መዳን በእምነት ብቻ:ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከህዳር 23-29

አስረኛ ትምህርት

December 2–December 8
 

የተስፋው ልጆች

 

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት:- ሮሜ 9ኝን ያንብቡ፡

 

የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል፡፡ ” (ሮሜ 9፡18)

‹‹ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደተጻፈ ነው . . . ለሙሴ እንዳልኩ ምህረት ለማደርገው ምሕረትን . . . ለምራራለትም እራራለሁ›› (ሮሜ 9፡13፣15)

ጳ ውሎስ በዚህ ምን እያለ ነው? የሰው ነጻ የሆነው የምርጫ ነጻነትስ የት ነው? እግዚአብሔርን ለመምረጥ ወይም እምቢ ለማለት ነጻ አይደለንም ? ወይስ እነዚህ ጥቅሶች ሰዎች የራሳቸው ምርጫ ምንም ሥፍራ ሳይሰጠው አንዳንዶች ለመዳን ሌሎች ደግሞ ለጥፋት እንደተመረጡ ነው እያስተማሩን ያለው?

እንደተለመደው መልሱ የሚገኘው ጳውሎስ የሚለውን ነገር ሰፋ ባለ ሁኔታ በማየት ይሆናል ፡፡ ጳውሎስ እየተከተለው ያለው እግዚአብሔር የራሱን ምርጦች የመምረጥ ነጻነት ያለው መሆኑን ለማሳየት እየሞከረ ነው፡፡ በአጠቃለይ ለዓለም ወንጌልን የማዳረስ ሥራ ኃላፊነት የሚወስደው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ የራሱ ተወካዮች የሚሆኑትን ለምን አይመርጥም? እግዚአብሔር ማንንም ከመዳን ዕድሉ የማያጎድል እስከሆነ ድረስ እርሱ ይህንን ማድረጉ ከምርጫ ነጻነት ጋር የሚቃረን አይደለም፡፡ በተጨማሪም ክርስቶስ ለሁሉም የሰው ልጆች ከመሞቱ እውነት ጋር እንዲሁም እርሱ ሁሉም እንዲድኑ ካለው ፍላጎት ጋር የሚቃረን አይደለም፡፡

ሮሜ 9 የሚናገረው በዚያ ስማቸው ስለተጠቀሱ ሰዎች ድነት ሳይሆን፣ ሊሰሩ ስለተጠሩበት የተለየ ተግባር በመሆኑ ይህ ምዕራፍ ምንም ችግር አይፈጥርም፡፡

*ለህዳር 30 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
 

ለህዳር 24
December 3
 

የጳውሎስ ሸክም

 

‹‹ እናንተም የካህናት መንግስት የተቀደሰም ህዝብ ትሆኑኛላችሁ፡፡ ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው›› (ዘጸ. 19፡6)፡፡

እግዚአብሔር ወደ አረማዊነት፣ ጨለማ እና ምንዝር እየሄደ ለነበረው ዓለም ወጌልን የሚያደርስ ህዝብ ፈለገ፡፡ እርሱም እሥራኤላውያንን መርጦ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ እቅዱም እነርሱን ምሳሌ የሚሆኑ ህዝቦች ማድረግና ዓለምን ወደ እውነተኛው አምላክ መሳብ ነበር፡፡ የራሱን ባህሪይ በእሥራኤል በኩል በመግለጥ ዓለምን ወደ ራሱ መሳብ ዓላማው ነበር፡፡ በመስዋዕቱ አገልግሎት ትምህርት፣ ክርስቶስ በህዝቦቹ ፊት ከፍ እንዲልና እርሱን የሚያዩ ሁሉ እንዲድኑ ማድረግ ነበር፡፡ የእስራኤላውያን ቁጥር እንደጨመረና በረከታቸውም እንዳደገ፣ መንግስታቸው ዓለምን እስኪያቅፍ ድረስ ድንበራቸውን ማስፋት ነበር፡፡

ሮሜ 9፡ 1-12 ያለውን ያንብቡ፡፡ በሰዎች ውድቀት መካከል እንኳ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት ጳውሎስ ምን እየተናገረ ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ጳውሎስ እያቀረበ ያለው ክርክር እግዚአብሔር ለእሥራኤላውያን የሰጠው ተስፋ ሙሉ በሙሉ የወደቀ አለመሆኑን ነው፡፡ አሁንም እግዚአብሔር አብሮ ሊሰራ የሚፈልጋቸው ቅሬታዎች አሉ፡፡ ጳውሎስ ቅሬታዎች የሚለውን ሀሳብ አስፈላጊነት ለማሳየት ወደ እስራኤላውን ታሪክ በጥልቀት ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ መራጭ አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡ (1) እግዚአብሔር የአብረሃምን ሥር በሙሉ ሳይሆን የይስሐቅን ዘር ብቻ መረጠ፡፡ (2) እንደገናም የይስሐቅን ዘር በሙሉ ሳይሆን የያዕቆብን ልጆች ብቻ መረጠ፡፡

በተጨማሪ ማየት የሚያስፈልገን ዘር ወይም ውርስ ለድነት ዋስትና ሊሆን እንደማይችል ነው፡፡ ትክክለኛ ደም ፣ ቤተሰሰብ ፣ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኖም እንኳ የመጥፋት ዕድል አለ፡፡ ‹‹የተስፋውን ልጆች›› የሚያሳየው በፍቅር የሚሰራ እምነት ብቻ ነው፡፡

በሮሜ 9፡6 ያለውን ጥቅስ ይመልከቱ፡፡ ‹‹ እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እሥራኤል አይደሉምና፡፡›› እኛ እንደ አድቬንቲስት የጥንቱ እስራኤለውያን በዘመናቸው ይጫወቱ የነበሩትን ሚና እንደሚጫወት ህዝብ ከዚህ ምን አስፈላጊ መልዕክት እናገኛለን?  

ህዳር 25
December 4
 

የተመረጡ

 

‹‹ ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደተጻፈ፣ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለ፡፡ (ሮሜ 9፡ 12፣ 13)፡፡

በሳምንቱ መግቢያ ላይ እንደተገለጸው አንድ ሰው ሮሜ ምዕራፍ 9ን፣ ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ግለሰብ መዳን አለመሆኑን ለይቶ እስኪያውቅ ድረስ በትክክል ሊረዳ አይችልም፡፡ በዚህ ሥፍራ የሚናገረው እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን ለተለየ ኃላፊነት እየጠራ መሆኑን ነው፡፡ እግዚአብሔር ያዕቆብን በዓለም ላይ ወንጌልን ለማሰራጨት ለሚጠቀምበት ህዝበ- ነገድ ግንድ እንዲሆን ፈለገ፡፡ በዚህ ንባብ ኤሳው ለመዳን አይችልም የሚል አንደምታ የለውም፡፡ እግዚአብሔር ሰው ሁሉ ለመዳን እስከፈለገ ድረስ እንዲድን የእርሱ ፈቃድ ነው፡፡

ሮሜ 9፡14 ፣ 15 ን ያንብቡ፡፡ እያነበብን በነበረው አውድ መሰረት እነዚህን ቃላት እንዴት እንረዳቸዋለን?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

አሁንም ጳውሎስ እየተናገረ ያለው ስለ ግል ድነት አይደለም ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ምህረቱን ለሰው ሁሉ አስፍቷል ‹‹ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ›› (1ጢሞ. 2፡4 )፡፡ ‹‹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጧል›› (ቲቶ 2፡11)፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ህዝቦችን ሚና እንድጫወቱ መምረጥ ይችላል፣ እናም እነርሱ ኃላፊነቱን እምቢ ማለት ይችላሉ፣ ሆኖም የእግዚአብሔርን ምርጫ ሊከለክሉ አይችሉም፡፡ ኤሳው ምንም ያህል ቢፈልግም የመሲሁም ሆነ የተመረጠው ህዝብ የዘር ግንድ አባት ሊሆን አልቻለም፡፡

በመጨረሻም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ አሻሚ የሆነ ምርጫ የሚባል የለም፣ ኤሳውን ከድነት ዕቅድ የሚያስወጣ አንዳችም መለኮታዊ ትዕዛዝ የለም፡፡ በክርስቶስ በኩል የተሰጡት የጸጋው ስጦታዎች ለሁሉም ናቸው፡፡ ‹‹ ሁላችንም ለጥፋት ሳይሆን ለመዳን መምረጥ እንችላለን፡፡ (ኤፌ. 1፡4፣5፤ 2ጴጥ. 1፡10 )፡፡ በክርስቶስ ከተሰጠን የዘላለም ህይወት ተስፋ ሊያስቀረን የሚችለው የእግዚአብሔር ሳይሆን የእኛ ምርጫ ነው፡፡ ኢየሱስ የሞተው ለሁሉም የሰው ልጆች ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነፍስ ለዘላለም ህይወት የሚመረጥበትን ፣ የተቀደሰን ከኃጥአተኛ (justified sinner) ወደ መታዘዝ የሚመራ በክርስቶስ የሆነ እምነትን የሚለማመድበትን ሁኔታዎች በቃሉ ውስጥ አስቀምጧል፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት አንድም ሰው በምድር ሳይፈጠር አንተ ለዘላለም ህይወት በክርስቶስ ተመርጠሃል፡፡ ይህ ሁሉም በክርስቶስ ለአንተ የተሰጠ ጥሪና ምርጫ ናቸው፡፡

እንዴት ያለ ዕድልና ተስፋ ነው! ከዚህ ታላቅ ተስፋ ጋር ሲነጻጻሩ ሁሉም ነገሮች ደብዛዛ ሆነው የሚታዩት ለምንድነው? ሥጋን ኃጢአትን እንዲያደርግ በመፍቀድ ይህንን በክርስቶስ ቃል የተገባልንን ተስፋ ማጣት ከአሳዛኝ ነገሮች ሁሉ የሚበልጠው ለምንድነው?
 

ህዳር 26
December 5
 

ምስጢሮች

 

‹‹ሀሳቤ እንደ ሀሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለችምና ይላል እግዚአብሔር ፣ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል እንዲሁ ሀሳቤ ከሀሳባችሁ ከፍ ይላል፡፡›› (ኢሳ. 55፡8 ፣9)፡፡

ሮሜ 9፡ 17- 24ን ያንብቡ፡፡ ከዚህ በፊት ባነበብነው መሰረት በዚህ ያለውን የጳውሎስን ነጥብ እንዴት እንረዳለን?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

እግዚአብሔር ከግብጽ ወደ ከነዓን በተደረገው ጉዞ ላይ ባደረጋቸው ነገሮች ለሰው ልጆች መዳን ይሰራ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር በወረደው መቅሰፍት እና ህዝቡን ነጻ በማውጣቱ ለግብጻውያንና ለሌሎች ህዝቦች የእሥራኤል አምላክ እውነተኛ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ነበር፡፡ ይህ ድርጊት ታቅዶ የነበረው የሀገሩ ህዝቦች አማልክቶቻቸውን አስወግደው ወደ እውነተኛ አምላክ እንዲመጡና እርሱን እንዲያመልኩ ጥሪ ለማስተላለፍ ነበር፡፡

ፈርኦን ልቡን በማደንደን እግዚአብሔርን እምቢ ለማለት ምርጫ አድርጎ የነበር ቢሆንም እግዚአብሔር ከድነት ውስጥ ዕድሉን እየቆረጠው አልነበረም፡፡ ፈርኦን የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመልቀቅ እምቢ ማለቱ እርሱ ለግል ህይወቱ ድነት የቀረበለትን ጥሪ እምቢ ማለቱ አይደለም፡፡ ክርስቶስ ለሙሴና ለአሮን እንደሞተ እንዲሁ ለፈርኦንና ለቀሩት የእስራኤል ህዝቦች ሞቷል፡፡

በዚህ ሁሉ ዋናው አንገብጋቢ ነጥብ እንደወደቁ ሰብአዊ ፍጡሮች ዓለምን፣ እውነታን እግዚአብሔርንና አሰራሩን ለማስተዋል አስተሳሰባችን ጠባብ መሆኑን ማሳየት ነው፡፡ በዙሪያችን ያለው ዓለም ስንቃኘው በሙሉ በታላላቅ ምስጢሮች የተሞላ ሆኖ ሳለ እኛ የእግዚአብሔርን አሰራር በሙላት ልናስተውለው እንችላለን ብለን ልናስብ የምንችለው እንዴት ነው ? ዶክተሮች እንኳ ቀዶ ጥገና ከማድረጋቸው በፊት እጃቸውን መታጠብ እንዳለባቸው የተረዱት ከዛሬ 171 ዓመት በፊት ነበር! ይህ በነበረን አለማወቅ እንዴት ርቀን እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ ምናልባትም ዘመን ሲያልፍ ከብዙ ዓመታት በኋላ ከሚደረስባቸው አዲስ ግኝቶች የተነሳ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ምን ያህል ድንቁርና እንደሆነ እንረዳለን፡፡

በእርግጥ የእግዚአብሔርን መንገድ ሁልጊዜ አንረዳውም፣ ነገር ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ሊገልጽልን መጣ፡፡ (ዮሐ. 14፡9)፡፡ ታዲያ ለምንድነው ምስጢር በሞላበት ህይወትና ባልተጠበቁ ነገሮች በተከበበ ዓለም ውስጥ እየኖርን የእግዚአብሔርን ባህሪይ በገለጸው ክርስቶስ እና በፍቅሩ መተማመን በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?
 

ህዳር 27
December 6
 

የአሚ፡ ‹‹ ህዝቤ››

 

በሮሜ 9፡25 ጰውሎስ ሆሴ 9፡2፣ 23ን ሲጠቅስ በሮሜ 9፡26 ደግሞ ሆሴ 1፡ 10ን ይጠቅሳል፡፡ ታሪኩ እስራኤል አምላኩን ትቶ ወደ ሌሎች አማልክት መሄዱን ለማሳየትና እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ላለው ግንኙነት ምሳሌ በሚሆን መልኩ እግዚአብሔር ሆሴዕን ‹‹ ጋለሞታ ሚስቱን እንዲወስድ ›› መመሪያ መስጠቱ ነው (ሆሴ 1፡2)፡፡ በዚህ ጋብቻ የተወለዱ ልጆች የተሰጣቸው ስም እግዚአብሔር ህዝቡን እንደተዋቸውና እንደቀጣቸው የሚያመለክቱ ስሞች ናቸው፤ ሶስተኛው ልጅ ስሙ ሎአሚ ተባለ (ሆሴ 1፡9) ግልጽ ትርጉሙም ፣ ‹‹ ህዝቤ አይደለም››።

ሆኖም በዚህ ሁሉ መካከል ሆሴዕ እግዚአብሔር ህዝቡን ከቀጣ በኋላ ቀን እንደሚመጣ ፣ የውሸት አማልክቶቻቸውን እንደሚያስወግድና ድንበሮቻቸውን በማስፋት ከእነርሱ ጋር ኪዳን እንደሚያደርግ ይተነብያል፡፡ (ሆሴ 2፡11-19)፡፡ በዚህ ነጥብ ‹‹ ህዝብ ያልሆኑት›› ‹‹ ህዝብ ይሆናሉ››፡፡

በጳውሎስ ዘመን አሚ ወይም ህዝብ የተባሉት አይሁዶች ብቻ ሳይሆኑ እኛም አህዛብም ነን (ሮሜ 9፡24)፡፡ ይህ ከመሰረቱም ለአለም ሁሉ የታሰበው ምንኛ ግልጽና ኃይለኛ የሆነ የወንጌል አቀራረብ ነው፡፡ ከራዕይ 14፡6 ላይ ‹‹ በምድር ለሚኖሩ ለህዝብም ለነገድም ለቋንቋም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ›› በሚለው መሰረት እኛ አድቬንትስቶች ጥሪ ተሰጥቶናል፡፡ ዛሬም እንደ ጳውሎስ ዘመን እና እንደ ጥንቱ እስራኤላውያን ዘመን፣ መልካሙ ዜና ለዓለም ሁሉ ሊሰራጭ ይገባል፡፡

ሮሜ 9፡25-29 ያለውን አንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዘመኑ እየሆነ የነበረውን ለመግለጥ ብሉይ ኪዳንን ምን ያህል እየተጠቀመ እንደሆን ያስተውሉ፡፡ በዚህ ስፍራ ለመግለጥ የፈለገው ሀሳብ ምንድነው? በዚህ ለአንባቢዎች የተሰጠ ተስፋ ምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የጳውሎስ ዘመዶች የወንጌልን ጥሪ አለመቀበላቸው ‹‹ ብዙ ኃዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ›› (ሮሜ 9፡2)፡፡ ነገር ግን ቢያንስ ቅሬታ ነበር፡፡ የሰው ተስፋ የሚቀር ቢሆንም የእግዚአብሔር ግን አይቀርም፡፡ በመጨረሻ ሊኖረን የሚችል ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ተስፋዎች ይፈጸማሉ ሳይፈጽሙ ቀርተው ያውቃሉ? ተስፋውንም የእኛ አድርገን ከጠበቅነው ለእኛም በህይወታችን ይፈጸማል፡፡

ሰዎች ለእርስዎ ተስፋ ሰጥተው ሳይፈጽሙ ቀርተው ያውቃሉ? እርስዎስ ለሰዎች የገቡትን ቃል ሳይፈጽሙ ቀርተው ያውቃሉ? ከዚህ ምን ትምህርት ይማራሉ? በእርግጠኝነት ማንን ማመን እንደሚገባዎ ይህ ምን ያስተምራል?

ህዳር 28
December 7

መሰናከያ

 

‹‹ እንግዲህ ምን እንላለን ? ያልተከተሉት አህዛብ ጽድቅን አገኙ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፡፡ እሥራኤል ግን የጽድቅ ህግ እየተከተሉ ወደ ህግ አልደረሱም፡፡ ይህስ ስለ ምንድነው ? በስራ እንጂ በእምነት ስላልተከተሉት ነው›› (ሮሜ 9፡ 30- 32)፡፡ የዚህ ጥቅስ መልዕክት ምንድነው? ከዚያ የበለጠ ከብዙ አመት በፊት እና ለተለየ ቦታ የተጻፈን መልዕክት ለእኛ ዘመንና ለራሳችን ልንጠቀመው የምንችለው እንዴት ነው? እኛ ባለንበት ሁኔታ እሥራኤላውያን ያደረጉትን ዓይነት ተመሳሳይ ስህተት እንዳናደርግ የሚንከላከለው እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በስህተት ሊስተዋሉ በማይችሉ ቃላት ጳውሎስ ዘመዶቹ እያስኬዱ ያሉት ነገር ግን አጥጋቢ ውጤት ያላገኙበትን እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር እንደሳቱ ይገልጽላቸዋል፡፡

በሚያስደንቅ ሁኔታ እግዚአብሔር የተቀበላቸው አህዛብ ይህንን ተቀባይነት ለማግኘት ምንም ሲጥሩ አይታዩም፡፡ የወንጌል መልዕክት በመጣላቸው ጊዜ እነርሱ የራሳቸውን ፍላጎትና ግብ ይዘው የሚጓዙ ነበሩ፡፡ ዋጋውን በማስተዋል ተቀበሉት፡፡ እግዚአብሄር ክርስቶስን ስለተቀበሉ ጻድቃን ብሎ ጠራቸው፡፡ ይህ የእምነት አሰራር ነበር፡፡

የእስራኤላውያን ችግር እነርሱ በመሰናከያው ድንጋይ ተሰናከሉ፡፡ (ሮሜ 9 ፡ 33ን) ያንብቡ፡፡ ሐዋ 2፡41ን ተመልከቱ፡፡ ሁሉም ሳይሆኑ ጥቂት ሰዎች እግዚአብሔር የላከውን የናዝሬቱን ኢየሱስ መሲህነት አልተቀበሉም ነበር፡፡ እርሱ እነርሱ ይጠብቁ የነበሩትን የመሲህ መስፈርት አላሟላም ነበር፣ ስለዚህም በመጣ ጊዜ ፊታቸውን አዞሩበት፡፡

ይህ ምዕራፍ ከማለቁ በፊት ጳውሎስ ሌላ የብሉይ ኪዳን ጥቅስ ይጠቀማል፡ ‹‹ እነሆ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የመሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱ የሚያምን አይሰናከልም፡፡›› (ሮሜ 9፡33)

በዚህ ንባብ እንደገና እውነተኛ አስፈላጊ እንደሆን ያሳያል። (1ጴጥ. ግን የማያፍርበት? አዎ ክርስቶስ ግን ለሚያውቁትና ለሚወዱትእምነት በድነት ዕቅድ ውስጥ ምን ያህል 2፡6–8 ይዩ፡፡ የመሰናከያ ዓለት በእርሱ ያመነ ለብዙዎች የመሰናከያ ድንጋይ ነው፣ ነገር ግን ሌላ ዓይነት ድንጋይ ነው፣ ‹‹የመዳኔ ዓለት›› (መዝ. 89፡26) ፡፡

ኢየሱስ የመሰናከያ ዓለት ወይም የእንቅፋት ድንጋይ ሆኖ ያውቁታል ወይ? ከሆነ እንዴት? ወደዚህ ሁኔታ ያመጣህዎት እየሰራህ የነበሩ ሥራ ነው? ከዚያ እንዴት ወጡ ከኢየሱስ ጋር ባለዎት ዝምድና እርስ በእርስ በሚጻረሩ መንገዶች እንዳይራመዱ ምን ትምህርት አገኙ?
 

ህዳር 29
December 8
 

ለተጨማሪ ጥናት፡-

 

የኤሌን ዋይትን “Later English Reformers,” pp. 261, 262, in The Great Controversy; “Faith and Works,” pp. 530, 531, in The SDA Encyclopedia; Ellen G. White Comments, pp. 1099, 1100, in The SDA Bible Commentary, vol. 1. የሚሉ መጻህፍትን ያንብቡ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ የሚገኝ በግልና በህዝብ ደረጃ ሰዎች ለመዳን የሚመረጡበት ምርጫ አለ፡፡ ብዙዎች በመጨረሻ ሰማያዊ በረከትን ለመውረስ የተመረጡ መሆናቸውን ያስባሉ፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጸው ምርጫ ይህ አይደለም፡፡ ሰው የራሱን መዳን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መፈጸም አለበት፡፡ እርሱ የጦር ዕቃውን እንዲለብስ ፣ የእምነትን መልካም ገድል እንዲጋደል ተመርጧል፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ሊደርስበት በሚችለው ርቀት ያስቀመጣቸውን ነገሮች ሁሉ በመጠቀም ፣ ሰይጣን ጌም ለመጫወት እየሞከረ ሳለ ቅዱስ ያልሆነውን ምኞት ሁሉ እንዲያስወግድ ተጠርቷል፡፡ እርሱ በጻሎት እንዲነቃ፣ ቃሉን እንዲመረምር እና ወደ ፈተና ከመግባት እንዲቆጠብ ተጠርቷል፡፡ ቀጣይነት ያለው እምነት እንዲኖረው ተጠርቷል፡፡ እርሱ ከእግዚአብሔር አፍ ለሚወጣ ለእያንዳንዱ ቃል እንዲታዘዝ ሰሚ ብቻ ሳይሆን አድራጊ ሆኖ እንዲገኝ ተጠርቷል፡፡ ” —Ellen G. White, Testimonies to Ministers and Gospel Workers, pp. 453, 454.

ማንኛውም ውስን አእምሮ የእግዚአብሔርን ሊለካ የማይችለውን ባህሪይ ሊያስተውለው አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን በፍለጋ ልናገኘው አንችልም፡፡ በጣም ጠንካራና በእውቀት የበለጸጉ አእምሮዎችም ሆኑ በጣም ዝቅተኛ ምንም ዕውቀት አልባ የሆኑ ሰዎችም ቢሆኑ ያ ቅዱስ የሆነው አካል ድብቅና ሚስጥር እንደሆነ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ምንም ‹‹ ዳመናትና ጨለማ በዙሪያው ያለ ቢሆንም ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሰረት ናቸው፡፡ ›› (መዝ. 97፡2) እርሱ ከእኛ ጋር እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ወሰን የለሽ ምህረቱና ኃይሉ በአንድነት መሆናቸውን ማስተዋል ነው፡፡ የእርሱን ብዙውን ዓላማዎች ማስተዋል እንችላለን፣ ከዚህ የበለጠ ሁሉን የሚችለውን እጅና ፣በፍቅር የተሞላውን ልብ ማመን ይኖርብናል፡፡” Ellen G. White, Education, p. 169.
 

የመወያያ ጥያቄዎች:-፡

 

  1. የተወሰኑ ክርስትያኖች ገና ከመወለዳችን በፊት እግዚአብሔር አንዳንዶቻችንን ለህይወት ሌሎቻችንን ደግሞ ለጥፋት መርጦናል ይላሉ፡፡ እርስዎ ምናልባት እግዚአብሔር ለጥፋት ከመረጣቸው ወገን አንዱ ከሆኑ ምርጫዎ ምንም ይሁን ምንም ቀድሞ ወደተወሰነልዎ ጥፋት ወይም ወደ ገሃነም እሳት ይሄዳሉ፣ አንዳንዶች በዚህ ምድር ሊያድን የማይችለውን ግንኙነት፣ ከክርስቶስ ጋር ቢያደርጉም ቀድሞ በተወሰነላቸው መሰረት እስከ ዘላለም እሳት ብቻ ይቆያሉ፡፡ በዚህ አስተሳሰብ ምን ችግር አለ? ለዚህ ሀሳብ ካለን ማስተዋል ጋር ይህ አስተሳሰብ ተጻራሪ ነው፡፡

  2. የሰባተኛውን ቀን አድቬንቲስት ጥሪን የጥንት እስራኤላውያን ከተሰጣቸው ሚና ጋር ጎን ለጎን ሲያስተያዩ ምን ይመስላል? ልዩነቶቹና አንድነቶቹ ምንድናቸው? በየትኛው መንገድ ነው እኛ የተሻለ የምንሰራው? ወይስ የከፋ እያደረግን ነው?