| 12ኛ ትምህርት | ዮሴፍ የግብጹ ልዑል |
|---|
የዮሴፋ አስደናቂ ዕድገት
ሀ) ለምንድን ነው ፈርኦን የ30 ዓመቱን ዕብራዊ ባሪያ የግብጽ ዋና ሀላፊ አድርጎ የሾመው ? ዘፍ41፡39-41ለ) ፈርኦን ለዮሴፍ ስም ሰጥቶት ብልጣሶር ነበር ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ ዮሴፍ በሚለው መጠሪያ ሲጠራው እንመለከታለን፡፡ ለምንድን ነው ይሄ ያስፈለገው ?ዳን 1፡7
ሐ) እንዴት ነው እግዚአብሀየር አዲስ በተሸበት ስልጣን የበረከው? ዘፍ/41፡46-57
መ) በሙሉ ልብህ እግዚአብሀየርን በማን እና እያንዱ የህይወት አቅጣጫህ ውስጥ እግዚአብሔርን ብታከብረው3 እግዚአበሔር በአንተ ውስጥ እና በአንተ በኩል ምን ሊያደርግ ይችላል?
የዬሴፍ ህልም እውን መሆን
ሀ) ከብዙ ዓመታት በፊት እግዚአብሔር ለዮሴፍ የሰጠው ህልም እንዴት እውን ሆነ?ዘፍ 42፡1-6.9ለ) በመጀመሪያ ዮሴፍ ማንነቱን ከወንድሞቹ የደበቀው ለምንድን ነው? ዘፍ 42፡21-23
ሐ) እግዚአብሔር በዚህ ልምምድ ውስጥ ሁሉንም የያዕቆብን ልጆች ምን እያስተማራቸው ነበር ?
የዮሴፍ ወንድሙን ቢኒያምን መልሶ ማግኘት
ሀ) መጀመሪያ ስለ ታናሽ ወንድሙ መቅረት ሲጠይቅ እንደረት ነው ዮሴፋ ቢንያምን እንዲያመጡት ያስገደዳቸው?ዘፋ 42:12-14ለ) ዘፍጥረት 42፡36.38 በዚህ ጥያቄ ውስጥ የያዕቆብ ምላሽ ምን ነበር?
ሐ) ያዕቆብ ሀሳቡን ለምን ቀየረ? ዘፍ 43፡1.12-13
መ) ያዕቆብ ልጆቹን መልሶ ሲልክ በጸለየው ጸሎት ላይ ምንድን ነው ሀሳባችሁ? ዘፍ 43፡14
ሠ) ዮሴፍ ከወንድሞቹ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ሲገናኝ የተገለጸው ስሜት ምን ነበር? ዘፍ 43፡26-30
የብር ዋንጫ
ሀ) ለምንድን ነው የብር ዋንጫውን በቢኒያም ስልቻ ውስጥ በመክተት ለሁለተኛ ጊዜ ወንድሞቹን የፈተናቸው? ዘፍ 44፡1-2ለ) ዮሴፍ የብር ዋንጫውን በቢኒያም ጉልቻ ውስጥ ሲያገኘው የወንድሞቹ ምላሽ ምን ነበር? ዘፍ44፡3-13
ሐ) ለምንድነው ይሁዳ በወንድሞቹ ፋንታ ባርያ ለመሆን የጠየቀው? ዘፍ37፡26-27
የዮሴፍ ማንነት መገለጥ
ሀ) ለምንድን ነበር ዮሴፍ ከዛ በላይ ራሱን ደብቆ ማቆየት ያልቻለው? ዘፍ 45፡1-3ለ) በዚህ አስደናቂ መገለጥ የዮሴፍ ወንድሞች ምንድን ነበር ምላሻቸው? ዘፍ 45፡3
ሐ) ዮሴፍ ለተደናገጡት ወንድሞቹ ምን አይነት ምስክርነት እና መጽናኛ ሰጣቸው? ዘፍ 45፡4-13
መ) ዘፍ 45፡14-15 ከዚህ ትይንት ላይ ምን ተማራችሁ?
ሠ) ለዛሬ ህይወታችሁ በዚህ ታሪክ ውስጥ ምን ምክርና መጽናኛ አገኛችሁ? ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።