መዳን በእምነት ብቻ: ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከመስከረም 20-26

አንደኛ ትምህርት

Sept 30 - Oct 06


ጳውሎስ በሮሜ



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት:- ሮሜ. 15:20–27, የሐዋ. ስራ 28:17–31, ፊልጵ. 1:12, ሮሜ. 1:7, ኤፌ. 1, ሮሜ 15:14ን ያንብቡ፡፡


የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ - “እምነታችሁ በአለም ሁሉ ስለተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በእየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ፡፡” (ሮሜ 1:8).

የሮሜ መጽሐፍ ተማሪ ለሆነ ሰው የመጽሐፉን ታሪካዊ አመጣጥ ማስተዋል እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለማስተዋል ስንፈልግ የታሪኩን አውድ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ በስፍራው የተጻፉትን ነገሮች በሙሉ ልናስተውላቸው ይገባል፡፡ ጰውሎስ በተወሰነ ጊዜና ቦታ ለሚገኙ ክርስትያኖች በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የጻፈ መሆኑን ማወቃችን ለጥናታችን በእጅጉ ይረዳናል፡፡ ስለዚህ በጊዜ ቀመር ወደ ኋላ እንሂድ፡፡ እስቲ ራሳችንን ወደ አንደኛ ምዕተ ዓመት ሮም ወስደን የዚያ ዘመን ክፍለ ማህበር ምዕመናን እና የመጀመሪያ ምእተ- ዓመት የቤተክርስትያን አባላት በመሆን፣በሮም ለነበሩ ምዕመናን መንፈስ ቅዱስ በጳውሎስ አማካይነት የሰጠውን መልዕክት እንስማ፡፡

ሆኖም ግን ምንም ያህል ስፍራውን እንዲመስሉ የተደረጉ ቢሆንም፣ ሰው የሚድነው እንዴት ነው? የሚለውን አስተምህሮ በተመለከተ የተሠጠው መግለጫ ሁሉን አቀፍ ነው፡፡ በእርግጥ ጰውሎስ እየጻፈ የነበረው የተወሰነ ቡድንንና አንድ ጉዳይን በአእምሮው በመያዝ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደሚታወቀው ቃላቶቹ ከብዙ ምእተ ዐመታት በኋላ ፍጹም ልዩ በሆነ የታሪክ ዓውድ ለነበረው ማርቲን ሉተር ጰውሎስ ለእሱ እንደጻፈው ሆነው ነበር፡፡ ልክ እንደዚያው ቃሎቹ ለእኛም ገጣሚ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ *ለመስከረም 27 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ፡፡

መስከረም 21
Oct-1

የሐዋርያው ጳውሎስ ደብዳቤ


ሮሜ 16:1, 2፤ የሚያመለክተው ጳውሎስ የሮሜን መጽሐፍ የጻፈው ምናልባትም ቆሮንቶስ አጠገብ በምትገኘው በግሪክ ከተማ በክንክራኦስ ሊሆን ይችላል፡፡ጳውሎስ ትልቋን የቆሮንቶስ ከተማ ነዋሪ የሆነችውን ፌቨንን መጥቀሱ ለሮሜ የተጻፈውን ደብዳቤ ተወዳጅ የሆነ ቅድመ ታሪክ ያለው እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የአዲስ ኪዳኑ ሐዋሪያ መነሻ የሆነችው ከተማ ከተጠቀሰበት ዓላማ አንዱ ታሪኩ የተጻፈበትን ትክክለኛ ጊዜ ለመመርመር ስለሚጠቅም ነው፡፡ ጳውሎስ ብዙ ጉዞ ያደረግ ስለነበር በተወሰነ ጊዜ የነበረበትን ስፍራ ማወቅ ስለ ዘመኑ ፍንጭ ይሰጠናል፡፡

ጳውሎስ በቆሮንቶስ ቤተክርሰትያንን ያቋቋመው ከ49-52 ዓ.ም በሁለተኛው የወንጌል ተልዕኮ ጊዜ ነበር፡፡ ሐዋ. 18:1–18):: ከ53-58 በነበረው ሶስተኛው ጉዞ (በጉዞው መጨረሻ አካባቢ) ግሪክን ለሁለተኛ ጊዜ በመጎብኘት በእየሩሳሌም ለሚገኙ ቅዱሳን ምዕመናን ስጦታን ተቀብሏል፡፡ (ሐዋ. 20:2, 3) (ሮሜ 15:25, 26). ስለዚህ ለሮሜ የተጻፈ መልእክት በ58 ዓ.ም በመጀመሪያዎቹ ወራት ሊሆን ይችላል፡፡

ጳውሎስ በሶስተኛው የመልዕክት ጉዞው የትኞቹን አስፈላጊ ቤተክርስትያናት ነበር የጎበኘው? ሐዋ. 18:23. ጰውሎስ የገላትያን ቤተክርስትያናት በመጎብኘት እርሱ ባልነበረበት ጊዜ ከሐሰተኛ መምህራን የውሸት ትምህርት የተነሳ የቤተክርስትያን አባላትን ሙሴ ወዳስተማረው የግርዛትና ሌሎችም ትምህርቶች ዘወር እንዲሉ እንዳሳመኗቸው አወቀ፡፡ ጳውሎስ የሮሜን ደብዳቤ የጻፈው ተቃዋሚዎቹ እርሱ ወደ ሮም ከመድረሱ በፊት ከደረሱ በቆሮንቶስ የሆነው አይነት የተዛባ ትምህርት ያመጣው ስቃይ እንዳይከሰት በመፍራት ነበር፡፡ ለገላትያ ሰዎቸ የተጻፈው መልዕከትም በጳውሎስ ሶስተኛው የወንጌል ጉዞ ወቅት በቆሮንቶስ እንደሆነ ይታመናል፡፡

“ጰውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልዕክት የወንጌልን ታላላቅ አስተምህሮዎች አቅርቧል፡፡ እርሱም መልእክቱን የጀመረው የአይሁድንና የአህዛብን ቤተክርስትያናት ጥንት የአይሁድ ብቻ ተደርጎ ስለሚገመተው ተስፋ ጥያቄ በማንሳት አሁን ግን ይህ ተስፋ ለአህዛቦችም የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ነበር፡፡” —Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 373.

አስቀድመን እንደተናገርነው ማንኛውንም የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ስናጠና ለምን እንደተጻፈ ማወቅ አስፈላጊ ነው፣ ይህም ማለት ለምን ዓይነት ሁኔታ እንደተጻፈ መረዳት ያስፈልገናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የሮሜን መልእክት ለማስተዋል ጳውሎስ የአህዛብንና የአይሁድን ቤተክርስትያናት የሚከራከራቸው ጥያቄዎች የትኞቹ እንደሆኑ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ የሚቀጥለው ሳምንት ትምህርት ይህንን የሚያብራራ ይሆናል፡፡

ዛሬ የእርስዎን ቤተክርስትያን ሰዎች የሚያከራክሩ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? አብዛኞቹ አስፈሪ ነገሮች ከውስጥ ናቸው ወይስ ከዉጭ? እርሰዎ በዚህ ክርክር ያለዎት ሚና ምንድን ነው? በጥያቄዎች፣ በአቋምዎ እና በባህርይዎ እንዲሁም በሚያጋጥምዎ ማንኛውም ነገር ያለ ጥያቄ የሚሆኑበት ጊዜ ምን ያህል ነው? እንዲህ ዓይነቱ ራስን መመርመር በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው?

መስከረም 22
Oct-2

ሮምን ለመጎብኘት ጳውሎስ የነበረው ፍላጎት


ከግንኙነት መንገዶች ሁሉ የተሻለው ፊት ለፊት መነጋገር ነው፡፡ ስልክ ልንደውል፣ ኢሜይል ልንጽፍ፣ በጽሑፍ መልዕክት ልናሰተላልፍ፣ እንዲሁም በእስካይፕ ልንነጋጋር እንችላለን፤ ሆኖም ግን በአካል እንደ መገናኘት የሚሆን ግን የለም፡፡ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክት ፊትለፊት ሊያያቸው መፈለጉን የጻፈው ለዚህ ነበረ፡፡ እየመጣ እንደሆነና ለምን እንደሚመጣ እንዲያውቁ ፈለገ፡፡

ሮሜ 15:20–27ን ያንብቡ፡፡ ከዚያ በፊት ሮምን ላለመጎብኘቱ ጳውሎስ የሰጠው ምክንያት ምንድነው? አሁን ለመምጣት እንዲወስን ያደረገው ምክንያት ምን ይሆን? እርሱ በሰጠው ምክንያት መሰረት የወንጌልን ተልዕኮ ማዕከላዊነት የገለጸው እንዴት ነበር? በዚህ ስፍራ ከተጻፉት የጳውሎስ ቃላት ስለ ወንጌል ተልዕኮና ምስክርነት ምን እንማራለን? ጳውሎስ በሮሜ 15፡27 ስለ አይሁድና አህዛብ የሚያነሳው በጣም አስፈላጊና ደስ የሚያሰኝ ነጥብ ምንድነው?




----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------


ለአህዛብ የወንጌል መልዕክተኛ የሆነው ታላቁ ጳውሎስ አስቀድሞ ወንጌል በደረሰባቸው ስፍራዎች የሚገኘውን የወንጌል ስራ ለሌሎች በመተው ሳያቋርጥ ያደርግ የነበረው ወደ አዳዲስ ስፈራዎች ወንጌል እንዲደርስ ማድረግ ነበር፡፡ ክርስትና ገና ልጅ ሳለ ሰራተኞችም ጥቂት በነበሩበት ጊዜ ለወንጌል መልእክት መዋል የነበረበትን ዋጋ ያለው ጉልበት ወንጌል በደረሰባቸው አካባቢዎች ብቻ መጠቀም ለጳውሎስ ብክነት ነበር፡፡ “እንዲሁ በሌላው ሰው መሰረት ላይ እንዳልሰራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ ነገር ግን ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ይሰማሉ ያልሰሙም ያስተውላሉ ተብሎ እንደተጻፈ ነው፡፡” (ሮሜ. 15:20, 21)::

የጳውሎስ ዓላማ በሮም ተደላድሎ መቀመጥ አልነበረም፡፡ ስፔንን በወንጌል መድረስ ዓላማው ነበር፡፡ ለዚህም ስራ የሮምን ክርስትያኖች ድጋፍ ማግኘት ይፈልግ ነበር፡፡ በአዳዲስ ስፍራዎች ወንጌልን ስለ ማሰራጨት ባለን ጥያቄ ጳውሎስ አስቀድመው ከተመሰረቱት ቤተክርስትያናት ድጋፍ ከመጠየቁ ምን ጥሩ የሆነ መመሪያ እናገኛለን?




----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------


በድጋሚ ሮሜ 15:20-27ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ ለአገልግሎት ምን ያህል ፍላጎት እንዳለው ያስተውሉ፡፡ ተግባርዎንና እርስዎን የሚያነቃቃው ምንድነው? ለአገልግሎት ያለዎት? የልብ ዝግጅት እንዴት ነው?

መስከረም 23
Oct-3

ጳውሎስ በሮም


“ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ተፈቀደለት” (ሐዋ. 28:16, በመጨረሻ ጳውሎስ ወደ ሮሜ እንዴት እንደገባ ይህ ጥቅስ ምን ይነግረናል?




----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------


እንደ እስረኛ እንኳ ቢሆን ጳውሎስ በመጨረሻ ወደ ሮም ገባ፡፡ በመልካም ዓላማ ለይ የተመሰረቱ ዕቅዶቻችን እንዳቀድናቸውና ተስፋ እንዳደረግነው ሳይሳኩ የሚቀሩት ምን ያህል ጊዜ ነው? ጳውሎስ በሶስተኛው የወንጌል ጉዞ መጨረሻ ላይ ከእስያ ክርስትያኖች የሰበሰበውን የድሆች ምጽዋት ይዞ ወደ እየሩሳሌም ደረሰ፡፡ ነገር ግን ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ፡፡ ተይዞ በሰንሰለት ታሰረ፡፡ በቂሳሪያ ለሁለት ዓመት እስረኛ ከሆነ በኋላ ለቄሳር ይግባኝ አለ፡፡ መጀመሪያ ደብዳቤ በጻፈላቸው ጊዜ በነበረው ዓይነት ስሜት ባይሆንም ከተያዘ ከሶስት አመት በኋላ ወደ ሮሜ ደረሰ፡፡ ሐዋ. 28፡ 17-31 ጳውሎስ በሮሜ ስለነበረው ጊዜ ምን ይነግረናል? ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን?

“ዳኞችን ወደ ክርስትና እንዲሳቡ ያደረገው የጳውሎስ ስብከት ሳይሆን እስራቱ ነበር፡፡ እርሱ እስረኛ በመሆን ብዙዎችን በኃጢአት ቀንበር ስር ያሉትን ነጻ ሊያወጣቸው ችሏል፡፡ ይህ ብቻ አልነበረም፡፡ ‘በጌታም ካሉ ወንድሞች የሚበዙት ስለ እስራቴ ታምነው የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገሩ ያለ ፍርሃት ከፊት ይልቅ ይደፍራሉ፡፡ ፊል. 1፡14’ ” —Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 464. ያልተጠበቁ አጋጣሚዎች በስተመጨረሻው ለመልካም ሲሆኑ በህይወትዎ ያዩት ምን ያህል ጊዜ ነው? ፊል. 1፡ 12ን ይመልከቱ፡፡ ከነዚህ ልምምዶች የተነሳ መልካም በማይመስሉ ነገሮች እንኳ ቢሆን በእግዚአብሔር ለይ እምነትዎ እንዲጨምር የረዳዎት እንዴት ነው?

መስከረም 24
Oct-4

“በሮሜ ያሉ ቅዱሳን”


“በሮሜ ያሉ ቅዱሳን” ለሮሜ ቤተክርስቲያን የጳውሎስ ልመና እንደሚከተለው ነበር፡፡ “በእግዚአብሄር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ ከእግዚአብሄር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችን ይሁን ” (ሮሜ 1:7):: ከእነዚህ ቃላት ምን ዓይነት የእውነት መመሪያ ማግኘት እንችላለን?




----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------


በእግዚአብሄር የተወደዳችሁ፡፡ እግዚአብሄር ዓለምን ሁሉ መውደዱ እውነት ቢሆንም እርሱን በመምረጥ ለፍቅሩ ምላሽ የሰጡትን በተለየ መንገድ ይወዳቸዋል፡፡ ይህን በሰው አመለካከት ስናየው እኛን የሚወዱንን በተለየ መንገድ እንወዳቸዋለን፣ ከእነዚህ ሰዎች ጋር እኩል የሆነ የፍቅር ልውውጥ እናደርጋለን፡፡ ፍቅር ምላሽ ይፈልጋል፡፡ ፍቅር ምላሽ ከሌለው በሙላት ሊገለጽ አይችልም፡፡

ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ፡፡ በአንዳንድ ትርጉሞች ‹‹ልትሆኑ›› የተጠራችሁ የሚለው በተለየ አይነት አጻጻፍ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ማለት ቃሉ የተርጓሚዎቹ አጠቃቀም መሆኑን ያሳያል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ቃላት ትርጉማቸው ሳይበላሽ መጠቀም ይቻላል፡፡ ከዚያም የምናገኘው ትርጉም ‹‹ የተጠራችሁ ቅዱሳን ›› የሚል ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ‹‹የተሰየማችሁ›› ቅዱሳን የሚለውን ትርጉም ይሰጣል፡፡ ቅዱሳን የሚለው የግሪኩን (hagio-) የሚለውን ሲሆን ትርጓሜውም የተቀደሰ ወይም ቅዱስ ማለት ነው ፡፡ ቅዱስ ማለት ደግሞ ‹‹የተሰጠ›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው፡፡ በመጸሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሰረት እርሱ ወይም እርሷ ገና በቅድስና መንገድ የሚጓዙት ብዙ ቢሆንም የዚህ ሰው ክርስቶስን የግል አዳኙ አድርጎ የመምረጡ(ዋ) እውነት እርሱን ወይም እርሷን ቅዱስ እንድትሆን (እንዲሆን)ያደርጋታል(ዋል)፡፡ ጳውሎስ ‹‹ቅዱሳን ለመሆን የተጠራችሁ ሲል ፤ አንዳንድ ሰዎች አልተጠሩም የሚል ትርጉም ይሰጣል? ኤፌ. 1፡4፣ ዕብ. 2፣9፣ 2ጴጥ. 3፣9 ጳውሎስ የሚለውን ለመረዳት እንዴት ይረዱናል? የወንጌል ትልቁ ዜና የክርስቶስ ሞት ለዓለም ሁሉ መሆኑ ነው፡፡ የእርሱ ሞት ለሰው ልጆች ሁሉ ነው፡፡ ገና ዓለም ሳይፈጠር በእርሱ ለመዳን ሁሉም ተጠርተዋል፡፡ የእግዚአብሄር የጥንቱ ዓላማ ሰውን ሁሉ በክርስቶስ ማዳን ነው፡፡ የመጨረሻው እሳትም የተዘጋጀው ለሰይጣንና ለመላዕክቱ ብቻ ነው (ማቴ. 25፣41)፡፡ ሁሉም ነገር በሞላበት የገበያ ሥፍራ ረሃብን እንደሚያውጅ ሰው፣ አንዳንድ አፈ-ታሪኮች ታላቁንና አስደናቂውን መስዋዕት ሊያስረሱ አይችሉም፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ጀምሮ እግዚአብሔር ለድነት ጠርቶሃል፡፡ ምንም እና ማንኛውም ነገር ከዚህ ጥሪ ወደ ኋላ እንዳያስቀርዎት ጥንቃቄ የሚያደርጉት ለምንድን ነው?

መስከረም 25
Oct-5

የሮሜ አማኞች


“እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በእየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ” (ሮሜ 1:8). በሮሜ የምዕመን አደረጃጀት እንዴት እንደሆን የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ጳውሎስና ጴጥሮስ ቤተክርስቲያንን የመሰረቱት የቤተክርስትያን አመሰራረት ቅድመ ታሪክ በሌለበት ሁኔታ ነበር ፡፡ ምናልባትም በእየሩሳሌም በጴንጤቆስጤ ቀን ጌታን ከተቀበሉ ምእመናን መካከል ወደ ሮሜ የሄዱ መስርተው እንደነበር ይገመታል ፡፡ ወይም ምናልባት ትንሽ ቆየት ብሎ የተለወጡና ወደ ሮሜ የመጡ አማኞች ስለ እምነታቸው መስክረውላቸው ይሆናል፡፡ በሐዋሪያት ያልተጎበኘ የአማኞች ጉባኤ ከጥቂት አስርት ዓመታት በኋላ የዚህን ያህል በስፋት የሚታወቅ መሆኑ በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ “ከነበረው ተቃውሞ በተቃራኒ ከክርስቶስ ስቅለት 20 ዓመት በኋላ በሮም ሕይወት ያላት ጠንካራ ቤተክርስትያን ነበረች፡፡ ይህች ቤተክርስትያን ትጉህና ጠንካራ ስትሆን እግዚአብሄርም ለእርሷ ሰርቶ ነበረ፡፡” —Ellen G. White Comments, The SDA Bible Commentary, vol. 6, p. 1067.

“እምነት” በዚህ ስፍራ በእየሱስ ክርስቶስ ለተገኘው ለአዲሱ አይነት አኗኗር ታማኝ ሆኖ መገኘትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ ሮሜ 15 14ን ያንብቡ፡፡ በሮሜ የነበረችውን ቤተክርስትያን ጳውሎስ የገለጸው እንዴት ነበር?

ጳውሎስ በሮሜ ክርስትያኖች ልምድ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ሦስት ዋና ዋና ነገሮች የሚያነሳው እዚህ ሥፍራ ነው፡፡

1. “በመልካምነት የተሞላችሁ፡፡” ከእኛ ልምድ በመነሳት ሰዎች እኛን እንዲህ ይሉናል? ከእኛ ጋር ሲሆኑ የእነርሱን ትኩረት የሚስበው የእኛ መልካምነት መብዛት ነው?

2. “በዕውቀት ሁሉ መሞላት” መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ስለ መገለጥ፣መረጃ እና ስለ ዕውቀት አስፈላጊነት አጥብቆ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ክርስትያኖች መጸሐፍ ቅዱሳቸውን እንዲያጠኑና ትምህርቱንም በትክክል እንዲያስተውሉ ያስፈልጋል፡፡ “አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ ማለት አዲስ አእምሮ እሰጣችኋለሁ ማለት ነው ፡፡ የልብ መለወጥ የሚገለጸው ግልጽ በሆነ የክርስትያን የህይወት ተግባር ነው፡፡ ይህም እውነትን ማስተዋል ነው፡፡” —Ellen G. White, My Life Today, p. 24.

3. “አንዱ ሌላውን መገሰጽ መቻል፡፡” ከአማኝ ወንድሞቹ ተለይቶ ማንም ሰው መንፈሳዊ ዕድገት ሊያድግ አይችልም፡፡ እኛ ሌሎችን ልናበረታታና ሌሎችም እኛን ሊያበረታቱን ይገባል፡፡

የእኛ አጥቢያ ቤተክርስትያን ምን ዓይነት ስም አላት? የዚህ ምላሽ ስለ አጥቢያ ቤተከርስትያንዎ ምን ይነግረናል? ይህን ሁኔታ ለመለወጥ እርስዎ ምን እገዛ ያደርጋሉ?

መስከረም 26
Oct-6

ተጨማሪ ሀሳብ፡-


ለተጨማሪ ጥናት:- የሚከተሉትን የኤሌን ዋይት መጻህፍት ያንብቡ፡፡ “The Mysteries of the Bible,” p. 706, in Testimonies for the Church, vol. 5; “Salvation to the Jews,” pp. 372–374, in The Acts of the Apostles. Read also The SDA Bible Dictionary, p. 922; and The SDA Bible Commentary, vol. 6, pp. 467, 468.

“የሰው ልጆች የድነት ዕቅድ ባልተጠበቀ ሁኔታ ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በመሄዳቸው በመለኮት ከዚያ በኋላ የተፈጠረ ወይም የታቀደ ነገር አልነበረም፡፡ በምትኩ ግን የሰዎች ድነት የታሰበው ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ ነበር፡፡ (1ቆሮ . 2:7; ኤፌ ,1:3, 14; 2ተሰ. 2:13, 14) ይህም የተመሠረተው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ባለው ዘላላማዊ ፍቅር ላይ ነው፡፡(ኤር. 31:3). “ይህም ዕቅድ የሚሸፍነው ወይም የሚያጠቃልለው ያለፈውን ዘላላም ፣የአሁኑን ጊዜና የወደፊቱን ዘላላም ነው ፡፡ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ምርጥ ህዝብ፣ ቅዱስ ለመሆን መወሰን እና የክርስቶስን አምሳያ መሸከም፣ በክርስቶስ የሚሆን የሁሉም ነገሮች አንድነት ፣ መዋጀትና ይቅርታ ማግኘት፣ በመንፈስ ቅዱስ መታተም፣ የዘለዓለምን ርስት መውረስ እና ክብር( ኤፌ. 1፡3-14)፡፡ የዚህ ሁሉ ዕቅድ ማዕከል የሆነው የእየሱስ መከራና ሞት የታሪክ ድንገተኛ ክስተት ወይም ዝም ብሎ የሰብዓዊ ውሳኔ ሳይሆን በእግዚአብሔር የማዳን ዕቅደ ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ (ሐዋ. 4:27, 28):: እየሱስ በእውነት ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የታረደ የእግዚአብሔር በግ ነው (ራዕይ 13:8).” —The Handbook of Seventh-day Adventist Theology (Hagerstown, Publishing®, 2000), pp. 275, 276. Md.: Review and Herald


የመወያያ ጥያቄዎች:



በክፍላችሁ ስለ ፕሮቴስታንት ተሓድሶ ትርጉም ተነጋገሩበት፡፡ በተለይም ያ ባይሆን የዛሬው ዓለማችን ምን ይሆን ነበር?

ከዓለም ፍጥረት በፊት ለድነት ተጠርተናል በሚለው ትኩረት ሰጥታችሁ ተወያዩበት( ትቶ. 1፡1, 2; 2 ጢሞ. 1:8, 9)፡፡ ይህ በጣም የሚያጽናናን ለምንድን ነው? ይህ እግዚአብሔር ለሰብዓዊ ዘር ሁሉ ስላለው ፍቅር ምን ይነግረናል? ሰዎች ለዚህ ለተሰጣቸው እጅግ አስደናቂና ውድ ለሆነው ሥጦታ ጀርባቸውን ሲሰጡ በጣም አሰቃቂ የሚሆነው ለምንድን ነው?

በሐሙስ ቀን ትምህርት ላይ ባለው ጥያቄ ትኩረት አድረጉ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የቤተክርስትያናችሁን ስም ለማደስ የእርስዎ ከፍል ተማሪዎች ምን ማድረግ ይችላሉ?