ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት፡- ሮሜ 7ን ያንብቡ፡፡
የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለሞትን ከህግ ተፈትተናል ፣ ስለዚህም በአዲሱ መንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው የፊደል ኑሮ አይደለም፡፡ ” (ሮሜ 7፡ 6)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሮሜ 7 የበለጠ ክርክር የፈጠሩ ምዕራፋት ጥቂት ናቸው፡፡ ይህንን በተመለከተ የአድቬንቲስት የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የሮሜ 7፡14-25 በወንጌላት ሁሉ ውስጥ በጣም ውይይት የተደረገበት ችግር ነው፡፡ ዋንኛው ጥያቄ ይህ እጅግ ጥልቅ የሆነ የግብረ-ገብ ትግል የህይወት ታሪክ ነው? ከሆነ ደግሞ ይህ በጳውሎስ ህይወት ከመለወጡ በፊት ወይስ በኋላ የሚለው ነው፡፡ ከንግግሩ ለመረዳት እንደሚቻለው ጳውሎስ ከኃጢአት ጋር ትግል እያደረገ መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡ (ሮሜ 7፡ 7- 11 )፡፡
Ellen white, steps to Christ, p. 19; Ellen white , testimonies for the church, vol. 3 p.475) እንዲህ ትላለች ‹‹ በእርግጥ እርሱ እየገለጸ ያለው በማንኛውም በእግዚአብሔር ሀሳብ ለመመራት በሚፈልግ ክርስትያን ህይወት ውስጥ የሚፈጠረውን ትግል ነው፡፡ ›› - The SDA Bible commentary, vol. 6 p. 553.
የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ሮሜ 7 ከጳውሎስ ህይወት መለወጥ በፊት ነው ወይስ በኋላ በሚለው አመለካከት ለይ ይለያያሉ፡፡ ማንም የትኛውንም አመለካከት ቢደግፍ ለእኛ አስፈላጊ የሆነው ነገር የክርስቶስ ጽድቅ እኛን እንደሚሸፍነን እና በእርሱ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሆነን እንደምንቆም፣ ሊቀድሰንና በኃጢአት ላይ ድልን እንደሚሰጠን ፣ እናም ‹‹ የልጁን መልክ እንድንመስል እንደሚለውጠን ›› (ሮሜ 8 ፡ 29 ) ማወቅ ነው፡፡ ‹‹የዘላለምን ወንጌል ›› ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ለማሰራጨት ስንፈልግ ልናውቃቸውና ልንለማመዳቸው የሚገቡን ነጥቦች እነዚህ ናቸው፡፡ (ራዕይ 14፡ 6)
*ለህዳር 16 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
ሮሜ 7፡1-6ን ያጥኑ፡፡ ከህግ ጋር ስላላቸው ዝምድና ለመናገር ጳውሎስ የተጠቀማቸው ምሳሌዎች ምንድናቸው? በምሳሌ ያስቀመጣቸው ነጥቦች ምንድናቸው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በሮሜ 7: 1-6 ያለውን ምሳሌ በጥንቃቄ ማየት እርሱ ለመናገር የፈለገውን ምክንያት በትክክል እንድንረዳ ያደርገናል፡፡
በዚህ ደብዳቤ አጠቃላይ አውድ ጳውሎስ እየተናገረ ያለው በሲና ተመስርቶ ስለነበረው የስግደት ሁኔታ ነበር፣ እርሱ ብዙውን ጊዜ ህግ የሚለው ይህንን ነው፡፡ አይሁዳውያን ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ህግ ከክርስቶስ መምጣት በኋላ የሚያበቃ መሆኑን የመረዳት ችግር ነበረባቸው፡፡ ጳውሎስ እየተናገረ የነበረው ይህንን አይሁዳውያን የህይወጣቸው ክፍል ያደረጉትን ለማስወገድ አለመቻላቸውን ለመግለጽ እየሞከረ ነው፡፡
ከጳውሎስ ምሳሌያዊ ንግግር አስፈላጊ የሆነው ነገር እንደሚከተለው ነው፡- አንዲት ሴት አንድን ሰው ሰገባች፡፡ እርሱ በህይወት እስካለ ድረስ በህግ የታሰረች ናት፡፡ እርሱ በህይወት ባለበት ዘመን ከሌላ ወንድ ጋር አትሆንም፡፡ ነገር ግን እርሱ ከሞተ ከሚያስራት ህግ ነጻ ትወጣለች፡፡ ( ሮሜ 7፡ 3 )
ጳውሎስ የጋብቻን ምሳሌ ከአይሁዳውያን አኗኗር ጋር ያመሳሰለው እንዴት ነው? ሮሜ 7፡ 4-5፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሴትዮዋን የባሏ ሞት ከህግ ነጻ እንደሚያወጣት ሁሉ ፣ ክርስቶስ እንደተናገረው ፣ የአሮጌው ህይወት መሞት አይሁዳውያንን ክርስቶስ እስከ ሞት ድረስ እንዲጠብቁ ከሚጠበቅባቸው ህግ ነጻ ያደርጋቸዋል፡፡
አሁን አይሁዳውያን ‹‹ዳግም ለመጋባት›› ነጻ ናቸው ፡፡ ዳግም የተነሳውን መሲሁን እንዲያገቡና ለእግዚአብሔር ፍሬ እንዲያፈሩ ተጋብዘዋል፡፡ ይህንን ምሳሌ ነበር አይሁዳውያን ከጥንቱን አኗኗራቸው ነጻ መውጣታቸውን ለመግለጽ የተጠቀመው፡፡
አስርቱን ትዕዛዛት ስለ መታዘዝ ጳውሎስና መጽሐፍ ቅዱስ የሚሉትን ስንመለከት ጳውሎስ ለአይሁዳውያን አማኞች አሥርቱ ትዕዛዛት በአማኞች ላይ ስልጣን የላቸውም ብሏል የሚል ትርጉም ብንሰጥ ስሜት አይሰጥም፡፡ ይህንን ጥቅስ አሥርቱ ትዕዛዛት ተወግደዋል የሚል ትርጉም አለው ብለው የሚወስዱ ሰዎች ፣ በእርግጥ አላማቸው ፣ ወይም ለማለት የሚፈልጉት ሌሎቹን ትዕዛዛት ሳይሆን የሰባተኛውን ቀን ሰንበት ብቻ ተወግዷል ለማለት ፈልገው ነው፡፡ ሮሜ 7: 4- 5ን አራተኛው ትዕዛዝ ተወግዷል ወይም በእሁድ ተተክቷል ለማለት ሲጠቀሟቸው ይህ በፍጹም ቃላቱ እንዲሰጡ የተፈለገው ትርጉም አይደለም፡፡
ጳውሎስ በአጠቃላይ በሲና ስለተሰጠው ሥርዓት እየተናገረ ከሆነ ስለ አንዱ ትዕዛዝ ለይቶ የሚናገረው ሮሜ 7፡7 ታዲያ ምንነድነው? ታዲያ ይህ ጳውሎስ ትናንት እየተናገረ የነበረው ስለ አስርቱ ትዕዛዛት መሻር አለመሆኑን አያረጋግጥም?
መልሱ አይደለም ነው፡፡ በአእምሮአችን በጳውሎስ አስተሳሰብ ህግ የሚለው ቃል አስርቱን ትዕዛዛት ጨምሮ ለእስራኤል ልጆች በሲና የተሰጠው ሁሉም ደንብ መሆኑን አንዘንጋ፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ ነጥቡን ለማስረዳት የሚጠቅሰው ከአጠቃላይ የአይሁድ ህግ ወይም ከህጉ ክፍል መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ይህ ሥርዓት በከርስቶስ ሞት ምክንያት ከተሻረ በኋላ ፣ ይህ ከሲና በፊት ለነበረው እንዲሁም ከመስቀል በኋለም የሚቀጥሉትን አስርቱን ትዕዛዛት አያጠቃልልም፡፡
ሮሜ 7፡ 8 – 11ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ሥፍራ ጳውሎስ ስለ ህግና ኃጥአት ግንኙነት ምን እያለ ነው?
እግዚአብሔር ራሱን ለአይሁዳውያን በግብረገብ ፣ በማህበራዊ፣ እና በጤና ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ነገር በጥልቀት የትኛው ትክክል እና የትኛው ስህተት እንደሆነ በመንገር ራሱን ገለጸላቸው፡፡ ደግሞም እነዚህን ትዕዛዛት በመተላለፍ የሚመጣውንም ቅጣት ገለጸላቸው፡፡ በዚህ ሥፍራ የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መተላለፍ ኃጢአት ተብሏል ፡፡
ስለዚህ ጳውሎስ ህግ አትመኝ ባይለኝ ኖሮ መመኘት ኃጢአት መሆኑን አላውቅም ነበር ይላል፡፡ ኃጢአት የተገለጸውን የእግዚአብሔር ፈቃድ መጣስ ሲሆን የታወቀ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆን በማይታወቅበት ኃጢአትም ምን እንደሆን አይታወቅም፡፡ የተገለጸው የእግዚአብሔር ፈቃድ ለአንድ ሰው ከተነገረው ፣ እርሱ ወይም እርሷ ከህግ በታች መሆናቸውንና የተፈረደባቸው መሆናቸውን ያውቃሉ፡፡ በዚህ ስሜት ሰውየው ይሞታል፡፡
በዚህ ሥፍራና በሌሎችም ክፍሎች በጳውሎስ የክርክር መስመር፣ ህግን አክባሪ የሆኑ አይሁዳውያንን የህግ ፍጻሜ ወደሆነው ክርስቶስ ሊያመላክታቸው ፈልጓል ፡፡ እርሱ ህግ አስፈላጊ መሆኑንና እንዲሁም ጥቅሙ ውስን መሆኑን ጭምር መግለጽ ፈለገ፡፡ ህግ የድነትን አስፈላጊነት የሚናገር እንጂ በራሱ ድነትን ማግኛ አይደለም፡፡
‹‹ ጳውሎስ ከራሱ ልምድ ጋር በማዛመድ ከመለወጥ በኋላ መደረግ ስላለበት ነገር በጣም አስፈላጊ የሆነ እውነት ያስቀምጥልናል፡፡ ‹ ከዚህ በፊት ያለ ህግ ህያው ነበርኩ› ፣ ይህም ማለት ኩነኔ እንዳለ አይሰማውም ነበር፡፡ ‹ ነገር ግን ህግ ሲመጣ እኔ ሞትኩ፡፡› ከዚያም ራሱን በመለኮታዊው ህግ የተኮነነ ኃጢአተኛ መሆኑን ተገነዘበ፡፡ የሞተው ህጉ ሳይሆን ጳውሎስ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡›› -Ellen G. white comments, The SDA Bible commentary, vol. 6, 1076.
ከህግ በፊት ሙተው የነበሩት በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ? በዚያ አውድ ሆነው ክርስቶስ ለእርሰዎ አዲስ ህይወት በመስጠት ያደረገውን እንዴት ያስተውሉታል?
ሮሜ 7 ፡ 12ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ ከዚህ በፊት ሲገልጽ በነበረው መሰረት ይህንን ጥቅስ እንዴት እናስተውላለን?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አይሁዳውን ህግን በጣም ያከብሩ ስለነበር ጳውሎስ የተቻለውን ሁሉ በመጠቀም ይህንን መግለጥ ይፈልጋል፡፡ እኛን ከኃጢአት ለማዳን ህግ ማድረግ የሚችለውን እንጂ ማድረግ የማይችለውን አያደርግም፡፡ አጠቃላይ የአይሁድ መተዳደሪያ ሥርዓት ወይም አሥርቱ ትዕዛዛት በተናጠል መዳን ሊያስገኙልን ስለማይችሉ እኛ ክርስቶስ ያስፈልገናል፡፡ ወደ እኛ በእምነት የሚመጣው የኢየሱስና የእርሱ ጽድቅ ብቻ ይህንን ያደርግልናል፡፡
ጳውሎስ ስለ እርሱ ሞት የሚወቅሰው ማንን ነው? እና ነጻ የሚያደርገውስ ምንድነው? ይህ ልዩነት አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በሮሜ 7፡13 ጳውሎስ ህግን በተቻለ መጠን ሁሉ ጥሩ በሆነ መንገድ ያቀርብልናል፡፡ አስቸጋሪ ስለሆነው የኃጢአት ሁኔታ እርሱ ህግን ሳይሆን ኃጢአትን ይኮንናል ‹‹ምኞትን ሁሉ በትዕዛዝ ሰራብኝ›› (ሮሜ 7፡8)። ህግ መልካም ነው ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሄር ባህሪይ መግለጫ ነው፣ ነገር ግን ጳውሎስ በዚህ ህግ ፊት እንደተኮነነ ሆኖ ቆሟል፡፡
ኃጢአት ጳውሎስ እንደዚህ የከፋ ኃጢአተኛ ሆኖ እንዲታይ የተሳከለት እንዴት ነው?
ጳውሎስ ሥጋዊ በመሆኑ ክርስቶስ ያስፈልገዋል፡፡ ኩነኔውን ሊያስወግድለት የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነው (ሮሜ 8፡1)፡፡ ከኃጢአት ባርነት ነጻ ሊያወጣው የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ጳውሎስ ራሱን ለኃጢአት እንደተሸጠ ይገልጻል፡፡ እርሱ የኃጥአት ባሪያ ነው፡፡ እርሱ ምንም ነጻነት የለውም ፡፡ እርሱ ማድረግ የሚፈልገውን አያደርግም፡፡ እርሱ ህግ የሚነግረውን መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ይፈልጋል ነገር ግን ኃጢአት አይፈቅድለትም፡፡
ጳውሎስ በዚህ ምሳሌ አድርጎ አይሁዳውያን ክርስቶስ (መሲሁ) እንደሚያስፈልጋቸው ሊነግራቸው እየሞከረ ነው፡፡ ድል መንሳት የሚቻለው በጸጋ ጥላ ሥር ብቻ እንደሆነ ከዚህ በፊት አሳይቷል፡፡ (ሮሜ 6፡14)፡፡ ይሄው ተመሳሳይ ሀሳብ በሮሜ 7 እንደገና ተጠቅሷል፡፡ በህግ ሥር መኖር ማለት፣ ምህረት ለሌለው ጌታ፣ ለኃጢአት ባሪያ መሆን ማለት ነው ፡፡
የኃጢአት ባርነትን በተመለከተ የእርሰዎ ልምድ ምን ይመስላል? ከኃጢአት ጋር ለመጫወት ሞክረው ያውቃሉ? እንደፈለጉ ሊቆጣጣሩት እንደሚችሉ ያስቡ፣ ሊሆን የሚችለው ራስዎን የሚያገኙት በምህረት የለሹ አለቃ ሥር ብቻ ነው፡፡ ወደ እውነታው እንኳን በዳህና መጡ! ለራስ ዕለት በዕለት በመሞት ለምን ለክርስቶስ በህይወት አይኖሩም?
‹‹ የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ህግ መልካም እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ እንደዚህ ከሆነ ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም በእኔ የሚያድር ኃጢአት ነው እንጂ፡፡» (ሮሜ 7፡16 -17 )፡፡ እዚህ ላይ የተገለጸው ትግል ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ህግን እንደ መስተወት በመጠቀም ፣ መንፈስ ቅዱስ ያንን ሰው የህግን ጥያቄ ባለመፈጸም እግዚአብሔርን እያሳዘነ እንደሆን ይነግረዋል፡፡ እነዚያን ህግ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ለመፈጸም በሚያደርገው ጥረት ኃጢአተኛው ህግ መልካም መሆኑን ይስማማል፡፡
በሮሜ 7፡18–20 ጳውሎስ አስቀድሞ የገለጻቸው ትኩረት እንዲሰጥበት ደግሞ እየጠቀሰ ያለው ነጥብ ምንድነው?
አንድ ሰው ክርስቶስ እንደሚያስፈልገው አስረግጦ ለመናገር መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው ወደ ‹‹አሮጌው ኪዳን ››ልምምድ ይመራዋል፡፡ ኤሌን ዋይት የእስራኤልን ልምምድ እንዲህ በማለት ትገልጠዋለች፡- ‹‹ህዝቦቹ የልባቸውን ኃጢአተኝነት አልተገነዘቡም፣ ስለዚህ ያለ ክርስቶስ ህግን መጠበቅ አይቻልም፤ እናም እነርሱ ከእግዚአብሔር ጋር ኪዳን አድርገዋል፡፡ እነርሱም የራሳቸውን ጽድቅ ለመፈጸም የሚችሉ ስለመሰላቸው ‹‹ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዝለታለን አሉ፡፡›› (ዘጸ. 24፡7)፡፡ ቃል ኪዳን በገቡ ሳምንት ሳያልፍ ኪዳናቸውን አፍርሰው ለወርቅ ጥጃ ሲሰግዱ ተገኙ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ኪዳን ስላፈረሱ ከእግዚአብሔር ምንም እርዳታ መጠየቅ አይችሉም፤ ኃጢአተኝነታቸውን በማየት ይቅርታን በሚፈልጉበት ጊዜ ፣ በአብረሃማዊው ኪዳን ወደተገለጸው አዳኝ ይመጣሉ፡፡›› -Ellen G. white , patrarichs and Prophets, PP. 371, 372.
እንደ አለመታደል ሆኖ ዕለት በዕለት ራሳቸውን ለክርስቶስ መስጠት ባለመቻላቸው፣ ብዙ ክርስትያኖች ኃጢአትን ቢጠሉትም በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ እነርሱ እንደማንኛውም ጊዜ ረዥም የሆነውን የቅድስና መንገድ እየተጓዙ እንደሆነ ቢናገሩም እውነታው ግን በኃጢአት መኖራቸው ነው፡፡ ስለዚህ የታወቀውን ኃጢአት ወደ ክርስቶስ በመውሰድ ለድል እርሱን በመጠያቅ ፋንታ፣ ትክክለኛ ነገር ለመስራት አይቻልም የሚል ስለሚመስላቸው ከሮሜ 7 ስር ለመደበቅ ይሞክራሉ፡፡ እውነታው ግን ይህ ምዕራፍ እየተናገረ ያለው አንድ ሰው በክርስቶስ እንጂ የኃጢአት ባሪያ ከሆነ ድል ማድረግ አይችልም፡፡
ክርስቶስ ቃል እንደገባልን እርሰዎ በራስና በኃጢአት ላይ ድል ነስተዋል? ምን አይነት ስህተት የሆኑ ምርጫዎችን እያደረጉ ነው?
ሮሜ 7፡21- 23ን ያንብቡ፡፡ ክርስቲያን ቢሆኑም ፣ተመሳሳዩን ትግል በህይዎትዎ የተለማመዱት እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በዚህ ንባብ ጳውሎስ የሰውነቱን ህግ ከኃጢአት ህግ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ‹‹በሥጋዬ›› ‹‹ለኃጥአት ህግ›› አገልግያለሁ ይላል፡፡ (ሮሜ 7፡25)፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን ማገልገልና የእርሱን ህግ መከተል ማለት ሞት ነው፡፡ (ሮሜ 7፡10, 11- 13)፡፡ ሰውነቱ ለኃጢአት ለመታዘዝ የሚመች እስከሆነ ድረስ ‹‹ሟች ሥጋ›› በመባል ሊገለጽ ይችለል፡፡
የአእምሮ ህግ የእግዚአብሔር ህግ ነው ይህም የፈቃዱ መገለጫ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ግሳጼ ጳውሎስ ከዚህ ህግ ጋር ይስማማል፡፡ አእምሮው ይህንን ህግ መጠበቅ ይፈልጋል፣ ነገር ግን ለመጠበቅ ሲሞክር አልቻለም ምክንያቱም ሰውነቱ ኃጢአት ማድረግ ይፈልጋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ትግል ያልገጠመው ማን ነው? በአእምሮህ ምን ማድረግ እንዳለብህ ታውቃለህ ፣ ነገር ግን ሥጋህ ሌላ ነገር ይፈልጋል፡፡
ከምንገኝበት ከዚህ አደገኛ ሁኔታ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን ? ሮሜ 7፡24፣ 25፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አንዳንዶች ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ›› ከሚያሰኝ ከፍታ ላይ ከደረሰ በኋላ ጳውሎስ ነጻ ወጥቶ ከነበረው ማንነቱ ጋር እንደገና መታገሉ ይገርማቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ማን ነጻ ያወጣኛል›› የሚለውን ጩኽት በምዕራፍ 8 የሚሰጠውን ስለ አስደናቂው ነጻ መውጣት ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይመለከቱ እዚያው ያቆማሉ፡፡ ጳውሎስ በመጀመሪያዎቹ ቁጥሮች የተናገረውን በመከለስ እንደገና ከኃጢአት ኃይሎች ጋር ይታገላል፡፡
አንዳንዶች ጳውሎስ ‹‹እኔ ራሴ›› ሲል ‹‹ ክርስቶስን ሳይጨምር ለእኔ ለራሴ የተተወ ነው›› ማለቱ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ሮሜ 24-25 ከተስተዋለ አንድ ነገር ግልጽ ሊሆን ይገባል፡- ራሳችን ብቻ ከቀረን ያለ ክርስቶስ ኃጢአትን ማሸነፍ አንችልም፡፡ ምንም እንኳ ራስ በተደጋጋሚ ብቅ ቢልም ክርስቶስ ጋር ከሆንን በእርሱ አዲስ ህይወት እና የእኛ እንደሆነ ከተቀበልነው የድል ተስፋም አለን፡፡ ማንም ሰው ለሌላው እንደማይተነፍስ፣ እንደማያስነጥስ፣ እንደማያስል እንዲሁ ክርስቶስን ለአንተ አይመርጥልህም፡፡ አንተ ብቻ ይህንን ምርጫ ታደርጋለህ፡፡ በክርስቶስ ተስፋ የተሰጡንን ድሎች ልንቀበል የምንችልበት ሌላ መንገድ የለንም ፡፡
‹‹ ህግን መተላለፍ ባለበት፣ ዕረፍትና ሰላምም ሆነ ቅድስና የለም፡፡ ሰው በኃጢአት እየቀጠለ በክርስቶስ ባገኘው ጸጋ በእግዚአብሔር ፊት ትሁት ሆኖ ሊቀርብ ተስፋ ማድረግ የለበትም፡፡ ›› -Ellen G. white, selected messages, book 1, p. 213 .
ጳውሎስ ወንድሞቹ ኃጢአትን ይቅር ባይ አዳኝ ታላቅ ክብር እና እርሱ ትኩረት የሰጠውን ነገር (የአይሁድ ህግ) ማየት እንዲችሉ ይመኛል፡፡ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ ጥላው አልፎ እውነተኛው መገለጡንና በሰው ፋንታ መሞቱን እንዲያስተውሉ ይፈልጋል፡፡
‹‹ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የኃጢአት መስዋዕት ሆኖ ከሞተ በኋላ ሜዳዊው ሥርዓት ምንም ኃይል አይኖረውም፡፡ ሆኖም ከአሥርቱ ተዕዛዛት ጋር የተገናኘ በመሆኑ ክብር አለው፡፡ መላው ሥርዓቶች የመለኮትን ማህተም የተሸከሙ በመሆናቸው የእግዚአብሔርን ቅን ፍርድ ፣ ጽድቅና ቅድስና ያመለክታሉ፡፡ የጥንቱ አገልግሎት ክብር በተሞላበት ሁኔታ ከተከናወነ ፣ ክርስቶስ ህይወት ሰጭ መሆኑን በሚገልጽበት ጊዜ፣ ቀዳሹንና ህይወት ሰጭ መንፈሱን ለሚያምኑ ሁሉ ሲሰጥ እውነተኛው ምን ያህል የተከበረ ይሆን! - Ellen G white comments, The SDA Bible Commentary , vol. 6, p. 1095 .