መዳን በእምነት ብቻ:ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከህዳር 30– ታህሳስ 6

አስራአንደኛ ትምህርት

December 9–December 15
 

የተመረጡት

 

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት:- ሮሜ 10፣ 11ን ያንብቡ፡፡

 

የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ እንግዲህ እግዚአብሔር ህዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ፡፡ አይደለም እኔ ደግሞ እሥራኤላዊና ከአብረሃም ዘር ከቢኒያም ወገን ነኝ፡፡ ” (ሮሜ 11፡1)

የዚህ ሳምንት ትምህርት ሮሜ 10 እና 11ን የሚሸፍን ሆኖ በተለይም ሮሜ 11 ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ የጳውሎስን አስተሳሰብ በትክክል ለመከታተል ሁለቱንም ምዕራፎች ሙሉ በሙሉ ማንበብ አስፈላጊ ነው፡፡

እነዚህ ሁለቱ ምዕራፋት የውይይት ትኩረት በመሆን የቆዩና የሚቀጥሉ ናቸው፡፡ በሁሉም ውስጥ በግልጽ የሚታየው ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ፍቅርና እርሱ ሁሉም ሰው እንዲድን መፈለጉ ነው ፡፡ ማንም ድነትን እንዳያገኝ የሚደረግበት ሁኔታ የለም፡፡ ሮሜ 10 ‹‹ በአይሁድና በግሪክ መካከል በዚህ ልዩ የለም›› በማለት ይናገራል፡፡ ‹‹ሁሉም ኃጢአትን ሰርተዋል ስለዚህ ለዓለም እንደተሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ ያስፈልጋቸዋል››፡፡ (ሮሜ 10፡12)፡፡ ይህ ጸጋ የመጣው በዜግነት፣ በትውልድ፣ እና በህግ ሥራ አይደለም ነገር ግን በሁሉም ሥፍራ ለሚገኙ ኃጢአተኞች ምትክ በሞተው በክርስቶስ ባለን እምነት ለሁሉም የተሰጠ ነው፡፡ ሚናዎች ሊቀየሩ ይችላሉ ነገር ግን መሰረታዊ የድነት ዕቅድ አይለወጥም፡፡

ጳውሎስ ይህንን መሰረታዊ ሀሳብ በምዕራፍ 11 ይቀጥላል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተነጋገርነው ፣ ጳውሎስ ስለ መመረጥ እና ጥሪ ሲናገር ጉዳዩ የድነት አለመሆኑን ማስተዋል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጉዳዩ እግዚአብሔር ዓለምን ለመድረስ ባወጣው ዕቅድ የሚኖረንን ሚና በተመለከተ ነው፡፡ ድነትን እንዳያገኝ የተደረገ ቡድን የለም፡፡ ይህ በፍጹም የዚህ ጉዳይ ትኩረት አይደለም፡፡ በዚህ ፋንታ ከክርስቶስ ስቅለት በኋላ፣ በተለይ በጳውሎስ አማካይነት ለአህዛብ ወንጌልን ለማድረስ የተደረገ የመጀመሪያ እንቅስቃሴን የሚመለከት ነበር፡፡

*ለታህሳስ 7 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
 

ታህሳስ 1
December 10
 

ክርስቶስና ህግ

 

ሮሜ 10፡1-4 ያንብቡ፡፡ እኛ ዛሬ ‹‹ የራሳችንን ጽድቅ›› የመስራት አደጋ ሊያጋጥመን የሚችለው እንዴት ነው?

ህጋዊነት በብዙ መንገድ ሊመጣ ይችላል፡፡ እነዚያ ራሳቸውን ወደ መልካም ሥራቸው፣ ወደ አመጋገባቸው፣ ጥብቅ የሰንበት አጠባበቃቸው፣ እነርሱ ወደማያደርጓቸው ክፉ ሥራዎች ወይም ስኬትን ወዳገኙባቸው መልካም ሥራዎች የሚያመጡ ሁሉ ወደ ህጋዊነት ወጥመድ እየወደቁ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የህይወታችን እንቅስቃሴ የእግዚአብሔርን ቅድስና ከእኛ ኃጢአተኝነት በተቃራኒ ልናስቀምጠው ይገባል፡፡ ሰዎችን የራሳቸውን ጽድቅ ያም የክርስቶስ ጽድቅ ተጻራሪ የሆነውን እንዳይፈልጉ ከሚያደርጋቸው አስተሳሰቦች ሊጠብቀን የሚችለው ይህ ብቻ ነው፡፡

ሮሜ 10፡4 የአጠቃላዩን የሮሜን መጽሐፍ ዋና ሀሳብ የያዘ ጥቅስ ነው፡፡ በመጀመሪያ አውዱን ማስተዋል ያስፈልገናል፡፡ ብዙ አይሁዶች ‹‹ የራሳቸውን ጽድቅ ወደ መስራት ናቸው፡፡›› (ሮሜ 10፡3) እና ‹‹ ከህግ የሆነውን ጽድቅ መፈለግ›› (ሮሜ 5፡10)፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ መምጣት እውነተኛው ጽድቅ ተገልጧል፡፡ እምነታቸውን በክርስቶስ ለሚያጸኑ ሁሉ ጽድቅ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የጥንቶቹ በዓላትና ሥነ-ሥርዓቶች ሁሉ ያመለክቱት የነበረው እርሱን ነበር።

የህግን ትንታኔ አንድ ሰው አስርቱ ትዕዛዛት ናቸው ቢል እንኳ አስርቱ ትዕዛዛት ተሽረዋል ማለት አይደለም፡፡ አሥርቱ ትዕዛዛት ኃጢአታችንን ፣ ስህተታችንን ፣ የሚጎድልብንን በማሳየት ሁሉም ወደሚገኝበት አዳኝ ወደሆነው ኢየሱስ፣ ወደ ንስሐ እና ወደ ጽድቅ ይመራናል፡፡ በዚህ ሁኔታ ክርስቶስ የህግ ፍጻሜ ነው ስለዚህ ህግ ወደ እርሱና ወደ ጽድቁ ይመራናል፡፡ ‹‹ፍጻሜ›› ለሚለው ቃል የግሪኩ መተኪያ ‹‹teloes›› የሚል ሲሆን ‹‹ ግብ ›› ወይም ‹‹ ዓላማ›› ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ለክርስቶስ የህግ የመጨረሻ ዓላማ ነው በዚህም ህግ ወደ ኢየሱስ ይመራናል፡፡

ይህ ጥቅስ የሚያስተምረው ስለ አስርቱ ትዕዛዛት ወይስ ስለ አራተኛው ትዕዛዝ (ይህ ተረት ምን ማለት እንደሆን) እነዚህን ዋጋ የላቸውም ማለት ከብዙው የአዲስ ኪዳንና የጳውሎስ ትምህርቶች በተቃራኒ መሄድ ይሆናል፡፡

ራስዎን ጥሩ ነኝ ብለው ተኩራርተው ያውቃሉ? በተለይም ራስዎን ከሌሎች ጋር በማነጻጻር? ምናልባትም የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ ታዲያ ምን ? ራስዎን ከክርስቶስ ጋር ያነጻጽሩና ምን ያህል መልካም እንደሆኑ ይመልከቱ፡፡
 

ታህሳስ 2
December 11
 

የጸጋ ምርጫ

 

ሮሜ 11፡፡1-7 ያንብቡ፡፡ ይህ ጥቅስ የትኛውን የተለመደ ትምህርት ነው የሚቃወመው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ለጥያቄው መልስ በሰጠበት የመጀመሪያ ክፍል ‹‹እግዚአብሔር ህዝቡን ጣላቸውን?›› እግዚአብሔር ህዝቡን አለመጣሉን ለማሳየት ጳውሎስ ወደ ቅሬታው ያመለክታል፡፡ ድነት ለሚቀበሉት ሁሉ አይሁድ ሆነ አህዛብ ክፍት ነው፡፡ የጥንቱ ወደ ክርስትና የተመለሱ ሰዎች ሁሉ አይሁድመሆናቸው ሊታወስ ይገባል፡፡ ለምሳሌ በጴንጠቆስጤ ቀን የተመለሱ ሁሉ አይሁዶች ነበሩ፡፡ አህዛብ ለመዳን ከአይሁዶች

ጋር እኩል የክርስቶስ ጸጋ እንደሚያስፈልጋቸው እና ወንጌል ወደ እነርሱ መድረስ እንደሚገባው ለጴጥሮስ ለማስረዳት የተለየ ራዕይ አስፈልጎ ነበር፡፡ (ሐዋ. 10 ን ከ15፡ 7-9) ጋር ያወዳድሩ፡፡

ሮሜ 11፡7-10 ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ የሚለው ክርስቶስን ያልተቀበሉ እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አውቆ መዳንን እንዳይቀበሉ ዘግቶባቸዋል ነው? በዚህ ሀሳብ ምን ስህተት አለ?

በሮሜ 11፡8-10 ጳውሎስ ከብሉይ ኪዳን አይሁድ ሥልጣን ያለው አድርገው የሚጠቀሙበትን ጥቅስ ይጠቅሳል፡፡ ጳውሎስ የሚያመላክተው ጥቅስ እግዚአብሔር በእሥራኤል ለይ እንዳያዩና እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስ አድርጎባቸዋል የሚለውን ነው፡፡ እግዚአብሔር የመዳንን ብርሃን እንዳያዩ የሰዎችን አእምሮ ያጨልማል? በፍጹም! ይህ ንባብ ሊስተዋል የሚገባው በሮሜ 9 አገላለጽ መሰረት ነው፡፡ ጳውሎስ የሚናገረው የግለሰቦችን ድነት በተመለከተ አይደለም ምክንያቱም እግዚአብሔር ማንንም ከድነት አያግድም፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው በዚህም ሥፍራ ያለው ጉዳይ እግዚአብሔር ለሰዎች ስለሚሰጠው የሥራ ኃላፊነት ነው፡፡

እግዚአብሔር አንድን ማህበረሰብ ድነትን እንዳያገኙ አድርጓል በሚለው ሀሳብ ውስጥ ያለው ስህተት ምንድነው? ይህ ከአጠቃላይ ክርስቶስ ሰውን ሁሉ ለማዳን ሞተ ከሚለው የወንጌል ትምህርት ጋር የሚቃረነው ለምንድነው? በአይሁዳውያን በኩል ይህ የስህተት ትምህርት ክፉ ወደሆነ ነገር የመራው እንዴት ነው?
 

ታህሳስ 3
December 12
 

የተፈጥሮ ግንድ

 

ሮሜ 11፡ 11- 15 ያለውን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ንባብ ያስቀመጠው ምን ዓይነት ትልቅ ተስፋ ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በዚህ ንባብ ሁለት ጎን ለጎን የሚሄዱ ሀሳቦችን እናገኛለን፤ (1) የእነርሱ (የእስራኤላውያን) ሙላት (ሮሜ 11፡12) እና (2) የእነርሱ ተቀባይነት ማግኘት (ሮሜ 11፡15)፡፡ ጳውሎስ የእስራኤላውያን መጣል ለጊዜው ብቻ እንደሆነና መጨረሻውም ሙላትና ተቀባይነት እንደሚሆን ራዕይ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ ለተነሳው ሁለተኛ ጥያቄ የጳውሎስ ምላሽ ይህ ነው፣ ‹‹እግዚአብሔር ህዝቡን ጥሏልን ?›› እርሱ እንደሚለው የተጣለ የሚመስለው ለጊዜው ነው፡፡

ሮሜ 11፡ 16-24ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ሥፍራ ጳውሎስ ምን እያለን ነው?

ጳውሎስ አማኞቹን የእስራኤልን ቅሬታዎች ጥቂቶቹ ቅርንጫፎች እንደተቆረጡበት እውነተኛ የወይራ ዛፍ ጋር ‹‹እግዚአብሔር ህዝቡን አለመጣሉን ለማስረዳት›› በሮሜ 11፡2 ያመሳስላል)፡፡ ሥሩና ግንዱ ግን አሁንም እዚያው ናቸው፡፡ አማኝ አህዛብ የተተከሉት እዚህ ዛፍ ላይ ነው፡፡ ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን የሚያገኙት አማኞችን ከሚወክለው ግንድና ሥር ነው፡፡

እግዚአብሔርን እምቢ ላሉ የደረሰው እጣ አማኝ ለሆኑ አህዛብም ያው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ አንዴ የዳነ ሁሌም የዳነ ›› ነው የሚል ትምህርት አያስተምርም፡፡ ድነት እንዲሁ በነጻ እንደተሰጠ እንዲሁ ይከለከላል፡፡ ቢሆንም በወደቅን ቁጥር ከድነት የጠፋን ወይም ፍጹም ካልሆንን አልዳንንም የሚመስለንን አስተሳሰብን ማስወገድ እንደሚገባን እንዲሁም በተቃራኒው አቅጣጫ ደግሞ አንዴ የእግዚአብሔር ጸጋ ከሸፈነን የተሰጠንን ድነት ከእኛ እንዲወሰድ የሚያደርግ እኛ የምናደርገው ምንም ነገር ፣ምንም ዓይነት ምርጫ የለም ብለን ከማሰብ መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ በመጨረሻ ‹‹በእርሱ መልካምነት የሚቀጥሉ›› ብቻ ይድናሉ (ሮሜ 11፡22)፡፡

ማንም አማኝ በራሱ መልካምነት ሊኩራራ ወይም ማንም አማኝ ከባልንጄራው የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሰብ የለበትም፡፡ የእኛ ድነት የከፈልንበት አይደለም ፤ በነጻ የተሰጠን ሥጦታ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ሚዛን ፣ በመስቀሉ ፊት ሁላችንም እኩል ነን፡፡ ኃጢአተኞች መለኮታዊ ጻጋንና ቅድስናን ስንፈልግ ሊሰጠን የሚችለው በጸጋው ብቻ ነው፡፡ ከራሳችን የሆነ ሊያኩራራን የሚችል ምንም ነገር የለንም ፣ ብቸኛ ኩራታችን የሚሆነው ክርስቶስ የሰውን ሥጋ በመልበስ ወደዚህ ምድር በመምጣት የእኛን መከራ በመውሰድ ፣ ለኃጢአታችን በመሞት ፣እንዴት መኖር እንዳለብን ለእኛ ምሳሌ በመተው እና ያን ህይወት ለመኖር የሚያስችለንን ኃይል ሊሰጠን ተስፋ በሰጠን እርሱ ለእኛ ባደረገው ነገር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ሙሉ በሙሉ በእርሱ የምንታመን ነን ፣ምክንያቱም ያለጌታ ተስፋ የለንም፡፡
 

ታህሳስ 4
December 13
 

እስራኤል ሁሉ ይድናል

 

ሮሜ 11፡25- 27 ያለውን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዚህ ሥፍራ እየተነበየ ያለው ምን ዓይነት ታላቅ ክስተትን ነው?

ክርስቲያኖች ለክፍለ ዘመናት ሮሜ 11፡25-27 ባለው ሲወያዩና ሲከራከሩ ኖረዋል፡፡ ነገር ግን ጥቂት ነጥቦች ግልጽ ናቸው፡፡ ለጀማሪዎች ዋናው ነጥብ እግዚአአብሔር አይሁዶችን መድረሱ ነው፡፡ ጳውሎስ የሚናገረው ‹‹ እግዚአብሔር ህዝቡን ጥሏልን›› ለሚለው በምዕራፉ መጀመሪያ ለሚገኝ ጥያቄ ምላሽ ሲሆን መልሱ አይደለም ነው፣ ገለጻው ደግሞ (1) እውርነት፣ በግሪክ (porosis) ‹‹ የልብ ጥንካሬ›› (2) ይህም ጊዜያዊ ነው ምክንያቱም የሚቆየው አህዛብ እስኪመጡ ብቻ ነው፡፡

የአህዛብ ሙላት ማለት ምን ማለት ነው? ብዙዎች ይህንን ሀረግ ዓለም ሁሉ ሊሰማ የተገባው የወንጌል ተልዕኮ መግለጫ እንደሆነ ይመለከታሉ፡፡ ወንጌል ለዓለም ሁሉ በተሰበከ ጊዜ የአህዛብ ሙለት ሆኗል፡፡ በክርስቶስ የተገለጸው የእስራኤል እምነት አለም ዓቀፋዊ ሆኗል፡፡ ወንጌል ለዓለም ሁሉ ተሰብኳል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጻት ቅርብ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙአይሁዶች ወደ ክርስቶስ መምጣት ይጀምራሉ፡፡

ሌላኛው አስቸጋሪ ትርጉም ‹‹ ሁሉም እስራኤላዊ ይድናል›› የሚለው ነው፡፡ (ሮሜ 11፡26)፡፡ ይህ በምንም መንገድ ሁሉም አይሁዳዊ በመለኮት ትዕዛዝ በመጨረሻ ድነትን ያገኛል በሚል ሊተረጎም አይገባም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በየትኛውም ሥፍራ ጅምላ ወይም የሰውን ዘር በሙሉ ሆነ አንድን የህዝብ ክፍል ሁሉን በአንድ ላይ የሚያጠቃልል ነገር አያስተምርም፡፡ ጳውሎስ ‹‹ጥቂቶችን ሊያድን ›› ተስፋ እያደረገ ነው (ሮሜ 11፡14)፡፡ አንዳንዶች መሲሁን ተቀብለዋል፤ አንዳንዶች ደግሞ ሌላው ህዝብ እንደሚያደርገው ሁሉ አልተቀበሉትም፡፡

ኤሌን ጂ. ዋይት ሮሜ 11 ላይ ሀሳብ ስትሰጥ እንዲህ ትላለች ‹‹ ወንጌል ለመጨረሻ ጊዜ ሲታወጅ ብዙ አይሁዶች በእምነት ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው ይቀበላሉ፡፡” —The Acts of the Apostles, p. 381.

‹‹ በዓለም ሊሰራ የሚገባው ታላቅ ስራ አለ፤ እግዚአብሔር አህዛብ እንደሚሰበሰቡ እና እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ አይሁዶችም ጭምር ይሰበሰባሉ፤ ከአይሁዳውያን መካከል ብዙዎች ይለወጣሉ ፤ በእነርሱ አማካይነትም የክርስቶስ ወንጌል ብርሃን እንደ ሻማ ይበራል፡፡ ከእነርሱ መካከል ብዙዎች ወደ ብርሃን ይመጣሉ እናም የእግዚአብሔር ህግ የማይሻር መሆኑን በሚያስደንቅ ኃይል ይመሰክራሉ፡፡ —Evangelism, p. 578.

የአይሁዳውያንን የእምነት መሰረት ለመፈተሽ ጥቂት ጊዜ ውሰድ፡፡ በአይሁዳውያን ሃይማኖት ላይ የሚደረግ ልዩ የሆነ ጥናት የክርስትናን እምነት በትክክል እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?

ታህሳስ 5
December 14

የኃጢአተኞች ድነት

 

ጳውሎስ ለራሱ ህዝብ ያለው ፍቅር በሮሜ 11፡25- 27 በግልጽ ተቀምጧል፡፡ የአገሩ ህዝቦች እርሱንና የወንጌልን እውነት ሲቃወሙ ምንኛ ከባድ ነገር ነው፡፡ነገር ግን በዚህ ሁሉ መካከል ብዙዎች ኢየሱስ ክርስቶስ መሲህ መሆኑን ይቀበላሉ፡፡

ሮሜ 11፡28-36 ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ እግዚአብሔር ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለሰው ዘር ሁሉ ያለውን ፍቅር የሚገልጸው እንዴት ነው? አስደናቂና አስገራሚ የሆነውን የጸጋውን ኃይል የሚገልጠው እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ምንም እንኳ በሮሜ 11፡28-36 ባለው ክፍል በአይሁድ እና በአህዛብ መካከል ንጽጽር የተደረገ ቢሆንም፣ አንድ ነጥብ ግልጽ ነው፣ ይኧውም የእግዚአብሔር ፍቅር ምህረትና ጸጋ በኃጢአተኞች ላይ መፍሰሱ ነው፡፡ ከዓለም ፍጥረት ከጥንትም ጀምሮ የእግዚአብሔር ዓላማ ሰውን ማዳንና ለድነቱም ሌሎችን ህዝቦችና መንግስታት መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙ ነው፡፡

በጥንቃቄና በጻሎት መንፈስ ሮሜ 11፡31ን ያንብቡ፡፡ ከዚህ ጥቅስ ስለ አይሁድ ብቻ ሳይሆን ለምናገኛቸው ህዝቦች ሁሉ ስለምንሰጠው ምስክርነት ምን መልካም የሆነ ነጥብ እናገኛለን?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በምዕተ- አመታት መካከል የክርስቲያን ቤተክርስትያን አይሁዶችን መሲሁን በሚመለከቱ ጉዳች ላይ በጥሩ አመለካከት ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ ከክርስቶስ በኋላ ባለፉት ምዕተ-ዓመታት ታላቁ ውድቀት የነበረው እና ሥር የሰደደው የክርስትና አረማዊነት፣ የእሁድን ሰንበትነት ደግፎ የሰባተኛውን ቀን ሰንበት መቃወምን ጨምሮ ወደ ክርስቶስ የተሳቡ አይሁዶች ላይ ሁኔታዎች እንዳይቀሉ አድርጓል፡፡

ሁሉም ክርስትያኖች የተሰጣቸውን ምህረት ማስታወስ ለሌሎች ምህረት የማድረግን አስፈላጊነት በእጅጉ ያስተምራል፡፡ይህን የማናደርግ ከሆነ ክርስቲያን ልንሆን አንችልም፡፡

ምናልባትም ምህረት ሊደረግለት የማይገባው እርስዎ ምህረት ለማሳየት የሚፈልጉት ሰው አለ? ምንም እንኳ እንደዚህ ማድረግ ከባድ ቢሆንም አሁን ምህረትን ለማድረግ ለምን አይሞክሩም? ክርስቶስ ለእኛ ያደረገው እንደዚህ አይደለም?
 

ታህሳስ 6
December 15
 

ለተጨማሪ ጥናት፡-

 

የሚከተሉ የኤሌን ዋይት መጻህፍትን ያንብቡ፡፡ “Beforethe Sanhedrin,” pp. 77–79; “From Persecutor to Disci ple,” pp. 112–114; “Written From Rome,” pp. 474, 475, in The Acts of the Apostles; “Reaching Catholics,” pp. 573–577, in Evangelism; “What to Preach and Not to Preach,” pp. 155, 156, in Selected Messages, book 1.

እስራኤል እንደ ህዝብ የወደቁ ቢሆንም መዳን የሚገባቸው ቅሬታዎች ተርፈዋል፡፡ በአዳኙ በዳግም ምጻቱ ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስን መልእክት በደስታ በመቀበል ስለ መሲሁ የተጻፉትን ትንቢቶች ያነበቡ ወንዶችና ሴቶች ይኖራሉ፡፡ የጥንቷ ቤተ ከርስቲያን የተቋቋመችው በእነዚህ የናዝሬቱ ኢየሱስን እንዲመጣ በናፍቆት ሲጠብቁት በነበሩ አይሁዶች ነበር፡፡” —Ellen G. White,The Acts of the Apostles, pp. 376, 377.

‹‹ ከአይሁዶች መካካል አንዳንዶች እንደ ታርሴሱ ሳውል በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት ኃያላን ነበሩ፣ እነዚህ የእግዚአብሔርን ህግ ጽኑነት በአስደናቂ ኃይል አውጀዋል፡፡ አገልጋዮቹ ለረዥም ጊዜ ተቀባይነት ያጡና የተናቁ ቢሆንም የእርሱ ማዳን ግን ይገለጻል፡፡ ››.” —Page 381.

‹‹በመጨረሻው የወንጌል አዋጅ ጊዜ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለሚቃወሙ የተለየ ሥራ በሚሰራበት ጊዜ እግዚአብሔር አገልጋዮቹ በየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚገኙ አይሁዶች የተለየ ትኩረት እንድሰጡ ይፈልጋል፡፡ የያህዌን ዘላለማዊ ዓላማ ለመግለጽ የአዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች አንድ ላይ ተቀላቅለው መገኘታቸው ለአይሁዳውያን የአዲስ ፍጥረት የንጋት ብርሃንና የነፍሳቸው ትንሳኤ ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን መጻህፍት ገጾች ሃይማኖታዊ ሥርዓት ውስጥ የተገለጸውን ክርስቶስን እና አዲስ ኪዳን እንዴት ብሉይ ኪዳንን በግልጽ እንደሚያብራራው ሲመለከቱ፣ የተኛው ማንነታቸው ይነቃና እነርሱም የሱስ የዓለም አዳኝ መሆኑን ይቀበላሉ፡፡ ብዙዎች በእምነት ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው ይቀበሉታል፡፡›› Page 381.
 

የመወያያ ጥያቄዎች:-፡

 

  1. በመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ህግ በተለይም ሰንበት የተለየ ትኩረት በሚሰጠው ጊዜ አድቬንቲስቶች በመጨረሻው ዘመን አንዳንድ ጉዳዮች ላይ መግለጫ መስጠት እንደሚገባቸው ሁሉ አይሁዶችም ትዕዛዛትን በሚመለከት ፍንክች የማይሉ መሆናቸው አስፈላጊ ነበር ብሎ ማሰብ ትክክል አይሆንም?

  2. አይሁዶችን በመድረስ ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ይልቅ አድቬንቲስቶች የተሳካላቸው የሆኑት ለምንድነው? እርስዎ በግልዎ ወይም እንደ ቤተክርስትያን በአቅራቢያዎ ያሉትን አይሁዶች ለመድረስ ምን ማድረግ ይችላሉ?

  3. ከጥንቶቹ እሥራኤሎች ምን እንማራለን? ዛሬ እነርሱ ያደርጉ የነበሩትን ተመሳሳይ ነገር ማድረግ የምንተወው እንዴት ነው?