| 7ኛ ትምህርት | ከአብርሃም ጋር የተደረገ ቃልኪዳን |
|---|
የአብርሃም እምነት
ሀ) ዘፍጥረት 15፡1-6( ሮሜ 4፡3) ምን ዓይነት የጠለቀ እውነት ነው የተገለጠው በእግዚአብሔር እና በአብርሃም ባለ ግንኙነት ውስጥ?ለ) ዘፍጥረት 15፡7-17 የመስዋዕት ስርዓት ጊዜ ምን ዓይነት ተጨማሪ እውተቶች ተገልጧል ቃልኪዳኑን የሚያረጋግጡልን?
ሐ) የአብርሃም እምነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው ወይስ ማደግ በሚያስፈልገው የሆነ ነገር?
የአብርሃም እና የሳራ ክርክር
ሀ) ዘፍጥረት 16፡1-4 የእግዚአብሔርን ዕቅድ በራስ መንገድ ለማድረግ መሞከር ለምድነው ሁልጊዜ ስተት የሚሆነው?ለ) የአብርሃም እና የሳራ ድርጊት እንዴት ነው ስለድነት የተሰጠውን ሃሰተኛ ትምህርት የሚያብራራው?
ሐ) ነገሮችን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ከማድረግ ይልቅ በራስ መንገድ ያደረጋችሁበትን ጊዜ አካፍሉ፡፡
የአብርሃማዊው ቃልኪዳን ምልክት
ሀ) ዘፍጥረት 17፡1-9 ይህ ቃለምልልስ ምን ያስተምረናል ሰለ እግዚአብሔር እና ስለ አብርሃም?ለ) ዘፍጥረት 17፡10-13 ከአብርሃም ጋር ባለው ቃልኪዳን ውስጥ ለምንድነው እግዚአብሔር ግዝረትን እንደ ምልክት የመረጠው?
ሐ) ስማቸው ከአብራም (የተሞገሰ አባት) እና ሦራ (የኔ ልዕልት) ወደ አብርሃም እና ሣራ መቀየሩ ጠቀሜታው ምንድ ነው?
ይስሐቅ የተስፋው ልጅ
ሀ) ዘፍጥረት 18፡1-15 በእግዚአብሔር ጉብኝት ውስጥ በመምሬ ወደ አብርሃም እና ሣራ የቱጋር ነው የእግዚአብሔር ያልወደቀው ፍቅር እና ምህረት የተገለጠው?ለ) ዘፍጥረት 21፡1-6 የእግዚአብሔር ተስፋ ፍፃሜውን ካየች በኋላ እንዴት ነው ሣራ ሣቋ የተቀየረው?
ሐ) እግዚአብሔርን ለማመን እና ተስፋውን ለማመን በምታደርገው ትግል ውስጥ ያሳለፍክበትን ጊዜ አካፍል፡፡
የሶደም እና ጎመራ ጥፋት
ሀ) ዘፍጥረት 18፡16-21 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ሊጎበኝ ለምን አስፈለገው? የነዚህን ከተሞች ክፋት አስቀድሞ አያውቅምን?ለ) ዘፍጥረት 18፡22-23 የአብርሃም አማላጅነት እግዚአብሔር የበልጥ መሐሪ እንዲሆን አሳምሆታል ወይስ የእግዚአብሔርን ምህረት እና ያልወደቀ ፍቅር ማንፀባረቅ ጀመረ? (2ኛ ጴጥሮስ 3፡9 ተመልከቱ)
ሐ) ዘፍጥረት 9፡1-11 የሰዶም ሰዎች ጠባይ የዚያችን ከተማ ታለቅ ክፋት ያረጋገጠው እንዴት ነው?
መ) በሰዶም ውስጥ መኖሩ እንዴት በሎጥ እና በቤተሰቡ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል?
ሠ) በዩሐንስ 17፡15-19 ውስጥ የተገለፀው የየሱስ ክርስቶስ ፀሎት ዛሬ ለህይወታችን እንዲህ ያለ ማበረታቻ የሆነው ለምንድነው? በዚህ ክፋት በተሞላ ዓለም ውስጥ ስንኖር፡፡
ረ) ለእያንዳዳችን እግዚአብሔር የሰጠን ምንድነው? ሮሜ 12፡2 ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።