| 3ኛ ትምህርት | ቃየን እና ትሩፋቱ |
|---|
ቃየንና አቤል
ሀ) ዘፍጥረት 4:1 የበኩር ልጃቸው ስም ስንመለከት ወላጆቹ አዳምና ሔዋን ምን እንደሚጠብቁ ያሳየናል (ቃናሕ - የተገኘ)ለ) በሁለተኛው ልጃቸው ገለጻ እና ስያሜ ላይ ምን ልዩነት ይታያል? (ሄበል - ትነት/ትንፋሽ)
ሐ) ከእነዚህ የተሳሳቱ አመለካከቶች ምን ትምህርት እናገኛለን?
ሁለት አይነት መባዎች
ሀ) ዘፍጥረት 4፡3-5 እግዚአብሔር አምላክ የአቤልን መስዋዕት ተቀብሎ የቃየንን መስዋዕት የናቀው ለምንድነው?ለ) የዕብራውያን ጸሐፊ የአቤልን መስዋዕት“እጅግ የሚበልጥ መሥዋዕት” በማለት ገልጾታል። ይህ ለምንድን ነው? ዕብራውያን 11፡4
ሐ) ሃይማኖታዊ ድርጊቶች የነበሩ ነገር ግን የዓመፅ ድርጊቶች የሆኑበት ጊዜያትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚገልጹ ሌሎች ምሳሌዎችን ያካፍሉ። (ንጉሥ ሳኦል መስዋዕትን አቀረበ፣ የነሐሱን እባብ የሚያመልኩት ሰዎች፣ ወዘተ.)
የመጀመሪያው ግድያ
ሀ) ዘፍጥረት 4:4ለ-5 ቃየን ተቆጣው የነበረው በእግዚአብሔር፣ በአቤል ወይስ በሁለቱም ላይ ነበር? ለምንድን ነበር? (በተጨማሪ 1 ዮሐንስ 3፡11-12 ተመልከት)ለ) አምላክ ቃየንን ከቀረበበት መንገድ ምን እንማራለን? ዘፍጥረት 4፡6-7
ሐ) ቃየን ኃጢአተኛ አስተሳሰቦች ባህሪውን እንዲቆጣጠሩት የመፍቀዱ ውጤቱ ምን ነበር? ዘፍጥረት 4፡8
መ) በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው የያዕቆብ ምክር በቃየን ላይ የደረሰውን ነገር እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ያዕቆብ 1፡13-15
ሠ) ከባድ ፈተና ሲያጋጥምዎ ተስፋ የሚሰጥዎትን የሚያበረታታ ቃል ያካፍሉ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡13 መዝሙረ ዳዊት 50፡15 ወዘተ.
የቃየን ቅጣት
ሀ) ዘፍጥረት 4:9ሀ አቤል ከሞተ በኋላ አምላክ ለቃየን የጠየቀው ጥያቄ ምን ትርጉም አለው?ለ) ቃየን የሰጠው ምላሽ የንስሐ ዝንባሌ እንዳለ ምን ምልክቶች ታያለህ? ዘፍጥረት 4፡9ለ
ሐ) ዘፍጥረት 4:10 ቃየን ምንም ዓይነት የጥፋተኝነት ስሜት ባለመሰማቱ እግዜአብሔር ከሰጠው ምላሽ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? ( ዕብራውያን 4:12-13 ተመልከት)
መ) ዘፍጥረት 4:11-15 ስለ ቃየን ቅጣትና ለዚያ የሰጠው ምላሽ ምን ይመስልሃል?
የቃየን እና የሴት ዘሮች
ሀ) ዘፍጥረት 4:17-24 በእነዚህ ሁለት ነፍሰ ገዳዮች ቃየንና ላሜሕ መካከል ምን ልዩነት ይታያል?ለ) ዘፍጥረት 6፡5-6 ይህ አሳዛኝ ምስክርነት ስለ አለመታዘዝ መንገድ ምን ይነግረናል? (በተጨማሪ መዝሙር 1:1ን ተመልከት)
ሐ) በቃየል ዘሮች መካከል ኃጢአትና ዓመፅ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሄድ፣ ሌላ የተለየ ክፍል የአዳም ቤተሰብ ነበር ። ዘፍጥረት 4፡25፣ 5፡24
መ) በዘፍጥረት 4፡26 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የትኛው የተስፋ ቃል ነው? (ወደ ሮሜ ሰዎች 10:13 ተመልከት) ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።