2ኛ ትምህርት መከራና ፈተናዎች
መከራ እና ፈተና በሚል ርዕስ አዲስ ተከታታይ ጥናት ጀምረናል ። የቅዱሳት መጻሕፍት መዝሙር፡- አትፍራ - ኢሳ 41፡10

መከራን እና ፈተናዎችን መጠበቅ

1) የመከራ ደራሲ ሰይጣን


ሀ) እግዚአብሔር መልካም ከሆነ፤ በዓለም ላይ ይህን ያህል መከራ የበዛው ለምንድን ነው?
ለ) 1 ጴጥሮስ 5:8 ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ስለ መከራ መንሰኤ ምን ተናግሯል?
ሐ) ኢየሱስ ይህን ጠላት የገለጸው እንዴት ነው? የዮሐንስ ወንጌል 8፡44
መ) በራእይ 12:​7-11 ላይ ስለ ሰይጣን ዓመፅ ምን ተጨማሪ ሃሳቦች ተመዝግበዋል?
ሠ) ስለ ዓመፀኛው መልአክ በነቢዩ ሕዝቅኤል ምን መረጃ ተሰጥቷል? ሕዝቅኤል 28፡13-17 (በተጨማሪ ኢሳይያስ 14፡12-14 ተመልከት)
ረ) አንድ ሰው ከሰይጣን ከባድ ጥቃት የደረሰበትን ታሪክ ከመፅሀፍ ቅዱስ ያካፍሉ። ኢየሱስ፣ ኢዮብ፣ ወዘተ.
ሰ) ሐዋርያው ጴጥሮስ በሰይጣን ጥቃት ለሚሰነዘርባቸው ሰዎች ምን ጠቃሚ ምክር ሰጥቷቸዋል? 1ኛ ጴጥሮስ 5፡9-11
ሸ) ሐዋርያው ጳውሎስ በሰይጣን ጥቃት ለሚደርስባቸው ሰዎች ምን ተጨማሪ ምክር ሰጥቷል? ኤፌሶን 6፡10-18

2) በራሳችን ላይ የምናመጣቸው መከራ እና ፈተናዎች


ሀ) በራሳችን ላይ መከራና ፈተና የምናመጣባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? ገላ 6፡7-8ሀ፣ ሮሜ 1፡18-25
ለ) ሰሎሞን በራሱ ላይ መከራ ስላመጣ ግድየለሽ ወጣት ምን ታሪክ ተናግሯል? ምሳሌ 7፡6-23
ሐ) በራስህ ላይ መከራና ፈተና ያመጣህበትን ጊዜ አካፍል። እግዚአብሄር ከዚያ አደገኛ መንገድ እንዴት ታደገህ?

3) በጌታ የተፈቀደ መከራ ወይም ፈተና


ሀ) ለበለጠ መልካም ነገር በልጆቹ ላይ መከራዎች ወይም ፈተናዎች እንዲመጡ ጌታ የፈቀደባቸውን አንዳንድ ምሳሌዎች ከመፅሀፍ ቅዱስ አጋራ። ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ፣ ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ፣ የናቡከደነፆር መዋረድ፣ ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ እስር ቤት ወዘተ.
ለ) ሐዋርያው ጳውሎስ በመከራ ውስጥ ካጋጠመው ተሞክሮ ምን እንማራለን? 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-10
ሐ) በሕይወታችሁ ውስጥ መልካም ነገርን ለማከናወን እግዚአብሔር በመከራ ወይም በፈተና ውስጥ እንድታልፉ የፈቀደበትን ጊዜ አካፍሉ።
መ) በሮሜ 8:28 ላይ መከራና ፈተናዎች ለሚደርስባቸው ምን የከበረ ተስፋ ተሰጥቷል?

4) ለመከራ እና ለፈተና ዝግጁ መሆን


ሀ) አንዳንድ ጊዜ፣ የኢየሱስ ተከታዮች ከማያምኑት በላይ የሚሠቃዩ ይመስላል። ለምን?
ለ) መከራና ፈተና ሲደርስብን መደነቅ የሌለብን ለምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡12-19
ሐ) ወደፊት ለሚደርስብን መከራና ፈተና ለመዘጋጀት ከሁሉ የተሻለው መንገድ የትኛው ነው? ያዕቆብ 4፡7-10

ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።