መዳን በእምነት ብቻ:ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከህዳር 2-8

ሰባተኛ ትምህርት

November 11–November 17
 

ኃጢአትን ማሸነፍ

 

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት፡- ሮሜ 6 እና 1ዮሐ. 1፡ 8- 2፡1ን ያንብቡ፡፡

 

የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጅ ከህግ በታች አይደላችሁም፡፡ ” (ሮሜ 6፡14)

ሥራ የማያድነን ከሆነ ፣ ምን የሚያስጨንቅ ነገር አለ? ለምን ኃጢአት ማድረጋችንን አንቀጥልም?

ምዕራፍ 6 ለዚህ አስፈላጊ ጥያቄ ጳውሎስ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ጳውሎስ በዚህ ሥፍራ እየተናገረ ያለው በተለምዶ ‹‹ ቅድስና ›› በመባል ስለሚታወቀው ፤ ይህም ኃጢአትን የማሸነፍ እና የበለጠ የክርስቶስን ባህርይ ማንጸባረቅ ሂደት ነው፡፡ ቅድስና የሚለው ቃል በሮሜ መጽሐፍ ሁለት ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡፡ እርሱም የሚገኘው በሮሜ 6፡19 እና 22 በግሪክ ቃሉ hagiasmos ይህም ማለት ቅድስና ነው፡፡

በእንግሊዝኛ በሁለቱም ጥቅሶች ‹‹ ቅድስና›› በሚል ተገልጧል፡፡

ይህ ማለት ጳውሎስ በተለምዶ ቅድስና ተብሎ ስለሚስተዋለው ነገር ምንም አልተናገረም ማለት ነው? በፍጹም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹መቀደስ›› ማለት ለእግዚአብሄር ‹‹መለየት›› ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቅድስና ተደርጎ እንዳለፈ ቀርቧል፡፡ ለምሳሌ ‹‹ለተቀደሱት ሁሉ›› (ሐዋ. 20፡32)፡፡ በዚህ ጥቅስ የተቀደሱት የሚላቸው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡትን ነው፡፡

ነገር ግን በምንም ዓይነት ይህ ‹‹ ቅድስና ›› የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አጠቃቀም በጣም አስፈላጊ የሆነውን የቅድስና አስተምህሮ ወይም ቅድስና የህይወት ዘመን ሥራ የመሆኑን እውነታ በፍጹም የሚክድ አይደለም፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ አጥብቆ የሚያስተምር ሲሆን፣ ይህንን ለመግለጽ ግን የተለያዩ ቃላትን ይጠቀማል፡፡

በዚህ ሳምንት በክርስቶስ ለዳነ ሰው የተሰጠን የኃጢአት ድል ፣ በቀላሉ በስህተት ሊስተዋል የሚችለውን የድነት በእምነትን ትምህርት፣ ሌላኛውን ገጽ እንመለከታለን፡፡

*ለህዳር 9 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
 

ህዳር 3
November 12
 

ኃጢአት የበዛበት

 

በሮሜ 5፡20 ጳውሎስ ኃይለኛ ዓረፍተ ነገር ጽፏል ‹‹ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፣ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዛ›› እርሱ እያስቀመጠው ያለ መልእክት ኃጢአት ምንም ያህል ቢበዛ ወይም ውጤቱ ምንም አስከፊ ቢሆንም ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ይህንን ለመቋቋ ም በቂ ነው፡፡ ኃጢአታችን ይቅር ሊባል ከሚቻለው በላይ ነው ለማለት ስንፈተን ይህ ምን ዓይነት ተስፋ ይሰጠናል! በሮሜ 5 ፡ 21 ጳውሎስ ምንም እንኳ ኃጢአት ቢበዛም፣ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ኃጢአትን በማሸነፍ የዘላለምን ህይወት ሊሰጠን ይችላል፡፡

ሮሜ 6፡1 ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ሥፍራ እየተጠቀመ ያለው አነጋገር ምንድነው? ለዚህ ዓይነት አስተሳሰብ በሮሜ 6፡2-11 ምላሽ የሚሰጠው እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ጳውሎስ በሮሜ 6 የተቀደሰ ሰው ለምን ኃጢአት እንደማይሰራ ለማሳየት ደስ የሚል መከራከሪያ መንገድን ይከተላል፡፡ ለመጀመር ያህል እንዲህ በማለት ይጀምራል፣ ኃጢአትን የማናደርገው ለኃጢአት የሞትን ሰለሆነ ነው ይላል፡፡ ከዚያም ምን ማለቱ እንደሆነ ይገልጻል፡፡

በጥምቀት ባህር ውስጥ መጥለም የሚወክለው መቀበርን ነው፡፡ መቀበር ምንድነው? ኃጥአተኛ የሆነው ‹‹አሮጌው ሰው›› ኃጢአትን የሚያደርገው ሰውነት ፣ እናም ለኃጢአት የተገዛው ማንነት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ‹‹ የኃጢአት ሰውነት›› ተደምስሷል፣ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ኃጢአትን አናገለግልም፡፡ በሮሜ 6 ኃጢአት አገልጋዮቹን እንደሚገዛ የበላይ ሆኖ ተጠቅሷል፡፡ አንድ ጊዜ ኃጢአትን ያገለገለው ‹‹ የኃጢአት ሥጋ›› ሲደመሰስ፣ የኃጢአት የበላይነት ያበቃል፡፡ ከጥምቀት መቃብር ውስጥ የሚወጣው ኃጢአትን የማያገለግል አዲስ ሰው ሆኖ ይነሳል፡፡ ከዚህ በኋላ እርሱ በአዲስ ህይወት ይመላለሳል፡፡

ክርስቶስ ሲሞት ሳለ፣ አንዴ ለሁሉም ሞቷል ፣ ነገር ግን አሁን ለዛላለም በህይወት ይኖራል፡፡ ስለዚህ የተጠመቀ ክርስትያን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ከሞተ ተመልሶ በኃጢአት ቁጥጥር ስር አይሆንም፡፡ በእርግጥ እንደማንኛውም የተጠመቀ ክርስቲያን ኃጢአት በአንድ ጊዜ ልክ ከውኃ ውስጥ እንደወጣን ከህይወታችን እንደማይወገድ ያውቃል፡፡ በኃጢአት አለመገዛት ማለት ከኃጢአት ጋር ትግል የለም ከማለት ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡

· ከዚህ የሐዋሪያው ቃላት ምን ማለት እንደሆን በግልጽ እንረዳለን፡፡ ‹‹ ለኃጢአት ሞተናል›› ፣ ‹‹ ለእግዚአብሄር በህይወት እንኖራለን›› ወዘተ የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች የሚያመለክቱት ኃጢአት በውስጣችን የሚቀጥል ቢሆንም፣ ኃጢአተኛ ለሆነ ምኞት ራሳችንን አናስገዛም የሚለውን የሚያስገነዝቡ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ እስከ ህይወታችን ፍጻሜ ድረስ ኃጢአት በህይወታችን የሚቀጥል ቢሆንም ፣ በገላ 5፡ 17

· ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ለይ ይመኛልና እነርሱም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ ፣ ስለዚህም የሚትወዱትን አታደርጉም፡፡›› ስለዚህ ሁሉም ሐዋሪያትና ቅዱሳን ኃጢአትና የኃጢአት አስተሳሰብ ሰውነት ወደ አመድ እስኪለወጥ ድረስ በሰውነት ይቆያል፣ ከዚያም ከኃጢአት ነጻ የሆነው አዲሱና የከበረው ሰውነት ይነሳል፡፡››” —Martin Luther, Commentary on Romans, p. 100.
 

ህዳር 4
November 13
 

ኃጢአት ሲነግስ

 

በሮሜ 6 ፡ 12 የተሰጠን ግሳጼ ምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

መንገስ የሚለው ቃል የሚያሳየው ‹‹ኃጢአት› › በንጉስ መወከሉን ነው፡፡ ‹‹ መንገስ ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል ‹‹ ንጉስ ለመሆን የሚል ትርጉም ያለው ነው ፣ ወይም ‹‹እንደ ንጉሥ ለማገልገል›› የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኃጢአት ማለት ሙሉ በሙሉ የሟች ሥጋችንን ንግሥና አምኖ ራስን መስጠት ማለት ነው፡፡

ጳውሎስ ‹‹ኃጢአት አይንገስብን ›› ሲል የተቀደሰ ሰው ኃጢአትን ላለማድረግ እና በራሱ ላይ ንጉስ እንዳይሆን ለመከላከል መምረጥ ይችላል ማለት ነው፡፡ የምርጫ ድርጊት የሚመጣው እዚህ ነው፡፡

‹‹ ማስተዋል የሚገባን የምርጫ ነጻነትን እውነተኛ ኃይል ነው፡፡ በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ገዥ የሆነው ኃይል፣ የመወሰን ወይም የምርጫ ነጻነት ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገር በትክክለኛው ምርጫ ለይ ይወሰናል፡፡ የምርጫ ነጻነትን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠ በመሆኑ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡ ልብህን መለወጥ አትችልም ፣ ፍቅሩንም በራስህ ለእርሱ መስጠት አትችልም፣ ነገር ግን ልታገለግለው መምረጥ ትችላለህ፡፡ ፈቃድህን መስጠት ትችላለህ፣ ከዚያም እርሱ እንደ መልካም ፈቃዱ እና ደስ እንደሚያሰኘው በአንተ ይሰራል፡፡ ከዚያም የአንተ ሙሉ ተፈጥሮ በክርስቶስ መንፈስ ቁጥጥር ሥር ይሆናል፤ የፍቅርህ ማዕከል ክርስቶስ ይሆናል፣ አስተሳሰብህም ከእርሱ ጋር የሚስማማ ይሆናል፡፡›› -Ellen G. White, Steps to Christ, p. 47.

በሮሜ 6፡ 12 ‹‹ ምኞት›› ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል ማለት ፍላጎት ማለት ነው፡፡ ይህ ፍላጎት ለመልካም ወይም ለክፉ መሆን ይችላል፤ ኃጢአት በሚነግሥበት ጊዜ መጥፎን እንድንመኝ ያደርገናል፡፡ እነዚህ ፍላጎቶች በራሳችን ከታገልናቸው ለማሸነፍ አስቸጋሪ እስኪሆኑ ድረስ ይጠነክራሉ፡፡ ኃጢአት በፍጹም የማይጠግብ አምባገነን በመሆን ደጋግሞ ሌላ ፍለጋ ይመጣል፡፡ የድልን ተስፋ የራስ በማድረግ፣ በእምነት በኩል ብቻ ይህንን ክፉ አለቃ ከላያችን ልናስወግደው እንችላለን፡፡

ስለዚህ በሮሜ 6፡12 ላይ ያለው ቃል አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ ኋላ በመሄድ በሮሜ 6፡10፣11 ከተባለው ቃል ጋር ይስማማል፡፡ የተጠመቀ ሰው አሁን ለእግዚአብሔር ይኖራል፡፡ ይህ ማለት የአዲሱ ህይወት ማዕከሉ ክርስቶስ ነው ማለት ነው፡፡ ሰውዬው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን እያደረገ እርሱን ያገለግላል ስለዚህ ይህ ሰው በተመሳሰይ ጊዜ ኃጢአትን ማገልገል አይችልም፡፡ ‹‹ እርሱ ወይም እርሷ በክርስቶስ ለእግዚአብሔር በህይወት ይኖራሉ፡፡››

በዛሬው ጥናት ላይ ወደሚገኘው የኤሌን ዋይት ጥቅስ ይመልከቱ፡፡ የምርጫ ነጻነት የሚለው ሀሳብ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያስተውሉ፡፡ እንደ ፍጥረታት ክፉውን ወይም ደጉን፣ መልካሙን ወይም መጥፎውን፣ ክርስቶስን ወይም ዓለምን የመምረጥ ነጻነት ሊኖረን ይገባል፡፡ በሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ይህንን የምርጫ ነጻነትዎን እንዴት እንደሚጠቀሙበት በትኩረት ያስቡ፡፡ ከዚህ የተቀደሰ ነገር ትክክለኛ ወይም አግባብ ከሌለው አጠቃቀምዎ ምን መማር ይችላሉ?
 

ህዳር 5
November 14
 

ከህግ በታች ሳይሆን ከጸጋ በታች

 

ሮሜ 6:14ን ያንብቡ፡፡ ይህንን ጥቅስ የምናስተውለው እንዴት ነው? ይህ ማለት አሥርቱ ትዕዛዛት አሁን በእኛ ለይ አይሰሩም ማለት ነው? እንዲህ ካልሆነ ለምን?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ሮሜ 6፡14 በሮሜ መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙ ቁልፍ ሐሳቦች አንዱ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የሰባተኛው ቀን ሰንበት ተሽሯል ለማለት ለእኛ አድቬንቲስቶች የሚነገረን ጥቅስ ነው፡፡

ነገር ግን ጥቅሱ የሚለው ይህንን እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ በፊት እንደጠየቅነውም ፣ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከተወገዱ ኃጢአት የሚኖረው እንዴት ነው? ምክንያቱም ኃጢአት ምን እንደሆነ የሚነግሩን አሥርቱ ትዕዛዛት ናቸው! በሮሜ መጽሐፍ ቀድሞ የተጻፉትን ለምሳሌ በምዕራፍ 6 ያለውን ብቻ እንኳ ቢያነቡ፣ እንዲህ ባለ ስለ ኃጢአት በሚሰጠው ዝርዝር መግለጫ ውስጥ ጳውሎስ በድንገት ‹‹ ኃጢአት ምን እንደሆነ የሚገልጹትን አስርቱን ትዕዛዛት ተደምስሰዋል ለማለት እንደሚችል ማሰብ ከባድ ነው፡፡ ይህንን ቢል ስሜት የሚሰጥ አይሆንም፡፡

ጳውሎስ እያለ ያለው‹‹ በህግ ስር›› የሚኖር ሰው ማለትም በእርሱ ዘመን የነበሩና የተለመዱ ሰው ሰራሽ ህጎችና መመሪያዎች በሙሉ በኃጢአት ይገዛሉ፡፡ በተቃራኒው፣ በጸጋ ሥር የሚኖር ሰው በኃጢአት ለይ ድልን ያገኛል፣ ምክንያቱም ህጉ በእርሱ ወይም በእርሷ ልብ ውስጥ ተጽፏል እናም የእግዚአብሔር መንፈስ የዚህን ሰው ዱካ ለመምራት ፈቃድ አግኝቷል፡፡ የኢየሱስን መሲህነት እንደ መቀበሉ እና በእርሱ እንደ መቀደሱ ፣ በሞቱም እንደ መጠመቁ በአዲስ ህይወት ለመመላለስ አሮጌው ተደምስሷል ፣ እነዚህ ነገሮች ናቸው ኃጢአት በህይወታችን ሥልጣን እንዳይኖረው የሚያደርጉ፡፡ በሮሜ 6፡ 14 የሚታየው አጠቃላይ አውድ ይህን ይመስላል ይህም በኃጢአት ላይ ድልን የመቀዳጀት ተስፋ፡፡

‹‹በህግ ሥር ›› የሚለውን በጣም ውስን አድርገን አንተረጉመውም ፡፡ በጸጋ ሥር እንደሚኖር የሚገመት ሰው ህግን ቢተላለፍ ኩነኔን እንጂ ጸጋን አያገኝም፡፡ ‹‹ በጸጋ ሥር ›› ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተገለጠው የእግዚአብሔር ጸጋ አይቀሬ የሆነ በኃጢአተኛው ላይ ህግ የሚያመጣው ኩነኔ ተወግዷል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በህግ ከመጣው የሞት ፍርድ ነጻ በመሆን ‹‹ በአዲስ ህይወት እንኖራለን›› ፣ ይህም ህይወት የተመሰረተውና የሚገለጸው ለራስ በመሞት ሲሆን ፣ እኛ ከዚያ ወዲያ ለኃጢአት ባሪያ አንሆንም፡፡

በክርስቶስ የሚገኘውን አዲስ ህይወት የተለማመዱት እንዴት ነው? ክርስቶስ በህይዎትዎ ስላደረገው ነገር ምን ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ ይችላሉ?
 

ህዳር 6
November 15
 

ኃጢአት ወይም መታዘዝ

 

ሮሜ 6፡16ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ እያነሳ ያለው ነጥብ ምንድነው? ይህ ክርክር በዚህ ሥፍራ ግልጽ የሆነው ለምንድነው? ሊሆን የሚችለው ከሁለት አንዱን እንጂ መካከለኛ ሥፍራ የለውም፡፡ ከዚህ ግልጽ ከሆነ ማወዳደሪያ ሀሳብ ምን ትምህርት እናገኛለን?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ጳውሎስ እንደገና በእምነት የተገኘው አዲሱ ህይወት ኃጢአትን ለማድረግ ዋስትና እንደማይሰጥ ለመናገር ወደ ኋላ ይሄዳል፡፡ የእምነት ህይወት በኃጢአት ላይ ድል ያደርጋል፣ በእርግጥ ለአሸናፊነት የተሰጠን ተስፋ በእምነት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡

ጳውሎስ ኃጢአትን ለሚታዘዙለት እንደ ገዥ (አለቃ) አድርጎ ከገለጸ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ከተገዢዎቹ መታዘዝን እንደሚፈልግ ባለሥልጣን ያብራራዋል፡፡ ጳውሎስ አንድ ሰው ገዢውን የመምረጥ ነጻነት እንዳለው ያመለክታል፡፡ ወደ ሞት የሚወስደውን ኃጢአትን ወይም ወደ ዘለዓለም ህይወት የሚወስደውን ጽድቅን ማገልገል ይችላል፡፡ ጳውሎስ ለድርድር የሚሆን ምንም መካከለኛ ሥፍራ አልተወልንም፡፡ ሊሆን የሚችለው አንዱ ወይም ሌላኛው ነው ምክንያቱም በመጨረሻው የሚጠብቀን የዘላለም ህይወት ወይም ሞት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡

ሮሜ 6፡17 ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በሮሜ 6፡16 ላይ የተናገረውን በስፋት ያብራራው እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በቂና አስደሳች በሆነ ሁኔታ መታዘዝ ከትክክለኛው ትምህርት ጋር ምን ያህል ቁርኝት እንዳለው ያስተውሉ፡፡ “doctrine” ለሚለው የእንግሊዝኛው ቃል የግሪኩ አቻው “teaching.” (ማስተማር) የሚለው ነው፡፡ የሮሜ ክርስትያኖች አሁን እየታዘዙ ያሉትን የክርስትና እምነት ከበፊት ጀምረው እየተማሩ ቆይተዋል፡፡ ስለዚህ ለጳውሎስ ‹‹ከልብ ከታዘዙለት›› እውነተኛው መመሪያና ትክክለኛው ትምህርት በሮሜ መጽሃፍ አንድ ሰው ‹‹ የጽድቅ አገልጋይ ›› እንዲሆን ይደግፋል፡፡ ( ሮሜ 6፡ 18) አንዳንድ ጊዜ ፍቅርን እስካሳየን ድረስ አስተምህሮ ምንም ቢሆን ችግር የለውም ሲባል እንሰማለን፡፡ ይህ አንድ በጣም ዝም ብሎ ተራ ያልሆነን ነገር እንደ ቀላል ለመግለጽ ሰዎች የሚጠቀሙት አባባል ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ተብሎ እንደተገለጸው ጳውሎስ የገላቲያ ቤተክርስቲያን ሰዎች በተቸገሩበት የስህተት ትምህርት ላይ ትልቅ ትኩረት አድርጓል፡፡ ስለዚህ የአንድን አስፈላጊ ትምህርት ትርጓሜ ሊያጣምሙ በሚችሉ አረፍተ ነገሮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡

የኃጢአት አገልጋዮች፣ የጽድቅ አገልጋዮች፤ የሚለው ንጽጽር በጣም ኃይለኛ ነው፡፡ ይህ ማለት ከተጠመቅን በኋላ ኃጢአት ብንፈጽም በእውነት አልዳንንም ማለት ነው? 1ዮሐ 1፡8 እና 2፡1ን ያንብቡ፡፡ ይህ ጥቅስ ለውድቀት የተጋለጥን መሆናችን እንዳለ ሆኖ የክርስቶስ ተከታይ የሚለውን ለመረዳት እንዴት ይረዳናል?

ህዳር 7
November 16

ከኃጢአት ነጻ

 

በሮሜ 6 ላይ የተማርነውን በአእምሮ እንደያዝን ሮሜ 6፡ 19- 23 ያለውን ያንብቡ፡፡ በሚቀጥሉት መስመሮች ላይ የጳውሎስን አባባል ጠቅለል አድርገው ያስቀምጡ፡፡ ጳውሎስ የሚናገረው እውነት በህይወትዎ እውን መሆኑን ራስዎን ይጠይቁ፡፡ ምን ዓይነት ችግሮች እንዳሉ ራስዎን ይፈትሹ፡፡

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በዚህ ስፍራ ያሉ የጳውሎስ ቃላት የሚያመለክቱት እርሱ የወደቀውን ሰብአዊ ዘር ባህርይ በትክክል ማስተዋሉን ነው፡፡ እርሱ ስለ ሥጋ አለመጽናት ይናገራል፡፡ አለመጽናት ለሚለው በግሪኩ የተወከለው ቃል ‹‹የስጋ ድካም›› የሚለው ነው፡፡ እርሱ የወደቀው የሰው ባህሪይ ብቻውን ከተተወ የማይችል መሆኑን ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ይህንን የወደቀውን ማንነታችንን ለአዲሱ ባለስልጣን ይድቅን ህይወት እንድንኖር ለሚያስችለን (ለኢየሱስ ክርስቶስ ) ለማስገዛት እንድንችል የምርጫ ነጸነታችንን እንድንጠቀም ይጋብዘናል፡፡

ሮሜ 6፡23 ብዙውን ጊዜ የኃጢአት ዋጋ ፣ ያም ህግን መተላለፍ ውጤቱ ሞት እንደሆነ ለማሳየት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በእርግጥ የኃጢአት ዋጋ ሞት ነው፡፡ ነገር ግን ሞትን እንደ ኃጢአት ዋጋ ከማየት በተጨማሪ ፣ ጳውሎስ በሮሜ 6 እንደገለጸው እንደ ጨቋኝ አለቃ በራቸውን ለሚከፍቱ አገልጋዮቹ ሞትን እንደዋጋቸው የሚከፍል ነው ፡፡

ጳውሎስ ስለ ሁለት ጌቶች በሰጠው ምሳሌ ፣ አንድን ጌታ ማገልገል ማለት ከሌላኛው ነጻ መውጣት እንደሆነ ያስቀመጠውን ያስታውሱ፡፡ እንደገና መምረጥ የሚቻለው አንዱን እንደሆነ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ ከሁለቱ ሌላ መካከለኛ የሚባል አቋም የለም፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ከኃጢአት ግዛት ነጻ መውጣት ማለት ኃጢአት የሌለበት እንሆናለን፣ በምንወድቅበት ጊዜ እንኳ ከኃጢአት ጋር ምንም ትግል የለብንም ማለት አይደለም፡፡ በዚያ ፋንታ እኛ ለኃጢአት አንገዛም፣ ነገር ግን በየእለቱ ድልን በተስፋ እየተጣባበቅን በህይወታችን ይቆያል፡፡

ስለዚህ ይህ ንባብ ኃጢአትን ለሚያገለግል ሁሉ ኃይለኛ ተማዕጽኖ ይሆናል፡፡ ይህ አምባገነን አሳፋሪ ድርጊት ለሚፈጽሙ ሞትን ዋጋቸው አድርጎ ይሰጣል፣ ስለዚህ በምክንያት የሚያምን ሰው ከዚህ ጨቋኝ ነጻ የሚወጣበትን ተስፋ በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡ በተቃራኒው ፣ ጽድቅን የሚያገለግሉ ድነትን ለማግኘት ሳይሆን የአዲስ ህይወታቸው ልምድ በማድረግ ፣ ትክክል የሆነውን ፣ ለምስጋና የሚያበቃ ሥራን ይሰራሉ፡፡ እነርሱ ድርጊቱን ድነትን ለማግኘት ብለው የሚፈጽሙት ከሆነ፣ የወንጌልን ሙሉ ነጥብ ይስታሉ፤ መዳን ምን እንደሆነ እና እነርሱ ክርስቶስ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው ዋና ነጥቡን ይስታሉ፡፡
 

ህዳር 8
November 17
 

ለተጨማሪ ጥናት፡-

 

የሚከተሉትን የኤሌን ዋይት መጻህፍት ያንብቡ፡፡ Read Ellen G. White, “Victory Appropriated,” pp. 105, 106, in Mes-sages to Young People; “The True Motive in Service,” pp. 93—95, in Thoughts From the Mount of Blessing; “Appeal to the Young,” p. 365, in Testimonies for the Church, vol. 3; pp. 1074, 1075, in The SDA Bible Commentary, vol. 6.

እርሱ (ክርስቶስ) የኃጢአት ፍላጎት አልነበረበትም፡፡ በሃሳቡ እንኳ ለፈተና ቦታ አልሰጠም፡፡ ስለዚህ በእኛም እንዲሁ ሊሆን ይችላል፡፡ የክርስቶስ ሰብአዊነት ከመለኮታዊነት ጋር አንድ ሆነ፤ በውስጡ በሚያድረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ተቃርኖን ለመከላከል ዝግጁ ሆነ ፡፡ እናም እርሱ የመጣው እኛን የመለኮታዊ ባህሪይ ተካፋዮች ሊያደርገን ነው፡፡ እኛ በእምነት ከእርሱ ጋር አንድ ከሆንን ፣ ኃጢአት በእኛ ላይ ሥልጣን አይኖረም፡፡ ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት እንድንደርስ እግዚአብሄር የእምነት እጃችንን አጥብቆ ከክርስቶስ መለኮታዊነት ጋር ያያይዘዋል፡፡›› —Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 123.

በጥምቀታችን ጊዜ ከኃጢአት፣ ከሰይጣን እና ከተወካዮቹ ጋር ያለንን ማንኛውንም ግንኙነት ለመለየት ቃል የገባን ሲሆን አእምሮአችንን ነፍሳችንን እና ልባችንን የእግዚአብሄርን መንግሥት ለማስፋፋት ቃል ገብተናል…አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከተቀደሰ ሰው ጋር ለመተባበር ቃል ገብተዋል፡፡” —Ellen G. White Comments, The SDA Bible Commentary, vol. 6, p. 1075.

ከእምነትና ከሥራ ጋር ያልተገናኘ ክርስትና ምንም አይጠቅምም፡፡ ማንም ሰው ሁለት ጌታን ማገልገል አይችልም፡፡ የክፉው ልጆች የሚገዙበት የራሳቸው ጌታ አላቸው ፣ እርሱንና ሥራውን ክደው ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ እግዚአብሔርን ማገልገል አይችሉም፡፡ ምንም እንኳ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለበት ብዙ ጊዜ ደጋግመው ቢናገሩም የእግዚአብሔር አገልጋዮች (የሰማዩ ንጉሥ አገልጋዮች) የሰይጣን አገልጋዮችን በሚያስደስተውና በሚያስደንቃቸው ተግባር ተካፋዮች ቢሆኑ ጉዳት አለው፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑትን ህዝቦች እርሱን ከማያውቁት ለመለየት የተቀደሱና የተለዩ እውነቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እምነታቸውን ሊኖሩ ይገባል፡፡” —Ellen G. White, Testi monies for the Church, vol. 1, p. 404.
 

የመወያያ ጥያቄዎች:-፡

 

  1. ኃጢአትን ድል ለማድረግ የዚህን ያህል ተስፋዎች ያሉን ቢሆንም ፣ ዳግም የተወለድን ክርስትያኖች ብንሆንም ምን ያህል ኃጥአተኞችና የወደቅን መሆናችንን እናውቃለን፡፡ እዚህ የሚጋጭ ሀሳብ አለ? ወይስ እንዴት ነው? መልስዎን ያብራሩ፡፡

  2. ምንም እንኳ መዳናችን ሙሉ በሙሉ ክርስቶስ ለእኛ በሰራው ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፣ ሌሎቹን ለድነት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን፣ ክርስቶስ እኛን ለመለወጥ ያደረጋቸውን ችላ ብንል ምን አደጋ ሊያስከትል ይችላል? እነዚህን የድነት አቅጣጫዎች ማወቅ የሚያስፈልገን ለምንድነው?