2ኛ ትምህርት ውድቀት
አዲስ ተከታታይ ጥናቶችን በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ እየጀመርን ነው። ዛሬ ፣ ውድቀት። የጥቅስ መዝሙር፡ እጆቻችሁን አጨብጭቡ መዝ 47:1-2,5-7

የእባቡ ማንነት

ሀ) ዘፍጥረት 3:1 ትክክለኛውን ርዕስ ያመላክታል—እባቡ። የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን በፈጣሪያቸው ላይ እንዲያምፁ የሚፈልግ ይህ ባላጋራ ማን ነው? ራእይ 12፡7-9
ለ) የእባቡ ዋና ስልት ምንድን ነው? ዘፍጥረት 3፡1-4 (በተጨማሪ 2 ቆሮንቶስ 11፡3፣ ዮሐንስ 8፡44 ይመልከቱ)
ሐ) ይህ ጠላት ከየት መጣ? ሕዝ 28፡13-15፣ ኢሳ 14፡12-14
መ) ራእይ 12:4 ሰይጣን አንድ ሦስተኛ የሚሆኑትን መላዕክት በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምፁ ያሳመነው እንዴት ነው? ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:12 ይመልከቱ)

የተከለከለው ፍሬ

ሀ) ዘፍጥረት 2፡16-17 በዚህ የመልካም እና ክፉ የእውቀት ዛፍ ላይ ያለው ፍሬ መርዛማ ነበር?
ለ) ሰይጣን ሔዋን ሆን ብላ ፈጣሪዋን እንዳትታዘዝ ያሳመናት እንዴት ነው? ( ዘፍጥረት 3:1-6 )
ሐ) ሔዋን አዳምን ከእርሷ ጋር በአምላክ ላይ እንዲያምጽ ያሳመነችው እንዴት ነው? ዘፍጥረት 3፡6
መ) ከዚህ ታሪክ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን?

ከአፍቃሪ ፈጣሪያቸው መደበቅ

ሀ) ዘፍጥረት 3:​7-8, 10 አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንደጣሱ ወዲያው የሰጡት ምላሽ ምንድን ነው?
ለ) ዘፍጥረት 3፡9 እግዚአብሔር አምላክ እነርሱን ሊፈልጋቸው የመጣው ለምንድነው እና የጥያቄው አስፈላጊነትስ ምን ነበር?
ሐ) ዘፍጥረት 3:10-13 በአምላክ ላይ የፈጸሙት የማመፅ ድርጊት በአስተሳሰባቸው ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?
መ) ለኃጢአታችን ሌላውን ከመውቀስ ይልቅ አምላክ ከዓመፀኛ ልጆቹ ምን ምላሽ ይፈልጋል? 1ኛ ዮሐንስ 1፡8-9
ሠ) በኃጢአታችን ውስጥ ለአምላክ ሐቀኛ ለመሆን ድፍረት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ሮሜ 2፡4፣ ኤርምያስ 31፡3

የእባቡ እጣፈንታ

ሀ) ዘፍጥረት 3፡15 የእባቡን ጭንቅላት የሚቀጠቀጥ የሴቲቱ ዘር ማን ነው? ( እብራውያን 2:9, 14-15 )
ለ) እባቡ ሰይጣን የመጨረሻውን ዕጣ ፈንታ ያውቃል? ራእይ 12፡12
ሐ) ሰይጣን በእግዚአብሔር እና እግዚአብሔርን ለመውደድ እና ለመከተል በመረጡት ሁሉ ላይ የሚያደርገውን አስከፊ ጦርነት ለምን አይተወውም? ( ዮሐንስ 3:19-20 )

የወደፊት ተስፋ

ሀ) ለመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አለመታዘዝ ያስከተለው ውጤት ምን ነበር? ዘፍጥረት 3፡15-24
ለ) በዚህ አሳዛኝ ታሪክ ውስጥ የተስፋ ቃል ተሰውሮ የሚገኘው የት ነው? ዘፍጥረት 3:15, 21
ሐ) ከዚህ አሳዛኝ ታሪክ ምን ትምህርት እንማራለን ብሎም ዛሬ ለህይወታችን ምን ተስፋ እናገኛለን?
መ) ጌታ ለመዳን የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ በሚያቀርብበት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገቡ ሌሎች ታሪኮችን ያካፍሉ።
ሠ) እግዚአብሔር ያዳነህና ተስፋ የሰጠህ እንዴት ነው?

ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።