የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

በፈተና ውስጥ ከክርስቶስ ጋር


3ኛ ሩብ ዓመት 2022

ሰኔ-መስከረም 2014/15

መደበኛ እትም

June 25 - September 23




አዘጋጆች ጋቪን አንቶኒ

ወርቅነህ ያዶሬ እንደተረጎመው



ይህ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ የሚዘጋጀው በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋና መስሪያ ቤት በሆነው በጀነራል ኮንፍረንስ ውስጥ ሆኖ፤ የጎልማሶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያን በሚያዘጋጀው ቢሮ ነው። መምሪያዎቹ የሚዘጋጁት የጀነራል ኮንፈረንስ አስተዳደር ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሆነውና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያዎችን በሚያሳትመው የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድ ነው። የታተመው መምሪያ በውስጡ ዓለም አቀፋዊ የሆነ የምዘና ኮሚቴ ሀሳቦችንና የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድን ማረጋገጫ ስለሚያንጸባርቅ የአዘጋጁን (የአዘጋጆችን) ሀሳብ ብቻ የሚወክል አይደለም። በኢትዮጵያ አድቬንቲስት ማተሚያ ቤት ታተመ

የተሰቀለው ፈጣሪ


‹‹ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳች እንኳ ያለእርሱ አልሆነም›› (ዮሐ 1፡3)። ሁሉም በእርሱ ተፈጥሯል፣ ሆኖም እንደ መጸሐፍ ቅዱስ ‹‹ክርስቶስ አለቀሰ››(ዮሐ 11፡35)። ፈጣሪ አለቀሰ? ከዚህም የበለጠ ‹‹ የተናቀ ከሰው የተጠላ የህመም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፣ሰውም ፊቱን የሚሰውርበት የተናቀ ነው›› (ኢሳ 53፡3)። ፈጣሪ ፡- የህመም ሰው፣ የተጠላ እና የተናቀ? አንዴ እንዲያውም ፣ ‹‹ አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ›› በማለት ጮሆ ነበር(ማቴ 27፡16)።

ይህ እንዴት ይሆናል? ይህ የሆነበት ክርስቶስ ፈጣሪያችን ራሱ ደግሞ የሚዋጀን፣እናም የተሰቀለልን ጌታ፡- በራሱ ሰብአዊነትን በመውሰዱ የመከራንና የድካምን ህይወት በመኖር መጨረሻም በሮማውያን መስቀል ላይ ህይወቱ አብቅቷል።

ስለዚህም፣ የእኛ ፈጣሪ፣ እኛ የምናምንበት ‹‹በእርሱ ህያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖራለንም››( ሐዋ 17፡28)፣ እርሱ ማናችንም ባልደረሰብን መጠን መከራን ተቀበለ። እኛም እያንዳንዳችን የራሳችንን ጭንቀትና፣ ሐዘናችንን እንለማመዳለን ‹‹ እርሱ በመስቀል ላይ ደዌአችንን ተቀበለ ህመማችንን ›› ( ኢሳ 53፡4)። ይህ በፈለክ(በሰማያት) ውስጥ ከሚገኙ ማናቸውም ታሪኮች ይልቅ እጅግ አስደናቂ የሆነው ታሪክ ነው።

በዚህ የታሪክ አውድ ፡- ማለትም (በእኛ ዙሪያ በሚያንዣብበውና ስለእኛ በተሰቀለው አምላክ)፣ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ለማስተዋል እጅግ ከባድ የሆነውን የክርስቲያን መከራ ፣ የእኛ የራሳችን ስቃይ እና ራሳቸውን ለክርስቶስ በመሰዋት ህይወታቸውን የሰጡ ክርስያኖች መከራን በተሻለ ሁኔታ ለማስተዋል እንሞክራለን። ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ እንሰጣለን ብለን አናስብም፣ እኛ የምንፈልገው እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ብቻ (1ዮሐ 4፡ 8)። እነዚህ ነገሮች ቢሆኑም እንኳ በእግዚአብሄር እናምናለን፣ በእርግጥም የእነዚህ ነገሮች ( መከራዎች መከሰት) ምንም ያህል የሚያሳምም ቢሆንም እኛን በጸጋ ያሳድጉናል ።

በዚህ ሩብ ዓመት በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር በመጣበቅ ሌሎች ስጋና ደም የለበሱ እንዴት መገፋትን፣ ክህደትን ፣ተስፋ መቁረጥን፣ ማጣትን ፣ የፍርድ መጓደልን፣ እና አግባባዊ ያልሆነ አጠቃቀምን እንዲሁም ሌሎችንም አስቸጋሪ ነገሮችን ጨምሮ እንዴት እንዳለፉ ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንዴት ተቋቋሙ፤ እነርሱ ምን ተማሩበት እና የእነርሱስ ምሳሌ ለእኛ ምን እንደሚያስተምረን እንማራለን።

የእነዚህንም ሰዎች ልምድ ፣ ትግሎች፣ የእምነት ፈተናዎቻቸው (ልክ እኛን እያጋጠመን እንዳለ) ማለት ነው። ይህ ማለት ማንም ምንም ነገር ቢያጋጥመው ሁኔታውን ሁልጊዜ ከመስቀሉ ትሩፋት ጋር በማወዳደር እናያለን ። ሁልጊዜ ማስታወስ የሚገባን ነገር ማንም ምንም ዓይነት ነገር የሚያጋጥመው ቢሆንም፣ ክርስቶስ የእኛ አዳኝ የሆነው ፈጣሪያችን ከዚህ ሁሉ በከፋ ሁኔታ ያለፈ መሆኑን ነው።

የእኛ አምላክ አዛኝ አምላክ ነው። አልበርት ከሙስ ፣ ‹‹ክርስትናው ብዙ ባይሆንም፣ የመስቀሉን ትርጓሜና ስለእኛ ስለሚጨነቀው አምላክ ብዙ ብሏል። የጎልጎታው ሌሊት በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው መለኮት የጽዋውን የመጨረሻ ጠብታ ድረስ ማድረግ ያለበትን ዕድሎችን ሁሉ በመጠቀም የሞትን ሥቃይ ጨምሮ ዋጋ የከፈለበት መሆኑ ብቻ ነው››። ኤሌን ዋይት ‹‹ መስቀል፣ ኃጢአት ከጥንስሱ ጀምሮ፣ በእግዚአብሄር ልብ ውስጥ የፈጠረውን ስቃይ ለማስተዋል ዝንጉ ለሆነው ሰብዓዊ ስሜታችን መግለጫ ነው። (ስነ-ትምህርት ገጽ 263 በእንግሊዝኛው )። ትምህርታችን በክፉው ፊት የእግዚአብሔርን መልካምነት ለመከላከል አይደለም። በዚህ ፋንታ ግን ኃጥአት ልክ እንደ አስትንፋስ በቀረበበት በዚህ ምድር ስንኖር ከዚህ ቀድም እንዳነሳነው ፣ በዚህ ዓለም ላይ ሁላችን በሚያጋጥመን ለማየት በሚያስቸግረው መከራ ውስጥ እንድንሰራ የሚረዳን መሆኑን ማስገንዘብ ነው።

ማሳየት የምንፈልገው፣ መከራ ጭንቀት፣ ስቃይ እና ማጣት እግዚአብሔር እኛን ትቶናል ማለት ሳይሆን እንደ ክርስቲያኖች የወደቀውን ዓለም ዕጣ የምንካፈል መሆኑ ነው። ልዩነቱ ትርጉም- አልባ እና ዓላማ- ቢስ በሚመስለው ሁኔታ ውስጥ በኢየሱስና እርሱ በሚሰጠን ተስፋ፣ ‹‹ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው›› (ሮሜ 8፡28) የሚለው ተስፋ እንዴት እንደሚፈጸም ለማስተዋል ብንቸገርም፣ ሁሉን የፈጠረው አምላክ፣ መከራንም ሁሉ የተቀበለ በመሆኑ ነው።



የዚህ ሩብ አመት ትምህርት ዋና ጸሐፊ ጋቪን አንቶኒ፣ እንደ ሚሽነሪ ህጻን በሴርላንካ አደገ።ፓስተር ሆኖ በእንግሊዝ አገር ሰርቷል። ይህንን ትምህርት በጻፈ ጊዜ የአይስላንድ አድቬንቲስት የስራ መሪ ነው።