ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ትምህርት ሮሜ 3፡19-28ን ያንብቡ፡፡
የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ ሰው ያለ ህግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለን ” (ሮሜ 3፡28)
በዚህ ትምህርት ወደ ሮሜ መጽሐፍ ዋና ሀሳብ እንገባለን፡፡ ይህም፤ ጽድቅ በሐይማኖት የሚለው የፕሮቴስታንትን ተሐድሶ ያመጣው ከሁሉ የሚበልጥ እውነት ነው፡፡ ይህን የሚቃረኑ ብዙ አስተሳሰቦች ቢኖሩም፣ የሮሜ መጽሐፍ ይህንን እምነት በተመለከተ በ1520 ጰጳስ ሊዮ ህጋዊ መመሪያ በማውጣት ሉተርንና የእርሱን ትምህርት በተቃወመበት ዘመን እንደነበር አሁንም አልተለወጠም፡፡ ጽድቅ በእምነት የሚለውን አስተምህሮ የሚቃወም አንዳችም ትምህርት በውስጡ እንዳይገኝ በማሰብ ሉተር ሰነዱን አቃጠለው፡፡
ሀረጉ ራሱ በህግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የህግ ተላላፊ ወደ ዳኛ ፊት ይቀርብና ህግን ስለመተላለፉ የሞት ፍርድ ይፈረድበታል፡፡ ነገር ግን ተተኪ ይመጣና የተላላፊውን ወንጀል በራሱ ይወስድና በደለኛውን ያነጻዋል፡፡ ተተኪውን በእምነት በመቀበል፣ አሁን ወንጀለኛው በዳኛ ፊት ይቆማል፣ መተላላፉ ይቅር ተብሎ ብቻ ሳይሆን፣ ቀደም ብሎ የተከሰሰበትንና ወደ ፍርድ ፊት የቀረበበትን ወንጀል ፈጽሞ እንዳልበደለ ተደርጎ ይታያል፡፡ ይህ የሆነው ምትኩ በመዝገቡ ላይ አንዳች ነቁጣ የሌለው በመሆኑ ወንጀለኛውን ፍጹም በሆነው ህግን ማክበሩ ነጻ ያወጣል፡፡
ስለ መልካም ዜና ተነጋገሩ፡፡ በእርግጥ ዜናው ከምታወሩት የበለጠ አይሆንባችሁም?
ለጥቅምት 18 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ሮሜ 3:19, 20ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ህግ ማድረግ ስለሚችለው ነገርና ስለማይችለው ነገር ምን እያለ ነው? ይህ ነጥብ ሁሉም ክርስትያኖች እንዲያስውሉት የሚያስፈልገው ለምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጰውሎስ ህግ የሚለውን ቃል እየተጠቀመ ያለው በዘመኑ የነበሩ አይሁዶች በሚረዱበት ሰፋ ያለ ትርጉም ባለው መልኩ ነው፡፡ ቶራ የሚለው ህግ ለሚለው ቃል የዕብራይስጥ አቻው ነው፡፡ አይሁዳውያን ዛሬም ድረስ የእግዚአብሄር መመሪያ ነው ብለው የሚያምኑት አምስቱ የሙሴ መጻህፍት እንዲሁም በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ነው፡፡ ግብረ-ገባዊ ህጎችና መገለጫቸው እና የፍርድና የባህርይ መለኪያዎች እንዲሁም ሜዳዊ ሥርዓቶች የዚህ መመርያ አካሎች ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ ምናልባትም እንደ አይሁዳውያን የኑሮ ዘይቤ ልናየው እንችላለን፡፡ ከህግ በታች ማለት በእርሱ ክልል መሆን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ህጉ የሰውየውን ጉድለትና በደሉን በእግዚአብሔር ፊት ያሳያል፡፡ ህጉ ኃጢአቱን ሊያስወግድ አይችልም፣ ማድረግ የሚችለው ግን ኃጢአተኛውን ይቅርታ ወደሚያገኝበት ይመራዋል፡፡
በዘመናችን የሮሜን መጽሐፍ ስንተገብረው፣ ህግ የሚለው በአይሁዳውያን አተረጓጎም ባለመሆኑ የምናስበው ስለ አስርቱ ትዕዛዛት ነው፡፡ የአይሁዳውያን የአኗኗር ዘይቤ እነርሱን እንዳላዳናቸው ሁሉ ይህ ህግ እኛን ሊያድነን አይችልም፡፡ ኃጢአተኛን ማዳን የትዕዛዛት ሥራ አይደለም፡፡ የእርሱ ተግባር የእግዚአብሄርን ባህርይ ማሳየትና ሰዎች እንዴት ባህርዩን ማንጸባረቅ እንዳቃታቸው ማሳየት ነው፡፡
አስርቱን ትዕዛዛት፣ ሜዳዊ ሥርአቶች ፣ ማህበራዊ ደንቦች ወይም ሁሉንም ህጎች በአንድ ላይ መጠበቅ ማንንም በእግዚአብሔር ፊት አያጸድቅም፡፡ ህግ ይህንን አያደርግም፡፡ በእርግጥ ህግ ይህንን ማድረግ አይጠበቅበትም፡፡ በተቃራኒው ህግ የጎደለንን ነገር በመጠቆም ወደ ክርስቶስ፡ይመራናል፡፡
የህመም ምልክት ህመሙን እንደማይፈውሰው ሁሉ ህግም እኛን አያድነንም፡፡ የበሽታ ምልክት ፈውስ እንደሚያስፈልግ ይጠቁማል እንጂ አያድንም፡፡ ህግ የሚሰራው እንዲህ ነው፡፡
ህግን ለመጠበቅ ያደረጉት ጥረት ምን ያህል የተሳካ ነበር? የዚህ ምላሽ ህግን ጠብቆ ለመዳን የሚደረግ ጥረት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ምን ይነግረናል?
“አሁን ግን በህግና በነብያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ህግ ተገልጦአል፡፡ ሮሜ 3፡21 ፡፡ ይህንን ጥቅስ እንዴት እናስተውለዋለን?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ይህ አዲሱ ጽድቅ፣ አይሁዳውያን ከሚያውቁት በህግ ከሚገኘው ጽድቅ ጋር በንጽጽር የቀረበው ነው፡፡ አዲሱ ጽድቅ ‹‹የእግዚአብሔር ጽድቅ ይባላል›› ፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚመጣ ፣ እግዚአብሔር የሚያዘጋጀው ጽድቅ እናም እርሱ በብቸኝነት እውነተኛ አድርጎ የሚቀበለው ጽድቅ ነው፡፡
ይህ ጽድቅ በእርግጥ ኢየሱስ የሰውን ሥጋ ለብሶ በምድር ላይ ሳለ የሰራው እና በእምነት ለመቀበል የእነርሱ እንደሆነ ተስፋ ለሚያደርጉ፣ ስለሚገባቸው ሳይሆን ስለሚፈልጉ የሚሰጣቸው ጽድቅ ነው፡፡
“ጽድቅ ለህግ መታዘዝ ነው፡፡ህግ ጽድቅ ይፈልጋል፤ እና ይህ ህግ ከኃጥአተኛ የሚፈልገው ነው ነገር ግን እርሱ ይህን ማድረግ አይችልም፡፡ ኃጢአተኛ ይህንን ማሟላት የሚችለው ብቸኛ መንገድ በእምነት በኩል ብቻ ነው፡፡ በእምነት አማካይነት በክርስቶስ የተፈጸመለትን ነገር ወደ እግዚአብሄር ያመጣል፤ እናም እግዚአብሔር የልጁን መታዘዝ ስለ ኃጢአተኛው ምትክ ይመዘግብለታል፡፡ የክርስቶስ መታዘዝ በሰው ውድቀት ፋንታ ተቀባይነት ያገኝና እግዚአብሔር ንስሐ የገባውን ፣የሚያምነውን ነፍስ እንደ ጻድቅ በመቀበል እንደ ራሱ ልጅ ይወደዋል፡፡” Ellen G. White, Selected Messages, book 1, p. 367. ይህን አስደናቂ እውነት ለራስዎ እንዴት ይቀበሉታል? ሮሜ 3፡22ን ይመልከቱ፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የክርስቶስ እምነት ማለት ይህ ነው ይህም በክርስቶስ ያለ ጥርጥር ማመን ነው፡፡ ይህ እምነት በክርስትያን ህይወት ሲሰራ ከዕውቀት ጋር ከመስማማት፣ የክርስቶስን ህይወትና ሞትን ከመቀበል እጅግ የሚበልጥ ነው፡፡ በዚህ ፋንታ በክርስቶስ እውነተኛው እምነት እርሱን እንደ አዳኝ፣ምትክ፣እና ጌታ አድርጎ መቀበል ነው፡፡ እርሱም የክርስቶስን አኗኗር መምረጥ ነው፡፡ እርሱን መተማመንና በእምነት እንደ ትዕዛዙ ለመኖር መፈለግ ነው፡፡
ህግ ምን ማድረግ እንደሚችልና ምን ማደረግ እንደማይችል ከዚህ ቀደም ብለን የተማርነውን በአእምሮአችን እንያዝ፣ ሮሜ 3፡24ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ስፈራ ምን እያለ ነው? በክርስቶስ መዋጀት ማለት ምን ማለት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በዚህ ጥቅስ እንደሚገኘው ‹‹ ማጽደቅ ምንድነው? Dikaioo የሚለው የግሪኩ ቃል ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጎም “justify,” ይህም ማለት‹‹ ጻድቅ ማድረግ›› “make righteous,”‹‹ጻድቅ እንደሆነ ማወጅ›› “declare righteous,” ወይም ‹‹ጻድቅ አድርጎ ማሰብ›› “consider righteous.”ቃሉ የተመሰረተው dikai-osune, “ጽድቅ,”በሚለው ቃል ላይ ሲሆን dikaioma, የሚለው ቃል “የጽድቅ መስፈርት ”ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹በመጽደቅና›› ‹‹ጽድቅ›› መካከል በጣም የቀረበ ግንኙት ሲኖራቸው ቅርርቡም በተለያዩ ትርጉሞች ብዙውን ጊዜ አብረው የማይመጡ ናቸው፡፡ የጸደቅነው በእግዚአብሔር ‹‹ጻድቅ ተብለን ስንታሰብ›› ነው፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት ማንኛውም ሰው ጻድቅ ባለመሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ እግዚአብሔር በልጁ አማካይነት ጻድቅ ሲያደርገው ተቀባይነትን ያገኛል ፡፡
ይህ ሊሆን የሚችለው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው፡፡ ጸጋ ማለት ሥጦታ ነው፡፡ ኃጢአተኛ ድነትን ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር ሲመለስ ያንን ሰው ጻድቅ አድርጎ መቀበል (ማወጅ) የጸጋ ሥራ ነው፡፡ ይህ የተገባው ሥጦታ አይደለም እናም አማኙ የሚጸድቀው የራሱ የሆነ ምንም ነገር በሌለበት ነው፣ በራሱ ፋንታ በእግዚአብሔር ፊት ሊያቀርበው የሚችል ነገር ከረዳተ-ቢስነቱ በቀር አንዳችም የለውም፡፡ ሰውየው የሚጸድቀው በክርስቶስ በኩል በተደረገለት መዋጀት ሲሆን ይህም ክርስቶስ በኃጢአተኛው ምትክ ሆኖ በሚያቀርበው ነው፡፡
በሮሜ መጽሐፍ ላይ ጽድቅ አንድ ነጥብ በሆነ ጊዜ የሚከሰት ነገር ነው፡፡ አንድ ጊዜ ኃጢአተኛው ተቀባይነት አልነበረውም ጻድቅ ስላይደለ ውጭ ነበር፣ በሚቀጥለው ጊዜ ሰውዬው ጽድቅን ተከትሎ ወደ ውስጥ ገባ ተቀባይነትን አገኘ፡፡
በክርስቶስ ያለ ሰው ጽድቅን የሚያየው ፣ራሱን ሙሉ በሙሉ ለክርስቶስ በሰጠ ጊዜ እንደተከናወነ እንዳለፈ ነገር ነው፡፡ “የጸደቀ” (ሮሜ 5:1) “ጽድቅን ያገኘ”
በእርግጥ የጸደቀ ክርስትያን ከክርስቶስ ከራቀ ቦኋላ እንደገና ወደ ክርስቶስ ቢመለስ እንደገና ይጸድቃል፡፡ በተጨማሪም ዳግም መመለስ የየዕለት ልምምድ ከሆነ መጽደቅም ተደጋጋሚ ልምምድ ሊሆን ይችላል፡፡
የመዳን መልካም ዜና ጥሩ እንደመሆኑ ሰዎችን እንዳይቀበሉ የሚያደርጋቸው ምንድነው? በራስዎ ህይወት እግዚአብሄር ከሚሰጠው ተስፋ ወደ ኋላ የሚያስቀርዎት ምን ምን ነገሮች ናቸው?
በሮሜ 3፡25 ጳውሎስ ስለ መዳን መልካም ዜና በሥፋት ይናገራል ፡፡ እርሱም ማስተሰሪያ የሚለውን አስደናቂ ቃል ይጠቀማል፡፡ ለዚህም የግሪኩ አቻ ቃል hilasterion የሚል ሲሆን በአዲስ ኪዳን በዚህ ስፍራና በዕብ. 9፡5 ላይ ብቻ የሚገኝ ነው ‹‹የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ›› በመባል ተተርጉሟል፡፡ በሮሜ 3፡ 25 ላይ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ስለተሰጠው ጽድቅና መዋጀት፣ እና መስዋዕትነት በብሉይ ኪዳን ጊዜ እንደ ጥላ ሆኖ በቤተ መቅደስ ውስጥ በምህረት መቀመጫ የነበረው በዋናው በክርስቶስ መተካቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም ማለት በእርሱ የመስዋዕትነት ሞት ኢየሱስ የመዳናችን ምክንያት በመሆን መስዋዕትነትን አቅርቧል፡፡ በአጭሩ እግዚአብሔር ለመዳናችን የሚያስፈልገውን አድርጓል ማለት ነው፡፡
ጥቅሱ በተጨማሪ ስለ ‹‹ኃጢአት ስርየት ይናገራል፡፡›› በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረን የሚያደርገው ኃጢአታችን ነው፡፡ ኃጢአታችንን ለመደምሰስ በራሳችን ምንም ልናደርግ አንችልም፡፡ ነገር ግን በድነት ዕቅድ ውስጥ እግዚአብሔር በክርስቶስ ባለን እምነት ኃጢአታችን እንዲደመሰስ መንገድን አዘጋጀልን፡፡
‹‹ማስተሰረይ›› የሚለው ቃል በግሪክ (paresi) የሚል ሲሆን ትርጓሜው ‹‹መታለፍ›› ወይም ‹‹አልፎ መሄድ›› የሚል ነው፡፡ ማለፍ ማለት ግን በምንም ትርጓሜ ኃጢአትን ችላ ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትን የሚያልፈው ክርስቶስ የሰዎችን ሁሉ ኃጢአት መቀጮ በሞቱ ስለከፈለው ነው፡፡ ስለዚህ ማንም በደሙ የሚያምን ክርስቶስ ለእርሱ ወይም ለእርሷ ስለሞተ የኃጢአትን ስርየት ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ (1ቆሮ. 15፡3)፡፡
ሮሜ 3፡26፣27ን ያንብቡ፡፡ ጰውሎስ በዚህ ስፍራ የሚያነሳው ነጥብ ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ ሊሰሙ ለሚፈልጉ ሁሉ የተዘጋጀ መልካም ዜና ለሰው ሁሉ የሚሆን የእርሱ የእግዚአብሔር ጽድቅ እርሱም ለእኛ የተሰጠን በሥራችን ስለተገባን ሳይሆን ክርስቶስ ለእኛ ባደረገውና በእርሱም ባለን እምነት ነው፡፡
በቀራንዮው መስቀል ምክያት እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ጻድቃን ብሎ ያውጃል፣ ይህም አሁንም ድረስ በዓለማት ሁሉ ዘንድ ቅንና እውነተኛ ነው፡፡ ሰማይ ከሁሉም የሚበልጥ መስዋዕትነትን ስለከፈለ ሰይጣን በእግዚአአብሔር ላይ ጣቱን መቀሰር አይችልም፡፡ የሰው ልጆች በራሳቸው ፈቃድ ማድረግ የማይችሉትን ነገር ነው እግዚአብሔር የጠየቀው የሚል ክስ ሰይጣን ያቀርብ ነበር፡፡ ይህንን አባባሉን መስቀል ውድቅ አድርጓል ( ትክክል አለመሆኑን አስረድቷል፡፡)
ሰይጣን ዓለም ኃጢአት እንደሠራች ወዲያው ያጠፋታል ብሎ አስቦ ነበር፡፡ በዚያ ፋንታ ግን እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ልጁን ላከ፡፡ ይህ ስለ እግዚአብሔር ባህርይ ምን ይነግረናል? ይህንን ባህርዩን ማወቃችን በህይወታችን ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው? እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል በማወቅዎ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ምን የተለየ ነገር ያደርጋሉ?
“ስለዚህ ሰው ያለ ህግ ስራ በእምነት እንድፀድቅ እናውቃለን” (ሮሜ 3:28):: ይህ ማለት ህግ ባያድነንም ህግን መታዘዝ አያስፈልገንም ማለት ነው? መልስዎን ይግለጹ፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሮሜ 3፡28 ለጳውሎስ የእምነት ህግ በራስ ከመተማመን የተለየ ስለመሆኑ ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጠበት ነው፡፡ ሰው በራሱ ሥራ የሚጸድቅ ከሆነ ስለ ራሱ የሚኮራበትን ያገኛል፡፡ ነገር ግን እርሱ በክርስቶስ ባለው እምነት ከጸደቀ ክብሩ ሙሉ በሙሉ ኃጢአተኛውን ላጸደቀው ለእግዚአብሔር ይሆናል፡፡
‹‹ጽድቅ በእምነት ምንድነው?›› ለሚለው ጥያቄ ኤሌን ዋይት አስደናቂ መልስ ትሰጣለች፡፡ ሰው በራሱ ሊያደርገው የማይችለውን ነገር እግዚአብሄር የሰውን ሥራ ወደ ትቢያ በመጣል ራሱ የሰራው ነው፡፡” —Ellen G. White, Testimonies to Ministers and Gospel Workers, p. 456.
የህግ ሥራ ላለፈው ኃጢአታችን ይቅርታ መስጠት አይችልም፡፡ ጽድቅ በዚህ አይገኝም፡፡ ጽደቅ ሊገኝ የሚችለው ሊዋጅ በሚችለው በክርስቶስ መስዋዕትነት በማመን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ትርጓሜ መሰረት የህግ ሥራ ከጽድቅ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ማለት ነው፡፡ ያለ ስራ መጽደቅ ማለት ከራሳችን የሆነ አንዳች ነገር ሳይኖር መጽደቅ ማለት ነው፡፡
ነገር ግን ይህንን ጥቅስ በስህተት በማስተዋል ተግብረውታል፡፡ ተግባርን ወይም መታዘዝን ወዲያ በመተው አስርቱን ትዕዛዛት ጨምሮ አንድ ሰው የሚያስፈልገው ማመን ብቻ ነውይላሉ፡፡ ይህንን በማድረጋቸው ጳውሎስን በስህተት ያነቡታል፡፡ ጳውሎስ በሮሜ መጽሐፍ በየትኛውም ስፈራ አሥርቱን ትዕዛዘት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራል፡፡ ያዕቆብና ዮሃንስ እንዳደረጉት ሁሉ ኢየሱስም አድርጓል፡፡ (ማቴ. 19፡17፣ ሮሜ 2፡13፣ ዕብ. 2፡10፣11 ራዕይ 14፡12)፡፡ ትዕዛዛትን ማክበር የጽድቅ ምክንያት ባይሆንም በእምነት የጸደቀ ሰው ህግን መጠበቅ አለበት፡፡ በእርግጥም ህጉን መጠበቅ የሚችለውም እርሱ ብቻ ነው፡፡ አዲስ ያልተፈጠረና ያልዳነ ሰው የህግን ሥራ ሊፈጽም አይችልም፡፡
ህግ አያድነንም ስለዚህ ህግን ስለመጠበቅ መጨነቅ የለብንም ብሎ ወደማሰብ ወጥመድ መግባት በጣም ቀላል መሆኑን ያውቃሉ? ጽድቅ በእምነት ነው በሚል ማስተባበያ ኃጢአትዎን ለመሸፈን ሞክረው ያውቃሉ? ይህ በጣም አደገኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ያለ አግባብ እንድንጠቀም በምንፈተንበት ጊዜ ያለ ድነት ተስፋ የት እንሆን ነበር?
የኤሌን ዋይትን “The Righteousness of Christ in the Law,” pp. 236–239; “Come and Seek and Find,” pp. 331–335; “Perfect Obedience Through Christ,” pp. 373, 374, in Selected Messages, book 1; “Things New and Old,” pp. 128, 129, in Christ’s Object Lessonsየሚሉ መጻህፍትን ያንብቡ፡፡
“ህግ የኃጢአትን ዕዳ ማስወገድ ባይችልም ነገር ግን ለኃጢአተኛው ያለበትን ዕዳ በሙሉ ይነግረዋል፣ ክርስቶስ በእርሱ ምህረት ለሚተማመኑ ሁሉ በቂ የሚሆን ይቅርታ አዘጋጅቷል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ንስሐ ለሚገባና ለሚያምን ነፍስ ሁሉ በበቂ ሁኔታ ተሰጥቷል፡፡ በነፍስ ለይ ያለው የኃጢአት የበላይነት ሊወገድ የሚችለው ከአባቱ ጋር እኩል በሆነው በሚዋጀው የክርስቶስ መስዋዕትነት ብቻ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥራና ህይወቱ፣ ራሱን ዝቅ ማድረጉ ፣ ሞቱ እና ለጠፊዎች አማላጅነቱ ህግን የበለጠ ከፍ ያለ እና የተከበረ ያደርገዋል፡፡” —Ellen G. White, Selected Messages, book 1, p. 371.
“የክርስቶስ ባህርይ በአንተ ባህርይ ፋንታ ይተካና በእግዚአብሄር ፊት ምንም ኃጢአት እንዳላደረግህ ተቀባይነትን ታገኛለህ፡፡” —Ellen G. White, Steps to Christ, p. 62.
“ጳውሎስ የጸደቅነው ያለ ህግ ስራ ነው ሲለን እርሱ እየተናገረ ያለው ስለ ጸጋ እና ስለ እምነት ሥራዎች አይደለም፣ እርሱ እነዚህን ሥራዎች የሚሰራ በሥራዎቹ አለመጽደቁን ያምናል፡፡ (እነዚህን የእምነት ሥራዎች እያከናወነ)፣ አማኙ በእምነት መጽደቅን ይፈልጋል፡፡ ሐዋሪያው ‹‹የህግ ሥራዎች›› ሲል አንድ የራሱን የጽድቅ ሥራዎች የሚቆጥር ሰው በሰራቸው ሥራዎቹ እንደሚጸድቅ ማመኑን ለመግለጽ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር መልካም ሥራን ሲሰሩ፣ የሚፈልጉት ጽድቅን ሳይሆን በመልካም ሥራቸው ምክንያት ጽድቅን እንዳገኙ በማሰብ መኩራራት ነው፡፡” Martin Luther, Commentary on Romans, p. 80.