ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት:- ሮሜ 14- 16 ያለውን ያንብቡ፡፡
የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ አንተም በወንድምህ ላይ ስለምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በክርስቶስ ወንበር ፊት እንቆማለን፡፡ ” ( ሮሜ 14፡ 10)
አሁን የፕሮቴስታንት ታሃድሶ የተወለደበት የሮሜ መጽሐፍ ጥናታችን የመጨረሻ ክፍል ነን፡፡ መጽሐፉ ማንኛውም ሌላ መጽሐፍ ሊያደርገው ከሚችለው በላይ ለምን ፕሮቴስታንት እንደሆንንና ለምንስ እንደዚህ ሆነን እንደምንቀጥል በእርግጠኝነት የነገረን መጽሐፍ ነው፡፡ እንደ ፕሮቴስታንትነታችን በተለይም እንደ አድቬንቲስትነታችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የእምነት መመሪያ ላይ ብቻ እንቆማለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የእምነት መሰረት መሆኑን እናምናለን፡፡ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ በኃይል የተገለጸው የድነት በእምነት ትምህርት፣ ከምዕተ-ዓመታት በፊት የመንፈሳዊ አባቶቻችን ከሮም ቤተክርስቲያን ራሳቸውን በለዩበት ጊዜም የመራቸው ይህ እውነት ነበር፡፡
ምናልባትም ሁሉም ነገር አረማዊው ጁሊየስ በጠየቀው ጥያቄ ይጠቃለላል ‹‹ እድን ዘንድ ምን ላድርግ›› (ሐዋ. 16፡30)፡፡ መልሱን ከሮሜ መጽሐፍ ውስጥ እናገኛለን፣
ነገር ግን ይህንን ምላሽ በሉተር ዘመን የነበረችው ቤተክርስቲያን ያልሰጠችው ምላሽ ነበር፡፡ ስለዚህ ታሃድሶው ጀመረ እኛም እዚህ አለን፡፡
በዚህ የመጨረሻ ክፍል ጳውሎስ ምናልባትም እንደ ዋና ነጥብ ባይሆንም በዚህ ደብዳቤ ግን አብረው ለመጻፍ በቂ ምክንያት ያላቸውን ሌሎች ርዕሶችን ይጠቅሳል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ለእኛ የተቀደሱ የእግዚአብሄር ቃላት ናቸው፡፡
ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ የሚደመድመው እንዴት ነው? ምን ጽፎ ነበር? እንደ ጳውሎስ ሀሳብ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን እንደ ፕሮቴስታንት እምነት አባቶች እምነትን እንደምንጋራ ክርስትያኖች በዚያ ለእኛ ምን እውነቶች አሉ?
*ለታህሳስ 21 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
በሮሜ 14፡1-3 ያለው ጥያቄ የሚያተኩረው ለጣኦት የታረደን ሥጋ ስለመብላት ነው? የእየሩሳሌም መማክርት ከአህዛብ ወገን የተመለሱ ክርስትያኖችን ለጣዖት የታረደ ሥጋን እንዳይበሉ አዘዋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ በገበያ ሥፍራ የሚሸጥ ስጋ ለጣዖት የታረደ ነው ወይስ አይደለም የሚል ጥያቄ ነበር፡፡ (1ቆሮ. 10፡25 ን ይመልከቱ)፡፡ አንዳንድ ክርስትያኖች ስለዚህ ጉዳይ ምንም ያልመሰላቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ ጥቂት እንኳ የሚያጠራጥር ነገር ካለበት አትክልትን መብላት መርጠዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ለጤነኛ ህይወት አትክልት ተመጋቢ ስለመሆን የሚናገር አንዳች ነገር የለውም፡፡ ጳውሎስ ንጹህና ንጹህ ባልሆነ ሥጋ መካከል ያለው ልዩነት ስለመወገዱም ያለን ነገር የለም፡፡
የትምህርቱ ትኩረት ይህ አይደለም፡፡ በሮሜ 14፡2 ‹‹ማንኛውንም መብላት ይችላል›› የሚለው ማንኛውንም እንስሳ፣ ንጹህ የሆነ ወይም ንጹህ ያልሆነ መብላት ይቻላል ለማለት ተወስዶ ከሆነ የተሳሰተ ግንዛቤ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በእምነት የደከመውን እንቀበለው ማለት በማህበረሰቡ ዘንድ እና በቤተክርስቲያን ያለውን ተቀባይነት ልናጎድልበት አይገባም የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ ግለሰቡ በዚህ ምክንያት ክርክር ሊገጥመው አይገባውም ፣ ለራሱ አስተሳሰብ መብት ሊሰጠው ይገባል ማለት ነው፡፡
ታዲያ ከሮሜ 14፡1 -3 የምንወስደው ትምህርት ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ በሮሜ 14 ፡ 3 ላይ ‹‹በእምነቱ ደካማ›› የሆነ ሰውን በአሉታዊ ሁኔታ እየተናገረ እንዳልሆነ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ሰው በእምነቱ እንዴት ጠንካራ እንደሚሆን ምክር እየሰጠም አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን በሚመለከት (በእግዚአብሔር ሳይሆን በሰዎች ጻድቅነቱ የተመሰከረለትን ሰውም ‹‹እግዚአብሔር ተቀብሎታል›› ፡፡
አሁን የተመለከትነውን ሀሳብ ሮሜ 14 ፡ 4 የሚያጎላው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በዛሬው ትምህርት ላይ የተሰጠንን መመሪያ በአእምሮአችን እንደያዝን ፣ በሰው የልብ ሀሳብ እንኳ ባይሆን በድርጊቱ ላይ ወደ ፍርድ የምንገባባት ጊዜ የለም? በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ራሳችን አግልለን ምንም ማለትና ማድረግ የለብንም? በኢሳ. 56፡10 ጠባቂዎችን እንደ ‹‹መጮህ እንደማይችሉ ድዳ ውሾች›› ይገልጻቸዋል፡፡ መቼ መናገርና መቼ ጸጥ ማለት እንዳለብን የምናውቀው እንዴት ነው?
ሮሜ 14፡10ን ያንብቡ፡፡ በሌሎች ላይ ስንፈርድ እንዴት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባን ጳውሎስ ምን ምክንያት ይሰጠናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ብዙውን ጊዜ እኛ ራሳችን ለምናደርጋቸው ነገሮች ሌሎች ላይ በጭካኔ እንፈርዳለን፡፡ እኛ ስናደርገው ክፉ ያልመሰለን ሌሎች ሲያደርጉት ግን እንፈርድባቸዋለን፡፡ በግብዝነታችን ‹‹ እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋልና በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ በዓይንህ ግን ያለውን ምሶሶ ስለምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን ከዓይንህ ጉድፍ ለውጣ ፍቀድልኝ እንዴት ትለዋለህ ? እነሆ በዓይንህ ምሶሶ አለ፡፡›› ያለንን እግዚአብሔርን ሳይሆን ራሳችንን እናታልላለን፡፡ ማቴ. 7፡ 1-4 ፡፡
ጳውሎስ ከብሉይ ኪዳን የተጠቀመው ዓረፍተ ነገር በዚህ ስፈራ ጠቀሜታው ምንድ ነው? ሮሜ 14፡ 11 ፡፡
በኢሳ. 45፡23 ላይ የተጠቀሰው ሁሉም በፍርድ ፊት ይቆማል የሚለውን አባባል የሚደግፍ ነው፡፡ ‹‹ ምላስ ሁሉ ›› እና ‹‹ጉልበት ሁሉ›› የሚለው ጥሪውን የእያንዳንዱ ሰው ያደርገዋል፡፡ ይህ የሚሰጠው ትርጓሜ እያንዳንዱ ሰው ላደረገው ድርጊትና ለኖረው ህይወት መልስ ይሰጣል ማለት ነው፡፡ (ሮሜ 14፡ 12)፡፡ ማንም ስለ ሌላው አይመልስም፡፡ በዚህ ስሜት እኛ የወንድማችን ጠባቂ አይደለንም፡፡
ይህን አውድ በአእምሮአችን እንዳስቀመጥን ፣ ጳውሎስ በሮሜ 14፡14 ላይ የሚናገረውን እንዴት እናስተውላለን?
አሁንም የትምህርቱ ዋና ነጥብ ለጣዖት የተሰዋ ሥጋን የሚመለከት ነው፡፡ ንጹህና ንጹህ ያልሆኑ ምግቦችን የመለየት ጉዳይ ሳይሆን ሀሳቡ ግልጽ ነው፡፡ ጳውሎስ እያለ ያለው ለጣዖት የተሰዋን ስጋ በመብላት ምንም ስህተት የለውም፡፡
ለማንኛውም ጣዖት ምንድነው? ምንም አይደለም (1ቆሮ. 8፡4ን ይመልከቱ) ፣
ታዲያ አንድ አረማዊ ለበሬ ምስል ሆነ ለእንቁራሪት ምስል ምግብ ቢያቀርብ የሚገደው ማን ነው?
አንድ ሰው አስተሳሰቡ በጣም ስሜታዊ ቢመስልም ፣ አስተሳሰቡን (ህሊናውን) እንዲቃወም አይደረግም፡፡ ወንድሞች ያላስተዋሉት ‹‹ጠንካራ›› የሚለውን ይህንን እውነት ነበር፡፡ እነርሱ ‹‹ የደካማውን›› ጥንቁቅነት ስላላስተዋሉ በወንድሞቻቸው መንገድ ላይ መሰናከያ ያስቀምጣሉ፡፡
ምናልባትም ለእግዚአብሔር ባለዎት ቅናት በዚህ ስፍራ ጳውሎስ እያስጠነቀቀ ባለው አደጋ ውስጥ ነዎት? አስተሳሰባቸው ምንም ያህል መልካም ቢሆንም የሌሎች ህሊና ላለመሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ለምንድነው?
ሮሜ 14፡15-23 እና 1ቆሮ. 8 ፡12-13 ን አንብበው በታች ባሉ መስመሮች ላይ ጳውሎስ የተናገረውን በአጭር ቃላት ይጻፉ፡፡ ከዚህ ንባብ በሁሉም የህይወታችን አቅጣጫ ልንጠቀመው የምንችለውን ምን ትምህርት እናገኛለን?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በሮሜ 14፡17-20 ጳውሎስ የተለያዩ የክርስትና አመለካከቶችን ትክክለኛ አቅጣጫቸውን ያስቀምጣል፡፡ አመጋገብ አስፈላጊ ቢሆንም ክርስቲያኖች አንዱ ሰው በአትክልት ፋንታ ለጣዖት የተሰዋን ሥጋ ለመብላት ባደረገው ውሳኔ ምክንያት መጣላት የለባቸውም፡፡ በዚህ ፋንታ ማትኮር ያለባቸው በመንፈስ ቅዱስ ባለው ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ ነው፡፡ ይህንን በቤተክርስቲያናችን በአመጋገብ ላይ ለሚነሳው ጥያቄ ልንጠቀመው የምንችለው እንዴት ነው? የጤና መልዕክት በተለይም፣ የአመጋጋብ ትምህርት ሁሉም ሰው ይህንን እንደ በረከት ባይወስደውም ነገር ግን ለእኛ በረከት ነው፣ ስለዚህ እንደዚህ አይነት ልዩነቶችን በግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለብን፡፡
በሮሜ 14፡22 ፣ ጳውሎስ ሰዎችን ለህሊናቸው ስለመተው በሚናገረው ንግግር መካከል አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ይጨምራል፤ ‹‹ ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቆጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብጹእ ነው፡፡›› ጳውሎስ እዚህ እየሰጠ ያለው መስጠንቀቅያ ምንድነው? በአውዱ በጠቅላላ ይናገር የነበረውን ንግግር ሚዛናዊ ሊያደርግ የሚችለው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አንዳንድ ሰዎች እኔ ምንም ብበላ፣ ምንም ብለብስ ፣ በፈለግሁት አይነት ብዝናና ፣ ማንንም አይመለከተውም ሲሉ ሰምተው ያውቃሉ? ለመልካም ይሁን ለክፉ ፣ድርጊታችን ፣ ቃላችንና ተግባራችን በሌሎች ለይ ተጽኖ ያደርጋል፡፡ ይህ እንዴት እንደሆን ማየት ከባድ አይደለም፡፡ አንድ ሰው አንተን ትክክል ያልሆነ ነገር ስትሰራ ቢያይህ፣ ያንን አይነት ነገር በማድረግህ በምሳሌነት ተጽዕኖ ይደርስበታል፡፡ እንደዚህ የማናስብ ከሆነ ራሳችንን እናታልላለን፡፡ ይህንን ሰው እንደዚህ ዓይነት ተግባር እንዲያደርግ አላስገደድሁትም ማለት በዚህ ላይ ተጨማሪ ስህተት ነው፡፡ እንደ ክርስትያን አንዳችን ለሌላችን ተጠያቂዎች ነን፣ ምሳሌነታች አንድን ሰው ወደ ጥፋት የሚያመራ ከሆነ፣ እኛ ጥፋተኞች ነን፡፡
ምሳሌነትዎ ምን ዓይነት ነው? ወጣቶች ወይም አዲስ አማኞች በሁሉም አቅጣጫ እርስዎን ቢከተሉ በምሳሌነትዎ ደስተኛ ነዎት? መልስዎ ስለ እርስዎ ምን ይናገራል?
ጳውሎስ ከእኛ አስተሳሰብ ጋር የማይስማማ አመለካካት ላላቸው ሰዎች ፣በሌሎች ድርጊት በሚጎዱት ሰዎች ላይ መፍረድ እንደሌለብን ሲናገር አንዳንዶች ስለሚጠብቁትና ሌሎች ስለማያከብሩት ቀናት ይጠቅሳል፡፡
ሮሜ 14፡ 4-10ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ቦታ የሚናገረውን የሚናስተውለው እንዴት ነው? ይህ ስለ አራተኛው ትዕዛዝ የሚለው ነገር አለ? ከሌለ ለምን?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ የሚናገረው ስለየትኞቹ ቀናት ነው? በጥንቱ ቤተክርስትያናት ውስጥ መከበር ስላለባቸውና መከበር ስለሌለባቸው ቀናት ክርክር ነበር? በግልጽ አዎን፡፡ የዚህን ዓይነት ክርክር በገላ. 4፡9፣10 ጳውሎስ ለገላቲያ ሰዎች ስለ ‹‹ቀናት ወራት ጊዜና ዓመታት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በሁለተኛ ትምህርት እንደተመለከትነው አንዳንዶች የሙሴን ህግ ስለመጠበቅና ስለ መገረዝ የገላቲያን ቤተክርስትያን ሰዎችን ግፊት ሲያደርጉባቸው ነበር፡፡ ጳውሎስ ተመሳሰይ ሀሳብ የሮሜ ቤተክርስትያንን እንዳይጎዳ ፈርቶ ነበር፡፡ ነገር ግን በሮሜ በተለየ መንገድ ችግር የነበረባቸው የአይሁድ በዓላትን ማክበር አስፈላጊ አይደለም በማለት ግፊት ያደርጉ የነበሩት አይሁድ ራሳቸው ይሆናሉ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ስፍራ እያለ ያለው በዚህ ጉዳይ ላይ ደስ እንዳለችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ፣ ነግር ግን ከእናንተ አስተሳሰብ በተለየ እምነት ያላቸውን አትፍረዱባቸው ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አንዳንድ ክርስትያኖች ከክርክር ነጻ ለመሆን አንድ ወይም ከዚያ የበለጡ የአይሁድ በዓላትን ያከብሩ ነበር፡፡ የጳውሎስ ምክር እንደዚያ ካመኑ በዚያ መልኩ እንዲያከብሩ ነጻ ይሁኑ የሚል ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚከራከሩት የሳምንቱን ሰንበት ወደ ሮሜ 14፡5 ማምጣት ዋስትና የለሽ ነው፡፡
ጳውሎስ ስለ አራተኛው ትዕዛዝ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ቸልተኛ በሆነ መልኩ ይናገራል ተብሎ ይጠበቃል? ሩብ ዓመቱን በሙሉ ሁላችንም እንደተመለከትነው ጳውሎስ ህግን ስለማክበር ብዙ ሀሳብ ሲሰጥ ተመልክተነዋል፤ ስለዚህ ጳውሎስ አንዳንድ ሰዎች ያደርጉት እንደነበር የሰንበትን ትዕዛዝ ለጣኦት የታረደ ሥጋን ብሉ አትብሉ ከሚለው ጋር በአንድ ጎራ እያስቀመጠው አይደለም፡፡ ነገር ግን በተለምዶ እነዚህን ጥቅሶች ፣የሰባተኛው ቀን ሰንበት ትዕዛዝ አስፈላጊነት እንደሌለው ለመናገር ይጠቀሙበታል ፣ እንደዚህ የሚል ነገር ግን የለም፡፡ ትክክለኛ ምሳሌነታቸው ጴጥሮስ ሰዎች በጳውሎስ ጽሑፎች ላይ ምን እያደረጉ እንደሆን በተናገረው ለይ ታይቷል ፤ ‹‹በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻህፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ፡፡ (2ጴጥ. 3፡ 16)፡፡
እርስዎ ስለ ሰንበት ያለዎት ልምምድ እንዴት ነው ? በታሰበው መልኩ በረከት እየሆነ ነው ?እግዚአብሔር በሰንበት በኩል የሚሰጠውን ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ምን ዓይነት ለውጦችን ማድረግ ይጠበቃል?
ሮሜ 15 ፡1-5 ያንብቡ፡፡ በዚህ ንባብ ምን አስፈላጊ የሆነ ክርስቲያናዊ እውነት እናገኛለን ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የክርስቶስ ተከታይ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ በሙላት ይዞ የሚገኘው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ተመሳሳይ ሀሳብን የሚያስተምሩ ሌሎች ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ፣ እርስዎ ራስዎ እነዚህን ደንቦች የሚኖሩት እንዴት ነው?
ጳውሎስ በደብዳቤው መጨረሻ ላይ ምን የተለያዩ ተማጽኖዎችን እያቀረበ ነው? ሮሜ 15፡5፣ 6፣13፣33፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የትዕግስት አምላክ ሲል ፣ ልጆቹ ጸንተው እንዲቆሙ የሚያደርግ አምላክ ማለት ነው፡፡ ‹‹ትዕግስት›› የሚለው ቃል hupomone የአስተሳሰብ ጽናትን ( ጥንካሬ) የሚያሳይ ነው፡፡ የመጽናናት አምላክ ማለት መጽናናትን የሚሰጥ ማለት ነው፡፡ የተስፋ አምለክ ማለት ለሰብአዊ ዘር ተስፋን የሰጠ ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ የሰላም አምላክ ማለት ሰላምን የሚሰጥ ማለት ነው፡፡
ከብዙ የግል ሰላምታዎች በኋላ ጳውሎስ ደብዳቤውን ወደ መጨረሻ የሚያመጣው እንዴት ነው? ሮሜ 16፡ 25-27፡፡
ጳውሎስ ደብዳቤውን የሚጨርሰው ደማቅ በሆነ መልኩ ለእግዚአብሔር ምስጋናን በማቅረብ ነው ፡፡ እግዚአብሔር የሮሜ ክርስትያኖች እና ሁሉም ክርስትያኖች፣ የዳኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆች መሆናቸውን፣ በእምነት የጸደቁ መሆናቸውን እናም አሁን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ መሆናቸውን ሊተማመኑበት የሚያስችል ነው፡፡
ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ በሚጽፍበት ጊዜ በአንድ ቦታ ለተወሰነ ጉዳይ መልስ ለመስጠት በእግዚአብሔር መንፈስ የተመራ ስለመሆኑ እርግጠኞች ነን፡፡ የማናውቀው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር የመጪውን ጊዜ በተመለከተ ለጳውሎስ የገለጠለትን ነገር ነው፡፡
አዎ ጳውሎስ ስለ ‹‹ መሳት ›› ያውቃል (2ተሰ. 2፡3 )፣ የሚያውቀው ምን ያህል እንደሆን ጥቅሱ ምንም አይናገርም፡፡ በአጭሩ ፣ ጳውሎስ የሚጽፋቸው የነበሩ ፣ በተለይም እነዚህ ደብዳቤዎች እና ራሱ በመጨረሻ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሚና በሚመለከት ጥርጥር ይኖረው እንደሆን አናውቅም፡፡ በአንዱ በኩል የተለየ ስሜት አይሰጥም፡፡ ዋና ነገሩ በእነዚህ ጥቅሶች ፕሮቴስታንትነት ተወልዷል፣ ዓለም ሁሉ እንኳን ‹‹አውሬውን በመደነቅ ቢከተለውም›› (ራዕይ 13፡3) ፣ በእነዚህም ጥቅሶች ላይ ለክርስቶስ ታማኝ መሆን የሚፈልጉ ለእምነታቸውንና ለመሰጠታቸው ምክንያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት መሆን የሚችል ነገር አግኝተዋል፡፡
የሚከተሉትን የኤሌን ዋይት መጻህፍት ያጥኑ፡፡ “Unity and Love in the Church,” pp. 477, 478; “Love for the Erring,” pp. 604–606, in Testimonies for the Church, vol. 5; “Helping the Tempted,” p. 166, in The Ministry of Healing; p. 719, in The SDA Bible Commentary, vol. 6.
‹‹የእግዚአብሔር ህዝብ ወደ ወንድም እና እህት ዋይት ጋ ሸክም የሆነባቸውን ነገር ይዘው በመሄድ ምክር ለማግኘት የመሞከራቸውን አደጋ እንዳይ ተደረግሁ፡፡ እንዲሆን የተፈለገው እንደዚህ አይደለም፡፡ እነርሱ በደከሙና ሸክም በከበዳቸው ጊዜ የተጋበዙት አፍቃሪና ርህሩህ ወደሆነው አዳኝ እንዲሄዱና እርሱ ነጻ እንደሚያወጣቸው ነው ፡፡ ብዙዎች፣ይህን ላድርግ? ፣በዚህ አይነት ንግድ ልሳተፍ? ፣ወይም ልብስን በሚመለከት ፣ይህንን ወይም ያንን ዓይነት ልብስ ልልበስ ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፡፡ እኔም የክርስቶስ ተከታይ እስከሆናችሁ ድረስ በምድር ለይ በሰዎች መካከል በነበረ ጊዜ አዳኛችን የኖረውን ህይወት በጥንቃቄና በጸሎት መንፈስ አንብቡ፡፡ እርሱ የኖረውን ህይወት ዓይነት ለመኖር ተለማመዱ ፣ ከጠባቡ መንገድ የመራቅ ችግር አይገጥማችሁም፡፡ ለእናንተ ሙሉ በሙሉ ህሊናችሁ መሆንን እንቃወማለን፡፡ ምን መስራት እንዳለባችሁ አሁን ብንነግራችሁ ፣ በቀጥታ እንዲመራችሁ ወደ ክርስቶስ በመሄድ ፋንታ እንድንመራችሁ ሁልጊዜ እኛን ትጠብቃላችሁ፡፡ ›› —Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 2,
pp. 118, 119.
‹‹እኛ ማድረግ የሚገባንን ሥራ ኃላፊነት በሌሎች ጫንቃ ላይ በመጫን ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግሩን ሌሎችን መጠበቅ የለብንም፡፡ ምክርን ለማግኘት በሰው ልጆች ላይ አንደገፍም፡፡ ሌላውን ሰው ምን መስራት እንዳለበት ለማስተማር ፈቃደኛ እንደሆነ ሁሉ እኛንም ምን መስራት እንዳለብን ሊያስተምረን ፈቃደኛ ነው፡፡ በማንኛውም መስመር እግዚአብሔርን የማያስከብር ምንም ነገር ላለማድረግ የወሰኑ ፣ ነገሮቻቸውን በእግዚአብሔር ፊት በማስቀመጥ ምን ሥራ መስራት እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡›› —The Desire of Ages, p. 668.
በቤተክርስቲያን ታሪክ በዘመናት ግለሰቦች በቋሚነት በራስ መደገፍ የሚያዘነብሉ ነበሩ፡፡ እነርሱ ለመንፈሳዊ ነገር በራስ መደገፍ ሰዎችን ከመጠን በላይ በራስ ለይ ወደ መታመን እንደሚያመራ እና የወንወድሞችን ምክር በመስማት ፋንታ በራሱ ፍርድ ላይ እንዲተማመን ያደርጋል፡፡ —The Acts of the Apostles, pp. 163, 164.