ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት:- ሮሜ 12 እና 13ን ያንብቡ፡፡
የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን ዓለም አትምሰሉ፡፡ ” (ሮሜ 12፡ 2)
ምንም እንኳ ጳውሎስ አይሁድ ህግን በተመለከተ የነበራቸውን ስህተት የሆነ ትርጓሜ እና አጠቃቀም ሊያስተካክል የሚፈልግ ቢሆንም፣ እርሱ ሁሉንም ክርስትያኖች ከፍተኛ ወደሆነው የመታዘዝ ደረጃ እንዲደርሱ ይፈልጋል፡፡ ይህ መታዘዝ የሚመጣው በልብና በአእምሮ ውስጥ የሆነ መለወጥ፣ እንዲሁም ራሱን ለእግዚአብሔር ከሰጠ ሰው ውስጥ በሚሰራ በእግዚአብሔር ኃይል የሚገኝ መለወጥ ነው፡፡
የሮሜ መጽሐፍ ይህ መታዘዝ አንዴውኑ ይሆናል የሚል ትምህርት አያስተምርም፡፡ ክርስትያን አስፈላጊ ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ማወቅ አለበት፡- እርሱ ወይም እርሷ እነዚህን ተፈላጊ መስፈርቶች ለመታዘዝ መወሰን አለባቸው፣ በመጨረሻም ክርስትያኑ ያለ እርሱ መታዘዝ የማይቻለውን የእግዚአብሔርን ኃይል መፈለግ ያስፈልገዋል ፡፡
ይህ ማለት ሥራ የክርስትና እምነት ክፍል ነው ማለቱ ነው፡፡ ጳውሎስ ሥራን ዋጋ እያሳጣ አይደለም፤ በምዕራፍ 13-15 የተለየ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ይህ ደግሞ አስቀድሞ ስለ ጽድቅ በእምነት ያስተማረውን መካድ አይደለም፡፡ በተቃራኒው ግን ሥራ ማለት በእምነት የመኖር መግለጫ ነው፡፡ አንድ ሰው ከክርስቶስ መምጣት በኋላ በተጨመረው መገለጥ ምክንያት በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ህጎች ይልቅ በአዲስ ኪዳን የተሰጡ ህጎች ለመጠበቅ አስቸጋሪ ናቸው ብሎ መከራከር ይችላል፡፡ የአዲስ ኪዳን አማኞች በክርስቶስ አማካይነት ትክክለኛው የስነ-ምግባር ምሳሌ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እርሱ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም ልንከተለው የሚገባንን መንገድ ሊያሳየን አይችልም፡፡ ‹‹ በክርስቶስ የነበረ ( በሄኖክ፣ በዳዊት፣ በዳንኤል፣ በሰለሞን፣ በዲቦራ ወይም በኤልያስ አይደለም) ይህ ሀሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን›› (ፊሊ. 2፡5) ፡፡ ሊደረስበት የተገባው ደረጃ ከዚህ በላይ አይደለም፡፡
*ለታህሳስ 14 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
የሮሜ መጽሐፍ አስተምሮ ነክ ትምህርቱ በምዕራፍ 11 ላይ ያበቃል፡፡ ከምዕራፍ 12-16 ያለው ተግባራዊ የሆነ መመሪያንና የሰዎች የግል ማሳሰቢያን የያዘ ነው፡፡ እነዚህ የማጠቃለያ ምዕራፋት መመሪያ ይያዙ እንጂ፣ የእምነት ህይወት እንዴት እንደምንኖር የሚያሳዩን በመሆናቸው እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡
ልክ እምነታችን ለአምላክ የሚገባንን መታዘዝ ሁሉ እንደሚሸፍን፤ ይሁንና ለጀማሪዎች እምነት የሥራ ምትክ አይደለም፡፡ አስርቱ ትዕዛዛት አሁንም ኃይል አላቸው፡፡ በአዲስ ኪዳን ከበፊት ይልቅ ጎልተው እንዲታዩ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡ እንዲያውም ለክርስትያን ህይወቱን ለመምራት ትዕዛዛቱ ቀላል ይሆናሉ የሚል ፍንጭም አልተሰጠም፡፡ በተቃራኒው ከራስና ከሥጋ ጋር የሚደረግ ውጊያ ከባድ መሆኑ ተነግሮናል፡፡ (1ጴጥ. 4፡1)፡፡ ክርስቲያን መለኮታዊ ኃይልና የድል ዋስትና የተሰጠው ቢሆንም አሁንም በዓለም ላይ የሚኖር በመሆኑ ብዙ ፈተናና ውጊያ ይጠብቀዋል፡፡ መልካም ዜናው፣ ብንወድቅ፣ ብንሰናከል የተጣልን ሳንሆን የሚራራልን ታላቁ ሊቀካህን አለን፡፡ (ዕብ. 7፡25)፡፡
ሮሜ 12፡1ን ያንብቡ፡፡ እዚህ የተሰጠው ምሳሌ ክርስትያኖች እንዴት መኖር እንዳለብን ሊገልጽ የሚችለው እንዴት ነው? ሮሜ 12፡2 ከዚህ ጋር የሚገጥመው እንዴት ነው?
በሮሜ 12፡1 ጳውሎስ ከብሉይ ኪዳን ያጣቅሳል፡፡ በጥንት ዘመን እንስሳት ለእግዚአብሔር እንደሚሰው፣ እንዲሁ አዳድስ ክርስቲያኖችም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መስጠት አለባቸው ፣ ይህም ማለት መሞት ሳይሆን፣ራሳቸውን ህያው መስዋዕት አድርገው ለአገልግሎት መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
በጥንት ዘመን ለመስዋዕት የሚቀርቡ እንስሳት በጥንቃቄ ይፈተሹ ነበር፡፡ እንስሳው ምንም አይነት ጉድለት ቢገኝበት፣ እግዚአብሔር እንስሳው እንከን የሌለበት ሊሆን እንደሚገባው መመሪያ ሰጥቶ ስለነበር ሳይሰዋ ይቀራል፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ሰውነታቸውን “በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው ህያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ ታዘዋል፡፡ ይህን ማድረግ እንዲችሉ ኃይላቸው ሁሉ እጅግ በተጠበቀ ሁኔታ መገኘት አለበት፡፡ ማናችንም ያለ እንከን የሆንን ባንኖርም ዋና ነጥቡ በተቻለ መጠን እንከን የለሽና ነቀፋ የማይገኝበትን ህይወት ልንኖር ይገባናል፡፡ ” በልባችሁ መታደስ ተለወጡ (ሮሜ 12፡2 )፡፡
ሐዋሪያው የክርስቲያንን እድገት በዚህ መንገድ ይገልጸዋል፡፡ እርሱ እየተናገረ ያለው ቀድሞውንም ክርስቲያን ለሆኑት ነው፡፡ የክርስቲያን ህይወት ባለበት ለመቆም አይደለም፣ ነገር ግን ከመልካም ወደ እጅግ በጣም ጥሩ ወደሆነው እንዲያድጉ ነው፡፡ ” Martin Luther, Commentary on Romans, pp. 167, 168.
በክርስቲያን ህይወት ከመልካም ወደ እጅግ በጣም ጥሩ ማደግ ማለት ምን ማለት ነው?
በዚህ ምዕራፍ ስለ እግዚአብሔር ህግ ዘላለማዊነት እና በሮሜ መጽሐፍ ውስጥ የጳውሎስ መልዕክት የእግዚአብሔር ህግ እንዳልተሻረ እና እምነትን ምክንያት በማድረግ ትዕዛዙን መሻር እንደማይቻል ደጋግሞ ማስረዳቱን ተመልክተናል፡፡
ሆኖም ግን ስለ ህግ በተጻፈው ደብዳቤ ላይ ያለውን ዋና መንፈስ የምንረሳበት ጊዜ አለ፡፡ ይህም መንፈስ ፍቅር ለእግዚአብሔር እና ፍቅር ለሰው ናቸው፡፡ አንድ ሰው ፍቅር አለኝ ማለት ይችላል ፣ነገር ግን በየዕለቱ ህይወቱ ውስጥ ማሳየት ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡
ሮሜ 12፡ 3 - 12ን ያንብቡ፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በቆሮንቶስ ምዕራፍ 12 እና 13 ላይ የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎችን ከዘረዘረ ቦኋላ ፍቅርን ከሁሉ ከፍ ያደርጋል፡፡ ፍቅር በግሪኩ (አጋፔ) በጣም ጥሩ የሆነው መግለጫ ነው፡፡ ‹‹ እግዚአብሔር ፍቅር ነው›› (1ዮሐ. 4፡8)፡፡ ስለዚህ ፍቅር የእግዚአብሔር ባህርይ መግለጫ ነው፡፡ መውደድ ማለት ሌሎችን በእግዚአብሔር ቦታ ሆኖ ማየት እና እርሱ እንደሚያገለግላቸው ማገልገል ማለት ነው፡፡
ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ይህ ፍቅር በተግባር ሊገለጽ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በዚህ ውስጥ የሚታይ አንድ አስፈላጊ የሆነው መመሪያ ቢኖር የግል ሰብአዊነታችን ነው፡፡ ‹‹ ማንም ስለራሱ ማሰብ ከሚገባው በላይ እንዳያስብ›› (ሮሜ 12፡3)፣ “በመከባበር አንዱ ለሌላው ክብር የሚሰጥበት ፈቃደኝነት” (ሮሜ 12፡10)፣ ‹‹በራስ ጠቢብ መስሎ ለመገኘት›› ፈቃደኛ መሆን (ሮሜ 12፡ 16)፡፡ ክርስቶስ ስለ ራሱ በተናገራቸው ቃላት ‹‹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ እኔ በልቤ የዋህና ትሁት ነኝ ›› (ማቴ. 11፡ 29)፡፡
ከሁሉም ሰዎች ክርስቲያኖች በጣም ራሳቸውን ያዋረዱ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ እኛ ምን ያህል ረዳተ-ቢስ መሆናችንን ተመልከቱ፡፡ እንዴት የወደቅን መሆናችንን ተመልከቱ፡፡ ለድነታችን ከእኛ ውጭ በሚገኘው ጽድቅ መደገፋችን ብቻ ሳይሆን እኛ ራሳችንን ልንለውጥ ከምንችለው በላይ ራሳችንን ሊለውጥ በሚችል በውስጣችን ባለው መንፈስ ስለመደገፋችን ተመልከቱ፡፡ ልንኮራ የሚያስችለን ምን አለን ? ሊያኮራን የሚችል በውስጣችን ያለ እና የራሳችን የሆነ ነገር ምን አለን? በጭራሽ ምንም የለንም! ከጅምሩ በመነሳት ራስን ዝቅ ማድረግን በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ሳይሆን በሰውም ፊት ጭምር ካሰብን ፣ ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የመከረንን መቀበል ያስፈልገናል፡፡
ሮሜ 12፡ 18ን ያንብቡ፡፡ አሁን ይህን የጳውሎስን ምክር በህይወትዎ እየተገበሩ የሚገኙት እንዴት ነው? በዚህ ስፍራ ቃሉ እንደሚናገረው ለመኖር የባህሪይ ለውጥ ያስፈልግ ይሆን?
ሮሜ 13፡ 1-7ን ያንብቡ፡፡ ከመንግስት ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት ይህ ጥቅስ ምን መሰረታዊ መርህ ይነግረናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የጳውሎስን ቃለት የሚያስደስቱ የሚያደርጋቸው እርሱ ይህን መልዕክት የጻፈበት ዘመን ዓለምን ይገዛ የነበረው ከልክ በላይ ጨካኝ ፣ብልሹ አሰራሮች የሞሉበትና ስለ እውነተኛ አምላክ ምንም እውቀት የሌለው ያንን አምላክ የሚያመልኩትን ለማጥፋት በአጭር ጊዜ በጣም ሰፊ የሆነ ስደት የጀመረ የአረማዊው ሮም ዘመን ነበር፡፡ በእርግጥ ጳውሎስ የተገደለው በዚህ መንግስት ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን በዚህም መንግስት ሥር እንኳ ክርስትያኖች ጥሩ ዜጎች እንዲሆኑ ጳውሎስ ይመክራል፡፡ አዎ ምክንያቱም የመንግስት ሀሳብ ራሱ የመነጨው ከመጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው፡፡ የመንግስት ህግ ዋና ሀሳቡ የተገኘው ወይም ምንጩ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰው ልጆች ህግና ሥርዓት ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ መኖር ይገባቸዋል፡፡ ሀገ- ወጥነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳብ አይደለም፡፡
ይህ ሲባል ግን ሁሉም ዓይነት መንግስታዊ አወቃቀር በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው ማለት ግን አይደለም እንዲሁም የትኛውንም መንግስታዊ አሰራር ይቀበለዋል ማለት አይደለም፡፡ በታሪክም ሆነ አሁን ባለንበት ጊዜ በጣም ጨካኝ መንግስታትን ለማግኘት ማንም ወደ ሩቅ ዘመናት ሁሉ ማየት አያስፈልገውም፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ክርስትያኖች በተቻለ መጠን የአገሪቱን ህግ መታዘዝ አለባቸው፡፡ የመንግስት ህግ የሚፈልገው ነገር እግዚአብሔር ከሚፈልገው ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ክርስትያኖች መንግስትን መደገፍ አለባቸው፡፡ አንድ ሰው አንድ ነገር ከመጀመሩ በፊት ከመንግስት አካለት ጋር ግጭት የሚያስነሳ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ በጸሎትና በጥንቃቄ ማጤን እንዲሁም ሌሎችን ማማከር ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ጊዜ ሁሉም የእግዚአብሔር ታማኝ ተከታዮች፣ በዘመን መጨረሻ የዚህን ዓለም ፖለቲካ ከሚቆጣጣሩ ኃይላት ፊት ለፍርድ መቆማቸውን እናውቃለን፡፡(ራዕ 13 )፡፡ እስከዚያ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት በየትኛውም ሀገር መልካም ዜጎች ለመሆን የምንችለውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፡፡
‹‹በምድር የተሾሙትን ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተመረጡ እንደሆኑ እና በተሰጣቸው የሥልጣን ክልል ልንታዘዝ እንደሚገባን እናስተምራለን፡፡ ነገር ግን የባለሥልጣናት ጥያቄ ከእግዚአብሔር ህግ ጋር ሲጣረስ፣ ሰውን ከመታዘዝ ይልቅ እግዚአብሔርን መታዘዝ ይበልጣል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ከሰው ህጎች ሁሉ የበላይ ነው፡፡
‹‹ባለሥልጣናትን ልንጋፋ፡፡ ቃሎቻችን የምንጽፋቸው ሆኑ የምንናገራቸው ቃላት በጥንቃቄ የተመረጡ ካልሆኑ ራሳችንን ከህግና ሥርዓት ጋር ተቃራኒ በሚሆን ስፍራ እንዳያስቀምጡንና መዝገባችንን እንዳያበላሹ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ መንገዳችንን ጥሩ ባልሆነ መልኩ ሊዘጋብን የሚችል ሥራ ሆነ ንግግር ለእኛ ተገቢ አይደለም ፡፡ ›› —Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 69.
‹‹ እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ ሌላውን የሚወድ ህግን ፈጽሞታል፡፡ (ሮሜ 13፡8)፡፡ ይህንን ጥቅስ የምናስተውለው እንዴት ነው? የምንዋደድ ከሆነ የእግዚአብሔርን ህግ ለመታዘዝ ግዳጅ የለብንም ማለት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ኢየሱስ በተራራው ሥብከት ለይ እንደተናገረው ፣ጳውሎስም ለምንሰራቸው ነገሮች ሁሉ መነሻ ሀሳባችን ሊሆን የሚገባው ፍቅር እንደሆነ በመግለጽ እዚህ ክፍል ላይ ህግን ያጎላዋል፡፡ ምክንያቱም ህግ የእግዚአብሔር ባህሪይ ማሳያ ጽሁፍ በመሆኑ ፣ እግዚአብሔርም ራሱ ፍቅር ነው፣ ስለዚህ የሚወድ ህግን ይፈጽማል፡፡ ሆኖም ጳውሎስ አንዳንድ ክርስትያኖች እንደሚሉት ሰፋ ያለውን የፍቅር መግለጫ ተዘርዝሮ ለተቀመጠው የእግዚአብሔር ህግ መተኪያ እያደረገው አይደለም፡፡ አስርቱ ትዕዛዛት ኃጢአትን የሚያሳዩ በመሆናቸው አሁንም ሥልጣን አላቸው ፡፡ ሆኖም ግን ህግን መታዘዝ የሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ክርስቶስን ወደ መስቀል ከወሰዱት በኋላ ህግን ለመታዘዝ የሮጡትን ያስታውሱ!
ጳውሎስ ህግን መጠበቅ የፍቅር መመሪያ መሆኑን ሲገልጽ የተጠቀመው የትኛውን ትዕዛዝ ነው? ይህንን የተለየ የሚያደርገው ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አስገራሚ በሆነ መልኩ የፍቅር ህግ አዲስ እየተዋወቀ ያለ ህግ አይደለም፡፡ ዘሁ. 19፡ 18ን በመጥቀስ ‹‹ ባልንጄራህን እንደ ራስህ ውደድ፣ ›› ጳውሎስ ሥርዓቱ የብሉይ ኪዳን አስፈላጊ ክፍል እንደሆን ያሳያል፡፡ ደግሞም ጳውሎስ ስብከቱን እንዲደግፍ ብሉይ ኪዳንን ይጠቀማል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነዚህ ጥቅሶች በማየት ጳውሎስ የሚጠቅሳቸው ብቻ ናቸው በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምንጠቀማቸው
በማለት ይከራከራሉ። ይህ ትክክል ከሆነ ክርስትያን እናቱንና አባቱን ሊያከብር አይገባውም ማለት ነው፣ ጣኦትን ማምለክ አለበት እና ከእግዚአብሔር ሌላ አማልክት ሊኖረው ይገባል? በእርግጥ አይደለም!
የዚህን አውድ ይመልከቱ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ሥፍራ እርስ ባርሳችን እንዴት መዋደድ እንዳለብን እየነገረን ነው፡፡ እርሱ እየተናገረ ያለው የግለሰቦችን ግንኙነት በሚመለከት ነው፡፡ ግንኙነቶች ላይ የሚያተኩሩ ትዕዛዛትን በተለየ መልኩ የተናገረው ለዚህ ነው፡፡ የእርሱን ክርክር ሌሎችን ህጎች ዋጋ የሌላቸው ያደርጋል ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ (ሐዋ. 15፡20 ፣ 1ተሰ. 1፡9 ፣ 1ዮሐ. 5፡21ን ይመልከቱ)፡፡ በተጨማሪ የአዲስ ኪዳን ጻሐፊዎች እንደጠቀሱት ፣ ፍቅርን ለሌሎች በማሳየት እኛ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር እናሳያለን፡፡ (ማቴ. 25፡40፤ 1ዮሐ. 4፡ 20፣ 21 )፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ስላለዎት ግንኙነት ያስቡ እና ይህ ከሌሎች ጋር ባለዎት ግንኙነት እንዴት እንደሚንጸባረቅ ያስተውሉ፡፡ ፍቅር በግንኙነት ላይ ምን ያህል ዋጋ አለው? እግዚአብሔር እኛን እንደወደደን ሌሎችን መውደድ ልንለማመድ የምንችለው እንዴት ነው?
‹‹ ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሠዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧል (ሮሜ 13፡11)፡፡
በሩብ ዓመቱ ትምህርት በሙሉ እንደገለጥነው በዚህ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ በተለይም በሮሜ ቤተክርስቲያን ለሚገኙ ኡይሁዳውያን አማኞች ሊገልጽ የፈለገው በአዲስ ኪዳን አውድ የእምነትንና የሥራን ሚና ግልጽ ለማድረግ ነው፡፡ ጉዳዩ ስለ ድነትና ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ቅዱስና ጻዲቅ እንደሚሆን ማሳየት ነው፡፡ አስተሳሳባቸው በሙሉ ህግ ላይ የሆኑትን ለማገዝ ጳውሎስ ህግን በትክክለኛው ሥፍራና አውድ ያስቀምጠዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን አይሁዳዊነት እንኳ በጸጋ ላይ የተመሰረተ ሃይማኖት ቢሆንም፣ ህጋዊነት በመነሳት ብዙ ችግሮችን ፈጥሯል፡፡ እንደ ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ስህተት እንዳናደርግ ምን ያህል መጠንቀቅ አለብን?
ሮሜ 13 ፡11-14 ያለውን ያንብቡ፡፡ በዚህ ቦታ ጳውሎስ የሚናገረው ስለምንድነው? ይህንን ሁኔታ የምንጠባበቀው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ አማኞችን ክርስቶስ ተመልሶ እየመጣ ስለሆነ ምን ያህል ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው የሚናገረው ክፍል በጣም አስደናቂ ነው፡፡ ይህ እውነት ከተጻፈ 2000 ዓመታት ማለፋቸው ምንም ችግር የለውም፡፡ እኛ ሁልጊዜ የክርስቶስን ዳግም ምጻት ቅርብ መሆን እየጠበቅን ልንኖር ይገባናል፡፡ ሁላችንን በተመለከተ፣ የየግል ልምምዳችንን ስንመለከት፣ የዳግም ምጻቱ እኛ ለሞት የቀረብነውን ያህል ቅርባችን ነው፡፡ ዓይናችን በሞት የሚከደነው ከሳምንት በኋላም ሆነ ከ40 ዓመታት እናም የምንተኛው ለአራት ቀን ሆነ 400 ዓመታት ለእኛ ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ ቀጥሎ ልናየው የምንችለው ነገር ቢኖር የክርስቶስ ዳግም ምጻት ነው፡፡ ለማናችንም ሞት በቅርባችን በእንድ ኮርነር ሁልጊዜ የተቀመጠ ሲሆን፣ ጊዜው በእርግጥ አጭር ፣ መዳናችንም ካመንንበት ጊዜ ይልቅ እጅግ የቀረበ ነው፡፡
ምንም እንኳ ጳውሎስ በሮሜ መጽሐፍ ስለ ዳግም ምጻት የማይናገር ቢሆንም በተሰሎንቄና በቆሮንቶስ ደብዳቤዎች ውስጥ በጥልቀት ይገልጻቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ይህ በመጽሐፍ ቅዱሳችን በተለይም በአዲስ ኪዳን ትልቁ ርዕስ ነው፡፡ ያለ እርሱና እርሱ ከሚሰጠው ተስፋ ውጪ እምነታችን ከንቱና ዋጋ የሌለው ይሆናል፡፡ ታዲያ ያለ ዳግም ምጻቱ ‹‹ ጽድቅ በሃይማኖት ›› ያን ሙሉ ፍሬ ከልሰጠ ምን ትርጉም አለው፡፡
በእርግጠኝነት ክርስቶስ የሚቀጥለው ሳምንት እየመጣ መሆኑን ቢያውቁ ፣በህይወትዎ ምን ዓይነት ለውጥ ያደርጋሉ? ለምን ? ይህ ለውጥ እንደሚያስፈልግዎ ካወቁ ታዲያ ለምን አሁን አይለውጡም? ልዩነቱ ምንድነው?
‹‹ በመጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ተገልጧል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች የቅዱሱ ታለቅ አምላክ የአፉ ቃላት ናቸው፡፡ ማንም እነዚህን እውነቶች የህይወቱ ክፍል የሚያደርጋቸው ሁሉ በማንኛውም ሁኔታ አዲስ ፍጥረት ይሆናል፡፡ እርሱ አዲስ የአእምሮ ኃይል አይሰጠውም፣ ነገር ግን በኃጢአትና ባለማወቅ ምክንያት በጨለማ ዳመና የተጋረደው ይወገዳል፡፡ ‹‹ አዲስ ልብን እሰጣችኋለሁ ›› ማለትም ‹‹ አዲስ አስተሳሰብ አሳያችኋለሁ ›› ፡፡ የልብ ለውጥ ሁልጊዜ የሚገለጸው እውነትን በማስተዋል፣ ንጹህ በሆነ ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ ጸሎት በተሞላበት ትኩረት የእግዚአብሔርን ቃል የሚያጠና ንጹህ ማስተዋልንና እውነተኛ ፍርድን እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ወደሚገኘው የእውቀት ከፍታ ጫፍ ላይ ይደርሳል፡፡ ” —Ellen G. White, My Life Today, p. 24.
አምላካችን በቶሎ ይመጣል እኛም ለመገለጡ ተዘጋጅተን ልንጠብቅ ይገባናል፡፡ እርሱን ማየት እና እንደዳኑ ወገን በእርሱ እንኳን ደህና መጣችሁ መባል እንዴት ድንቅ ነው? ለረዥም ጊዜ ጠብቀነዋል ፣ ሆኖም ግን ተስፋችን የደበዘዘ አይደለም፡፡ ንጉሱን በክብሩ ብናየው ለዘላለም የተባረክን እንሆናለን፡፡ ‹‹ ወደ ቤቴ ገባሁ ብዬ የምጮህ ይመስለኛል፡፡ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና በክብር የተዋጁትን ወደ ዘላለም ቤታቸው ሊወስድ የሚመጣበት ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ” —Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 8, p. 253.