ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ 1ቆሮ. 10:1–11፣ ራእ. 12:1–17፣ 19:11–15፣ ኤፌ. 1:20፣ ራእ. 11:19፣ 1:10–18፡፡
የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በእርሱ ዙፋን ላይ እንደ ተቀመጥሁ፣ ድል የሚነሳውንም ከእኔ ጋር ዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ፡፡” (ራእ. 3፡21)፡፡ “
አዲስ ኪዳንን ላይ ላዩን በፍጥነት እንኳ ብናነብ አንድ አስፈላጊ እውነት
ይገልጥልናል፤ አዎ አዲስ ኪዳን ከብሉይ ኪዳን ጋር ቀጥተኛ ትስስር
አለው፡፡ ወንጌል እና በደብዳቤ መልክ የቀረቡት የአዲስ ኪዳን መልእክቶች የብሉይ
ኪዳንን ታሪኮች በቀጥተኛ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በማመሳከሪያነት ጥቅም ላይ
ሲያውሉ ይስተዋላሉ፡፡ የሱስ ከራሱና ከአገልግሎቱ ጋር እያነጻጸረ ስለ ብሉይ ኪዳን
ትንቢቶችን ፍጻሜ ማግኘት ስንት ጊዜ ተናግሯል (ማቴ. 26:54፣ 56፣ ማር. 14:49፣
ዮሐ. 13:18፣ 17:12)?
ለዮሐንስ ራእይ መጽሐፍም እንዲሁ ከዚህ ተመሳሳይ ሊባል ይችላል፡፡
በእርግጥ የራዕይን መጽሐፍ ከብሉይ ኪዳን በተለይም ከዳንኤል መጽሐፍ መነጠል
መልእክቱ ትርጉም እንዲያጣ ያደርገዋል፡፡ ሁለቱን መጻሕፍት በተናጥል ሳይሆን
በአንድነት የምናጠናበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፡፡
በራእይ መጽሐፍ የምናገኛቸው አበይት ገጽታ የተላበሱ የብሉይ ኪዳን
ማጣቀሻዎች ከቀሪው የመጽሐፉ አካል ጋር በመሆን የሱስን ገልጠው ያሳያሉ፡፡
መላው የራእይ መጽሐፍ ገጾች ስለ የሱስ ይኸውም ስለ ማንነቱ፣ ለሕዝቡ
ስለከፈለው ውለታ እንዲሁም በመጨረሻው ጊዜ ስለሚያደርግልን ነገር
ይነግረናል፡፡ ማንኛውም በመጨረሻው ጊዜያቶች ላይ የሚደረግ ትኩረት በራእይ
መጽሐፍ በትክክል እንደቀረበው የሱስን የጉዳዩ ፊትና ማዕከል ማድረጉ የግድ
ይሆናል፡፡ የዚህ ሣምንት ትምህርት በራእይ መጽሐፍ የሱስ ላይ ትኩረት
ያደርጋል፡፡
የዳንኤልና የራእይ መጽሐፍ በጋራ ከያዟቸው በርካታ ነገሮች መሃል ሁለቱ
ክፍሎች ማለትም ታሪክን መሰረት ያደረገው አቀራረብ እና የመጨረሻው ጊዜ
ክስተቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለቱም ጽንሰ ሃሳቦች የተወሳሰበ
ተፈጥሮ ይዘው፤ ነገር ግን እርስ በርስ ተሳስረው በሁለቱም መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡
ምንም እንኳ በመጨረሻው ጊዜ ገቢራዊ ከሚሆኑት ታላላቅ ክስተቶች አኳያ
በአነስተኛ መጠን ቢቀርቡም፤ ታሪካዊዎቹን ክስተቶች እንደ ግንባር ቀደሞች ወይም
ምሳሌዎች አድርገን ልንመለከታቸው እንችላለን፡፡ ቀደም ብሎ በብሉይ ኪዳን ታሪክ
ተከስተው የነበሩ ነገሮችን በማጥናት በእኛ ዘመንና ባሻገር በሚኖረው ሁናቴ ላይ
ብርሃን ማግኘት እንችላለን፡፡ የሆነው ሆኖ ይህ መርኅ በዳንኤል እና በራእይ
መጽሐፎች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ቆሮ. 10፡ 1-11፡፡ ከላይ የተነጋገርንባቸውን መርኅዎች
በእነዚህ ቁጥሮች እንዴት እንመለከታቸዋለን?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ባለፈው ሣምንት ጥናታችን በዳንኤል መጽሐፍ (ዳን. 3:6፣ 15፣ 27፣ 6:6–9፣ 2122) ከተመለከትናቸው ታሪኮች ውስጥ አንዳንዶቹ ዓለማቀፋዊ አንደምታ
ባይኖራቸውም ነገር ግን በተወሰነ ደረጃ በራእይ መጽሐፍ የተገለጹትን
የመጨረሻውን ጊዜ ክስተቶች ያንጸባርቃሉ፡፡ እነዚህን ታሪኮች በማጥናት
በመጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በስፋት ከሚጋፈጧቸው ነገሮች መሃል
የአንዳንዶቹን ውጪያዊና ውስጣዊ ሁኔታ እንመለከታለን፡፡ ዛሬ የምንገኝበት ሁናቴ
ምንም ይሁን ምን ምናልባት በጣም አስፈላጊው ነጥብ በመጨረሻ የደኅንነት
ባለቤት ስለ መሆናችን የተሰጠን ማረጋገጫ ነው፡፡ የራእይ መጽሐፍ የቱንም ዓይነት
ተጨማሪ ትምህርት ቢያስተምር፤ ለታማኙ ባለ ድልነት ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡
የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነርሱም ከምዕ. 1-11-ታሪክ ነክ፤ ከምዕ. 13-22 ደግሞ የመጨረሻው ጊዜ መልእክቶች ናቸው፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 12፡1-17፡፡ ይህን ምዕራፍ የት ላይ እንመድበው--ታሪክ
ነክ ወይስ የመጨረሻው ጊዜ ክስተት--ለምን?
እንደምንመለከተው ይህ ምዕራፍ ከሁለቱም ክፍሎች ይመደባል፡፡ ለምን?
ምክንያቱም ስለ ታሪካዊ ሁነቶች ስለሚያወራ--ስለ ሰይጣን ከሰማይ መባረር (ራእ.
12፡7-9)፣ ሰይጣን በህፃኑ የሱስ ላይ ሊፈጽም ስለነበረው ጥቃት (ራእ. 12፡14)፣
እንዲሁም ተከታታይነት ስለ ነበረው የቤተክርስቲያን ስደት ታሪክ (ራእ. 12፡14-16)
ከተናገረ በኋላ በመጨረሻው ጊዜ በትሩፋኗ (ቅሬታዋ) ቤተ ክርስቲያን ላይ
ዲያብሎስ ስለሚሰነዝረው ጥቃት ይገልጻል (ራእ. 12፡17)፡፡
ከታሪክ ከምንማራቸው ትምህርቶች አንዱ፤ ከታሪክ ፈጽሞ አለመማራችን ነው-የሚል አባባል አለ፡፡ ሀሳቡ--ምንም ያህል ቢሆን ሰዎች ተመሳሳይ ስህተቶችን
መሥራታቸውን ይቀጥላሉ የሚል አንደምታ አለው፡፡ ትምህርት ልንቀስምበት
የሚያስችለን የታሪክ ክምችት ከበስተኋላችን እያለልን ተመሳሳይ ስህተቶችን
ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው?
የየሱስን የተለያዩ ስሞች የያዙትን የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ ስሞቹ እርሱ
ስላደረገው፣ እያደረገ ስላለው ወይም ስለሚያደርገው ነገር እርሱን ይገልጣሉ፡፡
ጥቅሶቹ ስለ የሱስ ምን ያስተምሩናል?
ራእ. 1:5___________________________________________________________________
ራእ. 1:18__________________________________________________________________
ራእ. 5:8___________________________________________________________________
ራእ. 19:11–15______________________________________________________________
ራእ. 21:6__________________________________________________________________
በራእይ መጽሐፍ የሱስን በተለያዩ ሚናዎች እና ተግባራት ከሚገልጹ በርካታ
ጥቅሶች መካከል እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እርሱ ራሱን የኃጢአት መሥዋዕት
አድርጎ ስላቀረበበት የመጀመሪያው ምጽአቱ ለመጠቆም እንደ በግ ተጠቅሶአል፡
“አሁን ያለ እርሾ እንደሆናችሁ ሁሉ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ
አስወግዱ፤ የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሰውቶአልና” (1ቆሮ. 5፡7)፡፡
እንዲሁም “እኔ ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ እነሆ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ
ሕያው ነኝ” (ራእ. 1፡18) በማለት ስለ ሞቱና ትንሳኤው ግልጽ ማመሳከሪያ
ይሰጠናል፡፡ “እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ ክርስቶስ መከራን ይቀበላል፤
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሳል” (ሉቃ. 24፡46)፡፡ እንዲሁም በራእ. 19፡11-15
በታላቅ ኃይል፣ ግርማ እና ፍርድ ወደ ምድር ሲመለስ በዳግም ምጽአቱ ከሚኖረው
ሚና አኳያ ተገልጾአል፡፡ “‘የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክት ጋር ይመጣል፤
ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል’ ” (ማቴ. 16:27)
ሕይወትን፣ ሞትን፣ ትንሳኤን እና የየሱስን ዳግም ምጽአት የህልውናችን ማዕከላዊ
ክፍል እና የግብረገባዊ ምርጫችን መሰረት እያደረግን በየዕለት ሕይወታችን መማር
የምንችለው እንዴት ነው?
በራእይ መጽሐፍ የቀረበው መቅደስ ከዕብራውያኑ ሁለቱ ዐቢይ ክፍሎች
በተጨማሪ በመቅደሱ ዙሪያ የተገነባ ሌላ ቅጥር አለው፡፡ ይህ ክፍል በሁለቱ ዋና
ዋና ክፍሎች ዙሪያ ከማለፍ ውጪ በአንዳቸውም አይገድብም፡፡
ምድራዊው ቤተ መቅደስ ለኃጢአት ሥርየት የመጣው እንስሳ ታርዶ
የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበትና መሠዊያው በሚገኝበት ቅጥር ይጀምራል፡፡
እንስሳው ታርዶ ከሞተ በኋላ ካኅኑ ወደ መጀመሪያው የመቅደሱ ቅጥር ይገባል
ይኸውም በመስቀሉ ተምሳሌት መሰረት የሱስ ከእርገቱ በኋላ ወደ ሰማያዊው
መቅደስ በመግባት የተወው ምሳሌ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የሱስ በመቅረዞቹ
መካከል መራመዱን ያመለክታል (ራእ. 1፡13)፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 4፡1-2፡፡ የተከፈተው በር ምን ይወክላል? ይህ
ትዕይንት የሚገኘው የት ነው? ሐዋ. 2:33፣ 5:31፣ ኤፌ. 1:20፣ ዕብ. 10:12-13፣ መዝ.
110:1፣ ራእ. 12:5፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ክርስቶስ በዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከፈተ በር ወደ ሰማይ እንዳረገ በሰማያዊው
መቅደስ ቅዱስ ክፍል ከበረ፡፡ ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ በራእይ መጽሐፍ የታየው
በሰማያዊው መቅደስ የመጀመሪያው ክፍል ከመቅረዙ ፊት ቆሞ ነው (ራእ. 1፡10-18)
፡፡
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ራእ. 11፡19፡፡ በሰማይ ያለው ቤተ መቅደስ ሲከፈት ዮሐንስ ልክ
በምድራዊው ሁለተኛ ክፍል የተቀመጠ የሚመስለውን--የኪዳኑን ታቦት ማየት
የቻለበት እውነታ አንደምታው ምንድን ነው? (ዘሌዋ. 16፡12-14)
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በሰማያዊው ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚስተዋለው የኪዳኑ ታቦት ምስል
ለቅድስተ ቅዱሳኑ ወይም ለሰማያዊው መቅደስ ሁለተኛው ክፍል የማያጠራጥር
ማስረጃ ነው፡፡ በራእይ መጽሐፍ መመልከት የምንችለው የየሱስን የሁለቱን
ክፍሎች አገልግሎት ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም በሰማይ እና በምድር ያሉ
ክስተቶች የመተሳሰራቸውን ወሳኝና አጽናኝ ነጥብ እንመለከታለን፡፡ የክርስትና
ታሪክ መከራ የበዛበት--የመጨረሻው ጊዜ ክስተቶችም በራእይ መጽሐፍ
እንደተገለጹት ቢሆንም “መላው ሰማይ ሕዝቡ ለጌታ ቀን እንዲዘጋጅ በማድረግ
ሥራ መጠመዱ እና በሰማይና በምድር ያለው ግንኙነት በጣም የተሳሰረ መምሰሉ”
ለእኛ መልካም ተስፋ ነው፡፡ —Ellen G. White, My Life Today, p. 307.
የራእይ መጽሐፍ ከመልእክት አወቃቀሩ እስከ ይዘቱ አንድ ብቻ ዓላማ አለው፡
የሱስ ክርስቶስን መግለጥ፡፡
በዚህ የተነሳ መጽሐፉ የሚጀምርባቸው ቃላት “የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ”
የሚሉ ናቸው፡፡ ይኸውም በአጠቃላይ “የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ” ወይም “ስለ
ኢየሱስ ክርስቶስ” (ራእ. 1፡2) በሚል ይስተዋላል፡፡ የመልእክቱ በ “ራእይ” መልክ
መሰጠት የራእይ መጽሐፍን ለማስተዋል በጣም ከባድ አድርገው የሚያምኑትን
ይሞግታል፡፡ ጌታ መጽሐፉን በሚያነቡት እንዲስተዋል እቅዱ ባይሆን’ማ ለምን
የመጽሐፍ ቅዱስ አካል ያደርገው ነበር?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ 1፡1-8፡፡ ጥቅሶቹ ስለ የሱስ ምን ያስተምሩናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በራእይ መጽሐፍ ክርስቶስ “የምድር ነገሥታት ገዥ” (ራእ. 1፡5) በሚል የቀረበ
ሲሆን በዚሁ መጽሐፍ መጨረሻ አካባቢ ደግሞ “የነገሥታት ንጉሥ” (ራእ. 19፡16)
የሚል ስያሜ ተሰጥቶት እንመለከታለን፡፡ ምድር ምስቅልቅሏ ቢወጣና ግራ
ብትጋባም ነገር ግን ሁሉም ነገር እስከ መጨረሻው በሚወደን ጌታና አዳኛችን
ቁጥጥር ሥር የመሆኑ ማረጋገጫ ለእኛ ታላቅ የምስራች ነው፡፡
በራእ. 1፡5 ክርስቶስ ቤዛችን ለመሆኑ ግልጽ ማጣቀሻ ተሰጥቶናል፡፡ “ለወደደንና
ከኃጢአታችንም በደሙ ነፃ ላወጣን” የሚለው ሀረግ ለዓለም ቤዛ የሆነበትን
የመስቀል ላይ ሞቱን ያመለክታል፡፡ እኛን ማጽደቅ ብቻ ሳይሆን ቀድሶናልም (1ቆሮ.
6፡11)፡፡ ኃጢአታችንን በብቸኝነት የሚያጥበው የሱስ መሆኑን በብቸኝነት
በሚያሳዩን በእንደነዚህ ዓይነቶቹ ጥቅሶች የደኅንነት ማረጋገጫ ማግኘት
እንችላለን፡፡ በእርግጥ እኛ በራሳችን ይህን ለማድረግ የማይታሰብ ነው፡፡
ጥቅሱን ያንብቡ፡--ራእ. 1፡7፡፡ መልእክቱ ስለ የሱስ ምን ያስተምረናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የክርስቶስ “በደመና መገለጥ” ዳግም ምጽአት ተስፋ የሁሉም የክርስትና እምነት
ተቋማት ማዕከላዊ ክፍል ነው፡፡ የሱስ ዳግም በሚገለጥበት ጊዜ ዐይን ሁሉ
ያየዋል፡፡ የዳግም ምጽአቱ ክስተት ማንኛውንም የዚህን ዓለም ሥቃይ፣
ምስቅልቅልና ውድመት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያከትም በማድረግ ሁሉንም
ዘላለማዊ ተስፋዎች ይዞ ከተፍ ይላል፡፡
ራእ. 1፡8 ስለ የሱስ ምን ያስተምረናል? ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ እየተጋፈጥን
ቢሆንም በዚህ ሁኔታችን መጽናናት ሊሰጠን የሚችል ምን ዓይነት ተስፋ በጥቅሱ
ማግኘት እንችላለን?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 1፡10-18፡፡ የሱስ ስለ ራሱ ምን ይላል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከጥቅሶቹ እንደምንመለከተው የሱስ በሰማያዊው መቅደስ የመጀመሪያ ክፍል
ቆሞአል፡፡ የሱስ በዚህ ስፍራ ከነበረው ሚና አኳያ የተገለጠበት ራእይ እጅግ ብርቱ
በመሆኑ ዮሐንስ በፍርሐት እግሮቹ ስር ወደቀ፡፡ ነገር ግን ሁሌም አጽናኝ የሆነው
የሱስ--ለዘላለማዊ አምላክነቱ ማጣቀሻ አልፋ እና ኦሜጋ ወይም የመጀመሪያውም
ሆነ የመጨረሻው እርሱ መሆኑን በማመላከት እንዳይፈራ ሲነግረው ይታይል፡፡
በመቀጠል ስለ ሞቱ፣ ስለ ትንሣኤው--ብሎም ትንሣኤው ስላስገኘው ተስፋ
ይናገራል፡፡ የሱስ “የሞትና የሲኦል” መክፈቻ በእጁ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ማርታና
ማርያም ወንድማቸው አልዓዛር በሞተ ጊዜ የነገራቸውን መልሶ በዚህ ቦታ ለዮሐንስ
እየነገረው ነበር፡፡ ዮሐንስ ይህንኑ ጉዳይ እንዲህ ሲል በወንጌል አስፍሮት ነበር
“‘ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤
በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽ?’ ” (ዮሐ. 11፡2526)፡፡
የሱስ ቀደም ሲል በማርታ አሁን ደግሞ በዮሐንስ አማካይነት የክርስትና እምነት
መደምደሚያና ከፍታ ወደ ሆነው የትንሣኤው ተስፋ ያመላክተናል፡፡ ይህ ተስፋ
ባይኖር ምን ይበጀን ነበር?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 22፡7፣12-13፡፡ በተጨማሪ ጥቅሶቹ ስለ የሱስ ምን
ይገልጣሉ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“የብሉይ ኪዳን ዘፍጥረት እና የአዲስ ኪዳን ራእይ የሆነው ክርስቶስ የሱስ አልፋ
እና ኦሜጋ ነው፡፡ ሁለቱም በክርስቶስ በአንድነት ይገናኛሉ፡፡ ሁለተኛው አዳም
የሰይጣንን ፈተና አሸንፎ ለመጀመሪያው አዳም አሳፋሪ ውድቀትና ጥፋት ቤዛ
በመሆኑ፤ በሁለተኛው አዳም መታዘዝ የመጀመሪያው አዳም እና እግዚአብሔር
እርቅ ፈጠሩ፡፡”— Ellen G. White Comments, The SDA Bible Commen-
tary, vol. 6, pp. 1092, 1093. አዎ የሱስ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ነው፡፡
እርሱ በመጀመሪያ እንደ ፈጠረን፤ በመጨረሻም እንዲሁ ይፈጥረናል፡፡
ገና ከመጀመሪያው፤ ያለፈውን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የወደፊቱን የምድር
ፍጻሜ የሚያስተምረን የራእይ መጽሐፍ እነሆ ዛሬም የየሱስ ክርስቶስ ራእይ ነው፡፡
ስለ መጪው ጊዜ ክስተቶች የቱንም ዓይነት ጥናት ብናካሂድ የሱስ ክርስቶስ
የሁሉም ነገር ማዕከል መሆኑን አንዘንጋ፡፡
የሱስን በየቀኑ የሕይወታችን ማዕከል አድርገን መጠበቅ የምንችልባቸው መንገዶች
የትኞቹ ናቸው?
“በራእይ መጽሐፍ ጥልቀት ያላቸው አምላካዊ ነገሮች ተገልጸዋል፡፡ ‘ራእይ’ በሚል ለመጽሐፉ የተሰጠው ስያሜ መጽሐፉ የተዘጋ ነው የሚለውን አባባል ይጣረሳል፡፡ ራእይ--የተገለጠ የሚል ፍቺ አለው፡፡ የመጽሐፉን ምስጢር ለአገልጋዩ የገለጠው ጌታ ራሱ እንደመሆኑ ሁሉም እንዲያጠኗቸው ክፍት አድርጎ ነድፎአቸዋል፡፡ መጽሐፉ የያዛቸው እውነቶች የተጻፉት ዮሐንስ ለኖረበት ዘመን ብሎም በምድር ታሪክ መዝጊያ ለሚኖሩ ወገኖች ነው፡፡ በዚህ ትንቢት ከተገለጹት ትዕይንቶች መካከል አንዳንዶቹ ቀደም ባሉት ዘመናት ፍጻሜ ሲያገኙ የተወሰኑት ደግሞ አሁን ባለንበት ዘመን በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹ በጨለማ ኃይላት እና በሰማይ ልዑል መካከል ሲካሄድ የኖረው ታላቁ ውዝግብ ሊቋጭ መቃረቡን ሲያሳዩ--ሌሎቹ ደግሞ በአዲሲቱ ምድር የተቤዡ አሸናፊዎችን ሐሴትና ደስታ ይገልጻሉ፡፡”—Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 584. በዚህ ሣምንት በመጽሐፉ መግቢያም ሆነ መጨረሻ የተመለከትናቸው ጥቅሶች ምን ያህሉ የራእይ መጽሐፍ ስለ የሱስ እንደሚናገር ያሳያሉ፡፡ የራእይ መጽሐፍ ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት እስከ ታሪክ ቀመስ ክስተቶች ያሉ ማመሳከሪያዎችን በመዳሰስ ስለ ጌታችን የሱስ ክርስቶስ አብልጦ ያስተምረናል፡፡ በተጨማሪ እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቱ፡ ራእ. 3:14፣ 5:5-6፣ 7:14፣ 19:11–16፡፡ ጥቅሶቹን በአንድነት በማኖር ለየሱስ ያላቸውን ብርቱ ውክልና ማግኘት እንችላለን፡፡ የመወያያ ጥያቄዎች፡ 1.በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስለ ብሉይ ኪዳን የተሰጡ ጽኑና የማያቋርጡ ማመሳከሪያዎች ለእኛ ምን ማለት ናቸው? አምላካዊው ቃል የእምነታችን ማዕከልና ብርቱ አጽንኦት ልንሰጠው የተገባ ስለመሆኑ ምን ሊነግረን ይገባል? በግል ህይወታችን እና በቤተክርስቲያን ህይወት የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን ለማቃለል የሚደረጉ ማናቸውንም ዓይነት ጥረቶች መከላከል የምንችለው እንዴት ነው? 2.በራእይ መጽሐፍ በተለይ ስለ የሱስ የሚናገሩ ጥቅሶቸን ለመሰብሰብ ይሞክሩ፡፡ ጥቅሶቹን በሰንበት ትምህርት ጥናት ያቅርቧቸው፡፡ ስለ ጌታ ተፈጥሮ፣ ሥራ፣ ኃይልና ባህሪ በተጨማሪ ምን ይገልጡሎታል? ጥቅሶቹ ከሚገልጡት እውነታ ምን ዓይነት መጽናናት ያገኛሉ? 3.በዚህ በሞት ዓለም--ለሙታን ከተሰጠው የትንሣዔ ተስፋ ውስጥ--ተስፋን ማግኘት መማር የምንችለው እንዴት ነው?