8ኛ ትምህርት ተስፋው
የዛሬ ርዕሳችን፡ ተስፋው መዝሙር -እጆቻችሁን አጨብጭቡ- መዝሙር 47፡1-2 5-7

በሞሪያ ተራራ ላይ ያለው ፈተና

ሀ) ዘፍጥረት 22፡1 በሞሪያ ተራራ ላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ፈተና ትርጉሙ ምን ነበር?
ለ) በድሮ ጊዜ በነብዩ ሙሴ አማካኝነት እግዚአብሔር የህፃን ልጅ መስዋዕትነትን ይከለክላል.(ዘሌዋውያን 18፡21) እግዚአብሔር ሃሳቡን ለውጧል?
ሐ) አብርሃም ባሳለፈው ፈተና ውስጥ ሲያልፍ ምን አይነት አበረታች ምልከታዎችን ይሰጠናል በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ?ዘፍጥረት 22፡8 ዕብራዊያን 11፡17-19
መ) በሞሪያም ተራራ ላይ አብርሃም በተፈተነው ፈተና ምን አይነት ትምህርት ይሰጠናል ለዛሬው ህይወታችን?

እግዚአብሔር ‹‹ያህዌህ ንሲ›› ያዘጋጃል

ሀ) እግዚአብሐር ለአብርሃም የገባውን የተስፋ ቃል እንዴት በሞሪያም ተራራ ፈፀመው?ዘፍጥረት 22፡11-14
ለ) ስለድነት ዕቅድ ከዚህ አስደናቂ ፈተና ምን እንማራለን?ዘፍጥረት 22፡18 ዩሐንስ 8፡56 ገላትያ 4፡4-7 28 ዩሐንስ 3፡16 ሮሜ 5፡6-8 …ወዘተ
ሐ) እግዚአብሐር ለደህንነትህ ያደረገውን ታላቅ ዝግጅት ይበልጥ የተረዳህው መቼ ነው?

የሳራ ሞተ እና ቀብር

ሀ) ዘፍ 23፡1-2 ላይ የሳራን ሞት አስመልክቶ ምን አስፈላጊ መልዕክት አልው?
ለ)አብርሃም ስለሳራ የመቃብር ርስት ዙርያ ምደራደሩን ሙሴ በዝርዝር ያስቀመጠብት መክንያት ለምን ይመስላችኃል?
ሐ) በትንተናው ላይ ሁለት ጊዜ የመቃብር ርስቱ ለመምሬ በቅርበት እንደሚገኝ ይናገራል? የቦታው አስፈላጊነት ለምን ነበር? ዘፍጥረት 13፡14-18 18፡1

ለአብርሃም ልጅ ይስሀቅ ሚስት መፈለግ

ሀ) ዘፍጥረት 24፡1-4 ለምን ነበር አብርሃም ለልጁ የወደፊት ሚስት ከከናናዊት ሴት አንዲቷ እንዳትሆን የግድ ያስባለው?
ለ) አብርሃም አገልጋዩን ይስሀቅን ወደ ሜሶፖታሚያ እንዳይመልሰው ያሰጠነቀቀው ለምንድነው?ዘፍጥረት 24፡5-9
ሐ) የአብርሃም አገልጋይ በናሆር ከተማ በደረሰ ጊዜ ሰለፀለየው ፀሎት ምን ዓይነት መረዳት አላችሁ?ዘፍጥረት 24፡10-14
መ) እንዴት ነው እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጅ ለይስሀቅ ያዘጋጀለት ልክ በሞራ ተራራ ላይ ለአብርሃም እንዳዘጋጀው? ዘፍጥረት 24፡15-27 ማስታወሻ ''መናገሩን ሳይፈፅም''
ሠ) ይስሀቅ እግዚአብሔር ላዘጋጀለት የሰጠው ምላሽ እንዴት ነበር? ዘፍጥረት 24፡66-67
ረ) ከታሪኩ የምንማረው ትምህርት ምንድ ነው?

በትዕይንት የተሞላው የመጨረሻዋቹ የአብርሃም ዕድሜ

ሀ) ዘፍጥረት 25፡1-6 ከኬጡራ ጋር የነበረውን ጋብቻ በእግዚአብሔር ምሪት እንዳልነበር የሚያመላክቱ ምን አይነት ምልክት ተገልጿል?
ለ) ዘፍጥረት 25፡7-11 የትኞቹ ማብራሪያዎች ናቸው ከአብርሃም ሞት እና መቃብሩ ጋር ተያይዞ አስፈላጊ የሆኑት?
ሐ) ከአብርሃም ህይወት የተማራችሁት አስፈላጊ ትምህርቶች ምንድ ናቸው? ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።

ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።