ (ሐዋ. 18፡27) በቆሮንቶስ ውጤታማ አገልግሎት እንዲኖረው አድርገዋል (1 ቆሮ. 3፡4-6፤ 4፡6፤ 16፡12)፡፡ የሐዋ. 19፡1-7 ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ ኤፌሶን በደረሰ ጊዜ ያጋጠመው ምን ነበር?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የአጵሎስ ታሪክ ጳውሎስ ኤፌሶን በደረሰ ጊዜ ካገኛቸው አስራ ሁለት ሰዎች ጋር ተያያዥነት ያለው ነው፤ ምክንያቱም ሁኔታቸው ተመሳሳይ ነበረ፡፡ ሰዎቹ የተሰጣቸው መገለጫ “ደቀመዛሙርት” (የሐዋ. 19፡1) የሚል ሲሆን ጳውሎስም ለእነርሱ ያቀረበው ጥያቄም (የሐዋ. 19፡2) በግልጽ የሚያሳየው በኢየሱስ ያመኑ ሰዎች እንደነበሩ ነው፡፡ በተመሳሳይም ለጳውሎስ የሰጡት መልስ የሚያሳየው እንደ አጵሎስ ሁሉ በመጀመሪያ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት የነበሩና የበዓለ ሃምሳው ልምምድ የሌላቸው የኢየሱስ ተከታዮች መሆናቸውን ነው፡፡ ከጌታ ጋር በሚኖረው የጠለቀ ትስስር የሚገኘውን ደስታ የማግኘት እድል ሊኖራቸው የተገባ ሰዎች ነበሩ፡፡ “ጳውሎስ ኤፌሶን በደረሰ ጊዜ አስራ ሁለት የሚሆኑ ወንድሞችን አገኘ፤ ልክ እንደ አጵሎስ ሁሉ እነርሱም የመጥመቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት የነበሩ እና እንደ እርሱ ሁሉ ስለ ክርስቶስ ተልዕኮ የተወሰነ ግንዛቤ ነበራቸው፡፡ የአጵሎስ አይነት ችሎታ ባይኖራቸውም በተመሳሳይ ቅንነትና ታማኝነት የተቀበሉትን እውነት ለሌላው ለማድረስ የሚወዱ ሰዎች ነበሩ፡፡” —Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 282. እንደ አዲስ መጠመቃቸውን ማየት ያለብን ሁኔታው ልዩ ከመሆኑ አንፃር ሊሆን ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከሌላ የክርስትና ቤተ እምነት አልመጡም፤ወይም የነበራቸውን የሕይወት ልምምድ የቀየሩም አይደሉም፤ ነገር ግን እራሳቸውን ከዋናው የክርስትና ልምምድ ጋር እያዋሃዱ ነበር፡፡ እናም መንፈስ ቅዱስን በመቀበል በሌሎች ቋንቋዎች(ልሳኖች) መናገር ጀመሩ። ይህም ማለት ምናልባትም ክርስትያን ሚስዮናውያንሳይሆኑ አይቀሩም፤ እንደ አጵሎስ ሁሉ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በሚወጡበት ሁሉ ለመመስከር የሚያስችላቸውን ሃይል በሙላት አግኝተዋል፡፡

ነሐሴ 28
Sep 03

ኤፌሶን፡ ክፍል ሁለት


በኤፌሶን፤ ጳውሎስ በመጀመሪያ የሰበከው በምኩራብ ውስጥ ነበር፡፡ ተቃውሞ በተነሳ ጊዜ ግን እርሱና አዲስ አማኞቹ በጢራኖስ ወደሚገኘው የትምህርት መስጫ አዳራሽ መሰብሰቢያቸውን ቀየሩ። በእዚያም ጳውሎስ ለሁለት አመታት በየእለቱ ቃሉን ይናገር ነበር (የሐዋ. ሥራ 19፡8-10)፡፡የሉቃስ ማጠቃለያ በኤፌሶን የነበረውን የጳውሎስ አገልግሎት የሚያስቀምጠው በሁሉም አውራጃዎች (ግዛቶች) ወንጌል በስፋት ተዳርሶ እንደነበር ነው (የሐዋ. ሥራ 19፡10፣26)፡፡ የሐዋርያት ሥራ 19፡11-20 ላይ አስማትና ሌሎች የአጉል ልማድ እምነቶች የተለመዱ በሆኑበት ከተማ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሃይል አሸናፊነት የሚያሳዩና ተአምራትን የያዙ ታሪኮችን ሉቃስ በጽሁፉ ውስጥ አካቷል፡፡

ጥያቄ ውስጥ የማይገባው ነገር እግዚአብሔር ጳውሎስን በመጠቀም መፈወሱ ሲሆን በሐዋሪያው የተነኩ መሀረቦችና ሽርጦች ሳይቀሩ የመፈወስ ኃይል ነበራቸው(የሐዋ. 19፡12)። ይህ ለአንዳንዶች እንግዳ ነገር ሊመስል ይችላል፤ ፈውሱ ግን ኢየሱስ ደም ሲፈሳት የነበረቸውን ሴት ከፈወሰበት ፈውስ ጋር ተመሳሳይነት አለው (ሉቃ 8፡44)፡ ፡ የኤፌሶን ሰዎች የልማድ እምነቶች እግዚአብሔር “ለየት ያለ” ተዓምርን እንዲፈጽም ምክንያት ሆነዋል ይላል ሉቃስ (ሐዋ. 19፡11)፡፡ ይህም እግዚአብሔር የሰዎችን ፍላጎት በማስተዋላቸው ልክ (ደረጃ) እንደሚያሟላ ምሳሌ ይሰጠናል፡፡

በኤፌሶን በነበረው የተልዕኮ ውጤታማነት የረካው ጳውሎስ ወደ እየሩሳሌም ለመሔድ ወሰነ፡፡ ሉቃስ ለዚህ ጉዞ ምክንያትን አልሰጠም፤ነገር ግን ከራሱ ከጳውሎስ ጽሁፎች እንደምንረዳው በእየሩሳሌም በምትገኘው ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጠረውን ድህነት በተወሰነ መልኩ ለመቅረፍ የሰበሰበውን እርዳታ ለማድረስ ምኞቱ እንደ ነበር ነው (ሮሜ 15፡25-27፣ 1 ቆሮ. 16፡1-3)፡፡ በመጀመሪያዎቹ ዓመታትየሸቀጦች መሰብሰብና እና በቀላውዲዎስ ዘመን የተነሳው አስከፊ ረሃብ የአይሁድ አማኞችን አደህይቶ ነበር። እናም ጳውሎስም ለእርዳታ ያቀረቡትን ተማጽኖ ሲያይ(ገላ. 2፡ 10) ምንም እንኳን ወደ እየሩሳሌም በመውጣቱ የሚገጥመውን ችግር ቢያውቅም አጋጣሚውን በሐዋሪያነቱ ላይ ያላቸውን አመኔታና የተለያየ የባሕል ስብጥር ያላትን ቤተክርስትያን ህብረት ለማጠናከር ለመጠቀም አሰበ (የሐዋ. 20፡22፣23፤ ሮሜ 15፡ 31)፡፡

ሐዋ. ሥራ 19፡23-41ን ያንብቡ፡፡ በኤፌሶን ቆይታው መጨረሻ አካባቢ በጳውሎስ ላይ ተነስቶ የነበረው ተቃውሞ ትክክለኛ ምክንያት ምን ነበር?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ተቃውሞው ከአረማውያን አምልኮ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም በጳውሎስ አገልግሎት ምክንያት አምልኮው የከፋ ኪሳራ ገጥሞት ስለነበር ነው፡፡ የዲሜጥሮስ ትክክለኛ እሳቤ ከገንዘብ ጋር የተቆራኘ ቢሆንም ነገሩን ወደ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ቀይሮት ነበር፤ ምክንያቱም አርጤምስ (ዲያና) ቤተመቅድስ ይገኝ የነበረው በኤፌሶን ስለነበር ነው። ይህም ቤተመቅድስ ጥንታዊ ሆነው አስደናቂ ታሪክ ካለቸው ሰባቱ ቅርሶች አንዱ ሆኖ ተመዘገቧል፡፡

ሐዋ. ሥራ 19፡27ን ያንብቡ፡፡ ዲሚጥሮስ የገንዘብ ምንጩ እንዳይቋረጥ ጥበብ በተሞላበት መልኩ ሃይማኖታዊ ተቆርቋሪነትን እንዴት እንዳነሳሳ ይመልከቱ፡ ፡ እኛም እንደ ክርስትያን እምነታችንን ወይም ለእምነታችን ተቆርቋሪ በመምሰል በተመሳሳይ መልኩላለመጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገባን ለምንድን ነው?

ነሐሴ 29
Sep 04

ጢሮአዳ


ከሁከቱ በኋላ (ሐዋ. ሥራ 19፡23-41) ጳውሎስ ኤፌሶንን ለቆ ለመውጣት ወሰነ፡፡ ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደውን ቀጥተኛ መንገድ አልነበረም የተጠቀመው። ቀጥተኛውን መንገድ ትቶ በመቄዶንያና በአካይ በኩል አለፈ(የሐዋ. 20፡1-3)፡፡ በጉዞም ላይ የአህዛብ ቤተክርስቲያናትን የሚወክሉ የተወሰኑ ሰዎች አብረውት ነበሩ (የሐዋ. 20፡4)፡፡

ሐዋ. 20፡1-7 ያንብቡ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች የሰንበት ቀን ወደ እሁድ እንደተለወጠእንደ ማረጋገጫነት ይቀርባሉ። የዚህ ሃሳብ ስህተቱ ምንድን ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ጳውሎስ ጉዞውን ገታ በማድረግ በጢሮአዳ ቆይታ አደረገ። ይህም ቆይታው የተጠናቀቀው “በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን”(የሐዋ. 20፡7) በቤተክርስቲያን ስብሰባ ነበር፡፡ በህብረት የነበሩት “እንጀራን ለመቁረስ” ነበር። ምናልባትም የጌታ እራት ሊሆን ይችላል፡፡ በቀደመው ጊዜ ከነበረች የእየሩሳሌም ቤተክርስትያን ጀምሮ ማዕድን አብሮ የመቁረስ ጊዜ የጌታ እራትን ተከትሎ ይከናወን ነበር (ሐዋ. 2፡42፣46)። በዚህ ጊዜ ግን በህብረት መመገቡ አብሮ ተከናውኖ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡ በዚህ ስፍራ ስለ ጽዋ ወይም ስለጸሎት አለመጠቀሱ ግምቱን ዋጋቢስ አያደርገውም፡፡ ዋናው ሃሳብ ግን ይህ ክፍል ብዙ ጊዜ በጳውሎስ ዘመን የነበሩ ቢያንስ ደግሞ የአህዛብ አብያተ ክርሰትያናት ሰንበትን በእሁድ የአምልኮ ቀን ተክተውት ነበር ለማለት በማስረጃነት ይቀርባል፡፡

ነገር ግን እንዲህ ብለን ከመደምደማችን በፊት ይህ ስብሰባ የተከናወነበትን ትክክለኛ ቀን እንዲሁም የስብሰባውን አይነት ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የጳውሎስ መልዕክት እስከ እኩለ ሌሊት ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ፤ መብራቶችን እንደተጠቀሙ መገለጹ (ሐዋ. 20፡ 7-8) ደግሞም እስከ ንጋትም የቀጠለ መሆኑን እንጂ (የሐዋ. 20፡11) የአውጤኪስን ከባድ እንቅልፍም መጥቀስ አስፈላጊ ባልሆነ ነበር (ሐዋ. 20፡9)። ይህም የምሽት ስብሰባ መሆኑን ያረጋግጥልናል፡፡

ጥያቄው ከእሁድ ማለዳ በፊት የነበረው ምሽት ነው ወይስ ከእሁድ በኋላ የነበረው ምሽት የሚለው ነው። መልሱ የሚወሰነው ሉቃስ በተጠቀመው የጊዜ አቆጣጠር ዘዴ ይሆናል፤ ይህም የአይሁድን የጊዜ አቆጣጠር ተጠቅሞ ከሆነ ከፀሐይ ግባት እስከ ፀሐይ ግባት ወይም የሮማውያን የጊዜ አቆጣጠር ከሆነ ደግሞ ከእኩለ ሌሊት እስከ እኩለ ሌሊት ይሆናል፡፡ የቀደመውን የጊዜ አቆጣጠር ተጠቅሞ ከሆነ ቀኑ ቅዳሜ ምሽት ነበር፤ የኋለኛውን ተጠቅሞ ከሆነ ቀኑ እሁድ ምሽት ነበር፡፡

በሁለቱም መንገድ የሐዋሪያት ሥራ 20፡7-12 አውድ የሚነግረን፤ ስብሰባው እሁድ ምሽት ተከናውኖ ከነበር እንኳን ስብሰባው መደበኛ የቤተክርስትያን ጉባኤ እንዳልነበረ ነው። ነገር ግን ጳውሎስ በሚቀጥለው ማለዳ ጉዞ ለማድረግ በማሰቡ የተደረገ ልዩ ስብስባ ነበር፡፡ እናም ይህ የተለየና የማይገናኝ ክፍል እሁድን ለመጠበቅ እንደ ድጋፍ ማረጋገጫ ተደርጎ ሊቀርብ መቻሉ በራሱ የሚከብድ ነው፡፡ እውነታው ደግሞ አለመሆኑ ነው፡፡

ሰባተኛውን ቀን ሰንበትን መጠበቅ ትክክል እንደሆነ የሚያስረዱ ምክንያቶች ላይ ቆይታ ያድረጉ። እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ክርስትያንነታችንና የሦስቱን መላእክት መልዕክት ለዓለም ለማድረስ ከተሰጠን ጥሪ አንጻር ስለ ስንበት የተሰጡ ጠንካራ የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፎች (ማረጋገጫዎች) ስለ ማንነታችን ምን ያህል ያስገነዝቡናል?

ነሐሴ 30
Sep 05

ሚሊጢን


ጳውሎስ ወደ እየሩሳሌም በጉዞ ላይ እያለ በሚሊጢን ሌላ ቆይታ አድርጎ ነበር። በዚህ ቆይታው ነበር ከኤፌሶን ለመጡ የቤተክሰርስቲያን መሪዎች የስንብት ንግግር የማድረግን እድል ያገኘው፡፡

ሐዋርያት ሥራ 20፡15-27 ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በንግግሩ መግቢያ ላይ አፅንእት የሰጠው ምን ነበር?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ሮምና እስፔንን የሚያጠቃልል ሌላ ጉዞ እቅዱ ውስጥ ስለነበር (ሮሜ 15፡2229) ጳውሎስ ከዚህ በኋላ ወደ እስያ እንደማይመለስ ተረድቷል፡፡ አናም ንግግሩን በመቀጠል በኤፌሶን ባሳለፋቸው አመታት የነበረውን ቆይታ በዝርዝር አቀረበ፡፡ የዚህ አይነቱ ገለጻ ዋና አላማው ስላለፈው ማውሳት ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ከፊቱ ባለው ጊዜ በእየሩሳሌም ምን እንደሚያጋጥመው ስለሚያስፈራው ነበር፡፡ የጳውሎስ ፍርሃት ያለምክንያት አልነበረም፡፡ በኢየሩሳሌም የሚገኙ አማኞች በጠላትነት ሳይሆን ባለፈው የአሳድጅነት ሕይወቱና ከግዝረት ነጻ በሆነው የወንጌል ስበከቱ ምክንያት እርሱን የሚያዩት በጥረጣሬ ነበር (ሐዋ. 21፡20-26)፡፡ በአይሁድ መሪዎች ዘንድ ከኃዲና መናፍቅ ነበር (ሐዋ. 23፡1፣2)፡፡ በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ላይ በተለይም ደግሞ የሮም አገዛዝ የተበላሸ በሆነበት ጊዜ ይሁዳም አብዮታዊ እና ብሔራዊ በሆኑ ጉዳዮች ተጨንቃ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ቤተክርስትያንን ጨምሮ በሁሉም የአይሁድ ማህበረሰብ ላይ ተጽዕኖ ነበረው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የቀድሞው ፈሪሳዊ በአህዛብ መካከል ያከናወናቸው ሥራዎቹ እንደ ስም አጉዳፊ እንዲፈረጅ አድርገውታል (ሐዋ 21፡27-36)፡፡

ጳውሎስ ሌላ ተጨማሪ ጭንቀት ነበረበት፡፡ ሐዋርያት ሥራ 20፡28-31 ላይ ጳውሎስ በኤፌሶን የሚገኙ የቤተክርስቲያን መሪዎች የሀሰተኛ መምህራንን ጉዳይ እንዴት መፍታት እንዳባለቸው ትኩረት ሰጥቷል፡፡ እነዚህን ሃሰተኛ መምህራን ጳውሎስ የመስላቸው በጎችን ከመንገዳቸው ለማሳትና ለማስቀየር እንደሚሞክሩ ነጣቂ ተኩላዎች አድጎር ነበር፡፡ እናም በቀድሞው ዘመን፣ በቤተክርስትያን ውስጥ እንኳን ሳይቀር ሀሰተኛ መምህራን ነበሩ፡፡ ሰሎሞን በራሱ ዘመንና በሌላ አውድ እንደተናገረው “ከፀሐይበታችምንምአዲስነገርየለም።”(መክ1፡9አ.መ.ት)፡፡ የቤተክርስትያን ታሪክ እንደሚገልጽልን ሃሰተኛ መምህራን በቤተክርስትያን ላይ የከፋ ጉዳት አስከትለው እንደነበር ነው፡፡ይህ ችግር ደግሞ እስከ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል (2ኛ ጢሞ 4፡3)፡፡ ጳውሎስ በአእምሮው ውስጥ የበዙ ጉዳዮችና ጭንቀቶች እነደነበሩ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ቢሆንም ግን የእርሱ ታማኝነትና ትጋት በጭራሽ አልተለወጠም ነበር፡፡ 2ኛ ቆሮ. 4፡8-14 ያንብቡ፡፡ በተለይ ፈተና ሲመጣለራሳችን ልንተገብረው ስለሚገባ ነገር ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ምን እያለ ነው? ጳውሎስ የመጨረሻ ተስፋውን ማን ላይ አደረገ?

ጳጉሜ 1
Sep 06

ጢሮስ እና ቂሳሪያ


ከሚሊጢን በኋላ ሉቃስ የጳውሎስን ጉዞ በዝርዝር አስፍሮታል፡፡ ወደ እየሩሳሌም በሚያደርገው ጉዞ ላይ፣መርከቧ ጭነቷን ባራገፈችበት በፊንቄያራውያን የባህር ዳርቻ፣በጢሮስ አንድ ሳምንት አሳለፈ (ሐዋ. 21፡1-6)፡፡ በዚህ ስፍራ እያለ ግን በዚያ የሚኖሩ አማኞች ወደ እየሩሳሌም ሊወጣ እንደማይገባ ሞገቱት። እነዚህ አማኞች በመንፈስ ተመርተው ጳውሎስን ወደ እየሩሳሌም እንዳይሄድ ማሳሰባቸው አስቀድሞ ለሐዋርያው ከተሰጠው ምሪት ጋር በእርግጥም አይጣረስም፡፡ ሐዋርያት ሥራ 19፡21 ላይ ያለው ክፍል ግሪኩ ሲያስቀምጠው etheto en tò pneumati (ኤትዮነቱ ኤነቱ ፒትማነቲ) ይለዋል። ሊተረጎም የሚገባውም “በመንፈስ ወሰነ/አሰበ” (1962 እትም) በሚል እንጂ ጳውሎስ ሁሉን ለማድረግ በራሱ እንደወሰነ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፡ ፡ ዋናው ሃሳብ መንፈስ በጢሮስ ለሚገኙ ክርስትያኖች ጳውሎስ ሊገጥመው ስላለው አደጋ ማሳየቱ ሲሆን፤እናም ከዚህ በመነሳት እንደ ሰው በመጨነቅ የጉዞ ዕቅዱን እንዲቀይር ሃሳብን ማቅረባቸው ነው፡፡ ጳውሎስ እራሱ በእየሩሳሌም በእርሱ ላይ ምን ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ አልነበረም (ሐዋ. 20፡22፣23)፡፡ መለኮታዊ ምሪት ሁሉንም ነገር ሁሌ ግልጽ ላያደርግ ይችላል፤እንደ ጳውሎስ ላለ ሰው እንኳን ቢሆን፡፡

ሐዋ. 21፡10-14 ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ ወደ እየሩሳሌም ስለሚያደርገው ጉዞ በቂሳሪያ ምን አይነት ለየት ያለ ክስተትተከናወነ?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

አጋቦስ ከእየሩሳሌም የሆነ ነብይ ሲሆን ስለ እርሱም በሐዋርያት ሥራ 11፡27-30 ስለ ረሀብ በሚናገረው ክፍል ላይ ቀድሞ ተነግሯል፡፡ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን አንዳንድ ትንቢቶች (ለምሳሌ ኢሳ. 20፡1-6፣ ኤር. 13፡1-10) መልእክቱ ድርጊታዊ ነበር። በጳውሎስ ላይ እየሩሳሌም ሲደርስ ሊሆን ያለውን ስዕላዊ በሆነ መልኩ በግልጽ ያሳየና ጠላቶቹ እንዴት አድርገው ለአህዛብ (ለሮማውያን) አሳልፈው እንደሚሰጡት ያስቀመጠ ነበር፡፡

ከጳውሎስ ጋር የነበሩት ሰዎች የአጋቦስን መልዕክት እንደ ትንቢት ሳይሆን በግልጽ እንደተሰጠ ማስጠንቀቂያ በመውሰድ እና የማሳመኛ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ በብርቱ ጥረው ነበር፡፡ ጳውሎስም ለእርሱ ያላቸውን አሳቢነት በጥልቀት ያስተዋለ ቢሆንም ተልዕኮውን ለመፈጸም ወስኖ ነበር። ሕይወቱን የሚያስከፍለው ቢሆንም እንኳን፤ ለእርሱ የወንጌል መዳረስና የቤተክርስትያን አንድነት ከራሱ የግል ደህንነት ወይም ፍላጎት ይልቅ ይበልጥ አስፈላጊዎች ነበሩ፡፡

“ሐዋርያው እየሩሳሌምን እንዲህ በሐዘን በተሞላ ልብ ቀርቧት አያውቅም፡ ፡ ጥቂት ወዳጆችና የበዙ ጠላቶች እንደሚገጥሙት ያውቃል፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ ወዳልተቀበለችውና ወደ ገደለችው ደግሞም የመለኮትን ማስጠንቀቂያ ወደ ገፋችውከተማ እየተጠጋ ነበር፡፡”(Ellen G. White, The Acts of the Apostles, pp. 397, 398.)

ጳውሎስን፡- ብዙዎች በተሳሳተ መልኩ ተረድተውታል። ግፍ ተሰርቶበታል፣ ተንገላቷል፣ ነቀፋም ደርሶበታል ነገር ግን በእምነቱ ጸና፡፡ እኛም ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍን እንዴት ልንማር እንችላለን?

ጳጉሜ 2
Sep 07
ጳጉሜ 2

ተጨማሪ ጥናት፡


“ወንጌል በመሰበኩ ምክንያት የመጣው ስኬት የአይሁድን ቁጣ እንደ አዲስ ቀስቅሶታል፡፡ አዲሱ አስተምህሮ በሁሉም ሥፍራ መዳረሱ ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው። በዚህም አስተምሮ ነው አይሁድ ይጠብቁት ከነበረው የሜዳዊ ሕግ ስርዓቶች ነጻየሆኑት፤ አህዛብም ከአይሁድ እኩል የአብርሃም ልጅነትን መብት አምነው የተቀበሉት…. እርሱ(ጳውሎስ) እርግጠኛ በሆነ ንግግሩ“ ግሪክ ወይም አይሁዳዊ፣የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣…”(ቆላ. 3፡ 11) በማለቱ ምክንያት ይህ ንግግሩ በጠላቶቹ ዘንድ እንደ የድፍረት ስድብ ተፈርጆ ነበር። እናም ድምጹ ጸጥ ማለት እንዳለበት ወስነው ነበር፡፡”—Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 390.

“እናም በእምነት ወንድሞቹ ከሆኑት በሚቀርብለት ርህራሄ እና ድጋፍ ላይ እንኳን አመኔታ አልነበረውም፡፡ ያልተለወጡት አይሁድ በሚጓዝበት ሁሉ በመከተል ከእርሱ የተቃረኑ ሃሳቦችን (ሪፖርት)፤ ስለ እርሱም ይሁን ስለ ሥራው፤ በደብዳቤም ይሁን በአካል በመገኘት በእየሩሳሌም ለመዝራት የዘገዩ አልነበሩም። እናም ደግሞ አንዳንድ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንኳን ሳይቀሩ እነዚህን ተራ ወሬዎች እንደ እውነት በመቀበል እነዚህን ሰዎች ለመቃረንም ሆነ ከእነርሱ ጋር ህብረት ላለማድረግ ፍላጎት አላሳዩም ነበር፡፡”—Page 398.


የመወያያ ጥያቄዎች



፡ 1. ጳውሎስ በኤፌሶን ያገኛቸው አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ቀደም ሲል የመጥምቁ ዮሐንስ ተከታዮች የነበሩ በኋላ ደግሞ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የሆኑ ነበሩ (ሐዋ 19፡1-7)፡፡ ይህን ክፍል በጥልቀት ተጠምቀው የነበሩ፣ከሌላ ቤተ-እምነት የመጡና የአድቬንቲስትን እምነት የተቀላቀሉ ክርስትያኖች እንደገና መጠመቅ እንዳለባቸው ለማስረዳት መጠቀማችን ትክክል የሆነው ለምን ይመስሎታል? አጵሎስ እንደገና ባለመጠመቁ ውስጥስ የምናስተውለው እውነታ ይኖር ይሆን?

2. ጳውሎስ ስለነበረበት ሁኔታ ያስቡ፡፡ በኢየሱስ በማያምኑ በራሱ ወገኖች ተቀባይነት አጣ፤ በኢየሱስ የሚያምኑ ብዙ አይሁድ እንኳን “ዋና መለያዎችን” ለውጧል በሚል ምክንያት ጳውሎስን የሚመለከቱት በትልቅ ጥርጣሬና ባለማመን ነበር፡፡ብዙ አረማውያን እርሱ በሚናገረው ወንጌል ላይ ጥላቻ ነበራቸው፡፡ ግን ይህ ሁሉ ለምን? በዚህ ሁሉ ተቃውሞ ውስጥ ግን ጳውሎስ በጽናት የቀጠለው ለምንድን ነው?

3. የሰንበት ቀን ወደ እሁድ ስለመቀየሩ ወይም ከዚህ በኋላ አስፈላጊ እንዳልሆነ በሰዎች ስለሚነሱ መከራከሪያዎች ያስቡ። ለእነዚህ የመከራከሪያ ሀሳቦች ሰንበትን መታዘዝ በእምነት ከሆነና የመዳናችን ብቸኛ ተስፋ ያረፈበትን በማስተዋል ከሆነ ሌሎቹን ዘጠኙን ትዕዛዛት ከመታዘዝ ተለይቶ ህጋዊነት ሊያስብለው እንደማይችል መልስ ለመስጠት የምንችለው እንዴት ነው?