Poster

የመሰብሰቢያ ቦታ: አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ

የሁሉ ነገር ፈጣሪ እና የህይወት ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር ምንም እንኳን ኃጢአተኛ ብንሆንም በኃጢአት ለተመታው የሰው ልጅ ያለውን የማይሻር ፍቅሩን በታማኝነት ማሳየቱን ቀጥሏል። የእርሱ የድኅነት ጥሪ የጊዜ ፈተናን የተቋቋመ እና በቃሉ ውስጥ በግልጽ የተነገረ ነው። የዘላለምን ሕይወት እንድንመርጥ እና ዘላለማዊነትን ከእርሱ ጋር እንድንወርስ ይፈልጋል። የሚመለስበት ጊዜ ለኛ ባይታወቅም በታማኝነት እንድንጠባበቅ፣ በጥበብ ጊዜውን እንድንረዳ እና እየጠበቅነው እንድንጸልይ አዞናል። የነገሥታት ንጉስ በቅርቡ ይመጣል፣ ስለሆነም ዝግጁ መሆን አለብን። ይህንን ታሳቢ በማድረግ የሻሎም አለማቀፍ ቴሌ ኮንፍራንስ ከኢትዮጵያ አለማቀፍ ሳይበር ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር ቅድስና ለእግዚአብሔር በዚህ ዘመን በሚል ርዕስ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቶላችኋል።

ፕሮግራሞቻችን ለአዋቂዎች ብቻ ሳይሆን እንደየ እድሜ ክልላችወ ለህፃናትና ለወጣቶች የሚሆኑ ምንፈሳዊ ትምህርቶችና የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያንን ታሪክ የሚያዩበት የጉዞና የጉብኝት ፕሮግራሞችም ተዘጋጅቷዋል። ቆይታዎት ቀለል ያለና ሙሉ ትኩረትዎ በሚያገኙት መንፈሳዊ በረከት ላይ ብቻ እንዲሆን በማሰብ የተለያዩ የመኝታ ክፍሎችና ምግብ ተዘጋጅቷል። የመኝታ ክፍሎቹ በሁለት አማራጮች ማለትም Campus Center እና Lamson Hall የቀረቡ ሲሆን

Campus Center 7 ክፍሎች አሉት ፣ ክፍሎቹ ሁለት double አልጋዎች እና የግል መታጠቢያ ቤት አላቸው።

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ክፍሎች እንደ ሆቴል የተዘጋጁና ሙሉ መገልገያዎች ያላቸው ናቸው። የእነዚህ ክፍሎች ከፍተኛው የማስተናገድ አቅም 4 እንግዳዎች ነው።

Lamson Hall 53 ክፍሎች አሉት እያንዳንዱ ክፍል ሁለት single አልጋዎች ያሉትና የጋራ መታጠቢያ ቤት አለው። የእነዚህ ክፍሎች አቅም 2 እንግዳዎች ነው።

አንሶላና ብርድ ልብስ ከዩኒቨርስቲው ስለሚቀርብ እንግዶች የራሳቸውን ማምጣት አይጠበቅባቸውም።

የመኝታ ቤቱ አይነት የክፍሎቹ ዋጋ በቀን የምግብ ዋጋ በቀን
Campus Center $100.45 $42.00
Lamson Hall $41.20

የእምነታችን ደራሲ እና ፈፃሚ የሆነውን ንጉሳችንን ለመገናኘት ስናጠና እና ምን እንደሚያስፈልገን ስንማር እርስዎም መጥተው አብረን እንድናጠና እንጋብዞታለን። ለዳግም ምጽአቱ እራሳችንን አሁኑኑ እናዘጋጅ።

መኝታ ቤቶቹ አስቅድመው በሌላ እንግዳ እስካልተያዙ ድረስ በምርጫዎ ልናስተናግድዎ ተዘጋጅተናል።

ካላችሁብት ስፍራ ወደ አንድሪውስ በአውሮፕላን ለመምጣት የምታስቡ ካላችሁ የሚከተሉትን የአየር ማረፊያዎች ልትጠቀሙ ትችላላችሁ፡ ከአየር መንገዶቹ ወደ Andrews universIty በመኪና ለመምጣት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ያስቀመጥነው የቦታውን ርቅት ለመገመት እንዲያስችል ነው።

  • South Bend International Airport: የ 30 ደቂቃ ርቅት ላይ የሚገኝ
  • Chicago O’Hare International Airport: የ 2 ሰዓት ርቅት ላይ የሚገኝ
  • Chicago Midway International Airport: የ 2:30 ሰዓት ርቅት ላይ የሚገኝ

ሆቴል ለማረፍ የምታስቡ ካላችሁ የሚከተሉትን ሆቴሎች ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። ከሆቴላችሁ ወደ Andrews universIty በመኪና ለመምጣት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ያስቀመጥነው የቦታውን ርቅት ለመገመት እንዲያስችል ነው። ሁሉም ተሳታፊዎች ማረፊያቸውን በተቻለ ፍጥነት እንዲያስይዙ እናበረታታለን። ኮንፈረንሱ የሚካሄደው በበጋ (Summer) ከፍተኛ የጉዞ ወቅት ሲሆን የሆቴል ፍላጎት ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ይጨምራል። በተጨማሪም፣ የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ በዚህ ወቅት በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የጉዞ እንቅስቃሴን ይጨምራል።
አካባቢያችን የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ከተማ ባይሆንም፣ አጠቃላይ የሆቴል አቅርቦት እና ዋጋ አሁንም ሊጎዳ ይችላል። ቀደም ብሎ ቦታ ማስያዝ የተሻለ ዋጋ፣ ተጨማሪ አማራጮች እና በኮንፈረንሱ ቦታ አቅራቢያ የበለጠ ምቹ ቆይታ እንዲኖር ይረዳል።

  • Courtyard by Marriott St. Joseph Benton Harbor: 15 minutes
  • Hilton Garden Inn Benton Harbor / St. Joseph: 15 minutes
  • SpringHill Suites by Marriott St. Joseph Benton Harbor: 15 minutess
ለበለጠ መረጃ ወይም ተጨማሪ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ እባክዎ በ +1 (202)-815-5241 ላይ
የጽሑፍ መልእክት ይላኩልን ወይም የድምጽ መልዕክት ይተውልን።

አሁኑኑ ለመመዝገብ የመመዝግቢያውን ቁልፍ ይጫኑ።

Register Now
Poster

Venue: Andrews University

Despite humanity's sinfulness, God, the Creator of all, offers His steadfast, unmatched love and salvation, desiring for us to choose eternal life with Him. His Word invites us to remain vigilant, pray, and prepare for His return, the timing of which remains unknown to us. In anticipation of the King of Kings' arrival, the Shalom International Teleconference and the Global Ethiopian Cyber Ministry have convened this spiritual gathering.

To ensure your spiritual journey is uninterrupted, we offer varied lodging options as follows:

The Campus Center features seven rooms, each equipped with two double beds and a private bathroom, ensuring comfort and convenience for all guests, including those with disabilities.

Designed with hotel-like amenities, the rooms mentioned above provide complete facilities, accommodating up to 4 guests comfortably.

Lamson Hall offers dormitory-style accommodations. Each room contains two single beds with shared community bathrooms, rooms are designed to host two guests.

Room Type Room Rate/Day Meal Rate/Day
Campus Center $100.45 $42.00
Lamson Hall $41.20

Guests are not required to bring their own bedding, including sheets and blankets.

Join us as we delve into understanding and preparing for the Second Coming,
guided by the author and finisher of our faith. We welcome you to study and ready
ourselves together for this significant event.

We are prepared to accommodate you on a first-come, first-served basis, provided the bedrooms are available.

If you are flying in, you can use the following airports. If you are driving from these airports to Andrews University, here are the estimated travel times:

  • South Bend International Airport: 30 minutes
  • Chicago O’Hare International Airport: 2 hours
  • Chicago Midway International Airport: 2.5 hours

If you want to stay in the nearby hotels, you can use the following nearby hotels. We encourage all attendees to book their accommodations as early as possible. The conference takes place during peak summer travel season, including the July 4th holiday, when hotel demand is already high. Additionally, the 2026 FIFA World Cup will bring increased travel activity across the United States during this period.
While our location is not a host city, overall hotel availability and pricing may still be affected. Booking early will help secure better rates, more options, and a more convenient stay near the conference location. If you are driving here are the estimated travel times from the hotels:

  • Courtyard by Marriott St. Joseph Benton Harbor: 15 minutes
  • Hilton Garden Inn Benton Harbor / St. Joseph: 15 minutes
  • SpringHill Suites by Marriott St. Joseph Benton Harbor: 15 minutess

For inquiries or further assistance, feel free to text us at +1 (202)-815-5241 or
leave us a voicemail.

To register, simply click the 'Register Now' button provided below.

Register Now