| 4ኛ ትምህርት | የጥፋት ውሃ |
|---|
የውሃ ጥፋት ምክንያት
ሀ) ዘፍጥረት 6፡1-7፣11-12 ለዚህ አስከፊ የጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያቱ ምን ነበር? (የአየር ንብረት ለውጥ አይደለም)ለ) ክፋት ከመጠን በላይ በመንሰራፋቱ ምክንያት የመለኮታዊ ፍርድ የታዩበት ሌሎች ጊዜያትን አካፍል። (ሰዶምና ገሞራ ወዘተ.)
ሐ) እነዚህ የእግዚአብሔር ፍርዶች እንዴት የምሕረት ሥራዎችም ናቸው?
ለጥፋት ውሃ መዘጋጀት
ሀ) እግዚአብሔር አምላክ ለምንድን ነው ለኖኅ ልዩ የሆነ ኃላፊነት የሰጠው? ዘፍጥረት 6፡8፣ 6፡13-22፣ 7፡1-5ለ) መርከብ ተብሎ የተተረጎመው ይኸው የዕብራይስጥ ቃል የሙሴን መሶብ እና የቃል ኪዳኑን ታቦት ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። ከነዚህ ምን ግንኙነት እንመለከታለን?
ሐ) ሃይማኖታዊ ድርጊቶች የነበሩ ነገር ግን የዓመፅ ድርጊቶች የሆኑበት ጊዜያትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚገልጹ ሌሎች ምሳሌዎችን ያካፍሉ። (ንጉሥ ሳኦል መስዋዕትን አቀረበ፣ የነሐሱን እባብ የሚያመልኩት ሰዎች፣ ወዘተ.)
መ) እግዚአብሔር ባዘጋጀው የደኅንነት መርከብ የኖኅ ቤተሰብ ብቻ የገባው ለምንድን ነው? ዕብራውያን 11፡7፣ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡9
የፍጥረት መጥፋት
ሀ) ዘፍጥረት 7:11-12, 17-24 በዚህ ዓለም አቀፉ የጥፋት ውኃ ክስተት ውስጥ የፍጥረት ሥራ ሲሻር የቱጋ እንመለከታለን?ለ) ዘፍጥረት 8:1ሀ “እግዚአብሔር ኖኅን አሰበ” የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር ረስቶ ያውቃል? ( ዘፍጥረት 19:29፣ መዝሙረ ዳዊት 106:4፣ ሉቃስ 23:42 ተመልከት)
ሐ) እግዚአብሔር አምላክ ከውኃ ጥፋት በኋላ ኖኅን ለማዳን የገባውን ቃል መፈጸም የቀጠለው እንዴት ነው? ዘፍጥረት 8፡1ለ-4
መ) በዚያን ጊዜ ኖኅ ካሳየው የትኛው ባሕርይ አሁንም ያስፈልጋል? (ዕብራውያን 11:7ን ተመልከት) ለምን?
የአዲስ ፍጥረት መጀመሪያ
ሀ) ዘፍጥረት 8:5-14 መርከቡን ለቀው የሚወጡበት ጊዜ እንደመጣ የሚያሳዩት ምልክቶች የትኞቹ ነበሩ?ለ) ኖኅና ቤተሰቡ መርከቡን ለቀው የሚወጡበት ትክክለኛ ጊዜው እንደደረሰ እንዴት አወቁ? ዘፍጥረት 8፡15-16
ሐ) እግዚአብሔር ኖኅህን ከመርከቧ እንዲወጣ ያዘዘውን ትእዛዝ እንዴት አከበረ? “የጥልቁ ምንጮች እንደገና ሊፈርሱ ስለሚችሉ እዚህ እቆያለሁ” ለምን አላለም ነበር?
መ) እንደዚህ ያለ ጥልቅ እና የማይለወጥ እምነት እና በእግዚአብሔር መታመን የምንችለው እንዴት ነው?
የእግዚአብሔር የህይወት ቃል ኪዳን
ሀ) ኖኅ ከመርከቡ ከወጣ በኋላ በመጀመሪያ ካደረገው ሥራ ምን እንማራለን? ኦሪት ዘፍጥረት 8፡20ለ) ዘፍጥረት 8፡21 የሚቃጠል የእንስሳት ሥጋ ሽታ ለእግዚአብሔር በእውነት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ነበረው?
ሐ) ዘፍጥረት 9:1-4 ከጥፋት ውኃ በኋላ የአመጋገብ ለውጥ የተደረገው ለምንድን ነው? ምን ገደቦችና መዘዞች አስከትለዋል?
መ) ዘፍጥረት 9፡8-17 የእግዚአብሔር የሕይወት ቃል ኪዳን ምልክት በእርግጥ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
ሠ) የእግዚአብሔር ተስፋ ቃላት እውነተኛ ናቸው። ለእናንተ ውድ የሆነው የእግዚአብሔር የተስፋ ቃላት አካፍሉ። ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።